በክርስቶስ ( in christ)
694 subscribers
98 photos
34 videos
41 files
37 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
(ደሙ ደምግባቴ)


ጌታ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ አይተነው እንወደው ዘንድ ደምግባት (ውበት) እንዳልነበረው መፀሀፍ ቅዱሳችን ይናገራል። በሰው አይን ምናልባት ሲታይ እዚህ ግባ የማይባል ሊወደድ የማችል ይሆናል ። ያፈሰሰው ደም ግን በእኛ ዘንድ ደምግባት አለው ደሙ ውበታችን ነው ። ደሙ ደምግባታችን ነው !!

በእርግጥም ያለጥርጥር የጌታችን የኢየሱስ ደም ደምግባታችን ነው ምክኒያቱም ደግሞ ለእኛ በፈሰሰው  የክርስቶስ ደም የተተረጎምን ፣ የህይወት ጣዕም ያገኘን ፣ በደሙ የተኳልን ፣ በደሙ የምንፈነድቅ ፣ በደሙ የፀደቅን ፣ በደሙ ያበራል ፣ በደሙ የተከለልን ፣ በደሙ መኖር መኖር የጓጓን የክርስቶስ ደም ፍሬዎች ስለሆንን ነው ።

ከክርስቶስ ደም በላይ ምን ውበት ፣ምን አይነት ትምክት አለን  በእርግጥም ደሙ ደምግባታችን ነው አዎን ደሙ ውበታችን ነው ።

@ownkin
@cgfsd
አስቀድሞ በዙፋኑ ያየኝን መስቀል ላይ አየሁት

            (ያየኝን አየሁት)


@ownkin
@cgfsd
ስለ ጌታ ሳስብ ስቅለቱ ይቀድመኛል፤ የተሰቀለው ስለው የተገኘሁበትን እውነት እና ፍቅር  ያስታውሰኛል ።

የተሰቀለው


@ownkin
@cgfsd
እግዚአብሔር ራሱ በፈጠረው አለም ምስኪን ሆኖ ገባ። ኅጢአት ወዳንኮታኮተው አለም የህማም ሰው ሆኖ መጣ። ዐመፃው ላዳሸቀውና በጠና ህማም ለሚያቃስተው የሰው ልጅ እግዚአብሔር ራሱን ቆረሰ። በባለሙያ አሰቃዮች እጅ በመገረፍ፣ በመዘለፍ፣ በመዋረድ እና በመስቀል በመቸንከር የዚህን አለም ውድቀት ግፍ በደስታ ተጎነጨ። ደሙን አፈሰሰ። ስጋውን ቆረሰ። በስቃዮና በፍዳው መኸል በእግዚአብሔርም ተተወ። በውድቀቱ ከእግዚአብሔር ለተለየው ፍጥረት እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ከፈለለት። እግዚአብሔር ለአለሙ ራሱን ሰጠለት። ከጠና ሕመሙ ፍጥረቱን ይፈውሰ ዘንድ አንድ ውድ ልጅ ተቸረው። ሰውን ከውድቀት ሸለቆ ያወጣው ዘንድ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠው።

ትዝ ይለኛል ያ መድኅኔ
በመስቀል ላይ የሞተው ስለኔ
ትውስ ይለኛል የመስቀል ፍቅሩ
ያደረገልኝ ውለታው ሁሉ

"ጥቂት የደም ጠብታ መላውን ዓለም ዐደሰው። በወተት ውስጥ ኾኖ ወተትን እንደሚያጣብቀው ፈሳሽ ደሙ የሰውን ዘር አንድ ላይ አያያዘው።" —ጐርጐርዮስ ዘኢንዚናንዙ (ኒዛናዙ)

Amanuel asegid

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ ሆይ ትንሳኤህ ሲገባን ከቀድሞ ይልቅ አብልጠን የመስቀሉን ስራ(ሞትህን) ወደድነው ።

@ownkin
@cgfsd
(  እግዚአብሔር ረክቷል )


እግዚአብሔር ቀድሞ በብሉይ ኪዳን ይቀርብ የነበረው የበግ ደም መስዋዕት ለመቀበሉ ሰዎች ማረጋገጫቸው  መብረቅ ወይም ንፋስ ከመስዋዕቱ መቅረብ በኋላ ሲታዩ በእርግጥ እግዚአብሔር መስዋዕቱን ተቀብሏል ብለው ያምናሉ ።

