Dawit Dreams Official
23.3K subscribers
2.38K photos
44 videos
1 file
765 links
Dawit DREAMS Official Channel
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሸናፊ ሰዎች በቅዝቃዜም በሙቀትም ያሸንፋሉ! ተሸናፊ ሰዎች ተኝተው ያሳብባሉ!

መልካም የማሸነፍ ቀን

ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
ድንቅ ቀን ተመኘን!
አሁኑኑ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
የማክሰኞ እንግዳችን

ድንቁ እና ተዓምረኛው የስብዕና ልህቀት አሰልጣኝ ማንያዘዋል እሸቱ የማክሰኞ ሰኔ 21/2014 ልዩ እንግዳችን ነው፣ ከ 11፡00 ጀምሮ በ22 ማዞሪያ ባታ ኮምፕሌክስ 3ኛ ፎቅ ላይ ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ምግብ ሊመግበን ተዘጋጅቷል።

መግቢያ በነፃ:-ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ማንም እንዳይቀር።

ለበለጠ መረጃ በ +251938252525 ይደውሉ። ያመለጣችሁን እንግዳ በ Dawit Dreams You Tube channel ላይ በመግባት ታገኙታላችሁ።

join us
https://t.me/DawitDreamsTelegram
አራት የለውጥ ደረጃዎች
፪ ማሰብ የለውጥ ደረጃ

ራስህን በትክክል በመፈተሽ፣ በሕይወትህ ወደ ባርነት የገባህባቸውን ውጤቶች መለየት፣ የስኬት የመጀመሪያ እርምጃ ነው። የስኬት የመጀመሪያ እርምጃ በሕይወት የት እንዳለህ መረዳት፣ የማትፈልጋቸውንና ወደ ባርነት የሚወስዱህን ተራ ውጤቶች ለይተህ ማወቅ ነው። የስኬት ሁለተኛው እርምጃ ደግሞ፣ በሕይወትህ የት መሄድ እንደምትፈልግ መወሰንና የምትፈልጋቸውን ወደ ነጻነት የሚወስዱህን ድንቅ ውጤቶች በግልጽ ማወቅ ነው። የመጨረሻውና የስኬት ሦስተኛው እርምጃ ደግሞ አሁን ካለህበት የማትፈልገው የባርነት ሕይወት በመውጣት፣ ወደምትፈልገው የነጻነት ሕይወት መራመድ ነው። ማሰብ የለውጥ ደረጃ፣ አሁን ከገባህበት እስር ቤት በመውጣት ወደ ነጻነት የምትራመድበትን መንገድ የሚያሳይህ የመጀመሪያ ደረጃ ነው።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ
ድንቅ የሆነ ቀን

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial
Forwarded from ABRSH ALIVE (Abrsh)
“ፓራዳይምህን ስትቀይር፣ ሕይወትህ ሙሉ በሙሉ ይቀየራል፤ መቀየሩ ደግሞ ዘለቄታዊ ነው!”

የ21 ቀን ፓራዳይም ሺፍት ስልጠና አሁኑኑ ይመዝገቡ።
ለበለጠ መረጃ +2519 38 252525 ይደውሉ!
ለትልቁ ሕልምህ አሁኑኑ መሮጥ ጀምር!

ምን "ሕልሜን ማሳካት አልችልም ብለህ ተስፋ የቆረጥክበት፣ ትልቅ ሕልም አለህ? ምናልባት ከጎንህ ያሉ ቤተሰቦችህና ወዳጆችህ "ትልቁን ሕልምህን ማሳካት እንደምትችል ላያምኑ ይችላሉ። ሕልምህን ለማሳካት ስትሠራ እና ስትሯሯጥም ላይደግፉህ ይችላሉ። ነገር ግን ሁሌም ቢሆን ማስታወስ ያለብህ ቀዳሚው ነገር፣ ሕልምህ ያንተ እንጂ የሌላ ሰው አለመሆኑን ነው። ትልቁ ሕልምህ ለአንተ እና ለአንተ ብቻ ነው የተሰጠው። ትልቅ ሕልምህን ለማሳካትም አንተ ብቻ ነህ ማመን ያለብህ! ሌሎች ሰዎች "ትችላለህ!" ብለው ቢያምኑም ባያምኑም፣ ሕልምህን ለማሳካት በምታደርገው ጉዞ፣ ብዙም ልዮነት መፍጠር የለበትም። ስለዚህ የማንም ሰው ዕርዳታ ሳትጠብቅ፣ ለትልቁ ሕልምህ መሮጥህን አሁኑኑ ጀምር!!

ትልቅ ሕልም አለኝ!
አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ

ድንቅ የማሸነፍ ቀን ተመኘን🙏
የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial
https://t.me/DawitDreamsTelegram
የማክሰኞ እንግዳችን

ድንቁ የስብዕና ልህቀት አሰልጣኝ ማንያዘዋል እሸቱ የማክሰኞ ሰኔ 21/2014 ልዩ እንግዳችን ነው፣ ከ 11፡00 ጀምሮ በ22 ማዞሪያ ባታ ኮምፕሌክስ 3ኛ ፎቅ ላይ ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ምግብ ሊመግበን ተዘጋጅቷል። ይህን ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ለመታደም ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ማንም እንዳይቀር።

መግቢያ በነፃ

ለበለጠ መረጃ በ +251938252525 ይደውሉ። ያመለጣችሁን እንግዳ በ Dawit Dreams You Tube channel ላይ በመግባት ታገኙታላችሁ።

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial
https://t.me/DawitDreamsTelegram
** ጀግናዬ ዛሬ ተወልዷል *

ኧረ
እንኳንም ተወለደ ፤ ቢወለድ እንጅነው
በእድሜየ እኩሌታ ዳግም ተወልጄ ህልሜን አግንቼው የህይወት ጥሪዬን መልስ ለመስጠት የተነሳሁ!

