Fontenina - ቁም ነገር
1.28K subscribers
71 photos
1 video
6 links
Media Service
Download Telegram
“የዕድሜዬ መግፋት ከትምህርት ፍላጎቴ አላስቀረኝም” የ70 ዓመቱ አዛውንት ተመራቂ

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ካስመረቃቸው ተመራቂዎች መካከል የ70 ዓመቱ ተመራቂ አዛውን የበርካቶችን ቀልብ የሳበ መሆኑ ተነግሯል።
የ70 ዓመቱ አዛውንት አቶ ዓሊ ሳፋ ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፤ የዩኒቨርሲቲው የ9ኛ ዙር ተመራቂዎች ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከ35 ዓመት በፊት እንዳገኙ ያስታወሱት አዛውንቱ፣ ለትምህርት ባላቸው ፍቅር የተነሣ የዕድሜያቸው መግፋት ሳይገድባቸው በ70 ዓመታቸው ዛሬ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ለመቀበል መብቃታቸውን ገልጸዋል።
“የዕድሜዬ መግፋት ከትምህርት ፍላጎቴ አላስቀረኝም” ያሉት አቶ ዓሊ ሳፋ፣ ስምንት ልጆች እና አራት የልጅ ልጆች አያት መሆናቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።
ከባለሥልጣን ቤት ንብረት የዘረፈችው የቤት ሠራተኛ ጠንቋይ ቤት ተያዘች!! ቢቢሲ

የኬንያ ፖሊስ እንዳለው በስርቆት ተጠርጥራ በቁጥጥር ሥር የዋለችው ሚሪያም ሙዌሉ የተባለችው ይህች የቤት ሠራተኛ “ታዋቂ ከሆነው” ጠንቋይ ቤት “ከእስር ያስመልጣል” የተባለለትን መተት ለማግኘት ተፍተፍ ስትል እጅ ከፍንጅ ይዣታለሁ ብሏል።

ተጠርጣሪዋ ግምቱ ከ33 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያወጣ ጥሬ ገንዘብ እና ውድ ጌጣ ጌጦችን ከዘረፈች በኋላ ለሦስት ሳምንታት ብትሰወርም መርማሪ ፖሊስ ሴቲቱን በጠንቋዩ ቤት በስርቆት ወንጀሉ ከተባበራት ግብረ አበሯ ጋር በቁጥጥር ሥር እንዳዋላት አሳውቋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲሞክር፣ በእድሜ የገፉት ጠንቋይ የፖሊስ አባላቶቹ ለማሸሽ ይረዳል ያሉትን የመተት ቃላት ቢደረድሩም፤ ሕግ አስከባሪዎች ግን ተልዕኳቸውን ከመወጣት አላገዳቸውም ብሏል በመግለጫው።

የኬንያ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት በሕግ የሚፈለጉ ሰዎች ጥንቆላ ከሕግ ተጠያቂነት ስለማያስመልጣቸው ጊዜያቸውን እንዳያባክኑ አሳስቧል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል
በጅብ ተበልቶ እግሮቹን ያጣው ወጣት አስገራሚ

“በግ ተራ አካባቢ ቁልቁለቱን እየወረድኩ፣ አንድ ጅብ ሲመጣ አይቻለሁ። ከዚያ በኋላ የሆንኩትን ነገር አላስታውስም።…”

ዝርዝሩን👇በዚህ እዩት
t.me/wasulife t.me/wasulife
ትዳር በገበያ

የህንድ ሴቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሄድ ባል የሚገዙበት የሙሽራ ገበያ

የሙሽራ ገበያው “ሳውራት ሜላ” ወይም “ሳባጋቺሂ” እየተባለ የሚጠራ ሲሆን፤ በዓመት አንድ ጊዜ የሚቆምና ለ9 ቀናት የሚቆይ መሆኑን ከኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከ700 መቶ ዓመታት በፊት እንደተጀመረ የሚነገርለት ይህ የባል ገበያ ሴቶች ይሆነኛል ብለው ያመኑበትን ባል እንዲመርጡ ለማስቻል እንደተጀመረ ተግሯል።

በገበያው ባል ለመሆን ለሚቀርቡ ለእያንዳንዱ ሙሽራ የትምህርት ደረጃቸውን እና የቤተሰቡን የኑሮ ሁኔታ መሰረት ባድረገ መልኩ ዋጋ የሚቆረጥለት መሆኑም ተነግሯል።
ፍቅረኛዬ ፈተና ወደቀች በሚል ትምህርት ቤቱን ያቃጠለዉ አፍቃሪ
👇
በግብጽ ሜኑፊያ ግዛት ነዋሪ የሆነዉ የ21 ዓመት ወጣት ፍቅረኛዉ የነበረባትን የትምህርት ፈተና ማለፍ ባለመቻሏ ትምህርት ቤቱን በእሳት አጋይቷል፡፡የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንደገለጸው በእሳት አደጋዉ የሞተ ሆነ የተጎዳ ሰው የለም ብሏል፡፡

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እጮኛው የትምህርት ቤቱን ፈተና መዉደቋ ክፍል እንድትደግም የሚያስገድዳት ሲሆን ይህ ደግሞ የሰርጋችንን ቀን ይገፋብናል ሲል ተናግሯል። ድርጊቱን ከፈጸመ በኃላ ከአካባቢዉ ተሰዉሮ የነበረ ሲሆን የዓይን እማኞች ለፖሊስ በሰጡት መረጃ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፍ ዴሊ ኒውስ ዘግቧል፡፡

@ t.me/fontenina2018
ሰሞኑን በታይላንድ አውቶቡሱ በትራፊክ መብራት ላይ ቆሞ ሳለ አንዲት ሴተኛ አዳሪ ወደ ባሱ ተሳፋሪዎች ዘላ ገብታ የ55 ዓመቱን ተጓዥ ቀኝ ጆሮ ነክሳዋለች ። የጆሮ ቅርፊቱን ቁራጭ እንደበላችውም ተሰምቷል።ጭካኔ ወይስ ስካር?
በህንድ ሀሰተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከፍተው ሲሰሩ የነበሩ ወንጀለኞች ተያዙ፤ ከትክክለኛው ፖሊስ ጣቢያ በ500 ሜትር ብቻ ርቀት ነበረው


በህንድ ቢሃር ግዛት ውስጥ ያለ የወሮበሎች ቡድን ለስምንት ወራት ያህል ሀሰተኛ ፖሊስ ጣቢያን ከፍቶ ሲሰራ እንደነበረ ተደርሶበታል። በቢሃር ግዛት ባንካ ከተማ ውስጥ ይህ ቡድን የመሰረተው ፖሊስ ጣቢያ ከእውነተኛው ፖሊስ ጣቢያ 500 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነበር።

አጭበርባሪዎቹ የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው፣ የጦር መሳሪያ ታጥቀው በመዘዋወር በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማጭበርበር፣ ቅሬታ ለመመዝገብ ጉቦ በመጠየቅ፣ፖሊስ በመምሰል አስገድደው ጣቢያቸው ድረስ በመውሰድ ዝርፊያ ሲፈፅሙ ነበር።አንድ ትክክለኛ የፖሊስ መኮንን እንቅስቃሴያቸውን ሲያጤን ቆይቶ ወደ ሀሰተኛው ጣቢያ ሲገቡ በመመልከቱ ከ8 ወራት ማጭበርበር በኃላ ተይዘዋል።

በስምኦን ደረጄ
ተአምረኛው ዲማ ...

በኢትዮጵያ፣ ነገሌ ቦረና፣ ጎብቻ ቀበሌ ውስጥ ከ32 ዓመት በፊት ሞቷል ተብሎ ወዳጅ ዘመድ እርሙን ያወጣለት ሰው፣ 'አለሁ' ብሎ የቤተሰቦቹን ደጃፍ አንኳክቷል።

ዲማ ዶዮ ቦሩ ይባላል በነገሌ ቦረና ነው ነዋሪነቱ በ1982 ዓ.ም. በወቅቱ አገሪቱን ያስተዳድር የነበረው መንግሥት ለብሔራዊ ውትድርና በግዳጅ አብረውት ከ100 የማያንሱ ወጣቶች ለጦርነት ይወሰዳል።

ከዘመተ በኋላ ቤተሰቦቹ የሰሙት ወሬ በሐዘን ማቅ እንዲለብሱ አደረጋቸው፤ ወላጆቹ በነበረው ጦርነት ላይ ጓደኞቹ መሞታቸውን፣ ዲማ ደግሞ መቁሰሉን ነበር የሰሙት፤ በእርግጥ ልጃቸው ስለመሞቱ ከማንም ምንም ዓይነት ማረጋገጫ አላገኙም።

ዲማ በወታደርነት በግዳጅ እንዲዘምት ሲደረግ አላገባም፤አልወለደም ነበር። ለዓመታት ድምፁ የጠፋው ዲማ ያፈራቸውን ንብረቶች፣ ከብቶች ቤተሰቡ ተከፋፈለ።ታዲያ ይህ ሁሉ ከሆነ ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ ነበር ዲማ ቤተሰቦቹን ፈልጎ የመጣው።

በብዙዎች ዘንድ እንደ ተዓምር የሆነው ዲማ ብዙዎች ቤተሰቦቹ ዘንድ እየመጡ የቤተሰቡን ደስታ ከመጋራት ባሻገር ጥያቄም አላቸው።

ከ32 ዓመት በፊት አብረውት ዘምተው የነበሩ የአካባቢው ወጣቶች፣ዛሬም በሕይወት ካሉ ለማረጋገጥ የሚፈልጉ መኖራቸውን የዲማ የወንድም ልጅ ይናገራል።

ዲማ ሞቶ አፈር ያላለበሱትን ልጅ ሞቷል ብለው እርማቸውን ለማውጣት የተቸገሩት እናት፥ሞቷል እርሺው ሲሉኝ እሺ አላልኩም ነበር፤ እንደ ሞተ አይሰማኝም ነበር፤ ይመጣል ብዬ አስብ ነበር ይላሉ።

ስንት ዓመቱ እንደነበር አላስታውስም የሚሉት እናት አብረን እየሄድን እያለ ነው መጥተው በጉልበት ነጥቀውኝ የወሰዱት እርሱ የመጣ ዕለት በደስታ ራሴን ስቼ ነበር፤እንደ ዐይናችን ብሌን የምንሳሳለት ልጅ ነበር በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።
እንኳን አደረሳችሁ