በክርስቶስ ( in christ)
700 subscribers
98 photos
34 videos
41 files
37 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
ኢየሱስን ለመናፈቅ ከህልውናው የተሻለ አንድም ነገር የለም ። በህልውናው ውስጥ የክርስቶስን ፍቅር ያንሰፈስፈናል .. በህልውናው ውስጥ ጎልጎታ የትናንት ያክል ቅርብ ያረገዋል ..ቀራኒዮን የዛሬን ያክል ያሳያል ..በህልውናው ውስጥ ኢየሱስ የሚለው ስም ተጠርቶ አይጠገብም ..በህልውናው ውስጥ እኔነት ፀጥ ይላል .. በህልውናው ውስጥ የኢየሱስ መምጣት በጉጉት ያስናፍቃል ያስጠብቃል ..በህልውናው ውስጥ የክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ተነስቶ አይጨረስም ..በህልውናው ውስጥ የክርስቶስ ደም ትርጉም ይሰጣል..በህልውናው ውስጥ የኢየሱስ ልብ ጮኽ ብሎ ይሰማል ..በህልውናው ውስጥ ኢየሱስ ያረካል..በህልውናው ውስጥ ኢየሱስ ብቻ ..በህልውናው ውስጥ የሞተልን፣የተሰቀለልን፣ የተሰቃየልን እርሱ ብቻ ይደምቃል ..


@ownkin
@cgfsd
ዉዴ ለእኔ ያለዉን የፍቅር መግለጫ የጻፈው በስጋና በደሙ ቀራኒዮ ነበር ፍቅሩ ደግሞ ከመቃብር በላይ ነው።

#ኢየሱስ

sharona

@ownkin
@cgfsd
የመስቀሉ ፍቅር ለየት ያረገው ዘላለማዊ መሆኑ ነው ።ዘላለማዊ መሆኑ ደግሞ እያደር የማይቀዘቅዝ፣የማይበርድ ፣የማይሰበር የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው የሚያስወድድ ፍቅር ነው ። ለተካፈለው ደግሞ በዘላለለም ውስጥ ሁልጊዜ ዘላለማዊን ፍቅር እያወቁ የሚያስኖር ነው ። የመስቀሉ ፍቅር የአንድ ጊዜ ክስተት አይደለም ዘላለማዊ እንጂ ። ይሔ ዘላለማዊ ፍቅር በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በደሙ ተፃፈ ፣ በደሙ ተበሰረ ፣ በደሙ ተተረከ፣ በደሙ ታየ ... በደሙ የፍቅሩን ጥንካሬ ፣ብርታት ፣ውበት ፣መልክ ፣ልክ አሳየን ... ለዚህ ነው ደሙ ፍቅሩ ላይ እርግጠኛ ያረገን .. የእኛ ጌታ ውዳችን ኢየሱስ በአንደበቱ ሳይሆን በደሙ የነገረን ፍቅር ሰምተናል ..በእርግጥም ይወደናል ።
(ጠበቃ አለን!!!)

ጠበቃ ብሎ በግሪከኛው ጵራቅሊጦስ ይለዋል ። ጵራቅሊጦስ  ለመንፈስ ቅዱስ የተሰጠ ስም ነበር አፅናናኝ ማለት ነው ።ሌላኛው ትርጉሙ እዚህ ጋር የተጠቀሰው ጵራቅሊጦስ በጥብቅናው  የሚታይ ፣ክስ የሚያስወግድ ጠበቃ  ነው  ። የድሮ የመፀሀፍ ቅዱስ ቅጅ ጠበቃ የሚለውን የሚከራከርልን ይላል ምናልባት እኛን የወከለ ብቁ የሆነ ተከላካይ ነው ።ማስተዋል ያለብን ኢየሱስ ጵራቅሊጦስ ተብሎ የተጠራበትን እውነት እና ምክኒያት ይሆናል።(1ዩሀ2:2-3)

