የኡስታዝ ኸይረዲን ሀሰን ምክሮችና ግጥሞች
1.06K subscribers
3 photos
6 videos
5 files
13 links
የኡስታዝ ኸይረዲን ሀሰን ቶኪቻው የስልጢኛና የአማርኛ መልእክቶች በተከታታይ እንለቃለን። የወንድማችን አጅር እንዳይቋረጥ ሁላችንም ቻነሉን እና መልእክቶቹን ሼር እናድርግለት!

ግንቦት 2/2010

www.t.me/ustaztokichaw
Download Telegram
Channel name was changed to «የኡስታዝ ኸይረዲን ሀሰን ምክሮችና ግጥሞች»
Audio
ኸይረዲን ረሂመሁላህ በስልጢኛ
ሰብር አድርጉ ይላል።

አላህ ጀነተልፊርደውስን ይለግሰው

http://t.me/ustaztokichaw
Audio
ከመሞቱ ጥቂት ቀናት በፊት ለነሲሀ ግሩፕ ዱአቶች ረመዳንን አስመልክቶ በርትተው መስራት... ማጋጋል እንዳለባቸው ሲያስታውስ!

Http://t.me/ustaztokichaw
ይህን ታላቅ ወንድማችንን ካወቅኩበት ግዜ ጀምሮ ባለፉት 23 ዓመታት ውስጥ በአካል ባገኘሁት ቁጥር ወይም መልእክቱን በሰማሁት አጋጣሚ እንዲሁም ከአንዳንድ ወንድሞች ጋር ስለሱ የዳእዋ ውስጥ ተሳትፎና የአኗኗር ዘይቤ ስናወጋ እንደታዘብኩት ታላቅ የሆነ የተግባር ሰው ነበር። አላህም ወፈቀውና እየተነገረለት ባለው ሁኔታ ይህችን አለም ኖራት። በዚያም ላይ ተለያት። ረሂመሁላሁ ራህመተን ዋሲኣ።

ወንድማችን ኸይረዲንን እንደታዘብኩት…

ንግግረ አጭር
መልእክተ ሠፊ

በሉ … ስሩ ብቻ ሳይሆን
ቀድሞ ተሰላፊ

ተስፋን ሚያለመልም
ሀሳብን ገፋፊ

ቀልዱ ቁምነገሩ
ልብ ላይ አራፊ።
ነበር!

ቋንቋ ቀይሮ እንኳን
ሀሳቡ የሚገባህ

የማትቃወመው
ከልብ የሚነግርህ

በመልካም ሚታወቅ
በበጎ የሚወሳ

ለገጠሩ የሚጮህ
ምንጩን የማይረሳ

ከከተሜው የሚኖር
ለኸይር ሚያነሳሳ

እንደኔ እንዳንተ ስራ ቤቴ ሳይል
ለዳዕዋ እንደሳሳ
ገጠሩን ለማንቃት
ለኪሱ ሳይሳሳ

ይኸው ዛሬ ሄደ
የጉዞው ቀን ደርሳ
በአቋሙ እንደፀና
ተግባራዊው አንበሳ።

እርግጥ
ምሉእ ሰው ባይኖርም
ከነቢያት በቀር
ሚደነቅ ባይኖርም
በሰሃቦች ወደር
ካለው ህዝብ መሃል
ለየት ያለ ሲኖር
ቢወሳ መልካሙ
ሳይበዛ ቢነገር
ማካበድ አይሆንም
አልፎ ከመማማር።

እሱስ ከስራው ጋር ይኸው ተገናኘ
ከኛስ ሚጠበቀው በወቅቱ ተገኘ?

የሰራውን ኸይራት
አላህ ይቀበለው
ስህተቱን ግድፈቱን
ሁሉንም ይለፈው
ወንጀል ሀጢኣቱን
ይተወው ይማረው
ከቀብር ስቃይም
ከአዛብ ያርቀው
ያቺ የለፋላትን
ምኞቱን ያድርሰው
ጀነተል ፊርደውስን
ሸልሞ ያስገባው
ልጅ ቤተሰቦቹንም
ፅናትን ይስጣቸው።
ከዱንያ ሃሳብ ከኣኺራ ስጋት
እሱ ይታደጋቸው።
ተተኪ ወገንም ረዳት ያርግላቸው።

እኛም ኸይር እንሸምት

ሰበቡ ሳያልፈን
ሂሳቡን በመዝጋት

የቁም እስረኛ እንዳይሆን
ዕዳው እስኪነሳለት
የቻለ በቻለው ካሁኑ ይሩጥለት።

አቡፈውዛን አህመድ ሙሀመድ (ሲራ)
Http://t.me/ustaztokichaw
Audio
#ስለ_ኸይረዲን

ኡስታዝ መሀመድ ሰዒድ አስልጢይ አልመደኒይ ሀፊዘሁላህ

Http://t.me/ustaztokichaw
ዛሬ ዳዕዋ ላይ የተፈጠረው ክፍተት እጅግ በጣም ሰፊ ነው። *ዳዕዋችን ያጣው አንድ ዳዒ ሳይሆን በብዙ ዳዒያን የማይተካ ታላቅ ዳዒ ነው።* ኸይረዲን ሀሰን *(ቶክቻው)* አብዛኛውን የህይወቱን ክፍል ለዳዕዋ ያደረገ ዘርፈ ብዙ የዳዕዋ ስራዎችን ለብቻው የሚወጣ በተለይ *ለክፍለ ሀገር ዳዕዋ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በገንዘብ በእውቀቱና በጉልበቱ ወደኋላ ሳይል የሚችለውን ሁሉ የሚያደርግ ታላቅ ዳዒ ነበር* ረሂመሁሏሁ ረህመተን ዋሲዓህ።
ኸይረዲን ሀሰን የሚገርም መካሪ፣ ዳዒዎችን ሞራል በመስጠት ተወዳዳሪ የሌለው፣ ለተራ ወሬ ቦታ የሌለውና ሰዓቱን በአግባቡ ለዳዕዋ የሚጠቀም ልዩ ተሰጥኦ የተቸረ ዳዒ ነበር። አሏህ ፊርደውስ ይወፍቀው ክቡር ወንድማችንን በማጣታችን እጅግ በጣም አዝነናል ይሁንና አሏህ የሚወደውን እንጂ አንናገርም።

رحمك الله أخانا الغالي رحمة واسعة وأسكنك الفردوس الأعلى اللهم أجرنا في مصيبتنا واخلف لنا خيرا منه

ዛዱል መዓድ የትምህርት መድረክ



Http://t.me/ustaztokichaw