Dawit Dreams Official
23.6K subscribers
2.43K photos
46 videos
1 file
781 links
Dawit DREAMS Official Channel
Download Telegram
Forwarded from ABRSH ALIVE (Abrsh)
"ዛሬ የሞት አልጋችሁ ላይ ብትሆኑ ኖሮ፤ መጨረሻ ቀናችሁ ቢሆን ኖሮ .. እስከአሁን የኖራችሁት ህይወት በቂ ይሆን ነበር ወይ???"
ዳጊ

ዳጊ የዛሬዋ የማክሰኞ እንግዳችን በመሆንሽ እጅግ በጣም እናመሰግናለን!

በቀጣይ ሳምንት በአዲስ እንግዳ እንጠብቃችኋለን!
Forwarded from ABRSH ALIVE (Abrsh)
አንተ ገና ስትወለድ አሸናፊ ነህ!

አንተ ገና ወደዚች ዓለም ከመምጣትህ በፊት፣ ፈጣሪ ድንቅና አሸናፊ አድርጎ ነው የፈጠረህ። የእናትህ ዕንቁላል እና ከአባትህ የወጣው የወንድ ዘር አንድ በመሆን፣ ጽንስ ሆነህ ከመፈጠርህ በፊት፣ አንድ ከባድ ጦርነትና ትልቅ ሩጫ አሸንፈህ ነው የመጣኸው። እናትህ እና አባትህ አንተን ለመውለድ ሲገናኙ፣ ወደ እናትህ ማኅጸን ከተላኩት ከሁለት መቶ ሚልየን በላይ የአባትህ የዘር ፈሳሽ ፍሬዎች መካከል፣ አብዛኞቹ ውድድሩን ሳይጨርሱት መንገድ ላይ ነው የሞቱት። አንተ አሁን በሕይወት ያለኸው፣ እነዚህን ከሁለት መቶ ሚልየን በላይ የሚሆኑ የወንድ ዘር ፈሳሾች በማሸነፍ፣ ወደ እንቁላሏ ቀድመህ በመድረስህ ብቻ ሳይሆን፣ ሩጫው ላይ የነበሩትን ሁሉንም ዕንቅፋቶች ስላሸነፍክ ጭምር ነው።
ይህንን ትንቅንቅ ያሸነፍክ ጀግና፣ አሁን ላይ ምናልባትም ከአስር ሰዎች ጋር ተወዳድረህ፣ እንድታሸንፍ ስትጠየቅ፣ ‘‘ከአቅሜ በላይ ነው!’’ ብለህ በራስህ እና በአቅምህ ትጠራጠር ይሆናል። ከመወለድህ አስቀድሞ፣ ዘር ከነበርክበት ማንነትህ አንስቶ እስከ አሁን፣ በሕይወትህ ያለፍካቸውን ፈተናዎችና የፈጠርካቸውን ተዓምሮች አንዴ መለስ ብለህ ካሰብክ፣ ማን እንደሆንክና ምን ማድረግ እንደምትችል ትረዳለህ።

ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
መልካም አዳር ተመኘን!
ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
እውቀት Vs ድርጊት

አብዛኛው ሰው በእውቀት ደረጃ ሕይወቱን ለመቀየር ራሱን መቀየር እንዳለበት ያውቃል፤ በተግባር ግን ሕይወቱን ለመቀየር ሌላ ሰው ወይም ነገር እስኪቀየር ይጠብቃል። አንተስ ሕይወትህን ለመቀየር ራስህን እየቀየርክ ነው ወይስ ሌላ ሰው አልያም ነገር እስኪቀየር እየጠበቅክ?

ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
መልካም ቀን ተመኘን!
ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
መርካት

ብዙ ሰው በጣም ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ይሠራል፣ ያሰበውን ያሳካል፣ ሕይወቱንም ይቀይራል፣ ከዚያም ይረካል። ከልጅነታችን ጀምሮ "አንተ ልጅ ባለህ ነገር አትረካም እንዴ"? እየተባልን ካደግን፣ አንድ ሥራ ስንጨርስ መርካትና መተኛት ልንመኝ እንችላለን። በርግጥ በሕይወት ስላለን እና ስላገኘነው ነገር ሁሌም ማመስገን አለብን። ስላለን ነገር ስናመሰግን፣ የምናመሰግንበት ሌላ ነገር ይጨመርልናል። ነገር ግን መቼም መርካት የለብንም። ምክንያቱም ስንረካ ማደግ እናቆማለን።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
ድንቅ ቀን ተመኘን!