ኢየሱስ ብቸኛ  የማይከራከር ጠበቃ ነው ምክኒያቱም ደግሞ ደሙ የታመነ ምስክር ነው። ደሙ ራሱ ይመሰክራል የታመነ ምስክር በንፁሁ ደም በኩል አቅርቧል  ። የእኛ ጠበቃ አያሳፍርም የታመነ ደም አለው እርሱን ደሙን ጥብቅና ስለቆመላቸው  አሳይቷል ። ጠበቃ የሚያቀርበው አንዳች ማስረጃ የተከሰሰውን አካል ነፃ የሚያወጣ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል የእኛ ጠበቃ ጌታችን ኢየሱስ ያቀረበው ማስረጃ ደሙን ነው ይሔው እኔ ሙቻለሁ ስለ እርሱ በደል ተሰውቻለው ሞታቸውን በሞቴ ወስጃለሁ በቀራኒዮ ላይ አልፊያለሁ እኔ እንደዚህ የሆንኩት የእነርሱን እዳ ለመክፈል ነው እና ይሔው ንፁህ ደሜ እነርሱ ከእኔ እንከን አልባ ንፁህ ደም የተነሳ ንፁህ ናቸው የሚል ማስረጃ አቅርቧል ።

ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን ሲባል የብሉይን ስርአት ማስታወስ አለብን .. ምሳሌ በመፀሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች ሀጢያት ሲያደርጉ ወይም ባያደርጉ የሚከሳቸው ከሳሽ ነበር ። ኢዮብ 1... ኢዩብን ለመጣል በእግዚአብሔር ፊት ሰይጣን ከሳሽ ሆኖ ቀርቧል እዬብን በማጣጣል በእግዚአብሔር ፊት እደ ከሳሽ ቁሟል ።
ሌላው ታላቁ ካህን ኢያሱ (ዘካ3&4) ካህኑ ኢያሱ የለበሰው ልብስ ቆሽሾ ነቀፋ ተገኝቶበት በእግዚአብሔር ፊት ከሳሽ ሁኖ ሰይጣን ቆመ ። አሁን ግን ክሱ ስለተዘጋ ከሳሽ ሁኖ አይቆም ለምን ሲባል አሁን ጠበቃው ነው የቆመው ለከሽ መዝገቡ ተዘግቷል አበቃ ካላስ ጠበቃ አለን ።የወንድሞች ከሳሽ ተጥሏል("ራዕ 11) አሁን ከሳሼን ሳይሆን ጠበቃዬን ነው ማስበው ..እዚህ ጋር ማስተዋል ያለብን ዋና ነገር ጠበቃ አለን በማለት በሀጢያት መመላለስን ሳይሆን ጠበቃ አለን ብለን ጠበቃችን ዋጋ ለከፈለበት ክቡር እና ቅዱስ ደም በፅድቅ መኖር ነው ።

ይሔ ጠበቃ ፃዲቅ ነው ። ስራው ትክክል ነው ጠበቃው ፃዲቅ ነው። 


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ሁልጊዜ የማስተውለው አንድ ባለ ጋሪ  ነበር ። የፈረሱን አይኖች አራት በአራት በተከረከመ የጄሪካን ቁራጭ   ወደ ጎን እንዳይመለከት አይኖቹን ይሸፍነዋል ። በመሆኑም ፈረሱ ወደ ግራም ሆነ ወደ ቀኝ አያማትርም የፊት ለፊቱን ብቻ እየተመለከ ይጓዛል ።

  ይሔ እውነት በተለይም ክርስቶስ ኢየሱስን አምኖ ዳግም ለተወለደ ክርስቲያን የግድ ግድ አስፈላጊ ነው  ። ወደ ግራም ወደ ቀኝም በሄድንበት በሙሉ አይናችን እንዳንኳትን ፣ ያየነው ሁሉ እንዳያምረን ፣ በመንገድ ሁሉ እየተደነቅን ፣  እየተገረምን እንዳንቆም በአይኖቻችን ዙሪያ የሚከል አንድ ወሳኝ ጉዳይ ያስፈልጋል ፤ እሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ነው ። የክርስቶስ መስቀል ወደ ሌላ ቦታ እንዳንመለከት ይከልለናል ፣ ሁሉን ጉዳይ ያቀልብናል ፣ የክርስቶስ ፍቅር ፣ ይቅርታ ፣ ምህረት ፣ መወደድ ፣ ፅድቅ ፣ ቅድስና ሁሉ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ..ያኔ ሁሉ በአይናችን ፊት ይቀላል ፣ እንደምናምንቴ እንድናይ ያረጋል ። የክርስቶስ መስቀል አለምን ፣ ሰይጣን ፣ ሀጢያት ፣ ሞት እንዳናይ የተለያየንበት የእግዚአብሔር የመንግስት ሚስጥር ፣ ፈቃድ ፣ ዕቅድ ፣ ህብረትን እንድንረዳ እና እንድንመለከት ያግዛል ።




@ownkin
@cgfsd
ፀጋ በህይወታችን ፀጋነቱ የሚታወቀው በእኛ በኩል ያለው ድካም በክርስቶስ ስራ በመሸፈኑ ነው ።
          (የዱባ ጥጋብ)


@ownkin
@cgfsd
ስጋውን ቆርሶ ፣ ደሙን አፍስሶ ድግስ የጠራው ጌታችን ኢየሱስ ብቻ ነው ። 

እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ በሞቴ ብሉኝ እያለ በተወጋው እጁ ሞቶ ያጎረሰን ጌታችን ኢየሱስ ❤️ ብቻ ነው ።

     (ኢየሱስ)


@ownkin
@cgfsd
(ደሙ ደምግባቴ)


ጌታ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ አይተነው እንወደው ዘንድ ደምግባት (ውበት) እንዳልነበረው መፀሀፍ ቅዱሳችን ይናገራል። በሰው አይን ምናልባት ሲታይ እዚህ ግባ የማይባል ሊወደድ የማችል ይሆናል ። ያፈሰሰው ደም ግን በእኛ ዘንድ ደምግባት አለው ደሙ ውበታችን ነው ። ደሙ ደምግባታችን ነው !!

በእርግጥም ያለጥርጥር የጌታችን የኢየሱስ ደም ደምግባታችን ነው ምክኒያቱም ደግሞ ለእኛ በፈሰሰው  የክርስቶስ ደም የተተረጎምን ፣ የህይወት ጣዕም ያገኘን ፣ በደሙ የተኳልን ፣ በደሙ የምንፈነድቅ ፣ በደሙ የፀደቅን ፣ በደሙ ያበራል ፣ በደሙ የተከለልን ፣ በደሙ መኖር መኖር የጓጓን የክርስቶስ ደም ፍሬዎች ስለሆንን ነው ።

ከክርስቶስ ደም በላይ ምን ውበት ፣ምን አይነት ትምክት አለን  በእርግጥም ደሙ ደምግባታችን ነው አዎን ደሙ ውበታችን ነው ።

@ownkin
@cgfsd
አስቀድሞ በዙፋኑ ያየኝን መስቀል ላይ አየሁት

            (ያየኝን አየሁት)


@ownkin
@cgfsd
ስለ ጌታ ሳስብ ስቅለቱ ይቀድመኛል፤ የተሰቀለው ስለው የተገኘሁበትን እውነት እና ፍቅር  ያስታውሰኛል ።

የተሰቀለው


@ownkin
@cgfsd
እግዚአብሔር ራሱ በፈጠረው አለም ምስኪን ሆኖ ገባ። ኅጢአት ወዳንኮታኮተው አለም የህማም ሰው ሆኖ መጣ። ዐመፃው ላዳሸቀውና በጠና ህማም ለሚያቃስተው የሰው ልጅ እግዚአብሔር ራሱን ቆረሰ። በባለሙያ አሰቃዮች እጅ በመገረፍ፣ በመዘለፍ፣ በመዋረድ እና በመስቀል በመቸንከር የዚህን አለም ውድቀት ግፍ በደስታ ተጎነጨ። ደሙን አፈሰሰ። ስጋውን ቆረሰ። በስቃዮና በፍዳው መኸል በእግዚአብሔርም ተተወ። በውድቀቱ ከእግዚአብሔር ለተለየው ፍጥረት እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ከፈለለት። እግዚአብሔር ለአለሙ ራሱን ሰጠለት። ከጠና ሕመሙ ፍጥረቱን ይፈውሰ ዘንድ አንድ ውድ ልጅ ተቸረው። ሰውን ከውድቀት ሸለቆ ያወጣው ዘንድ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠው።

ትዝ ይለኛል ያ መድኅኔ
በመስቀል ላይ የሞተው ስለኔ
ትውስ ይለኛል የመስቀል ፍቅሩ
ያደረገልኝ ውለታው ሁሉ

"ጥቂት የደም ጠብታ መላውን ዓለም ዐደሰው። በወተት ውስጥ ኾኖ ወተትን እንደሚያጣብቀው ፈሳሽ ደሙ የሰውን ዘር አንድ ላይ አያያዘው።" —ጐርጐርዮስ ዘኢንዚናንዙ (ኒዛናዙ)

