(ኢየሱስ ያስቀናል )
የፈንሳዩ የጦር አበጋዝ ናፖሊዮ ቦናባርቴ በርከት ያሉ የውጊያ ድሎች አስመዝግቧል፣ ብዙዎች ማርኳል ነገር ግን ስለ ጌታ ኢየሱስ ማራኪነት ተደንቆ ያለ ጠብመንጃ ሚሊየኖች በፍቅር እንደሚከተሉት በአግራሞት ተናግሯል ። የክርስቶስ ማንነት በእጅጉ የሚገዛው በሰባአዊነቱ የሚጠቀሰው ማህተመ ጋንዲ የኢየሱስ ባህሪ ለዕድሜ ዘመኑ እንደጠቀመው ፣ ስብዕናው ውስጡ እንደሚገዛው አትቷል ።አለም በመዝገቧ ከትባ ያስቀመጠቻቸው ታላላቅ ሰዎች በናዝሬቱ ኢየሱስ የተነሳ እየተገረሙ ወቸው ጉድ በማለት እጃቸውን በአፋቸው አጣምረው ጭነዋል ። በአሜሪካን ለሰው ልጆች እኩልነት ወገቡን አስሮ በቀዳሚነት ዘብ የቆመው ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ ይላል "ኢየሱስ ለፍቅር ፣ ለእውነት ፣ ለመካምነት ፅንፈኛ ነበር " በማለት ሀሳቡን አጋርቷል ። በዘመነ አብርሆት ለአለም መንቃት አስተፆ የተጫወተው ፈላስፋው ሩሶ ደግሞ በበኩሉ "ሶቅራጥስ እንደ ፈላስፋ ሞተ ኢየሱስ ግን እንደ እግዚአብሔር ሞተ " በማለት እይታውን አስቀምጧል ።
የቀጠናው አስተዳዳሪ ሔሮዶስ እልፍ እየተከተሉት እንደሆነ በተአምራቱ እና በትምህርቱ አካባቢውን አልፎ ዙሪያ ገባውን የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደሞላ ሲሰማ ስለ ስልጣኑ ስጋት ቢኖረው እሱን ሊሰማ ይናፍቅ ነበር ። መሲሁ ኢየሱስ ላይ ጥርስ የነከሱት የካህናት አለቆች ወታደር አሰማርተው ተጠፍንጎ እንዲመጣ ትዕዛዝ ቢሰጡም የተላኩት ወታደሮች ግን በማንነቱ ፣ በትምህርቱ እና በስራው ተመስጠው የተላኩበትን ረስተው ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ስለ ንፅህናው ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል ። የሸንጎ አባሉ ፈሪሳዊው ኒቆዲሞስ ኢየሱስን ለማወቅ በሌሊት ያለበት ድረስ አነፍንፎ መቷል ። ኢየሱስ ያስቀናል !! እንስማህ፣ እንይህ፣ እንንካህ ፣እንከተልህ ያስብላል ።
በጨዋታችን መሃል አንድ የምቀርበው ወዳጄ በቤተክርስቲያን መሃል ስለተንሰራፋው ክርስቶስን ስለማይመስለው ልምምዳችን ሲያስብ እንዲህ ይለኛል " እኔ ግን አይገባኝም ክርስቶስን እንዲህ አለውቀውም ኧረ እኔ ኢየሱስ እንደዚህ አላውቀውም ..ይገርምሃል ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝ አድርጌ የተቀበልኩት በመፀሀፍ ቅዱስ የዕለት ተለዕለት ጥናት ወቅት ነበር ። በተለይም ደግሞ የወንጌል መፀሀፍት ማቴዎስ ፣ ማርቆስ ፣ሉቃስ እና ዩሀንስ ወንጌላት ላይ ያነበብኩት ጌታ ባህሪው፣ ትህትናው ፣ ፍቅሩ ፣ አላማው ፣ ታዛዥነቱ ያስቀናኝ ነበር " በማለት አውግቶኛል ። በትክክል !! በተጨባጭ !!! ለዚህም ነው የዕውቀት ቀንዲሉ ሊቁ አልበርታን አንስታይል እንዲህ ያለው " ማንም የኢየሱስን እውነተኛነትን ሳይሰማ ወንጌልን ማንበብ አይችል " ያለው። ይሔው ነው !! የወንጌል መፀሀፍት ስናነብ የኢየሱስ የማንነት ውበት ይወረናል ፣ የባህሪው ማራኪነት ይማርከናል፣ አስደናቂነቱ ቀልባችንን ይገዛዋል ። የህይወት ታሪክ አይደለም አምላክ በስጋ የኖረው ህይወት እንጂ ። በቃ እንዲህ ነው የክርስትና ወጉ ኢየሱስን ከሰማበት ፣ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ መመረቅ ለሌለው ጊዜ ዘወትር በውስጥ እየተቃጠሉ ፣ እጅ እየነሱ መኖር ።
