ناصر الدين(ናሲሩዲን)
479 subscribers
557 photos
87 videos
6 files
369 links
[[ وَجَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا ]]

{እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።}

ሼር add በማድረግ የበኩላችን እንወጣ


https://t.me/joinchat/jhrmqQH66YtiOGFk
Download Telegram
የጠቅላዩ ቢሮ ስብሰባ

ሰኔ 29/2014 ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ከጠቅላይ አብይ አህመድ ጋር በመጅሊሱ ወቅታዊ ሁኔታ ስብሰባ ተደርጓል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አዳራሹ እንደገባ " የስብሰባው አጀንዳ ሙስሊሙ አንድ ሆኖ እንዲቀጥል መፍትሄ ለመፈለግ ነው። እዚህ ያላችሁት ከሁለት ወገን የተጠራችሁ ናችሁ" አሉ። በዚህ ሰአት የወሀቢያ ተወካዮች "ሁለት ወገን" መባል የለበትም ሙስሊም ነን የሚል የተለመደ ማደናገሪያቸውን አቀረቡ። ጠቅላዩም በምላሹ "እናንተ አንድ አይደላችሁም፣ አንድ እንዳልሆናቹ ዓለም ያውቃል፣ ውስጣችሁ አንድ እንዳልሆናቹህ ታውቁታላችሁ፣ ዝም ብሎ አንድ ነን ሚባል ነገር አያስፈልግም መፍትሄ መፈለግ ነው ሚሻለው" ብሎ መለሰ።

ከወሃብያው ወገን ህግ ይከበር ሁለት ቡድን አይደለንም። ህግ አክብሮ የሚሰራ እና ህግ አልቀበልም ያለ ያፈነገጠ ቡድን ነው ያለው በሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የሚመራው የቤረወጎው መጅሊስ እውቅና ይሰጠው አፈንጋጮቹ ይቀጡ… …ወዘተ ብለው ብዙ ቀባጠሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን አጭር መልስ ነው የሰጠው " ሀጂ ኢብራሂም ያካሄዱት ምርጫ በድምፅ ብልጫ እጅ በማውጣት ነው፣ ይህ የሚሰራው ለእኛ ለፖለቲከኞች ነው። የሃይማኖት ሰዎች በመስማማት በቀልብ አንድ ሆነው መወሰን ነው ያለባቸው" ብሎ የሀጂ ኢብራሂም የቤርጎው መጅሊስ ተቀባይነት እንደሌለው ደጋግሞ አስረግጦ ነገራቸው።

በመቀጠልም ጠቅላዩ " በሸራተን የተመረጠው 26ቱ ዑለማ የሙስሊሙን ችግር በመፍታት ሙስሊሙን አንድ ማድረግ ስላልቻለ ለመፍትሄ የምንመለሰው ወደ ቀድሞው 26ቱን ዑለማ ወደ መረጠው ወደ ሸራተኑ ጉባኤ ነው። 150 ሰው ከሱፊ 150 ሰው (ከወሃቢ) ተመርጠው የነበሩ ሰዎች ድጋሚ በቴሌቪዥን ጥሪ ይደረግላቸውና ይሰብሰቡ፣ ሰነዱ ቀርቦላቸው ይወያዩ ከዛ አዲስ አመራር ይምረጡ፣ አዲስ የሚመረጠው አማራር የመጅሊሱነ ቁልፍ ይረከባል፣ ከዛ በኋላ አልተመችኝ የሚል ካለ ዞር ማለት ነው ያለበት እንጂ ሙስሊሙን እንዲረብሽ አንፈቅድም። የሸራተኑ ጉባኤ ይመለስ በሚለው አልስማማም ካላቹ ቀድሞ የነበረው በመሀመድ አሚን የሚመራው መጅሊስ ይመለሳል ግን ይሄ መፍትሄ አይሆንም። ዳግም የሚሰበሰበው የሸራተን ጉባኤ መስማማት ካልቻለ ህዝቡ እንዲወስን ይደረጋል። ከሁለቱም ወገን ከ150 ሰው ውጭ ስብሰባው ላይ መገኘት አይችልም ፖሊስ ይህን አስፈፅም ስማቸው ዝርዝር ውስጥ ካሉት ሰዎች ውጭ ማንም ወደ አዳራሹ እንዳይገባ። ምርጫ አትጠቀሙ በመስማማት ሥሩ፣ 26ቱ ዑለማ ቢስማማ ይህ ሁሉ ችግር ባልተፈጠረ ነበር" በማለት ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