Amanuel asegid

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ ሆይ ትንሳኤህ ሲገባን ከቀድሞ ይልቅ አብልጠን የመስቀሉን ስራ(ሞትህን) ወደድነው ።

@ownkin
@cgfsd
(  እግዚአብሔር ረክቷል )


እግዚአብሔር ቀድሞ በብሉይ ኪዳን ይቀርብ የነበረው የበግ ደም መስዋዕት ለመቀበሉ ሰዎች ማረጋገጫቸው  መብረቅ ወይም ንፋስ ከመስዋዕቱ መቅረብ በኋላ ሲታዩ በእርግጥ እግዚአብሔር መስዋዕቱን ተቀብሏል ብለው ያምናሉ ።

የእኛ መስዋዕት የበግ ደም አይደለም ንፁህ ፣ቅዱስ ፣ ህያው  የሆነው ራሱን አሳልፎ የሰጠው ኢየሱስ ነው ። የቀረበው መስዋትም በመስቀል ላይ ነበር ። እግዚአብሔር ግን በቀረበው መስዋት ተደስቷል ፣ ረክቷል ያኔ የአቤል መስዋዕት አይቶ የቃየልን ሊያይ እንዳልወደደ ሁሉ እግዚአብሔር በኢየሱስ መስዋትነት ብቻ ረክቷል። ለዛም ነው እንደ ብሉይ ኪዳን ነፋስ ወይም መብረቅ አምጥቶ መስዋቱን ተቀብያለሁ ያላለው !!  መቀበሉን ያረጋገጠል ክርስቶስን ከሙታን በማስነሳት ነበር ። እግዚአብሔር የክርስቶስን መስዋዕት መቀበሉን በዛም መርካቱን መደሰቱን ያወቅነው ክርስቶስን ከሙታን በማስነሳቱ ነው ። ትንሳኤ ማረጋገጫ ነው የእግዚአብሔር ርካታ እና ደስታ ።


@ownkin
@cgfsd
እግዚአብሔር ለእኛ ባደረገው የደም ኪዳን ታማኝ መሆኑን ያረጋገጥነው በክርስቶስ ትንሳኤ ነው ።

@ownkin
@cgfsd
በማይነቃነቅ ተስፋ የተሞላ ሰው ምን ይመስላል ??🤔

👇
  በክርስቶስ ትንሳኤ የታወደ ነዋ ።

    (ትንሳኤው ያውዳል )


@ownkin
@cgfsd
እጅግ አብልጠን ለክርስቶስ የመኖር ፍላጎት በህይወታችን ሞልቶ የሚተርፈው ከክርስቶስ ጋር አብረን ከሙታን  እንደተነሳን በቅጡ ስንረዳ ነው ።

ለክርስቶስ መኖር የትንሳኤ ኑሮ ነው ። ምክኒያቱም የራሳችን የመኖር ጉጉት ፣ አላማ ፣ መሻት መስቀል ላይ ከእርሱ ጋር ተሰቅሏል ለራሳችን እንዳንሆን እኛ  ተገለናል ። አሁን እኛነታችን የለም በመስቀሉ ሂሳብ ሙተናል !! አለን የምንለው ኑሮ በትንሳኤው የተቀጠለ ነው ። ትንሳኤ ደግሞ የክርስቶስን ህይወት ለመኖር ፤ ለእግዚአብሔር ህያው ለመሆን ነው የጀመርነው ።ትንሳኤ የኔን ሞት ለሞተልኝ ለእርሱ እኖራለሁ ያስብላል ....ትንሳኤ የኔን ሞት ሙቷል የእሱን ህይወት እኖራለሁ ያስብላል ...ትንሳኤ የኔን ሀጢያት ወስዶልኛል በእርሱ ፅድቅ ፀድቀናል ያስብላል ።

ለክርስቶስ መኖር በልባችን ውስጥ በብርቱ መሻት የምንፈልገው በትንሳኤው የክርስቶስን ህይወት ለመኖር እኛ ሙተን ለእርሱ በመነሳታችን  ነው ።




@ownkin
@cgfsd
(   ውዴ ኢየሱስ )


