አፍላ መፅሔት
151 subscribers
6 photos
1 file
2 links
ነፃ እና ፅዱ ወጣትነት

ለማንኛውም አስተያየቶ ፣ ሀሳቦ እና ለህትመት እንዲበቃ የሚፈልጉትን ፅሁፍ ለመላክ በ @Etsegenet_Melkamu ወይም @Yilo15 ይጠቀሙ።
Download Telegram
Channel created
Channel photo updated
ልዩ የመዝናኛ መፅሔት!

"አፍላ"

ሁሉንም በዓይነት በዓይነቱ የምናገኝበት
📌የህግ ጉዳዮች
📌ፍልስፍና
📌ወቅታዊ እና የማህበረሰቡን ትርታ የያዙ ትንታኔዎች
📌አኗኗራችንን የሚያቀሉ ጥቆማዎች
📌በጥልቅ እይታ የታጀቡ ምስሎች እና ሌሎችም እምቅ ሀሳቦች የተተነፈሱበት መፅሔት ይዘንላቹ ብቅ ብለናል።

በጣም በቅርቡ ይጠብቁን!!!
ትልቅ ዜና❗️

አፍላ መፅሔት ለንባብ ወደ እናንተ ቀርቧል።

መፅሔቱን ለማግኘት እና ለማንበብ የምትፈልጉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ከ97.7 ራዲዮ ጣቢያ ፊት ለፊት በሚገኘው የምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ ቤተ-መፃህፍት ማግኘት እንደምትችሉ በደስታ እንገልፃለን።

በተጨማሪም ነገ እና ከነገ ወድያ በሚኖሩ መድረኮች ማለትም
📌አርብ ሰኔ 3 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ UNA-ET HU Chapter በሚያዘጋጀው ታላላቅ እንግዶች በሚገኙበት የፕሮጀክት ማስጀመርያ መድረክ
📌ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ በሚኖረው የህግ ት/ቤት ከ ILO ፕሮጀክት ጋር በሚያዘጋጀው የMoot Court ውድድር ለይ የምናቀርብላቹ መሆኑን እናሳውቃለን።

ከዚህ ውጭ ላላቹ አንባቢዎቻችን በዲጂታል አማራጭ አቅርበንላችኃል።

ታድያ "አፍላ መፅሔት" የሚለውን የቴሌግራም ገፃችንን በ@Aflamagazine በመግባት ይከታተሉ። አስተያየት እና ሀሳቦን ያድርሱን። ለህትመት እንዲበቃ የሚፈልጉትን ፅሁፍ በዛው ያቀብሉን።

ከዚህም ሌላ @Etsegenet_Melkamu ወይም @Yilo15 አልያም በ0982006262 ይፃፉልን።

#አፍላ_መፅሔት
#ነፃ_እና_ፅዱ_ወጣትነት
@Aflamagazine

@Aflamagazine
Forwarded from JULSA - JU Law Students' Association (NaThan)
The magazine, which is prepared by Etsegenet Melkamu a 5th year law student of Hawassa university, is published!

This entertaining and educational magazine has
✍🏾 Legal matters
✍🏾 Philosophy
✍🏾 Current societal issues
✍🏾 Life tips
✍🏾 Immersive pictures &
✍🏾 Potential ideas
are put in it in a colorful and eye-catching manner.

✍🏾 Such a motivating piece!

✔️ Check it out!
👉🏽 You can contact the author at @Etsegenet_Melkamu


It is a well known fact that our JULSA magazine team has been established. They are gathering people and ideas to drop #JULSA_Magazine in this summer. You can contact @Morka_D & @natigrace if you want to be part of it.
Forwarded from Hawassa ማዕድ
Team hawassa maed is glad to be featured in afla magazine. We invite you all to check it out.

