Dawit Dreams Official
23.1K subscribers
2.37K photos
44 videos
1 file
759 links
Dawit DREAMS Official Channel
Download Telegram
ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ ወደ ዳዊት ድሪምስ በመምጣት ድንቅ በሆነ መንገድ አዕምሮአችንን ስለመገቡልን እጅግ በጣም እናመሰግናለን።

ክቡራን ቤተሰቦቻችን በቀጣይ ሳምንት በአዲስ እንግዳ እንጠብቆታለን!
የዘራኸውን ታጭዳለህ

በዚህ ድንቅ በሆነ ፍጥረት ዓለማችን፣ ሁሌም የዘራነውን ማጨዳችን አይቀርም። አንተስ በድብቁ አዕምሮህ ምን እየዘራህ ነዉ?
ፈጣሪ እኛን የሰው ልጆች ከእንስሳት እና ዕፅዋት በተለየ መንገድ ስለፈጠረን፣ በድብቁ አዕምሯችን የምንፈልገውን ሕልም የመዝራት እና የመምረጥ ነፃነት ሰጥቶናል። ታድያ ይህንን የምርጫ ነፃነት በጥንቃቄ ካልተጠቀምንበት፣ አንዴ ስለትልቁ ሕልማችን በማሰብ እና በመደሰት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በየቀኑ ስለሚገጥሙን ችግሮች ስናስብ እና ስናማርር በአዕምሯችን የተደበላለቁ ዘሮችን እንዘራለን፣ በዚህም ጊዜው ሲደርስ ድብልቅልቅ ያሉ ውጤቶችን እናጭዳለን። ስለዚህ አሁን ራስህን፣ ቤተሰብህን፣ መሥሪያ ቤትህን፣ አገርህን፣ አህጉርህንና ዓለምህን ሊቀይርልህ የሚችለውን ትልቁን ሕልምህን በንቁ አዕምሮህ ቅረጸው። ስለ ሕልምህ እና ሕልምህን ስለሚያሳኩ ሀሳቦችና መፍትሄዎች ብቻ በተደጋጋሚ በማሰብ፣ የሕልምህን ዘር በድብቁ አዕምሮህ በእምነት ስትዘራው የሕልምህን ውጤት በሰዓቱ ማጨድህ አይቀርም!

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.
 መልካም ቀን

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
እንዲሁም ለአዲሱ 30ኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ +251938252525 በመደወል ይመዝገቡ
ዛሬ ሀሙስ ሰኔ 30/2014 ከ 11:30 ጀምሮ ዳዊት ድሪምስ ልዮ በሆነ ርዕስ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ሊሰጠን ተዘጋጅቷል፣ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ማንም እንዳይቀር.

መግቢያ 100 ብር
አድራሻ:- 22 ባታ ኮምፕሌክስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ድሪምስ ሲኒማ

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
እንዲሁም ለአዲሱ 30ኛ ዙር ምዝገባ +251938252525 በመደወል ይመዝገቡ
ራስን መገሰጽ

ራስን መገሰጽ ወደ ሕልምህ የምትሻገርበት ልዮ ድልድይ ነው። ራስን መገሰጽ ማለት ለራስህ አንድ ግልጽ የሆነ ትዕዛዝ መስጠትና የሰጠኸውን ትዕዛዝ በትክክል መፈጸም ሲሆን፣ በሕይወት ውስጥም ትላልቅ ነገሮችን የሠሩና ተጽዕኖ የፈጠሩ ሰዎች ራሳቸውን በትክክል የሚገስጹ ሰዎች ናቸው። በዓለማችን ላይ ታሪክ የቀየሩ ድንቅ ሰዎች ምን ያክል ራሳቸውን እንደሚገስጹ መገመት አይከብድም። እነዚህ ታሪክ ቀያሪ ድንቅ ሰዎች፣ ከ ሌሎች ሰዎች ይልቅ የተለየ ዕድል ስለተሰጣቸው ሳይሆን፣ ትልቅ ሕልም አስቀምጠው፣ ሕልማቸውን ለማሳካት መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት ያለ ምንም ድርድር በመክፈል ራሳቸውን ስለሚገስጹ ነዉ። አንተም ራስህን በትክክል መገሰጽ ስትችል፣ የምትፈልገውን ውጤት ማግኘትና ሕይወትህን መቀየር ትችላለህ። ውጤታማ በሆነ መንገድ ራስህን በመገሰጽ ሕይወትህን መቀየር የምትችለው ደግሞ ትልቅ ዓላማ ሲኖርህ ነው። ማሳካት የምትፈልገው ትልቅ ዓላማ ከሌለህ ራስህን መገሰጽ ከባድ ነው የሚሆንብህ፣ ነገር ግን በአዕምሮህ በግልጽ የሚታይህ ማሳካት የምትፈልገው ትልቅ ዓላማ ሲኖርህ፣ ዓላማህን ለማሳካት ራስህን መገሰጽ ቀላል ነው፣ ትልቅ ሕልም የሚያስፈልግህም ለዚህ ነው። ስለዚህ በሕይወትህ ትልቅ ለውጥ ለመፍጠር የሚረዳህን ትልቅ ሕልም አስቀምጥ፣ ትልቁን ሕልምህን ለማሳካትና ሕይወትህን ለመቀየር ለራስህ ቃል ግባ፣ ቃልህን ለመጠበቅም ራስህን ገስጽ።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.
  
የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
ለ30ኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ +251938252525 በመደወል ይመዝገቡ
ለመላው የእስልምና እምነት ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችው በዐሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የስኬት እና የፍቅር ይሁንላችው!


ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.
  
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
መሥዋዕትነት

ብዙ ሰው መክፈል ያለበትን መሥዋዕትነት የማይከፍለው፣ መሥዋዕትነት ምን እንደሆነ ስለማያውቅ ነው። አብዛኛው ሰው መሥዋዕትነት ሲባል፣ ወደ አዕምሮው የሚመጣለት "መክፈል፣ መክሰር፣ ማጣት ወይም መሰቃየት" የሚል ሀሳብ ብቻ ነው ይህ ግን መሥዋዕትነት ምን እንደሆነና ለምን እንደሚያስፈልግ አለማወቅ ነው። መስዋዕትነት አሁን ያለህን እሴት፣ ይበልጥ የተሻለ እሴት ለማግኘት መስጠት ነው፣ ነገር ግን አሁን ያለህን እሴት ዝም ብሎ መስጠትና መክፈል ሳይሆን፣ ትክክለኛ መሥዋዕትነት፣ አሁን ያለህን ትንሽ ጥቅም ያለው ነገር በመስጠት፣ የበለጠ ጥቅም ያለው ነገር ለማግኘት የምትከተለው ሂደት ነው። አንተ ትክክለኛ መሥዋዕትነት በመክፈል ሕይወትህን መቀየር የምትፈልግ ከሆነ በመጀመሪያ፣ መሥዋዕትነት በመክፈል የምታገኘው ትልቁ ነገር ምን እንደሆነ መወሰን አለብህ!

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.
መልካም ቀን

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
ለ30ኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ +251938252525 በመደወል ይመዝገቡ