ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
362 subscribers
1.3K photos
11 videos
146 files
169 links
Download Telegram
#ቡሄ_ሔ
የደብረ ታቦር በዓል ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ቢሆንም በምዕመናን ዘንድ ቡሄ/ሔ በመባል ይታወቅል ለመሆኑ የደብረ ታቦር በዓል ለምን ቡሄ/ሔ እያልን እንጠራዋለን? ስለምንስ ችቦ እናበራለን? የሚጮኸው የጅራፍ ድምጽ ምንድነው ምሥጢሩ የሚለውን በአጭሩ እንመከታለን፡፡
=================_//_==============
ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ስለ ደብረ ታቦር በዓል አከባበር በኢትዮጵያ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ “ቡሄ/ሔ ዘውእቱ በዓለ ኖሎት ደቀ መዛሙርት “ ይህውም ደብረ ታቦር ወይም የቡሄ/ሔ በዓል የደቀ መዛሙርትና የእረኞች በዓል ነው እንደ ማለት ፡፡ ምክንያቱም በጥንቷ ኢትዩጵያ የደብረ ታቦርን በዓል እረኞች የቆሎ ተማሪዎች በስፋት ስለሚያከብሩት ነው፡፡
===============_//_=================
#ቡሄ፡- ማለት “የበራ የደመቀ የጐላ ብርሃን“ የብርሃን በዓል እንደ ማለት ነው ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈው ጌታችን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን በገለጠ ጊዜ ፊቱ እንደ ፀሐይ በማብራቱ፥ ልብሱም አጣቢ በምድር ላይ ሊያነጣው እስከማይችል ድረስ በጣም ነጭ አንጸባራቂ በመሆኑ ነው ማቴ 17፥2 ማር9፥3 ሉቃ9፥29
=============_//_===================
#ቡሔ፡- ማለት ደግሞ “ደስታ ፍሥሐ“ማለት ይሆናል፡፡ ይህውም በትንቢት እንደተፃፈው ታቦር ወአርምንዔም በስመ ዘአከ ይትፈሥሑ መዝ88፥12 በዚህ ትንቢታዊ ቃል መሠረት በወቅቱ የጌታ ብርሃን በዙሪያቸው አብርቷል ከታቦርም እስከ አርምንዔም ተራራ ድረስ ታይቷል፡፡ ይህም መለኮታዊ ብርሃን በወረደበት ጊዜ ከብቶቻቸውን ይጠብቁ የነበሩ በታቦርና በአርሞንየም አካባቢ ያሉ መዓልቱ የሌሊቱን ቦታ ስለ ወሰደው በሁኔታው ሐሴትን አድርገዋል፡፡ሙልሙል/ኀብስቱ፡- በታቦር ተራራ ዙሪያ ለነበሩት እረኛች ወላጆቻቸው ምግባቸውን ይዘው መሄዳቸውን ያጠይቃል፡፡ አንድም የኀብስቱ ምሳሌነት ለክርስቶስ ነው “አነ ውእቱ ኅብስተ ሕይወት ዘወረደ እምሰማያት” ዮሐ 6፥32-59
=================_//=================
#ጅራፍ፡- በደብረ ታቦር ዋዜማ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ሆነን ጅራፍ የምናጮኸው መሠታዊ ሃይማኖታዊ ምሥጢር ምሳሌነት አለው።
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
እግዚአብሔር አብ በመልክ የሚመስለኝ በባህሪ የሚተካከለኝን ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጄ ነው፡፡ እርሱን ስሙት ተቀበሉት ብሎ ድምጹን በደመና በደብረ ታቦር ተራራ ላይ የመሰከረበትን እያሰብን ነው፡፡
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የጅራፍ ጩኸት ከጫፍ ጫፍ ይሰማል በመዝሙረ ዳዊት “……….. ድምጻቸው ወደ ምድር ሁሉ ቃላቸውም አስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ፡፡” መዝ18፥4 በማለት የሐዋርያት ስብከት በዓለም ዳርቻ መድረሱን ያመለክታል፡፡ መኃ 2፥12
ሌላው የጅራፍ ጩኸት ማስደንገጡ ደግሞ ሦስቱ አዕማድ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ድምጸ መለከትን ሰምተው ደንግጠው መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በተጨማሪም የልጆቹ ወላጆች በታቦር ተራራ ዙሪያ የነበሩትን ልጆቻቸው ለመፈለግ ችቦ እያበሩ ሲሄዱ ልጆቹም ጅራፍ በማጮኽ ያሉበትን ሥፍራ መጠቆማቸውን ያስረዳል፡፡