ኧረ እንኳንም ተወለደ ፤ ቢወለድ እንጅነው...
ህዝበ አዳም በየህልም ዓለሙ እራሱን ፈልጎ እያገኘ እንደ ኮከብ ያንፀባረቀ! አንተ ባትወለድ እኺ ማ'ረግ ፤ እኺ ሁሉ ሲሳይ ወት ይገኝ ኑሯል?

ኧረ እንኳንም ተወለደ ፤ ቢወለድ እንጅነው...
መዓዛና መቅኖ ያጣው አሰልቺው ህይወቴ ፈክቶ የመኖር ጉጉት ውስጥ ገብቼ ፤ የድንቅ ደራሲነትን የህልሜን ካባ ደርቤ እንዲንህ በትፍስህት ውየ እንዳድር አዲስ ሰውነትን አዲስ ጉልበታም አዲስ ተመልካች ፤ ድንቅ ፀሐፊ ሆኜ ለመውጣት አንተ ባትወለድ የት አገኘው ነበር ?

ኧረ ደግ አረጉ አቦይ ገ/ሔር ፤ እንኳንም አደይን አስወለዷቸው ፤ ኦሆሆኣኣኣ ቢያስወልዱ እንጅ ነው ብዙዎቻችን እንድንወለድ ምክንያት የሆኑ ። ኧረ አበጁ ፤ እንኳን ፤ አሰይ ፤ ደግ አርጉ ። አደዬም እንኳን አንተን ወለዱ ።

እንኳዕ ተወለድኻ ፤ እስኻ ተዘይትውለድ ኔርኻ ኻበይ አምፂኧ ፒሮ ኣልዒለ ምፅሓፍኹ ፤ እንታዬይ ኽሕልም ፤ እንታዬይ ኸ ኽዕወት ፤ ኣየናይ ናይ ሕይወት ቓልሰይ ስዒረ ብኸመይ ጌረ ሳዓራይነት ምረኸብኩ ! ኣታ ናይ ልበይ .. እንኳዕ ተወለድኻ !

እንኳነም ተወለድልነ !

በእኛ ዘየ ....ሙቸ. ነው እምወድህ !!!

አስቻለው ምስጋናው
ማንያዘዋል እሸቱ በድንቅ ኢነርጂ ወደ ዳዊት ድሪምስ በመምጣት ያለህን በሙሉነት ስለሰጠኸን እና መንፈሳዊ አካላችንን ስላስታወስከን እጅግ በጣም እናመሰግናለን ክብረት ያድልልን።

ድንቅ የዳዊት ድሪምስ ቤተሰቦች ድንቅ ቆይታን ከማንያዘዋል ጋር ነበረን በቀጣይ ሳምንት በድንቅ እንግዳ እንጠብቃችኋለን። ያመለጣችሁን እንግዳ በ DAWIT DREAMS You Tube ቻናል ላይ ያገኙታል።
አራቱ የለውጥ ደረጃዎች
፫ ግጭት የለውጥ ደረጃ

ግጭት የለውጥ ደረጃ ወደ ሕልምህ የሚወስድህ ልዩ የለውጥ ደረጃ ነው። በማሰብ የለውጥ ደረጃ፣ በንቁ አዕምሮህ የምታስበው ድንቅ ሀሳብ በተደጋጋሚ በተራ ፓራዳይምህ ቢሸነፍም፣ ወደዚህ የግጭት የለውጥ ደረጃ ያደርስሀል። ነገር ግን በግጭት የለውጥ ደረጃም የድሮ ተራ ፓራዳይምህን የምታሽንፈው፣ በንቁ አዕምሮህ በምታስበው ድንቅ ሀሳብ ነው። አሁን የፓራዳይምን ተጽዕኖ በትክክል በመረዳት፣ በንቁ አዕምሮህ አሁን እያገኘህ ያለኸውን የማትፈልገውን ተራ ውጤት በመዝጋት፣ ስለምትፈልገው ውጤት ብቻ በማሰብ፣ በዚሁ ግጭት የለውጥ ደረጃ፣ ድንቅ ለውጥ ማምጣት ትችላለህ። የፓራዳይምን ትግል አልፈህ፣ አምስቱን የስሜት ህዋሶች ዘግተህ፣ በስድስቱ የአዕምሮ መሣሪያዎችህ የምትፈልገውን ውጤት ማሰብና መፍጠርህን በትግስትና በትኩረት ስትቀጥል፣ በድብቁ አዕምሮህ ድንቅ ፓራዳይም መገንባት ትጀምራለህ። ይህ ድንቅ ፓራዳይም ደግሞ በድብቁ አዕምሮህ ካለው ተራ ፓራዳይም ጋር ጦርነት ይከፍታል።

የግጭት የለውጥ ደረጃ ውስጥ የምትገባው፣ አዲስ የተፈጠረው ድንቅ ፓራዳይምህ፣ ከድሮው ተራ ፓራዳይምህ ጋር ሲጋጭ ነው። አዲሱ ፓራዳይም የድሮ ፓራዳይምህን ካሸነፈው፣ ወደ ነጻነት ሕይወት ትገባለህ፤ የድሮው ፓራዳይም አዲሱን ፓራዳይም ካሸነፈው ግን፣ ወደ ባርነት ሕይወት ትመለሳለህ።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ
ድንቅ የሆነ ቀን

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial