Dawit Dreams Official
23.3K subscribers
2.38K photos
44 videos
1 file
766 links
Dawit DREAMS Official Channel
Download Telegram
ምሁርነት

ምሁር የሚባለው ሰው፤ ፊደል መቁጠር የቻለ ሰው ብቻ አይደለም። ድንቅ የክፍለ ዘመናችን ምሁር፣ የአዕምሮ መሣሪያዎቹን በመጠቀም፣ የሌሎች ሰዎችን መብት ሳይነካ፣ የሚፈልገውን ውጤት ማግኘት የሚችል ሰው ነው። በሕይወታችን ከሚገጥሙን የመሀይምነት ችግሮች በመውጣት ወደ ነፃነት ሕይወት ለመግባት፣ የሚያስፈልገን ዐብይ ጉዳይ "ትክክለኛ ዕውቀት ነው" ትክክለኛውን እና እውነተኛውን ዕውቀት ማወቅ መረዳትና መጠቀም ስንችል፣ ከማንኛውም የመሀይም እና የፓራዳይም እስር ቤት ነፃ መውጣት እንችላለን፣ ስለዚህ የክፍለ ዘመናችን ምሁር፣ በሕይወቱ የሚፈልገውን ውጤት ለማግኘት ጠቃሚ የሆነውን ዕውቀት የሚያውቅ የሚረዳና የሚጠቀም ነው።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.
     መልካም ምሽት

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
እንዲሁም ለአዲሱ 30ኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ +251938252525 በመደወል ይመዝገቡ
ተመስገን ዛሬ ከራሴ ጋር መሀላ ገብቻለሁ። 🖐🖐🖐
ትልቁ ህልሜ እስኪሳካ ከህልሜ ጋር ተጣብቄያለሁ። ሁሉንም የውስጥ ሀብቴን አውጥቼአለሁ። እምነቴ ሁሌም ከስበት ህግ ጋር አንድ ነው፤ ተገጣጥሟል። ሀሳቤ፣ስሜቴ፣ደስታዬ፣እምነቴ፣መንፈሴ፣እንቅስቃሴዬ ወደ ትልቁ ህልሜ ዘወትር ያመራል። ለትልቁ ህልሜ የሚያስፈልገኝ ሁሉ እዚህ አለ። የእኔ ስራ ማገጣጠም ብቻ ነው። በውስጤ ሰላምና መረጋጋት አለ። በጣም ደስተኛ ነኝ። ፊቴና መላ ሰውነቴ በደስታ ተሞልቷል። ትልቁ ህልሜ የእኔ ሆኗል።

ተመስገን!! ድንቅ፣ በስኬት የተሞላ፣ በማስተዋል በጥበብ የታጠረ ቀን ተመኘሁ!!!
የማክሰኞ እንግዶች
የሰኔ ወር የመጨረሻ እንግዶች ትዕግስት ዋልተንጉስ እና ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ የማክሰኞ ሰኔ 28/2014 እንግዳችን ናቸው፣ ከ 11፡00 ጀምሮ በ22 ማዞሪያ ባታ ኮምፕሌክስ 3ኛ ፎቅ ላይ ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ምግብ ሊመግቡን ተዘጋጅተዋል። ይህን ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ለመታደም ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ማንም እንዳይቀር።

መግቢያ በነፃ

ለበለጠ መረጃ በ +251938252525 ይደውሉ። ያመለጣችሁን እንግዳ በ Dawit Dreams You Tube channel ላይ በመግባት ታገኙታላችሁ።

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial
ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ ወደ ዳዊት ድሪምስ በመምጣት ድንቅ በሆነ መንገድ አዕምሮአችንን ስለመገቡልን እጅግ በጣም እናመሰግናለን።

ክቡራን ቤተሰቦቻችን በቀጣይ ሳምንት በአዲስ እንግዳ እንጠብቆታለን!
የዘራኸውን ታጭዳለህ

በዚህ ድንቅ በሆነ ፍጥረት ዓለማችን፣ ሁሌም የዘራነውን ማጨዳችን አይቀርም። አንተስ በድብቁ አዕምሮህ ምን እየዘራህ ነዉ?
ፈጣሪ እኛን የሰው ልጆች ከእንስሳት እና ዕፅዋት በተለየ መንገድ ስለፈጠረን፣ በድብቁ አዕምሯችን የምንፈልገውን ሕልም የመዝራት እና የመምረጥ ነፃነት ሰጥቶናል። ታድያ ይህንን የምርጫ ነፃነት በጥንቃቄ ካልተጠቀምንበት፣ አንዴ ስለትልቁ ሕልማችን በማሰብ እና በመደሰት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በየቀኑ ስለሚገጥሙን ችግሮች ስናስብ እና ስናማርር በአዕምሯችን የተደበላለቁ ዘሮችን እንዘራለን፣ በዚህም ጊዜው ሲደርስ ድብልቅልቅ ያሉ ውጤቶችን እናጭዳለን። ስለዚህ አሁን ራስህን፣ ቤተሰብህን፣ መሥሪያ ቤትህን፣ አገርህን፣ አህጉርህንና ዓለምህን ሊቀይርልህ የሚችለውን ትልቁን ሕልምህን በንቁ አዕምሮህ ቅረጸው። ስለ ሕልምህ እና ሕልምህን ስለሚያሳኩ ሀሳቦችና መፍትሄዎች ብቻ በተደጋጋሚ በማሰብ፣ የሕልምህን ዘር በድብቁ አዕምሮህ በእምነት ስትዘራው የሕልምህን ውጤት በሰዓቱ ማጨድህ አይቀርም!

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.
 መልካም ቀን

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
እንዲሁም ለአዲሱ 30ኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ +251938252525 በመደወል ይመዝገቡ
ዛሬ ሀሙስ ሰኔ 30/2014 ከ 11:30 ጀምሮ ዳዊት ድሪምስ ልዮ በሆነ ርዕስ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ሊሰጠን ተዘጋጅቷል፣ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ማንም እንዳይቀር.

መግቢያ 100 ብር
አድራሻ:- 22 ባታ ኮምፕሌክስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ድሪምስ ሲኒማ

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
እንዲሁም ለአዲሱ 30ኛ ዙር ምዝገባ +251938252525 በመደወል ይመዝገቡ