የእኛ መስዋዕት የበግ ደም አይደለም ንፁህ ፣ቅዱስ ፣ ህያው  የሆነው ራሱን አሳልፎ የሰጠው ኢየሱስ ነው ። የቀረበው መስዋትም በመስቀል ላይ ነበር ። እግዚአብሔር ግን በቀረበው መስዋት ተደስቷል ፣ ረክቷል ያኔ የአቤል መስዋዕት አይቶ የቃየልን ሊያይ እንዳልወደደ ሁሉ እግዚአብሔር በኢየሱስ መስዋትነት ብቻ ረክቷል። ለዛም ነው እንደ ብሉይ ኪዳን ነፋስ ወይም መብረቅ አምጥቶ መስዋቱን ተቀብያለሁ ያላለው !!  መቀበሉን ያረጋገጠል ክርስቶስን ከሙታን በማስነሳት ነበር ። እግዚአብሔር የክርስቶስን መስዋዕት መቀበሉን በዛም መርካቱን መደሰቱን ያወቅነው ክርስቶስን ከሙታን በማስነሳቱ ነው ። ትንሳኤ ማረጋገጫ ነው የእግዚአብሔር ርካታ እና ደስታ ።


@ownkin
@cgfsd
እግዚአብሔር ለእኛ ባደረገው የደም ኪዳን ታማኝ መሆኑን ያረጋገጥነው በክርስቶስ ትንሳኤ ነው ።

@ownkin
@cgfsd
በማይነቃነቅ ተስፋ የተሞላ ሰው ምን ይመስላል ??🤔

👇
  በክርስቶስ ትንሳኤ የታወደ ነዋ ።

    (ትንሳኤው ያውዳል )


@ownkin
@cgfsd
እጅግ አብልጠን ለክርስቶስ የመኖር ፍላጎት በህይወታችን ሞልቶ የሚተርፈው ከክርስቶስ ጋር አብረን ከሙታን  እንደተነሳን በቅጡ ስንረዳ ነው ።

ለክርስቶስ መኖር የትንሳኤ ኑሮ ነው ። ምክኒያቱም የራሳችን የመኖር ጉጉት ፣ አላማ ፣ መሻት መስቀል ላይ ከእርሱ ጋር ተሰቅሏል ለራሳችን እንዳንሆን እኛ  ተገለናል ። አሁን እኛነታችን የለም በመስቀሉ ሂሳብ ሙተናል !! አለን የምንለው ኑሮ በትንሳኤው የተቀጠለ ነው ። ትንሳኤ ደግሞ የክርስቶስን ህይወት ለመኖር ፤ ለእግዚአብሔር ህያው ለመሆን ነው የጀመርነው ።ትንሳኤ የኔን ሞት ለሞተልኝ ለእርሱ እኖራለሁ ያስብላል ....ትንሳኤ የኔን ሞት ሙቷል የእሱን ህይወት እኖራለሁ ያስብላል ...ትንሳኤ የኔን ሀጢያት ወስዶልኛል በእርሱ ፅድቅ ፀድቀናል ያስብላል ።

ለክርስቶስ መኖር በልባችን ውስጥ በብርቱ መሻት የምንፈልገው በትንሳኤው የክርስቶስን ህይወት ለመኖር እኛ ሙተን ለእርሱ በመነሳታችን  ነው ።




@ownkin
@cgfsd
(   ውዴ ኢየሱስ )


ኢየሱስ ውዴ ብሎ መጠራት ይቻላል ?? እንዴ በደንብ ይቻላል !!  ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ውዴ ብሎ መጠራት ከክብሩ ዝቅ እንደማድረግ ፣ አክብሮትን እንደመንፈግ ይቆጥሩታል ። እንደውም አንድ ሰው ብላችሁ ብላችሁ የቆሎ ጓደኛ አደረጋችሁት እንዴ ውዴ እያላችሁ የምትጠሩት ብሎ የተናገረም አልጠፋም ። በእርግጥም ግን ኢየሱስን ውዴ ብሎ መጠራት ከክብሩ ማውረድ ሳይሆን በክብሩ መረዳት ያሳያል እንጂ አያሳንሰውም ።

