ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
15.6K subscribers
616 photos
41 videos
1 file
79 links
ምንም አይነት መፅሀፍ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናመጣሎታለን፡
በሚያስገርም "ከ10-50%" በሆነ የዋጋ ቅናሽ ሞክረው ይዩን በአገልግሎታችን ይደሰታሉ

Free delivery
@Guramaylebooks

@Guramayelie 0912319263
Download Telegram
#ችግሩ_አንተ_ራስህ_ነህ!

በሕይወት ውስጥ የሚያናድዱ፣ የሚያበሳጩ፣ የሚያሳዝኑና የሚያበሽቁ ሰዎችና ሁኔታዎች የመኖራቸውን ያህል፤ አነቃቂ፣ ተስፋ ሰጪ፣ አጋዥ እንዲሁም ለሕይወት አላማና ትርጉም የሚሰጡ ሰዎችና ሁኔታዎችም ይኖራሉ።

ከስሜቶችህ ግማሹን ብቻ እያስተናገድክ ከቀጠልክ፣ ራስህን ባጭር ታስቀረዋለህ። የሚያበሳጭና የማይመች ነገርን ሊያመጣ የሚችል ማንኛውንም ሁኔታ ሲያጋጥምህ፣ ያንን ስሜት ለመቋቋም የሚያስችል መሳሪያ ስለሌለህ ሁኔታውን ለማስወገድ ከመንገድህ ወጥተህ መሄድ ትጀምራለህ። ይህ ማለት በመጨረሻ ሕይወትህን ወደተሻለ ሁኔታ የሚቀይሩትን አጋጣሚዎችና ድርጊቶች ማስወገድ ትጀምራለህ ማለት ነው።

በተጨማሪም ስሜቶችህን ማስተናገድ አለመቻል ማለት፣ ከእነሱ ጋር ተጣብቀሃል ማለት ነው። ቁጣህንና ሀዘንህን እንዴት ማስወገድ እንዳለብህ ስለማታውቅ በእነርሱ እንደተሞላህ ትቀመጣለህ። ግማሹን ስሜትህን ብቻ ማስተናገድ የምትችል ከሆነ፣ በመጨረሻ የምትኖረው ከምትፈልገው ሕይወት ግማሹን ብቻ ነው።

#ችግሩ_እና_ተራራው_አንተ_ራስህ ነህና ረጋ ብለህ ሙሉ ስሜትህን አስተናግድ፤ ለዚህ ደግሞ ተራራው ራስህ መሆንህንና እንዴት ደልዳላ ሜዳ እንደምታደርገው መጽሐፉ ያስተምርሀል።

መጽሐፉን በአማርኛም በእንግሊዝኛም ገበያ ላይ ያገኙታል።