ችቦ፡- ተሰብስበን ችቦ የማብራታችን ምሳሌ ደግሞ ጌታችን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለፀበት ምሳሌ በመሆኑ ነው፡፡ የሐ 8፥1፣ መዝ 26፥1 “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሐኒቴ ነው……..”
================_//=================
#ማጠቃለያ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደብረ ታቦርን በዓል በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን ታከብረዋለች፤ ይኸውም በዕለቱ በዓሉን የሚያዘክር በቤተክርስቲያን ምንባባት ይነበባል፡፡ ቅዳሴ ይቀደሳል፣ ምስባክ ይሰበካል፣ ቃለ እግዚአብሔር ይሰጣል፣ ወረብ ይወረባል………… ወዘተ በዚህም ዕለት የቤ/ክ አባቶችና ምእመናን በዓሉን በደማቅ ሥነ ሥርዓት ያከብሩታል፤ ምክንያቱም ከላይ በስፋት እንደ ተመለከትነው ደብረ ታቦር እሥራኤላውያን የድል ካባ የደረቡበት መሳ 4፥1—3 የትርጓሜ ትምህርት የተሰጠበት ማቴ 15፥15፣ ኑፋቄ (ጥርጥር) የተወገደበት ማቴ 16፥13—20፣ ምሥጢረ ሥላሴን የተረዳንበት፣ የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት የተሰበከበት፣ የሐዋርያት ባለሟልነት የተገለጠበት፣ የተግባር ትምህርት የተሰጠበት፣ አሉባልታና ተራ ወሬ የከሸፈበት፣ የቅዱሳን ነቢያት ሐዋርያት ክብር የተገለጠበት፣ የተቀደሰን ቦታ አክብሮት፣የተማርንበት የታየበት፣ ብሔረ ሕያዋን መኖሩ የተመሠከረበት፣ የትንሣኤ ሙታን ዋስትና የተረጋገጠበት ነው፡፡
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
“በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል…………” ኢሳ ፪፥፪
••MIKIYAS DANAIL••
https://t.me/mikiyasBRANAbook
https://www.facebook.com/mikiyas.danail
=============//================
መልካም የደብረ ታቦር በዓል
••••••••••••••
©መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
ነሐሴ12/2014
የማይቀርበት ጉባኤ
የማይቀርበት ጉባኤ
በሥጦታ ወር የተሳተፋችሁበትን (ገቢ ያደረጋችሁበትን) ወረቀተ(bank sleep) ፖስት አድርጉልን።
እናመሰግናለን!
†††_ርኅወተ ሰማይ_†††

`````

"እውነት እውነት እላችኋለሁ:: ሰማይ ሲከፈት: የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ::"
(ዮሐ. ፩፥፶፪)

• ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት: አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት: ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን::" ትባላለች::

አሁን በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም:: የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት: አንድም ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ::

እመቤታችን ድንግል ማርያም ለአጼ ናዖድ እንደ ነገረቻቸው በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ: የእግዚአብሔር የምሕረት መዝገቡ ስለሚከፈት: ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል:: በቅዱስ ሩፋኤል አበጋዝነት (መሪነት) በዚህች ዕለት ለዓመት የሚበቃ ምሕረት ይገኛል::

ስለዚህም አባቶቻችን በዚህች ሌሊት ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ:: በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል::
ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን::

•ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት•

```````````````````````

"በሰው ቊስል ላይ የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሩፋኤል ነው" ሄኖክ፮÷፫
ቅዱስ ሩፋኤል በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በደረጃው ሦስተኛ ነው:: በመጀመሪያዋ ዕለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክትን ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው የቅዱስ ሩፋኤል ዕድል ፈንታው ራማ ሆነች::

በዚያም "መናብርት" ተብለው ለሚጠሩ አሥሩ ነገድ አለቃ (መሪ) ሆኖ በፈጣሪው ተሹሟል:: በኋላም "መጋብያን" በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ሹሞታል:: ይህች ዕለትም በዓለ ሲመቱ ናት::

አንድ ቀን ጌታችን ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ሐዋርያቱ ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲያስተዋውቃቸው ለመኑት:: ጌታም ሦስቱን ሊቃናት (ሚካኤል: ገብርኤል እና ሩፋኤል) ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው::

ቀጥሎም ቅዱስ ሩፋኤልን "ክብርህን ንገራቸው::" አለው:: እርሱም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምሥጢር ነገራቸው:: በተለይ ስሙን ለሚጠሩ: መታሰቢያውን ለሚያከብሩ የሚደረገውን ጸጋ አብራርቶላቸው ዐረገ::

በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱሱ መልአክ ሰው (አዛርያን) መስሎ: ጦብያን ለትዳር አብቅቶ: ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ: የጦቢትን ዓይን አብርቷል:: በገድላተ ቅዱሳን እንደምናየውም ለብዙ ቅዱሳን ረዳታቸው ሆኖ ገድላቸውን አስፈጽሟል::

ታሪክ እንደሚለው ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱም ናት:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ አማካኝነት ቤቱ ታንጿል:: የሚገርመው ደግሞ የታነጸው በዓሣ አንበሪ ጀርባ: ደሴት ላይ ነው:: በመልአኩ አጋዥነትም ለሦስት መቶ ዓመታት አገልግሏል::

ቅዱስ ሩፋኤል
• መራኄ ፍኖት (ጦቢያን መንገድ መርቷልና)
•መልአከ ከብካብ (የጦቢያና የሣራን ጋብቻ ስለባረከ
•መስተፍስሒ (ልቡናን ደስ የሚያሰኝ)
• አቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ)
• መዝገበ ጸሎት (የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው)
• ሊቀ መናብርት (በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ)
• ፈታሔ ማኅጸን (የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማኅጸን የሚፈታ)
• መወልድ (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) ይባላል::
"ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማኅጸኖሙ አንተ" እንዲል::

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” መዝሙር ፴፫፥፯

•ዳግም ምጽአት-የአለም ፍጻሜ•

``````````````````````

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ዳግም ምጽአትና ስለ ዓለም መጨረሻ፣ ስለ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንም ሁልጊዜ የምታስተምር ቢሆንም በተለይ በዐቢይ ጾም ውስጥ ‹‹ደብረ ዘይት›› በሚለው ዕለተ ስንበትና በዓመቱ መጨረሻም በወርኃ ጳጉሜን ስለ ዳግም ምጽአትና ስለ ዓለሙ ፍጻሜ ከቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ነገረ ምጽአቱንና ምሥጢረትንሣኤ ሙታንን የሚመለከቱ ጥቅሶችን እያነበበችና ምእመናንን እያስጠነቀቀች በየጊዜው ትኵረት ሰጥታ ታስተምራለች። በእነዚህ ወቅቶች በቤተ ክርስቲያናችን የሚዘመረው መዝሙር፣ ቅዳሴውና ትምህርቱም ሁሉ ይህንኑ የተመለከተ ነው

"ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል።
አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤ እሳት በፊት ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ።" መዝሙር ፵፱÷፪ ማቴ፳፬÷፩

•ቅዱስ መልከ ጼዴቅ•

```````````

ካህኑ መልከ ጼዴቅን ቅዱስ ጳውሎስ "የትውልድ ቁጥር የለውም: ለዘመኑም ጥንትና ፍጻሜ የለውም::" ይለዋል:: (ዕብ.7:3) ሐዋርያው ይህንን ያለው ለወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ ሲያደርገው እንጂ ትውልዱ ከነገደ ካም ነው:: ወላጆቹም "ሚልኪ እና ሰሊማ" ይባላሉ::

ገና ከእናቱ ማኅጸን የተመረጠው ቅዱሱ "ካህነ ዓለም: ንጉሠ ሳሌም" ይባላል:: የዛሬ አምስት ሺ አምስት መቶ ዓመት አካባቢ ሴም ባኖረበት ቦታ (በደብረ ቀራንዮ) ለዘላለም ይኖራል:: ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከሰው ወገን እጅግ ክቡርም ነው::