ኢየሱስ ውዴ ብሎ መጠራት ይቻላል ?? እንዴ በደንብ ይቻላል !!  ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ውዴ ብሎ መጠራት ከክብሩ ዝቅ እንደማድረግ ፣ አክብሮትን እንደመንፈግ ይቆጥሩታል ። እንደውም አንድ ሰው ብላችሁ ብላችሁ የቆሎ ጓደኛ አደረጋችሁት እንዴ ውዴ እያላችሁ የምትጠሩት ብሎ የተናገረም አልጠፋም ። በእርግጥም ግን ኢየሱስን ውዴ ብሎ መጠራት ከክብሩ ማውረድ ሳይሆን በክብሩ መረዳት ያሳያል እንጂ አያሳንሰውም ።

ሐዋሪያው ጳውሎስ  ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ ሲፅፍ ውድ ልጁ ብሎ ያስቀምጣል ። እንዴት አይነት አንጀት አርስ አገላለፅ ነው ውድ ልጁ (የተወደደ , የከበረ , ብርቅዬ, ) የሚል ትርጓሜ አለው ። ኢየሱስ ከአባቱ ከአብ ጋር በዘላለማዊ ህብረት አብሮ እንደመሆኑ በአባቱ ዘንድ የተወደደ ነው  ስለዚህ ምክኒያት ጳውሎስ ኢየሱስን ውድ ልጁ በማለት ተጠርቶታል ።

በእኛም ዘንድም ቢሆን የኢየሱስን ውድነት የቀመስነው በመዳናችን ነው ። በመዳናችኝ ምክኒያት አዳኛችን ኢየሱስ በእኛ ዘንድ ውድ እንደሆነ ገብቶናል ። መዳናችን የማይቀልብን አዳኛችን የቀለለ ፣ ያነሰ ስላልሆነ ነው ። ኢየሱስ ከዘላለም በመኖሩ በአባቱ ዘንድ ውድ እንደሆነ ሁሉ በእኛም ዘንድ በመዳናችን ምክኒያት ውድ ነው ።

   ውዳችን ኢየሱስ


@ownkin
@cgfsd
( ኢየሱስ )

ኢየሱስ አንተ ማለት ለኔ ምን ማለት እንደሆንክ የማቀው እኔ ነኝ #በደምህ የምኖር #ነፍስህ ነፍስ የሆነኝ

🎼🎧
@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ 
 
  * ተገፎ ልብስ ሆነን !! እርሱ ለብሰን ይሞቀናል ..እርሱን ለብሰን አምሮብናል..

* ተቆርሶ ምግብ ሆነን !! እርሱ በልተን ጠግበናል ..እርሱ በልተን ተስማምቶናል ...እርሱን በልተን የነፍስ ርሃባችን ተገፏል ።


@ownkin
@cgfsd
( አገልጋዩ አዳኝ)


ማን ይሆን እያገለገለ የሚያድን ?? በአንድ ጊዜ በወንጌል አድራሽነቱ የሚወሳው ዲኤል ሙዲ (evangelist) የመጋቢዎች ኮንፈራንስ (summer) ላይ ያሰናዳል ። ከእየ ሀገሩ መጋቢዎች፣ ወንጌላዊያን በብዛት ወደ አሜሪካ በዲኤል ሙዲ በተዘጋጀው ፕሮግራም ለመካፈል በተለይ ከአውሮፓ መጡ ። ባረፉበት ሆቴል የመጡት መጋቢዎች ጫማ የሚያፀዳላቸው ሰው ይፈልጉ ነበር ..በተለይ በአውሮፓ የተለመደ ነው ጫማ የሚያፀዱ እና ሌሎች አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች ነበሩ( hall servant)  በአሜሪካ ግን የለም ። እናም በምኝታ ክፍላቸው በር ላይ ጫማቸው አስቀምጠው እርሱ ወደ ክፍላቸው ገብተው ይተኛሉ ። አንድ ቀን ሙዲ እየተንቀሳቀሰ በሆቴሉ መኝታ ክፍሎች በር ላይ ጫማዎች በእየ በሩ አጠገብ ቁጭ ቁጭ ብለው ይመለከታል ። መጋቢዎች ወደ ክፍላቸው ሲገቡ ጠብቆ ጫማዎቹን ሰብስቦ ወስደ አፀዳቸው ...በድንገት ክፍሉ መተው ያዩት ወዳጆቹ ነበሩ ። ጠዋት ሲነሱ በራቸው ላይ የቆሸሸው ጫማ እያብረቀረቀ አምሮበታል እንደተፀዳ ገባቸው ። ግን ማን አፀዳ ብሎ ሲያወጡ ሲያወርዱ ...ሙዲ እንደሆኑ በድብቅ ያዩት ተናገሩ ።...ሙዲ ከታይታ ውጭ ዝና ሳይዘው ወንድሞቹ አገለገላቸው......
  ዝቅ ብሎ ማገልገል የልብ ጉዳይ ነው !!

