በክርስቶስ ( in christ)
694 subscribers
98 photos
34 videos
41 files
37 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
ኢየሱስ ብቻውን ነው ድል የነሳው ድሉ ግን የተቆጠረው ለእኛም ጭምር ነው ።

@ownkin
@cgfsd
በ1970 ዓ.ም በዚሁ ከተማ Wilmore - Asbury university ታላቅ መነቃቃት ሆኖ ነበር ይላሉ ታሪኩን የሚያውቁ ሰዎች። በወቅቱ ለ144 ሠዓታት የጸሎት፣ የዝማሬ፣ የቃል ትምህርትና የንስሓ ጊዜ እንደነበር ያስታውሳሉ። ከዚያም በኋላ ታላቅ የወንጌል ሥርጭት ተካሂዶ በርካታዎች ወደ ጌታ የመጡበት ጊዜ ነበር ይላሉ።

ባለፈው ረቡዕ ዕለት ጠዋት Feb. 8, 2023 በተለመደው የዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ጸሎት ወቅት (regular chapel) በHughes መታሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነበር የመንፈስ ቅዱስ እሳት በወጣት ተማሪዎች ውስጥ የተቀጣጠለው። ከጠዋቱ 10:00AM በተለመደው ሁኔታ አምልኮውን የሚመሩ ወጣቶች ለአገልግሎት ቆሙ። ማቆም ተሳናቸው። ሰዎች ያለቅሳሉ፣ ንስሓ ይገባሉ፣ አንዱ ሌላው ላይ እጁን እያኖረ ይጸልያል በቃ ቀጠለ። ዘመሩ፣ በየመሐሉ ጸለዩ፣ ቀጠሉ ቀጠሉ። ያልተገኙ ተማሪዎችና ፕሮፌሰሮች ተጨመሩ፣ የቤተ ክርስቲያን መጋቢዎች የሌላ ከተሞች አገልጋዮች ወደ አዳራሹ መግባት ጀመሩ። የሚገባ እንጂ የሚወጣ ሳይኖር መሸ። ነጋ፣ መሸ፣ ሌላም ቀን ነጋ ይኼው ዛሬ ሳምንት ሆኖታል። ❤️

ሰዎች ከተለያዩ ከተሞች ከተለያዩ ግዛቶች ይመጣሉ። ይቀጣጠላሉ። አንዱ ይሄዳል ሌላው ይመጣል… አንዱ ያለቅሳል፣ ሌላው ይደሰታል፣ … ሌላው ይመሰክራል፣ ሌላው ይንበረከካል፣ ሌላው ይያያዛል፣ ሌላው ይዘምራል፣ ሌላው እጁን ወደ ላይ ያነሳል፣ ሌላው ዝም ብሎ ይቀመጣል፣ ሌላው ይነሳና መድረክ ላይ ወጥቶ መልዕክት ያስደምጣል። የጊዜ ጉዳይ የሥራ ጉዳይ የሌክቸር ጉዳይ የሪሰርች ጉዳይ ማን ያስባል? “Lord I need you every hour I need you” ይላሉ። “Way maker, miracle worker, promise keeper” ይላሉ። የክፍል ጓደኞቼ ሲነግሩኝ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ነው። ነገ ሄጄ እስክሳተፍ ልቤ ቸኩሏል። 😲😲

ቤተ ክርስቲያን ትንቃ ትነቃቃም።

werkneh koyera

@ownkin
@cgfsd
መቼ ነበር ልገልፀው በማልችለው የእግዚአብሔር አብሮነት እያለቀስሁ በጉልበቴ የወደቅሁት?

መቼ ነበር ከተንበረከክሁበት መነሳት የሞት ያህል ከብዶኝ የነበረው?

መቼ ነበር ፍፁም በሆነ የእግዚአብሔር ፍቅር ልቤ የተሞላው?

መቼ ነበር . . .

የሰሞኑ የ Asbury University የመንፈስ ቅዱስ "እንቅስቃሴ" ራሴን እንዲህ እንድጠይቅ አስገድዶኝ ነበር: በእኔ ቁጥጥር ስር እንዳልሆነና በመፍጨርጨር እንደማላመጣው አውቃለሁ፣ ነገር ግን ምን ያህል የዚህ ንፋስ ርሃብተኛና ጥማተኛ ነኝ ብዬ ከመጠየቅ አልታቀብሁም::

ሰሞኑን በፖለቲካና በሃይማኖት በሰከርንበት ወቅት Asbury University ውስጥ ሰዎች በመንፈስ "ይሰክሩ" ነበር::

ክርስትና ከእግር ጥፍር እስከራስ ጠጉር ድረስ በዶክትሪን ጢም ብሎ መሞላት ብቻ ከሆነ How boring would it be. እንደዛ አይነት ክርስትና የሰው ጥበብ እንጂ የእግዚአብሔር ጥበብ የሚገለጥበት አይደለም:

What we missed is not theology as such but God - about whom our theology is all about.