ሐዋሪያው ጳውሎስ  ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ ሲፅፍ ውድ ልጁ ብሎ ያስቀምጣል ። እንዴት አይነት አንጀት አርስ አገላለፅ ነው ውድ ልጁ (የተወደደ , የከበረ , ብርቅዬ, ) የሚል ትርጓሜ አለው ። ኢየሱስ ከአባቱ ከአብ ጋር በዘላለማዊ ህብረት አብሮ እንደመሆኑ በአባቱ ዘንድ የተወደደ ነው  ስለዚህ ምክኒያት ጳውሎስ ኢየሱስን ውድ ልጁ በማለት ተጠርቶታል ።

በእኛም ዘንድም ቢሆን የኢየሱስን ውድነት የቀመስነው በመዳናችን ነው ። በመዳናችኝ ምክኒያት አዳኛችን ኢየሱስ በእኛ ዘንድ ውድ እንደሆነ ገብቶናል ። መዳናችን የማይቀልብን አዳኛችን የቀለለ ፣ ያነሰ ስላልሆነ ነው ። ኢየሱስ ከዘላለም በመኖሩ በአባቱ ዘንድ ውድ እንደሆነ ሁሉ በእኛም ዘንድ በመዳናችን ምክኒያት ውድ ነው ።

   ውዳችን ኢየሱስ


@ownkin
@cgfsd
( ኢየሱስ )

ኢየሱስ አንተ ማለት ለኔ ምን ማለት እንደሆንክ የማቀው እኔ ነኝ #በደምህ የምኖር #ነፍስህ ነፍስ የሆነኝ

🎼🎧
@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ 
 
  * ተገፎ ልብስ ሆነን !! እርሱ ለብሰን ይሞቀናል ..እርሱን ለብሰን አምሮብናል..

* ተቆርሶ ምግብ ሆነን !! እርሱ በልተን ጠግበናል ..እርሱ በልተን ተስማምቶናል ...እርሱን በልተን የነፍስ ርሃባችን ተገፏል ።


@ownkin
@cgfsd
( አገልጋዩ አዳኝ)


ማን ይሆን እያገለገለ የሚያድን ?? በአንድ ጊዜ በወንጌል አድራሽነቱ የሚወሳው ዲኤል ሙዲ (evangelist) የመጋቢዎች ኮንፈራንስ (summer) ላይ ያሰናዳል ። ከእየ ሀገሩ መጋቢዎች፣ ወንጌላዊያን በብዛት ወደ አሜሪካ በዲኤል ሙዲ በተዘጋጀው ፕሮግራም ለመካፈል በተለይ ከአውሮፓ መጡ ። ባረፉበት ሆቴል የመጡት መጋቢዎች ጫማ የሚያፀዳላቸው ሰው ይፈልጉ ነበር ..በተለይ በአውሮፓ የተለመደ ነው ጫማ የሚያፀዱ እና ሌሎች አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች ነበሩ( hall servant)  በአሜሪካ ግን የለም ። እናም በምኝታ ክፍላቸው በር ላይ ጫማቸው አስቀምጠው እርሱ ወደ ክፍላቸው ገብተው ይተኛሉ ። አንድ ቀን ሙዲ እየተንቀሳቀሰ በሆቴሉ መኝታ ክፍሎች በር ላይ ጫማዎች በእየ በሩ አጠገብ ቁጭ ቁጭ ብለው ይመለከታል ። መጋቢዎች ወደ ክፍላቸው ሲገቡ ጠብቆ ጫማዎቹን ሰብስቦ ወስደ አፀዳቸው ...በድንገት ክፍሉ መተው ያዩት ወዳጆቹ ነበሩ ። ጠዋት ሲነሱ በራቸው ላይ የቆሸሸው ጫማ እያብረቀረቀ አምሮበታል እንደተፀዳ ገባቸው ። ግን ማን አፀዳ ብሎ ሲያወጡ ሲያወርዱ ...ሙዲ እንደሆኑ በድብቅ ያዩት ተናገሩ ።...ሙዲ ከታይታ ውጭ ዝና ሳይዘው ወንድሞቹ አገለገላቸው......
  ዝቅ ብሎ ማገልገል የልብ ጉዳይ ነው !!

ለአንድ አመት ያክል የተሰራን መሳሪያ በብዙ የሰው ሀይል እየተገፋ ይውል ይታደር ነበር ... አንድ ቀን ዋና አዛዥ ፣ገዢው አብሮ ወታደሮቹ ጋር ተቀላቅሎ ይገፋል ይሄን ያየ ወታደር ። በጣም አለቀሰ እንደ ክቡርነቶ እንዴት ከእኔ እኩል ይገፋሉ ። ....

ጌታችን፣ውዳችን ኢየሱስ ክርስቶስ  የመላ አለሙ ፈጣሪ፣ መለኮት ፣ገዚ፣ ዘላለማዊ፣መላዕክት የሚያመልኩት፣የሚያገለግሉት ሆኖ ሳለ እንደ አገልጋይ ሁኖ ወደ እዚህ ምድር ብቅ አለ ። በተለይ የማርቆስ ወንጌል መፀሀፍ ስናጠና ኢየሱስ ባለየንበት መልኩ ያሳየናል ያውም አገልጋይ ነው ብሎ ነዋ ። እንደውም  ኢየሱስ ራሱ እንደዚህ ተናገረ  ...
          ማርቆስ 10 (Mark)
45፤ እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።

ኢየሱስ እንድታገለግሉኝ አልመጣሁም ላገለግላችሁ እንጂ ብሎ እንቅጩን በማርቆስ ወንጌል ላይ ተናገረ ። ማርቆስ የክርቶስን አገልጋይነት ሲያስረግጥልን ... ወፎ ጎጆ አላት ቀበሮም ዋሻ ነበረው ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ  ቤት  አልነበረውም ይሔም ራሱን ሊያገልግል ሳይሆን ለሌሎች ለማልለልለ ያለውን ልብ ያስገነዝባል ።
  የሚገርመው የማርቆስ ወንጌል ኢየሱስ ካስተማራቸው ትምህርቶች ይልቅ ያደረጋቸው ድርጊት ፣ተአምራት ተጠቅሰዋል። አገልጋይ ደግሞ ድርጊት ፈፃሚ ሰሪ ነው ። ሌላ በዚህ ወንጌል ላይ ወዲያዉኑ ወዲያዉኑ ወዲያውኑ የሚለው ቃል ተደጋግሞ ይገኛል  ።ኢየሱስ ከአንድ ስራ ወደ ሌላ ስራ በፍጥትተ መሻሩረን ፍጥቱተን ያተኩራል ይሔ ተግባር የአገልጋይ ነው ።

በኢየሱስ  አገልጋይነት ውስጥ 2 ነገሮች እንመከታለለን
    1, ትህትና
ክርስቶስ ከልዕልና ("ከክብር) ወደ ትህትና ሰው በመሆኑ የወረደው (የእግዚአብሔር ልጅ) ... ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን እግር ሲያጥብ እያገገላለቸው ነበር  ስናስበው ዝቅ ማለት ብቻ  ሳይሆን በትህትና መቅረቡ ነበር ።

2, ፍቅሩ
ጌታ ሲያገለግል የነበረው ስለሚወዳቸው እና ደግሞ በወዳደቸው በእርሱ እንዲዋደዱ ነው።

ምን አይነት አዳኝ ነው ግን ዝቅ ብሎ ከፍቅር ከትህትና የተነሳ የሚያገለግል!!
 
በአለም ላይ አንድ የአመራር መንገድ አለ አገልጋይ መሪ(servant leadership )እንደዚህ አይነት አመራር ከክርስቶስ ነው የተማርነው የሚመራን ፣የሚያድነን የሚያስተዳድረን ሉአላዊው አምላክ አገለገለን ።

   አገልጋዩ አዳኝ😍 ኢየሱስ


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ለዘላለም እንጂ ለዛሬ አልሰራም #ስለ ህይወት እንጂ ለመበል አልሰራም #ኢየሱስ እውነቴን መቼ አላስነካም።

🎼

@ownkin
@cgfsd
ተስፋ ስም አለው! - ኢየሱስ

Yamlak

@ownkin
@cgfsd
አልተካህም - Hawaz Tegegn
ተወዳጁ የደስታዬ እልልታ
.        አልተካህም
 ዲ/ን ሐዋዝ ተገኝ - Live
@yedestaye_elilta
@yedestaye_elilta
           △Join Us
( ቁስልን በቁስል )


ሀኪምን እና ህመምተኛ ያገናኛቸው ዋና አላማ ፈውስ ነው ። ህመምተኛው አንዳች ለፈውስ የሚሆን መድሃኒት እየናፈቀ ከሀኪም ዘንድ አብዝቶ ይመላለሳል። ምን ያስደስተሃል ቢባል ካለብኝ ደዌ ፈፅሞ መፈወስ በማለት መልስ ይሰጣል ።

ከሰው ልጅ በላይ ደዌ ያደቀቀ ከወዴት ይገኛል???  በጥቅልሉ ሰው ታሟል !! ሀጢያት እያሳደደው ቁስሉን ይመዘምዝበታል፤ ህመሙን ያበዛበታል  ። ከሁሉ የሚበልጠው ደግሞ በሀጢያት ከመውደቃችን  የተነሳ ከተፈጠርንበት አላማ ማለትም ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ህብረት መለየታችን ይብሱን ያማል አዎን ከአምላክ ህልውና መጉደል እንዴት ያም ይሁን ?? እንጃ😭 !!!

መታከም አስፈለገን !! ያውም የማያዳግም ህክምና ግድ አለን ። ቁስላችን የሚያክ ሳይሆን ከስር መሰረቱ ነቅሎ የሚጥል ፍቱን የሆነ ህክምና አሰኝቶናል ። ምን መሰኘት ብቻ እውነትም ለእኛ እውነተኛ የሆነ ሰማያዊ ህክምና በምድር ላለን ለእኛ ተገኝቷል ። ህክምናው በእጅጉ ከአይምሮ በላይ ነው ። ሀኪሙ ...ኢየሱስ ፣ መድሃኒቱ..ኢየሱስ ፣ ፈዋሹ ...ኢየሱስ ፣ ቁስለኛው...ኢየሱስ ...ወይ ጉድ እንዴት ያለ ህክምና ይሆን ??😭

ቁስላችንን በቁስሉ አሻረው በሚፈሰው ክቡር ደሙ ቁስላችን ታጠበ ፣ በቁስሉ የቁስላችንን ህመም ወሰደ (የህማም ሰው ተባለ) ፣ ቁስሉ  ምንም ጠባሳ የማያስቀር መድሃኒት ሆነን  ፣ በቁስሉ ውስጥ አይዞአችሁ ወዳችኋለው አለን።  ጴጥሮስ ይሆን አይቶ እኮ ነው በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ ያለው ። ከእግዚአብሔር ጋር የለያየን ያንን ክፉ በሽታ ፣ደዌ ፣ ህመም ማለትም የሀጢያት በሽታ በመገረፉ ቁስሉ ፣ በመስቀል ላይ የመዋረድ ጥግ ህመም  ቁስላችን ወሰደው ፣ የሀጢያት አበሳችን ነቀለው ወደ እግዚአብሔር ወደ ልጁም ህብረት ሳበን ፣ ጠራን ። አሜን የሚያድን ፣ የሚፈውስ፣ ወደ ህይወት የሚጣራ ቁስል የጌታ የኢየሱስ ቁስል ብቻ ነው ።

ጌታ ኢየሱስ ቁስለኛው ፈዋሽ ፣ ህመምተኛው ሀኪም ፣ ቁስለኛው መድሃኒት ነው ።ቁስላችን በቁስሉ አሻረው ።



ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
( የህዝቡ አንበሳ )


 
 እግዚአብሔር ህዝብ አለው ። በስሙ የተጠራለት ፣ለእርሱ የሚወግን ፣ ለመንግስቱ የሚያደላ ፣ ከእርሱ ለእርሱ የሆነ ህዝብ አለው !!

ይሔ ህዝብ ከየትኛው ወገን በተለየ መልኩ የሚመላለስበት እሴት ይለየዋል ።እነዚህ እሴቶች ሰማያዊ መልክ ያላቸው መንፈሳዊ እውነት ያዘሉ መርህ ናቸው ። እነዚህም :- ፍቅር ፣ ተስፋ ፣እምነት ናቸው ። በእነዚህ እሴቶች ይሔ ህዝብ ወደ ላይ ከአምላኩ ጋር በእምነት ይወዳጃል ፣ ወደጉን እርስ በእርሳቸው አልፎም ከሌሎች ወገኖች ጋር በፍቅር ይዘረጋል ፣ በእምነት እና በፍቅር የጨበጣቸውን እውነቶች በተስፋ ይኖራል ። እንዴት የታደለ ህዝብ ይሁን ??