ለአንድ አመት ያክል የተሰራን መሳሪያ በብዙ የሰው ሀይል እየተገፋ ይውል ይታደር ነበር ... አንድ ቀን ዋና አዛዥ ፣ገዢው አብሮ ወታደሮቹ ጋር ተቀላቅሎ ይገፋል ይሄን ያየ ወታደር ። በጣም አለቀሰ እንደ ክቡርነቶ እንዴት ከእኔ እኩል ይገፋሉ ። ....

ጌታችን፣ውዳችን ኢየሱስ ክርስቶስ  የመላ አለሙ ፈጣሪ፣ መለኮት ፣ገዚ፣ ዘላለማዊ፣መላዕክት የሚያመልኩት፣የሚያገለግሉት ሆኖ ሳለ እንደ አገልጋይ ሁኖ ወደ እዚህ ምድር ብቅ አለ ። በተለይ የማርቆስ ወንጌል መፀሀፍ ስናጠና ኢየሱስ ባለየንበት መልኩ ያሳየናል ያውም አገልጋይ ነው ብሎ ነዋ ። እንደውም  ኢየሱስ ራሱ እንደዚህ ተናገረ  ...
          ማርቆስ 10 (Mark)
45፤ እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።

ኢየሱስ እንድታገለግሉኝ አልመጣሁም ላገለግላችሁ እንጂ ብሎ እንቅጩን በማርቆስ ወንጌል ላይ ተናገረ ። ማርቆስ የክርቶስን አገልጋይነት ሲያስረግጥልን ... ወፎ ጎጆ አላት ቀበሮም ዋሻ ነበረው ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ  ቤት  አልነበረውም ይሔም ራሱን ሊያገልግል ሳይሆን ለሌሎች ለማልለልለ ያለውን ልብ ያስገነዝባል ።
  የሚገርመው የማርቆስ ወንጌል ኢየሱስ ካስተማራቸው ትምህርቶች ይልቅ ያደረጋቸው ድርጊት ፣ተአምራት ተጠቅሰዋል። አገልጋይ ደግሞ ድርጊት ፈፃሚ ሰሪ ነው ። ሌላ በዚህ ወንጌል ላይ ወዲያዉኑ ወዲያዉኑ ወዲያውኑ የሚለው ቃል ተደጋግሞ ይገኛል  ።ኢየሱስ ከአንድ ስራ ወደ ሌላ ስራ በፍጥትተ መሻሩረን ፍጥቱተን ያተኩራል ይሔ ተግባር የአገልጋይ ነው ።

በኢየሱስ  አገልጋይነት ውስጥ 2 ነገሮች እንመከታለለን
    1, ትህትና
ክርስቶስ ከልዕልና ("ከክብር) ወደ ትህትና ሰው በመሆኑ የወረደው (የእግዚአብሔር ልጅ) ... ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን እግር ሲያጥብ እያገገላለቸው ነበር  ስናስበው ዝቅ ማለት ብቻ  ሳይሆን በትህትና መቅረቡ ነበር ።

2, ፍቅሩ
ጌታ ሲያገለግል የነበረው ስለሚወዳቸው እና ደግሞ በወዳደቸው በእርሱ እንዲዋደዱ ነው።

ምን አይነት አዳኝ ነው ግን ዝቅ ብሎ ከፍቅር ከትህትና የተነሳ የሚያገለግል!!
 
በአለም ላይ አንድ የአመራር መንገድ አለ አገልጋይ መሪ(servant leadership )እንደዚህ አይነት አመራር ከክርስቶስ ነው የተማርነው የሚመራን ፣የሚያድነን የሚያስተዳድረን ሉአላዊው አምላክ አገለገለን ።

   አገልጋዩ አዳኝ😍 ኢየሱስ


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd