ብርጭቆ [high school ] MEMES
797 subscribers
1.28K photos
72 videos
49 links
# Ethiopian [High school] life meme

በሁሉም ት/ቤት meme የሚሰራበት channel

Tik tok
Download Telegram
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የ2015 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስከረም 3 ቀን 2015 እንዲሁም የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ነገር ግን በከተማ ደረጃ ወጥ አድርጎ ማስጀምር በማስፈለጉ ፤ ከመስከረም 2 እስከ 6 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ለአጀማመሩ ሙሉ ዝግጅታቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።

መስከረም 3 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች #ማጠናከሪያ_ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

በሁሉም የትምህርት ተቋማት መስከረም 9 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ሃደት እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

https://t.me/birchekomeme
https://t.me/birchekomeme
Boom 🙏
🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼🌼
           🌼happy new year🌼
                     💛2015💛
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ!!

የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:-

2014/15 የኢትዮ ዩኒቨርሲቲ መግቢያና
የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ካምፖስ ጉዞ ሲያደርጉ #መያዝ #የተፈቀደላቸው#መያዝ #የተከለከሉ እና #የጊዜ #ሠሌዳ እንደሚከተለው ያለው ሲሆን ተማሪዎች ከወዲሁ ራሣችሁን እንድታዘጋጁ ይሁን።

#መያዝ #የተፈቀደላቸው
✡️አንሶላ፣
✡️ትራስ ጨርቅ፣
✡️የማታ ልብስ፣
✡️ደረቅ ምግብ፣
✡️ልብስ፣ቦርሳ፣
✡️የመፈተኛ ካርድ፣እርሳስ፣ላጲስ፣የማስታወሻ ደብተር፣ባዶ ወረቀት፤መጽሐፍ

❷፣#መያዝ #የተከለከሉ
☸️ማንኛውም ድምፅ የሚቀዳ፤ቪዲዮ የሚቀዳ ወይም ፎቶግራፍ የሚያነሳ፤
☸️ካሜራ
☸️ማንኛውም ከቴሌ መስመርም ይሁን ከቴሌ ውጭ መልዕክት በድጂታል ቴክኖሎጂ መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ ውጤቶች(ታብሌት፣ኮሚፕዩተር፣ላብቶፕ፣ ስልክ፣አይፓድ፥ሃርድ ዲስክ፣ፍላሽ)

#የጊዜ #ሠሌዳ
✡️ማህበራዊ ሳይንስ $social science dep't
➤26_28/1/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
➤29/01/2015 ኦሬንተሽን
➤30/01/2015_02/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።

✡️የተፈጥሮ ሳይንስ Natural Science dep't
➤05_06/2/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
➤07/02/2015 ኦሬንተሽን
➤08/02/2015_11/02/2015 ፈተናው
የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።

ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ሼር ያድርጉ።
መረጃው ከትምህርት ሚኒስተር ነው የተገኘው።
    T.me/ethio_mereja
     
@ethio_mereja
Forwarded from Addis Ababa Education Bureau (Abebe Chernet)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች እንዲሁም ለተፈታኞች የተፈቀዱ እና የተከለከሉ ነገሮች ያቀረቡ ሲሆን በዚህም
የተፈታኞች መብቶች የሆኑት፡-
👉ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት
👉 በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት
👉ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት
👉 የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት
. በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት
👉ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት
የተፈታኞች ግዴታ የሆኑት፡-
. ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ
👉 ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት
👉 ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ
👉 ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም
👉 ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት
👉ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ
👉ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት
👉ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት
👉ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት
👉ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት
👉 ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት
ለተፈታኞች የተፈቀዱ ነገሮች
👉 አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማርና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር ፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት
👉 ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንዱች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)
👉ገንዘብ (ብር)
👉 የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ
👉 የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)
ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች
👉 ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
👉 ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው
👉ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
👉 በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
👉ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሓኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
👉 ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
👉ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)
👉 ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡
👉 ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡
👉በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
👉በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡
የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/