የዒዱን ሶላት በተመለከተ "ምንም አይነት ንግግር ሳይኖር ሰላትና ኹጥባ ብቻ ተደርጎ እንዲበተን ከተስማማቹ ከሰላት በፊት ሙፍቲ ዱዓ ቢያደርጉ ከሰላት በኋላ ሀጂ ኢብራሂም ዱዓ ቢያደርጉ ምን ችግር አለው? ዋናው የእናንተ መስማማት ነው" በማለት ጠቅላዩ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን ያለ ንግግር ሰላትና ኹጥባ ተሰግዶ ዒዱ ይለፍ በሚለው ሁሉም በአንድ ድምፅ ተስማምቷል። የዒዱን ሶላት በተመለከተ ሀጅ ጣሃ እና ክቡር አቶ አደም ፋራህ እንዲያስተናብሩና በመጨረሻም አዲስ አበባ መጅሊስ ያግዛቸው የሚል ሃሳብ አቅርበዋል ጠቅላዩ።


ሙፍቲና ሀጅ ኢብራሂምን ትወዱኛላችሁ ወይ? ብለው ጠቅላዩ ለየብቻ የጠየቁ ሲሆን ሁለቱም አዎ እንዎዶታለን የሚል መልስ ሲሰጡ " ለእኔ ለልጃችሁ ስትሉ የሸራተኑ ጉባኤ ድጋሚ ተሰብስቦ አዲስ አመራር እስኪመጥ ይህችን 10 ቀን አብራችሁ ብትሰሩ እንደ አባት ሆናችሁ ብታስተባብሩ!" ብለው ጠቅላዩ ላቀረቡት ሃሳብ ሙፍቲ በዝምታ አልፈውታል።

★ የስብሰባው ጭብጥ ማጠቃለያ

1) የሚያዝያ 23 ስብሰባ በነበሩ 300 ሰዎች ብቻ እንዲደገም ምንም ተጨማሪ አዲስ ሰው እንደማይገባ

2) ከሁለቱም ወገኖች የሚመጡ 300 ሰዎች አዲስ አመራር ይምረጡ ለሚመረጠት አዲስ የመጅሊሱን ቁልፍ እናስረክባለን እነዚህን አዲስ አመራሮች ከተመረጡ በኋላ እረብሻለሁ የሚል እበጠብጣለሁ የሚል ካለ ከየትኛውም ወገን ቢሆን ጠንካራ እርምጃ እንወስድበታለን

3) ሚያዝያ 23 የተመረጡት 26 ዑለሞችንም እናንተ የሙስሊሙን አንድነት ማስጠበቅ ስላልቻላችሁ አዲስ አመራር ይመረጣል ብሏል። በዚህም 26ቱ ዑለማ ከዚህ በኋላ ዋጋ እንደሌለው አመላክቷል።

4) የቱፋ መጅሊስን በተመለከተ ያደረጉት ተግባር ትክክል እንዳልሆነ በድምፅ ብልጫ የሚመረጠው እኛ ፖለቲከኞች ጋር ነው ሀይማኖት በድምፅ ብልጫ አይመራም ሀይማኖት በልብ ነው ተስማምታችሁ ነበር መወሰን የነበረባችሁ በማለት ተናግሯል ህገወጥ ናችሁ አልላችሁም፣ ህገወጥ ናችሁ ለማለት የትኛውን ህግ እንዳፈረሳችሁ በዝርዝር ማወቅ አለብኝ። ነገር ግን አካሄዳቹ የፖለቲከኞች ነው በማለት በግልፅ ተናግሯል

5) በ10 ቀን ውስጥ ሁሉም ሚያዝያ 23 የነበሩ ሰዎችን ሰብስቡ አዲስ ምርጫ አድርጉ ይህ የመንግስት ውሳኔ ነው መቃወም አትችሉም ብሏል

6) እንደባለፈው ሸራተን ስብሰባ ችግር እንዳይፈጠር የእኛ ሰዎች ጥያቄ አንስተው ነበር አይነሳም ይህን ጉዳይ አደም ፋራህ ፌዴራል ፖሊስ ደምመላሽ ከ150 ሱፊ ሰለፊ ውጭ አንድ ሰው ዝር እንዳይል የስም ዝርዝሩን ከሙፍቲ እንዲቀበሉ ፖሊስ እንዲያስፈፅም ደጋግሞ ትዕዛዝ ሰጥቷል

7) የዒዱን ነገር በተመለከተ ማንም ንግግር አያድርግ ሰግዳችሁ ውጡ ከተስማማችሁ ሙፍቲም ቱፋም ዱዓ ያድርጉ ካልሆነ ያለ ንግግር በሰላም በዓሉን አክብሩ