•አፄ ዘርዓ ያዕቆብ

```````

ሃይማኖቱ የቀና ኢትዮጵያዊው ንጉሥ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በኢትዮጵያ በነገሠባቸው ሠላሳ አራት ዓመታት (ከ1426 እስከ 1460 ዓ/ም) ብዙ በጐ ነገሮችን ሠርቷል:: ላለፉት ሰባ ዓመታት ግን አንዳንድ ጥቃቅን ሰብአዊ ስህተቶችን እየነቀሱ ተሐድሶዎቹ ስሙን ሲያጠፉት ኑረዋል::

ዛሬ ዛሬ ደግሞ የእኛ ቤት ሰዎችም ተቀላቅለዋቸዋል::
እነርሱ ያሉትን ይበሉ እንጂ ለእኛ ግን ዘርዓ ያዕቆብ ማለት:-
1.ጣዖት አምልኮን ከሃገራችን ለማጥፋት ብዙ ሺህ ካህናትን አሰልጥኖ አሰማርቷል::
2.የኑፋቄ ችግሮችን ለመቅረፍ ጉባኤያትን አዘጋጅቷል::
3.ከአሥራ አንድ ያላነሱ መጻሕፍትን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ደርሶ ለአገልግሎት አብቅቷል::
4.ብዙ መጻሕፍትን ከውጪ አስመጥቶ አስተርጉሟል (በተለይ ተአምረ ማርያምን)
5.ሰው ሁሉ ለእመ ብርሃንና ለመስቀሉ ፍቅር እንዲገዛ ጥረት አድርጓል
6.እመቤታችንን በፍጹም ልቡ ከመውደዱ የተነሳ ዛሬ ድረስ በሃገራችን ድንግል ማርያም "የዘርዓ ያዕቆብ እመቤት" እየተባለች ትጠራለች::
7.ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጾ: ብዙ ሥርዓቶችም በሊቃውንት እንዲሠሩ አድርጐ: ሌሎች ብዙ በጐ ተግባራትንም ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል::
ቤተ ክርስቲያን ስለውለታቸው ዘርዓ ያዕቆብን: እናታቸው ጽዮን ሞገሳን እና አባታቸው ዳዊትን በክብር ታስባለች::

•ቅዱስ ሰራጵዮን ዘሰንዱን•

````````````````

ይህ ቅዱስ እጅግ የበዛ ሃብቱን ለነዳያን አካፍሎ: ወደ ሌላ ሃገር ሔዶ ለባርነት ተሽጧል:: በተሸጠበት ሃገርም በጸሎት ተግቶ ከክህደት ወደ ሃይማኖት መልሷቸዋል:: ክብሩን ሲያውቁበትም በተመሳሳይ ወደ ሌላ ሃገር ሒዶ አሕዛብን አድኗል:: በፍጻሜው ወደ በርሃ ገብቶ በተጋድሎ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::

አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ሁሉ በረከትና ጸጋ ያብዛልን:: ለዓለምም ሰላሙን ይዘዝልን::
ጳጉሜን 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ርኅወተ ሰማይ (የሰማይ መከፈት)
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
3.ቅዱስ መልከ ጼዴቅ ካህን
4.አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ንጉሥ (የእመቤታችን ወዳጅ)
5.ቅዱስ ሰራጵዮን ዘሰንዱን
6.ቅዱስ አኖሬዎስ
7.ቅዱስ ቴዎፍሎስ
8.አባ ዮሐንስ
9.ቅዱስ ጦቢት
10.ቅዱሳን ጦብያና ሣራ

•መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል•
•ጷግሜ 0፫/2014 ዓ/ም•
______†
ከበዓሉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን።
~•••••••~•••••••~•••••~
“ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤”
፩ኛ ዮሐንስ ፩፥፩!
••••••••••••••••••
የፌስቡክ ፔጃችንን ይቀላቀሉ ፤ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, እና Share ያድርጉ :-
~•••••••~•••••••~•••••~
የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/mikiyas.danail

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063973695479

https://www.facebook.com/mikiyas24/

የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/brana_Book