#Teamhawassamaed
Executive producer Etsegenet_melkamu
አቦጮሮ

ከእኛ ሰፈር እንደ አቦጮሮ የቡሄ ትዝታ ሊኖረው የሚችል ሰው አይገኝም፡፡ በልጅነታችን የሆያሆዬ ቡድን አደራጅ ከመሆን ጀምሮ ሙልሙል እና ገንዘብ ያዥ ሆኖ በመስራት ፣ በአከባቢያችን ቡሄ ሲመጣ በሚደረገው የጅራፍ ግርፍያ እስከመሳተፍ ድረስ አገልግሏል፡፡ በጅራፍ ግርፊያው የእኛ ሰፈር ሁሌ እንዳሸነፈ የዘለቀውም በአቦጮሮ የጅራፍ ገመዳ እና አገራረፍ ጥበብ አመካኝነት ነው፡፡ የአቦጮሮ ጅራፍ ከፈረስ ጭራ እና ከቃጫ የተገመደ ጫፍ ሲኖረው ውስጡም የተደበቀ ቀጭንና ጠንካራ ሽቦ ይጨመርበታል፡፡ ለጅራፍ ግርፊያ የሚወጣ ማንኛውም ተጋራፊ ተበድሮም ይሁን ተለክቶ ያለውን ሰብስቦ ደራርቦ መልበስ ካልቻለ የአቦጮሮን የሽቦ ጅራፍ በየትኛውም አቅም መቋቋም እንደማይችል ግልፅ ነው፡፡ የፈለገውን ያህል ልብስ የደረበ ጎረምሳ በግርፊው የለበሰው እላዪ ለይ እስኪያልቅ ስለሚፋለም ትዕይንቱ ማራኪም አሳቃቂም ነበር፡፡ ከሁሉም ከሁሉም በአቦጮሮ የቡሄ ትዝታ ውስጥ የሚገኑት ግን ወ/ሮ አጋረደች እና ጋሽ ተምትሜ ናቸው፡፡ ወ/ሮ አጋረደች በፀባያቸው ሰው ማቅረብም ሆነ ከቤታቸው ማስገባት የማይጥማቸው ስለሆኑ አቦጮሮ እና ጓደኞቹንም በአንዱ ቡሄ ጉድ ሰርተዋቸዋል፡፡ እንደልማዳቸው ሆ ለማለት በሄዱበት የአሳማ ስጋ ቅንጣቢ እየቀለቡ ያሳደጉትን አንበሳ የሚያህል ተናካሽ ውሻ ለቀው ያልያዘውን አባሮ አፉ የገባውን አቦጮሮ ሱሪ ጎትቶ ከመሬት ካንከባለለው በኃላ ለማስለቀቅ ሲወራጭ የጆሮውን በጥርሱ ስለጎመደው አቦጮሮ እስካሁን በግማሽ ጆሮ ቀርቷል፡፡ ሆኖም ግን ከወይዘሮ አጋረደች በተለየ ጋሽ ተምትሜ በራፍ መድረስ የማይቻለው የቡሄ እና የእንቁጣጣሽ ቀን ብቻ ነው፡፡ሰበቡ ደግሞ ጋሽ ተምትሜ ልመና አጥብቀው በመጥላታቸው የእኛ በበአል እና በጭፈራ እያመካኙ ገንዘብና ሙልሙል መቀበል ስለማይጥማቸው ነው፡፡ ያም ሆኖ ልባቸው ቡቡና መንፈሳቸውም ደና ግጥም ወዳድ ስለሆነ ሁላችንም በዚም በዚያም ገብተን ተሸልመን መውጣታችን አይቀሬ ነው፡፡ እንደውም በዚህ አጋጣሚ ባለፈው ማለዳ ለይ ከጊቢያቸው በራፍ ለልመና የቆመች የጠዋት አዝማሪ (ላሊበላ)
"የዘንድሮ ነገር ቁርጡም አልታወቀ ፣
ወሬ በመጠየቅ ልባችን ወለቀ፡፡ " ብላ በመግጠሟ ሀምሳ ብር ሰጥተው አሰናብተዋታል፡፡ አቦጮሮና ጓደኞቹም ሆያ ሆዬ ለመጨፈር ቤታቸው በሄዱ ቁጥር ጋሽ ተምትምን የሚያሞግስ ግጥም ስለሚያወርዱ ተሸልመው መላካቸው የታወቀ ነው፡፡ የነ አቦጮሮን ድምፅ ከሩቅ ሲሰሙ "በይ ማነሽ ነይ በሬን ገጥመሽ ዝጊልኝ ፍጠኚ!" እያሉ የቆዩት ተምትሜ ሆ ባዮቹ ደርሰው.....
"የኔማ ጌታ ጌታ ጠንበለል ፣
ዝናቡ መጣ ወዴት ልጠለል፡፡" ማለት ሲጀምሩ "ድሮስ እኔ ተምትሜ እየዞርክ ቂጣ ልቀም ብዬሃለው ነይ ክፈቺ አንቺ!" ይሉና የቤት አገልጋያቸውን ያዛሉ፡፡ አቦጮሮም ስሜታቸውን እያነበበ ......
"የኔማ ተምትም የሰጠኝ ሙክት ፣
ግንባረ ቦቃ ባለምልክት፡፡" ይላል ይሄኔ ከሙልሙሉ አንድ ሁለቱን ከብሩም እጃቸው የገባውን አድርገው ያሰናብታሉ፡፡ ታድያ ከቆዳ የተሰራውን የሙልሙል መያዣ ከረጢት የሚያነግተው አቦጮሮ ከየቤቱ የሰበሰቡትን ሙልሙል በየአይነቱ ተሸክሞ መጎዝ ብቻ ስለማይሆንለት ወደኃላ ቀረት እያለ ካማረው ለይ ስለሚገምጥ ከፊት የቀደሙት ጓደኞቹ ፈጥኖ እንዲራመድ ለመንገር ስሙን ሲጠሩ በአፉ የሚወትፈው ዳቦ ድምፁን እያፈነው ነበር "አቤት" የሚለው፡፡እንዲሁ እንደልማዱም በአንዱ ቡሄ ከአንዱ ቤት ለመግባት ሲጣደፉ ከየቤቱ ከተገኘው ሙልሙል እየቆረሰ የሚበላው አቦጮሮ ከመጠን በላይ ሆዱ ተነፍቶ ስለነበር መራመድ አቅቶት ሲወላገድ ከጋሽ ተምትሜ ቤት ፊት ለፊት መንገዱ ተቦርቡሮ ጎርፍና ለብዙ ወራት የተጠራቀመ ቆሻሻ ከሞሉት ጉድጓድ ተሻገርኩ ብሎ ስለወደቀ እከክ ይዞት ሁላችንም ከአጠገቡ እንዳንደርስ ማስጠንቀቂያ ይሰጠን ነበር፡፡ ይኸው አሁንም ቢሆን ቆሻሻ ውሃ ውስጥ በመውደቁ የያዘው እከክ ለረጅም ጊዜ ከአካሉ ጋር በመቆየቱ ተሽሎት እንኳን ቆዳው ተዥጎርጉሮ ቀርቷል፡፡ አቦጮሮና ቡሄ በሰፈራችን ታሪክ ካለመላቀቃቸው የተነሳ ይኸው ዛሬ እንኳን አዳዲሶቹ የሰፈራችን ሆያ ሆዬ ተጨዋቾች ከአቦጮሮ በራፍ ቆመው በራሳቸው ግጥም
"ሆያ ሆዬ ጉዴ ፣
ጋሽ ቡራቡሬ ጆሮ ጎማዴ ፣
ሙልሙል ሙልሙል ይላል ሆዴ፡፡" እያሉ በነገር ሲወርፉት ውለዋል፡፡

እፀገነት መልካሙ
መልካም የቡሄ በዓል!!!

@Aflamagazine
@Aflamagazine