ኢየሱስ ያስቀናል
✍ ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd

(ጌታ ኢየሱስ )
የራሴ ድምፅ ብዙ ጊዜ ረበሽኝ ፣ እኔነቴ ያለ ቅጥ መፈናፋኛ አሳጣኝ ፣ ድካሜ ጉልበቴን ለግሞ ያዘኝ ፣ የምሰማው ነገር አስደነገጥ በዚህ ሁሉ ግን ስምህ መማፀኛ ግንብ ሆነኝ ። በዙሪያ ካሉት ሁሉ ዘልዮ አመለጥኩበት ። ቃላት አጥቼ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ እያለኩ ለማምለጥ ጠራሁት ነገር ግን ማምለጡን ረስቼ የጠራሁት ስምህ ጣፈጠኝ ጌታ ኢየሱስ ብዬ ሳልጨርስ ከእንደገና ስሙን መጥራት ናፈቀኝ ። ጌታ ኢየሱስ ስለው የተወጋው ጎኑ ትውስ ይላል፣ጌታ ኢየሱስ ስለው የፈሰሰው ደሙ እንደ ወንዝ ጅረት በአይነ ህሊናዬ እልፍ ይላል፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው በመስቀል እንደ ተንጠለጠ ወድሃለው ሲለኝ ይሰማኛል ፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው ልክ በሌለው ጭንቀቴ ውስጥ ልክ የሌለው ሰላሙ ይፈሳል፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው ሀዘን ጥላውን ባጠላብኝ ነፍሴ ውስጥ ደስታው እንደ ማለዳ ፀሀይ ይፈነጥቅብኛል ፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው በውስጤ ያለው ቅዱሱ መንፈስ ደግሜ እንድጠራው ጉልበት ይሆነኛል ።
ሰሞኑን ብዙ ተጨነኩ ፣ ብዙ አዘንኩ ፣ብዙ አነባሁ ፣ ብዙ ተልፈሰፈስኩ እና ብዙ ብዙ ልል አስቤ ልፀልይ ተንበረከኩ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ብዬ ስጣራ በአንድ ቃል ብዙ ተነፈስኩ ፣ አረፍኩ ፣ እፎይይ አልኩ !!
ጌታ ኢየሱስ😍

የተሳለው መልኩ
ከሀምሳ አመታት በላይ አስቆጥሯል አንድ ስመጥር የሀገሪቱ ሹም ወደ ገጠር ከአንድ አማረኛ ከሚችል ፈረንጅ ጋር እግር ጥሎት ይሄዳል ። የስራ ጉዳያቸውን እያጧጧፉ እያለ አንዲት እናት እየሮጠች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስትል ወደ ፈረንጁ ተጠጋች ። ፈረንጁም አማረኛ ይችል ኖሯል ሳቁን ለቀቀው ያ ሹም ግን ደነገጠ አፈረ ተሸማቀቀ ።
(የታሪኩ ምንጭ (መልህቅ በዘነበ ወላ))
ይሔን ታሪክ ማውጠንጠን ስጀምር የተሳለብን ስዕል እንዴት ነው የሚል ጥያቄ ውስጤ ላይ ፈነጠቀ ።
ክርስቶስ ሲባል በዘልማድ እንደዛች እናት ፈረንጅ ሁሉ ወይስ በልጅነታችን ለገና እና ለፋሲካ በቴሌቭዥን መስኮት የምንከታተለው ክርስቶስ ሆኖ ፊልም ላይ የሚተውነው መልከመልካም ሰው ድቅን ይልብን ይሆን??? ደግሞም ይሆናል ብዙዎቻችን ይህን ስናይ ስላደግን ስንፀልይ ወይም ጌታን ስናስብ ያ ክርስቶስ ሁኖ የተወነው ተዋናይ በሀሳባችን መምጣቱ የማይቀር መሆኑን አያከራክረንም !
በመጀመሪያው ገላቲያ ላይ ተስሎ እንደነበረው የክርስቶስ ኢየሱስ መልክ ዛሬም በዚህ ዘመን ላለን ሁላችን ኢየሱስ እንደተሰቀለ መንፈስ ቅዱስ ሊስልብን እና በደማቁ ሊያደምቅብን ግድ ይላል !!!!
ትክክለኛው የክርስቶስ ማንነት ነፍሳችን ላይ እንዲሳል መንፈስ ቅዱስ ይርዳን ።