የድሪምስ ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን. ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
Forwarded from ABRSH ALIVE (Abrsh)
የማሸነፍ ምስጢር

አብዛኛውን ሰው ‘‘...አንድ ሴት ልጅ፣ ከአንድ ወንድ ልጅ እኩል ወይም ከወንድ ልጅ በላይ መሮጥ ትችላለች?” ብለህ ብትጠይቀው፣ ለሰከንድ ሳያስብ፣ ‘‘አትችልም’’ ብሎ ሊመልስ ይችላል። “አንድ ሴት፣ ከአንድ ወንድ እኩል ወይም በላይ መሮጥ አትችዪም” የሚል ፓራዳይም ከልጅነቷ ከተቀረጸላት፣ ይህንን የተደጋገመላትን ውሸት ነው የምታምነው። ነገር ግን በሕይወት አጋጣሚ እንደ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት ደፋር፣ አልማዝ አያናና ሌሎች ሴት አትሌቶቻችን ይመጡና ውሸቱን አጋልጠው እውነቱን ግልጽ ያደርጉታል። እነ ሳህለወርቅ ዘውዴ ይመጡና የአገር ንጉስ ይሆናሉ። ወላጆች፣ ሴት ልጆቻችሁ እንደ ፕሬዚደንታችን፣ አትሌቶቻችንና በተለያዩ ዘርፎች ላይ ትላልቅ ደረጃ ላይ እንደደረሱ ሴቶች ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ፣ እና ታሪክ እንዲሰሩ የምትፈልጉ ከሆነ፣ የሴት ልጆቻችሁን አዕምሮ እንዴት እየቀረጻችሁ እንደሆናችሁ ማስተዋል አለባችሁ።

አንዳንድ ሴቶች ‘‘አሁን ዳዊት እያለ ያለው እኮ እውነቱን ነው... ነገር ግን የኔ ቤተሰብ ‘ይቻላል’ እያሉ አላሳደጉኝም’’ ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ሕይወትሽን ለመቀየር፣ ራስሽን መቀየር ብቻ ነው ያለብሽ። አሁን አንዴ ሰከን ብለሽ ማሰብ ያስፈልግሻል። ‘‘በአዕምሮሽ እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ’’ ብለሽ ነው የምታምኚው? በአዕምሮሽ “ምን ማድረግ አትችይም” ብሎ የገባ የውሸት እምነት አለ? አዕምሮሽንና በአዕምሮሽ ያለውን ሀሳብና እምነት ስትቀይሪ፣ ሕይወትሽ ይቀየራል። ትልቁን ሕልምሽን ለማሳካት ራስሽን ካልከለከልሽ፣ ማንም አይከለክልሽም። ራስሽን ከረዳሽ ደግሞ የማንም እርዳታ አያስፈልግሽም።

ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
መልካም አዳር ተመኘን!
ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
Follow our Facebook page
Channel name was changed to «Dawit Dreams Official»
መሀይም ስለሆንን ነው የፈለግነውን ውጤት የማናገኘው!

የምትፈልገውን ውጤት የምታገኝበትን ምስጢር ካላወቅክ፣ የፈለግከውን ውጤት ማግኘት ይከብድሀል። አስቀድመን ስለመሀይምነት ትርጉም ስንነጋገር እንዳነሳነው፣ መሀይምነት ማለት፣ ነገሮችን የማከናወኛ ምስጢርን አለማወቅ ነው። በዚህም በርካታ ሰዎች መሀይም ናቸው። ቀለም ለቆጠርነው እንኳ፣ እንዴት አድርገን ትልቅ ሕልም በማስቀመጥ፣ ሕይወታችንን መቀየር እንዳለብን፣ ትምህርት ቤቶቻችን አላስተማሩንም። ሕልሙን የሚያሳካበትን ምስጢር ያላወቀ ሰው፣ ስለ ትልቅ ሕልሙና ሕልሙን ማሳካት ስለሚችልበት መንገድ ሲያስብ ይጠራጠራል፤ ይፈራል፤ ይጨነቃል፤ ደግሞም ተስፋ ይቆርጣል። ሕልሙን የሚያሳካበትን ምስጢር ተምሮ መሀይምነቱን ሲያሸንፍ ግን፣ የማንንም ሰው መብት ሳይነካ፣ ትልቁን ሕልሙን በማሳካት የሚፈልገውን ሕይወት መኖር ይጀምራል።

ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
መልካም ቀን ተመኘን!
አሁኑኑ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
ዛሬ ሀሙስ ሰኔ 16/2014 ዳዊት ድሪምስ ድንቅ በሆነ ልዮ ርዕሰ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ሊሰጠን ተዘጋጅቷል፣ እናንተስ ይሄን ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ለመታደም ዝግጁ ናችሁ?

መግቢያ 100 ብር
አድራሻ:- 22 ባታ ኮምፕሌክስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ድሪምስ ሲኒማ በመገኘት ይሄን ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ምግብ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።