እግዚአብሔር ሲፈቅድልን ብቻ የምንገባበት የላቀና የሰው እጅ ያልነገሰበት ሕይወት አለ: ከጅረቱ ስር ነፍሳችን በውሃ ጥም እንዳትሞት እግዚአብሔር ወደዛ ጅረት ያስገባን::

Yilu danu
@ownkin
@cgfsd
በጎቹ የበሉት ብቸኛ እረኛ ኢየሱስ ይባላል ።

  melos

@ownkin
@cgfsd
ከAsbury ሪቫይቫል 2023 ምን ተማርኩ?

1. Revival እግዚአብሔር በወደደው ጊዜና ቦታ ከወደዳቸው ሰዎች ጋር የሚሠራው ነገር መሆኑን ነው። እንደ እኔ ከየአገሮች የሥነ መለኮት ትምህርታቸውን ለመከታተል የመጡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ለሌላ የአገልግሎት ኃላፊነት ራሳቸውን የሚያዘጋጁ “አዋቂም ታዋቂም” የሆኑ ማስትሬታቸውን ዶክትሬታቸውን የሚያጠኑ ትጉሃን የሰሚነሪ ተማሪዎች ከመንገዱ ማዶ አሉ። አልፎአቸው ሄደና ከመንገዱ ወዲያ በሚገኙ “ገና ምናቸውንም አልለዩም” በሚባሉ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ሊሠሩ በመጡ ለግላጋ ወጣቶች መካከል ነው ይህንን ያልተጠበቀ እሳት ጌታ የጣለው። የኛ ጸሎት ትጋት ያመጣው፣ የኛ መንፈሳዊ ልምምድ ያስከተለው፣ የኔ ቅድስና ያወረደው፣ የኔ የስብከት ብቃት ያመጣው የሚል ተጠሪ ማንም እንዳይኖር አድርጓል። የተለየ ሰው እንዳይጠራ ሌላው ይቅርና የአንድ ቤተ እምነትም ብቻ (የሜቶዲስት የባፕቲስት) ምናምን እንዳይሆን ለአገርና ለዓለም እንዲሆን university ውስጥ ማድረጉን መረጠው የሚል ትምህርት አግኝቼበታለሁ።

2. እውነተኛ revival የመንፈሳዊ ረሃብና የመንፈሳዊ ጥማት ምላሽ መሆኑን ነው። መጠማት ጌታን ነው። መራብ ጽድቅን ነው። ሕልውናውን አብሮነቱን ራሱን ጌታን ነው። ያ ሲሆን ጌታ የሚሰጠው ምላሽ እንዲህ ያለ revival ነው። አሁን በአገሪቱ ያለውን አምላክ ጠል የክህደት አካሄድ፣ የሥነ ምግባር አንጻራዊነት፣ የግብረገብ ብልሽት የተጸየፉ ልቦች በዙሪያቸው እየሆነ ያለው ከንቱነት ያንገሸገሻቸው ጌታንና ክብሩን ብቻ የሚጠሙ ቃሉን የሚራቡ ፊቱን የሚፈልጉ በእውነት በመንፈስ ጌታን የሚያመልኩ ሰዎች የሚያገኙት ምላሽ ነው ሪቫይቫል። እንዲህ ያሉ ሰዎች የተጠሙትን የጌታን ክብር የሚያዩበት ቀን መቼና እንዴት እንደሆነ ባይታወቅም ጌታ ለእንዲህ ዓይነቶቹ ራሱን የሚገልጥ መሆኑን ተማርኩ። ማንም ይሁን የትም ይሁን ጉዳዩ ጌታንና ክብሩን የመጠማት የመራብም ጉዳይ ነው። የአንዳንድ ወጣቶችን ምስክርነት ስሰማ ከሪቫይቫሉ በፊት የምድረ በዳ ጥም ዓይነት ነገር ወጣቶቹ ውስጥ እንደነበር ተረድቻለሁ።

ጊዜ ሳገኝ እመለሳለሁ።

Workneh d.koyera
#መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር #ይቀሰቀቅሰኛል #ለስሙ እንድዘምር

@ownkin
@cgfsd
(እግዚአብሔራዊ አቆጣጠር)
     (ክፍል 1)


ብዙ አይነት በእጄ የሚያስብል የአቆጣጠር ስሌት አለ ደግሞ ይኖራል ።የእግዚአብሔር አቆጣጠር በእጅጉ አብዝቶ ይለያል እግዚአብሔርማ ይቁጠር በደንብ ይቁጠር እንጂ ከእግዚአብሔር ጀምሮ ምን የማያምር ነገር አለ?? ምንም ነዋ መልሱ ።

እሺ እግዚአብሔር ግን ምን ቆጠረ? 😁 ፅድቅ አዎን ፅድቅን ቆጠረ ። ፅድቅን ለመገንዘብ የእግዚአብሔር አቆጣጠር ሊገባህ ይገባል ካለ በለዚያ ፅድቅን እንደ ራስ ፣ እንደ ሀይማኖት፣ እንደ ሰው፣ እንደ አቅምህ ለመረዳት እና ለመቁጠር ትሞክርና ተራራ የመግፋት ያክል ሲገዝፍህ አርፈ ትቀመጣለህ ስለዚህ ፅድቅ በእግዚአብሔር አቆጣጠር ተመልከት ። ፅድቅ ስሌት ፣ቀመር ፣አሰራር አለው እሱ እግዚአብሔራዊ ነው እደግመዋለሁ የፅድቅ ቀመር እግዚአብሔራዊ ነው ።

ብዙ ሰው በአዳም በኩል ሀጢያት እደደረሰው ያምናል ። በክርስቶስ በኩል ደግሞ ፅድቅ እንደደረሰው ለማመን ለመቀበል ሲቸገር ይስተዋላል ። እግዚአብሔራዊን አቆጣጠር ለመገንዘብ ይሔን መንፈሳዊ እውነት ማመን ይጠይቃል በአዳም በኩል ሀጢያት  እንደገባ በክርስቶስ በኩል ፅድቅ እንደመጣ ሊቀበሉት ግድ ይላል። በአንዱ አዳም በኩል ሀጢያት ሞት በሰው እንደነገሰ በአንዱ በኢየሱስ በኩል ፅድቅ በፀጋው በኩል እንደነገሰ መንፈሳዊ እውነት ነው ይሔ እግዚአብሔአዊ አቆጣጠር ነው ።

መፀሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይናገራል " እኛ በእርሱ በኩል ሁነን የእግዚአብሔር ፅድቅ እንሆን ዘንድ ሀጢያት ያላወቀውን እሱን ሀጢያት አደረገው"         2ቆሮ 5:21
  እኛ በኢየሱስ ሁነን እርሱ ደግሞ በእኛ ቦታ ሁኖ የሚቆጠር ፅድቅ ነው ። ይሔ ምትክነት በመተካካት ወይም ቤዛነት ይባላል ።እኛ ፅድቅ አያውቀን ከፍጥረት የቁጣ ልጆች ነን እርሱ ደግሞ ሀጢያት አያውቀው ፃዲቅ ቅዱስ ነው ። የእኛ በደል በእርሱ ላይ በመስቀል ላይ ሊኖርበት ሀጢያተኛ ሳይሆን ሀጢያት ሊሆን እኛ ደግሞ የእርሱ ፅድቅ ልንወስድ ምትክነት ቤዛነት ሊደረግ የተሰራ ስራ ነው ። አቤት ግን እግዚአብሔር እንዴት ነው የሚቆጥረው ያውም በቤዛነት (ምትክነት ) የተደረገ ቆጠራ ነው ። በልጁ ኢየሱስ የቆጠረን ፣የተቆጠረን ፅድቅ ያስደምማል ምን አይነት ጌታ አለን ያስብላል ክብር ፅድቁን በልጁ ቤዛነት ለቆጠረን አባት ይሁን ።

   በቤዛነቱ የሆነው እግዚአብሔራዊ አቆጣጠር!!

  ይቀጥላል....

ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ


#በመወለዱ አብሪያችሁ ነኝ አለ

#በመሰቀሉ ወዳችኋለው አለ

#ከሙታን በመነሳቱ አብራችሁኝ ናችሁ አለ


@ownkin
@cgfsd
ዘፀአት ውስጥ ግብፅ ትንሳኤ ውስጥ እኔነት የለም ።


Barbi
@ownkin
@cgfsd
መሲሃዊ አገዛዝ
     (ንጉሱ ኢየሱስ)
  

#የእግዚአብሔር መንግስት በኢየሱስ ማንነት የተብራራ ፣የተገለጠ፣የተበሰረ፣የታወጀ ፣የታየ ፣የተነገረ ነው ።
  


  በፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
እናት :- በጣም ስጨናነቅ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ በእጅ መሃል የፈሰሰውን ደም  አያለው አስባለሁ እፅናለለሁ

ልጅ :- እንደተሰቀለ ሁኖ ስላየሽው ብቻ ?

እናት:- እኔን እይኝ እያለኝ እኮ ነው ።

@ownkin
@cgfsd
(#ኢየሱስን መውደድ)

ሕይወት ማለት #ኢየሱስን መውደድ ነው

#ኢየሱስ እንደምንወደው መንገር ብቻ ሳይሆን መወደዱን ማየት ይፈልጋል... እንደተወደደ እንዲሰማው ይሻል

#ኢየሱስን የሚወድ ሰው እነዚህ ምልክቶች ይታዩበታል

1. ልዩ ትኩረት እና ልዩ መሰጠት #ለኢየሱስ ይሰጣል
2. አለምን እና ስራዋን ሁሉ ይጠላል
3. የጠፉትን ይፈልጋል

  kira
@ownkin
@cgfsd