AL-faruq-tube
6.15K subscribers
255 photos
88 videos
3 files
419 links
Download Telegram
ስራ የሚያስደስት እና ትርፋማ የሚያደርገው ፋፃሜው ሲያምር ነው

ደጉ ወራችን፣ እንደ ካባ ገበር ገመና ከታቻችን፣ የዝነቱ የዒባዳቱ ወር ረመዷን ካስማውን ነቅሎና ጓዙን ሸክፎ ሊወጣ እየዳዳው ነው። ታዲያ ለተቀሩት የፍፃሜ ቀኖቹ ያለ የሌለ አቅማችንና ነሻጣችን እንጠቀማቸው
ታላቁ ዓሊም አል ሐፊዝ ኢብኑል ጀውዚይ እንዲህ ይላሉ

إن الخيل إذا شارفت نهاية المضمار بذلت قصارى جهدها لتفوز بالسباق، فلا تكن الخيل أفطن منك! فإنما الأعمال بالخواتيم، فإنك إذا لم تحسن الاستقبال لعلك تحسن الوداع!

«ፈረስ የውድድሩ መጨረሻ ዙር ላይ ስትደርስ ለማሸነፍ ስትል ያለ የሌለ አቅሟን ትጠቀመዋለች፤ ፈረስ በጮሌነት የምትበልጥህ አትሁን!

ሐሰኑል ቢስሪይም እንዲህ ይላሉ

أحسن فيما بقى يغفر لك مامضى، فاغتنم مابقي فلا تدري متى تدرك رحمة الله.

«በተቀሩት ቀናቶች ላይ መልካምን ስራ፤ ያለፈው ይማርልሃልና።
የተቀሩትን ተጠቀምባቸው የአሏህን እዝነት መች እንደምታገኘው አታውቅምና!


ስለዚህ ወዳጆች በተቀሩት የረመዷን ቀኖች ውስጥ ያለ የሌለ አቅማችን በመጠቀም ፍፃሜው ያማረልን እንዲሆን እናድርግ

انما الأعمال بالخواتيم
(ፍትህ ለጎንደር ሙስሊሞች )
ዲነል ኢስላም በማንም ሴራ የሚጠፋ እና የሚደናቀፍ አይደለም ሙስሊሞችም የካሀዲያን ሴራ አይበግራቸዉም ሁሌም ዲነል ኢስላም አሸናፊ እና የበላይ ነዉ አሏህ እንዲህ ይላል :-
وَمَكَرُواْ وَمَكَرَ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ ...

ከሀዲያን ሴራን አሴሩ አሏህም የሴራቸዉን ጀዛ ሰጣቸዉ አድማቸዉን መለሰባቸዉ አሏህም ከሴረኞቹ ሁሉ በላጭ ነዉ .
.اللهم انصر الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ودمر أعداءك أعداء الدين
ጌታየ ሆይ የጎንደር ሙስለሞችን ፣መሳጂዶችንእና ንብረታቸዉን ለአንተ አደራ ሰጠናል ሁሉም የአንተ ነዉና
ለአማፂያን ጀዛቸዉን በአሳማሚ ሁኔታ አስከፍልልን የካሀዲያን በላእ በራሳቸዉ ላይ ይዝነብልን
አሚን አሚን አሚን 🤲🤲🤲
#ኡስታዝ_ሰኢድ_አህመድ በብዕራቸው ተቃውመዋል!

የወንዶቹ ቁና ያ የዲኑ ማገር
ዑመር የሉም ተብሎ
ኢማም አህመድ ጋዚ አልፈዋል ተብሎ
በጎንደር ሙስሊሞች ስቃይ ቢበረታ
አለላቸው ጀሊል
ፍፁም የማይሞተው የነ ዑመር ጌታ


ታምኖ፣ ችሎ፣ ትቶ፣ ታግሶ ቸልቶ
ገራገሩ ሙስሊም ባለ ልዋል ልደር
መስጂዱ ተቃጥሎ ሰጋጁ ሲገደል
ምን አርጎሽ ነው ብልሽ
መልስ አለሽ ወይ ጎንደር??!!

ይቅር ብሎ አልፎ፣ ሰላምን አንግሶ
ሲነፍጉት ለግሶ፣ ለችግርሽ ደርሶ
የሚኖርን ሙስሊም ሲገደል እያየሽ
በዋዛ አሳለፍሽው ጆሮ ዳባ ብለሽ?!!
እንዴት አይባባስ የኔማ ችግሬ
ሰምታ እንዳልሰማች አይታም እንዳላየች
ሆናብኝ አገሬ።

ሙስሊም የተገፋ የተነካ ለታ
ሚዲያሽ ካለወትሮው
ደንቁሮ ታውሮ
ወሬ ነጋሪሽም አፉ ዱዳ ሆኖ
የመዋሉን ምስጢር አውቃ ዝም አለችኝ
ይህ ነው ወይ ምላሼ አገር እያለችኝ

ያውም በረመዷን
ፆም ውለው ፆም ሟቾች
እጣቸው ያስቀናል እንደ በድር ዘማቾች


አይተሽ እንዳላየሽ ዝም ያልሽው አገሬ
ንገሪው ለዛ ሰው
ከጠጣበት ጉድጓድ አፈር ለመለሰው
የንፁሃንን ደም በግፍ ላፈሰሰው
ያጎረሰውን እጅ ጅሎ ለነከሰው
ንገሪው ለዚያ ሰው
ያን ቀቢፅ ተስፋውን ካፎት ይመልሰው
አለዚያ ሙስሊሙ
ልክ እንደ ቀስት ናቸው ኋሊት ሲሸሽቱ
ሃይ ብለው ተነስተው ከተወነጨፉ
እንኳን የደፈሩት ያሰቡም አይተርፉ
መስጂድ በማቃጠል፣ ሙእሚንን በመግደል
ብትፍረመረሙም ለቀቢፀ_ግዛት
ኢስላም ልማዱ ነው
ሲነቅሉት አፍርቶ ሲቀንሱት መብዛት

ግንስ ያስለቅሳል ከእንባም አልፎ ደም
ያንች አውቆ ዝምታ ለፍትህ መግደርደር
የሰላም ነዋሪን ሰላም ነስቶ ማደር
እንዲያ መጨከኑ በሙስሊሙ መንደር
ምን አርጎ ነው ብልሽ
መልስ አለሽ ወይ ጎንደር
።።።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን! በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የመተዛዘን የአብሮነት ይሁንልን!

ዒድ ሙባረክ! 🥳

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
كل عام وأنتم بخير
#ሐረር
የሸዋል ኢድን በሐረር ዛሬ ምሽት አንድ ላይ እናከብረዋለን !
#ኸሚስ_ሙባረክ
በጣም ድንቅ ነሺዳ በፉአድ ሸምሱ
#ሀቢበሏህ
የተሰኘ ልዩ ነሺዳ ዛሬ ምሽት 2:00 #በፋአድ_ሸምሱ የYouTube ቻናል ይዞላችሁ ይቀርባል!!

Youtube:
https://youtu.be/ywY_lKMM2G8

ግጥም ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