ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
361 subscribers
1.3K photos
11 videos
146 files
169 links
Download Telegram
የጸሎተ ሃይማኖት ትንታኔ.pdf
2.2 MB
#ጸሎተ_ሃይማኖት

የቤተክርስቲያናችን ዋና ጸሎት የሆነውና በቤተክርስቲያናችን የ11 ሰዓቱ የማታ ጉባኤ ከመጀመሩ በፊት የሚፀለየው ጸሎተ ሃይማኖት ትንታኔ ወይም ማብራሪያ እነሆ
@የቴሌግራም ቻናል 
: https://t.me/brana_Book
የአባታችን_ሆይ_&_እመቤታችን_ሆይ_አንድምታ.pdf
16.3 MB
የአቡነ ዘበሰማያት / የአባታችን ሆይ ሙሉ ፀሎት ትርጓሜ
የቴሌግራም ቻናል 
: https://t.me/brana_Book
"አድዋ" በታሪክ መጻሕፍት
ብራና መጽሐፍ BRANA BOOK
https://t.me/brana_Book
ዜና መጽሐፍ !!! ለአንባቢያን በሙሉ ታላቅ የምሥራች
ጉባኤ ቤቶች መሠረትነታቸውን ሳይለቁ ዘመኑን ከዋጁ ለዓለም ይደርሳሉ። ዘመኑን መዋጀት ማለት የዓለምን ሁኔታ እና ርዕዮት ዓለሙን በትክክል መረዳት ነው ይህ ደግሞ የጉባኤ ቤትን መሠረትነቱን ሳይለቅ ነው።
አሁን ዘመኑን የዋጁ ጉባኤ ቤቶች እየፈሩ ነው !! በትክክል የቤተ ክርስቲያንንን ዓላማ ግብ ያደርሳሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
ለዛሬ ከገባነበት ችግር መውጫ መንገዳችን አንዱ ዘመኑን የተረዳ ጉባኤ ቤት ሲኖር እና ስንሰራ ብቻ ነው።
ለማንኛውም የደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚኢ ኪዳነ ምህረት ወቅዱስ መሪቆረዮስ ቤተ ክርስቲያን የመጻሕፍት ምሥክር ጉባኤ ቤት መምህር የሆኑት ወጣቱ ሊቅ መር ፍሬሕይወት አረጌ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ የሚል ሀርድ ከቨር መጽሐፍት አዘጋጅተውልናል። የመጽሐፉ ገቢ የሚውለው በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት እየተገነባ ላለለው G+3 ህንፃ በጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚኢ ኪዳነ ምህረት ወቅዱስ መሪቆርዮስ ቤተ ክርስቲያን የመጻሕፍት ምሥክር ጉባኤ ቤት ማስፈጸሚያ የሚውል ነው ። ሁለት ጥቅም አለው
1. ይህ የሚገርም ምሥጢር ያለውን መጽሐፍ በመግዛት ተጠቃሚ መሆን
2. በመግዛታችን ለጉቤኤ ቤቱ ማስፈጸሚያ አሻራችን እናስቀምጣለን።
የመጽሐፉ የገጽ ብዛት :340
የዋጋው ብዛት በነጭ እና በጥቁር እንዲሁም በሐርድ ከቨር በመሆኑ :850 ብር ብቻ
መታሰቢያነቱ : ለአለቃ ወልደ አብ ለጉባኤ ቤቱ መሥራች
ትንሽ እትም ስለሆነ ፈጥነው መጽሐፈን ይግዙ !!!
በቅርብ ቀን
እኔ ጋሽ ግርማን በአካል አግኝቸው አላውቅም። ስሙንም ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ያረፈ ጊዜ ነበር። አንድ እርሱን የሚያውቅና ከእርሱ የተማረ ወንድሜ ጋር ተቀምጠን መንፈሳዊ ነገር ስንጨዋወት ባለበት የጋሽ ግርማን ሞት አረዱት ። ያለቀሰው ለቅሶ ያዘነውም ሐዘን እስካሁን ፊቴ ላይ አለ፣ ትኩስ ሆኖም ይሰማኛል። በዚህ መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁለት ቢሆንም እያደር በዙ ነገር ከሰማሁላቸውና ትምህርታቸውን ካልሰማሁላቸውና ነፍሴ ክምታከብራቸውና ከምትወድዳቸው መምህራን መካክል አንዱ ሆነ። ይህን መጽሐፍ ሳነብብ አንድ የተረዳሁት ነገር ደግሞ ጋሽ ግርማ ሀብተ ክህነት ከተሰጣቸው ሰዎች አንዱ መሆኑን ነው።
ጋሽ ግርማ ሥልጣነ ክህነት ይኑረው አይኑረው አላውቅም፣ ሀብተ ክህነት እንዳለው ለመረዳት ግን የሚያስቸግር አይመስለኝም። ሀብተ ክህነት የሚባለው ሥልጣነ ክህነት ሳይኖራቸው በሃይማኖታቸው ጽናት በምግባራቸው ስፋት ምክንያት ግብረ ክህነት ከሚያስገኘው ጥቅም የተወስኑትን የሚያሰገኝ ረቂቅ ሀብት ነው። መገለጫዎቹም ትምህርት፣ ምክር፣ ተግሣጽ በመስጠት ነፍስን ወደ እግዚአብሔር የማቅረብ ጸጋ ነው። በሀብተ ክህነት ውስጥ ምስጋና ዝማሬ እና ሥርየተ ኃጢአት አስገኝቶ ማስታረቅም ቀዳሜዎቹ ናቸው። ሆኖም ይህ የተሰጣቸው ሰዎች ሀብተ ክህነት እንጂ ሥልጣነ ክህነት ስለሌላቸው ገብቼ ልቀድስ፣ ላጥምቅ ልጠን፣ ልናዝዝ፣ ልቀንን አይሉም። ከዚህ ባልተናነሰ ግን አማኞችንና የተጠጓቸውን በሚገባቸው መንገድ በማስረዳት ይጠቅማሉ። ሌላው ቀርቶ “የተዋችሁላቸው ተትቶላቸዋል፣ የያዛችሁባቸውም ተይዞባቸዋል” የሚለው በወንጌል ላይ የሰፈረው ኪዳነ ክህነት ስለሚፈጸምላቸው ያዘኑበት ይጎዳል፣ እነርሱ ይቅር ያሉትም ሥርየት እስከማግኘት ይደርሳል። ትልቅ ሰው አይዘንባችሁ የሚባለውም ለዚህ መዐርግ ከደረሰ ስሜቱም ሆነ ቃሉ የካህን ያህል ተጽዕኖ ስለሚኖረው ነው።
ሥልጣነ ክህነት ይዘው ሀብተ ክህነቱን ያቃለሉ እንዳለ ሁሉ ሥልጣነ ክህነት ሳይኖራቸው ለሀብተ ክህነት የሚበቁም ሞልተዋል። ይህ ጸጋ ለብዙ ምእመናን ተስጥቷልና። ለምሳሌ ዳዊት ሥልጣነ ክህነት አልነበረውም፣ ሀብተ ክህነት ግን ነበረው። ስለዚህ መቅደስ ገብቶ አልፈተፈተም፣ በሀብተ ክህነቱ ግን ጠቅሞበታል። ከዝሙት ሕይወት የመጣችው ማርያም ግብጻዊት በድንግልና በምንኩስና የኖረውን መናኙን ጻድቁንና ሥልጣነ ክህነት ያለውን አባ ዞሲማስን በተማጽኖ አስገድዷትም ቢሆን የባረክችው ሀብተ ክህነት ስለተሰጣት ነው።
ከዚህ መጽሐፍ ንባቤና ከታሪኩ ከሰማኋቸው ነገሮች አንጻር ሳየው ጋሽ ግርማ ከዚህ ሀብት በመጠኑም ቢሆን እንደተቋደሰ ይሰማኛል። ይህ ሁሉ የሆነውና ሊሆንም የቻለው ደግሞ ጌታችን በወንጌል እንደገለጸው በእውነት ከእርሱ ስለተሰጠው ይመስለኛል። በእኔ እምነት ጋሽ ግርማ ከበደ፣ አሚን ከፈሊጥ፣ ትሕትና ከተልእኮ (ከአገልጋይነት) የተሰጠው፣ ሐኪት የጠፋለት ለሀብተ ክህነት የደረሰ የዘማንችን ቀንዲል የነበረ ይመስለኛል። ስለዚህም ርትዕት ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖቱን ያለ ሐኬት መረዳትና ማስረዳት የሚፈልግ ሁሉ ምእመን ካህን፣ አገልጋይ ተገልጋይ ሳይል ይህን ኦርቶዶክስያ የተባለውንና የትምህርቶቹ ስብስብ የሆነውን መጽሐፍ ሊያነብበውና ሊጠቀምበት የሚገባው ድንቅ መጸሐፍ ነው።
በዚሁ አጋጣሚ አድካሚ የሆነውን ከድምፅ ወደ ጽሑፍ የመገልበጡን ሥራ ለሠራችሁ፣ አርትዖቱን ለሠራችሁ፣ የህትመት ሓሳቡን ላመጣችሁና ለዚህ ውጤት ላደረሳችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በተለይ አገልጋዮች ነን የምንለው ደግሞ ከመጽሐፉ በይዘቱ ከተካተተው አልፈን ክይዘቱ ባሻገር ከእርሱ ተምረንና ፍኖተ ተልእኮውን ተከትለን የደረሰበት የአገልግሎት ደረጃ ደርሰን ሲሆን በዚያ በኩል አልፈን ካልሆነም ወደዚያ ደርሰን ለመጠቀም እንዲያበቃን ልባዊ ምኞቴ ነው።
ስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