የህዝቡ ታሪክ ቢታይ በዚህ አለም ኑሮ እንደምናውቃቸው የሃገረ መንግስት ግንባታ በታላላቅ አብዮቶች የጎለመሰ ወገን አይደለም ። አለማችን ላይ በአብዮት ያልተቀጣጠለ ፣ ያልተቀጠለ የህዝብ ክፍል አለ ለማለት ያዳግታል ። ይሔ ህዝብ ግን ያለ አንዳች የሰዎች አመፅ ፣ የሁኔታዎች ጋጋታ የቆመ ህዝብ ነው ። የኋሊት ተጉዘን የእግዚአብሔር ህዝብ ታሪክ ብንቃኝ ጎልቶ የሚታየው መነሻው ጎልጎታ ነው እርሱም የጎልጎታው ገድል ነው ።   አንዴ የተደረገ ነገር ግን ዘላለማዊ የሆነ ገድል በእነርሱ ላይ ይውለበለባል ። ጀግናዋ ደግሞ በቀራንኒዮ ላይ እርቃኑ ፣ ተዋርዶ የተሰቀለው መሲህ(ክርስቶስ) ነው። በዚህ ህዝብ ከእርሱ ከተሰቀለው ውጪ አንዳች ጉዳይ የላቸው ነጋ ጠባ ፣ መሸ ሄደ የሚደጋገመው ፣ የማያረጀው ህያው ዜና ይሔው ነው ። የተሰቀለው በዚህ ህዝብ ዘንድ አይሰለችም ፣ አይቀልም እንደ እንደዘበት አይታይም መስቀሉ ደግሞ ምልክታቸው ብቻ ሳይሆን ህይወታቸውም ጭምር ነው ። በህይወታቸው ተሸክመውት ይዞራሉ መስቀሉን በመሸከም ጀግናቸው ይመስላሉ ።

ምንስ ሲሆን ጀግናቸው ሆነ  ??
ዘመን በሌለው እሱነቱ ዘመን ኖረው፣  በማይወሰነው እሱነቱ በስጋ ተወስኖ ፣ በማይዋረደው ክብሩ ስለ ሰው ተዋርደ ፣ የአርያምን ርቀትን እንደቁብ ሳይቆጥር ጨክኖ መጣ ፣ የአባቱን እቅፍ ሊተረክ በሌሎች እቅፍ ስር ብቅ አለ ።  ከእርሱ በቅር ማን ጀግና ሊኖር ይሁን ??ለንግስና አይዋደቅም ሁሉ በእጁ  ነው ። ዙፋን አያጓጓውም ለሌሎች ብቻ እየቃተተ ለመሞት የመስቀልን ጉዞ ይጓዛል ። ወትሮም በእየ አደባባዪ ፣ በእየ ምስባኳ፣ በእየ ክብረ በአሏ እሱ በደመቀ ልብ ታሳዋለች ። የህዝቡ አንበሳ እንደ በግ ለእርድ የተሰቃየው መሲሁ ኢየሱስ ነው ።

የህዝቡ ታሪክ ከተሰቀለው መሲህ ላይ ይመሰረታል ። በደም የተሰራ ፣ በክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ድንኳኑን የጣለ ህዝብ ነው ። ይሔም ህዝብ የእግዚአብሔር ህዝብ (ቤተክርስቲያን ) በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው ወደ እግዚአብሔር መንግስት የተጨመሩ ፣ ወደ ፍቅሩ የፈለሱ ፣ሰማያዊ ወገኖች ፣ የንጉስ ካህናት ፣ የጌታ ቅዱሳን ናቸው ።



ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
መዳፉ ላይ ቁስል ካያችሁ #የህመም ሰው ካስተዋላችሁ #ውዴ እርሱ ነው #ነፍሴን የያዛት #በእንቁ ሳይሆን በደም የገዛት 😭


🎼
@ownkin
@cgfsd