8) ፌስቡክ ላይ የማይሆን መረጃ እየሰጣችሁ ሙስሊሙን አትበጥብጡ በሚል ሁለቱንም ወገኖች አስጠንቅቋል ለአስር ቀን ታገሱ ከዛ በኋላ አዲስ አመራር ይመረጣል

9) ሁለቱም ወገን በዚህ የማትስማሙ ከሆነ ግን የቀድሞን መጅሊስ አመራር ሸህ መሀመድ አሚንን እንመልሰዋለን እኔ ነኝ ለሰላም ብዬ ያለ አግባብ ያወረድኩት ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክቡ ያደረግኩት ብሏል በጣም በተደጋጋሚ

ህጋዊው የመጅሊስ አመራሮች እነ መሀመድ አሚን እንደሆኑ በግልፅ ተናግሯል

10) ስለ ቦርድ ምንም የተነሳ ነገር የለም ያለፉት ሶስት ዓመታት ሱፍያው የሚያነሳቸው ቅሬታዎችን ጠቅላዩ ተረድቷቸዋል ዑለሞቹ ህዝብ እንዳልመረጣቸው ቦርድ የሚባል ነገር እኛ እንዳልመረጥን ለዚህ ደግሞ በድጋሚ ስብሰባ አድርጋችሁ እራሳችሁ አዲስ አመራር ምረጡ ። ነ ከሚረጠው አዲስ አመራር ጋር መንግስት ተባብሮ ይሰራል።

11) አዲስ አበባ መጅሊስ ባለፈው ሳምንት ብዙ ወንድሞቻችን ታስራችሁ እንደነበር ይታወቃል እናም ያ ክሰተት ትልቅ ለውጥ አምጥቷል መንግስትም ይህን ስብሰባ ለመጥራት ሰበብ የሆነው ያ ክስተት ነበር መንግስት ጋር ትልቅ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጓል ስለ ረብሻው በሰፊው ነገሮችን ደስሷል የጀመዓው ትግል ፍሬ አፍርቷል አልሃምዱሊላህ

12) ወሀብዮቹ ብዙ ያነሱት ሙፍቲን ለማጠልሸት ህዝብን ለአመፅ ለሁከት እያነሳሱት እንደሆነ ብዙ ብዙ ብለዋል። እንደ አቡበከር አህመድ አይነት ወሃብዮቹም ለአመፅ ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር በግልፅ ተነግሯል።

13) ለዚህ 10 ቀን አዲስ አመራር እስኪመረጥ ሁሉም ቀድሞ ወደነበረበት መጅሊስ ይመለስ፣ አዲስ አበባ መጅሊስም በነበረበት ይቀጥል፣ ሀጂ ኢብራሂም ቲፋም ወደነበሩበት (ኦሮሚያ መጅሊስ) ይመለሱ ምንም ነገር መለወጥ የለበትም ከአዲስ አመራር መረጣ በኋላ የሚሆነው ይሆናል ብለዋል ጠቅላዩ።
🅰️♻️ *قال الإمام النووي رحمه الله في كتابه "الأذكار " عن يوم عرفة :*

١) فيُستحبّ الإِكثارُ من الذكر والدعاء، ويَجتهدُ في ذلك، فهذا اليوم أفضلُ أيام السنة للدعاء، ...
٢) فينبغي أن يستفرغَ الإِنسانُ وُسعَه في الذكر والدعاء، وفي قراءة القرآن،
٣) وأن يدعوَ بأنواع الأدعية،
٤) ويأتي بأنواع الأذكار،
٥) ويدعو لنفسه،
٦) ويذكر في كلّ مكان،
٧) ويدعو منفرداً ومع جماعة، ويدعو لنفسه، ووالديه، وأقاربه ومشايخه، وأصحابه، وأصدقائه، وأحبابه، وسائر مَن أحسن إليه، وجميع المسلمين،
٨) وليحذرْ كلَّ الحذرِ من التقصير في ذلك كله، فإن هذا اليوم لا يمكن تداركه، بخلاف غيره، ...
٩) والسُّنّة أن يخفضَ صوتَه بالدعاء،
١٠) ويكثر من الاستغفار والتلفّظ بالتوبة من جميع المخالفات، مع الاعتقاد بالقلب،
١١) ويلحّ في الدعاء، ويكرّره، ولا يستبطئ الإِجابة،
١٢) ويفتح دعاءه ويختمه بالحمد لله تعالى والثناء عليه سبحانه وتعالى، والصلاة والتسليم على رسول الله صلى الله عليه وسلم، وليختمه بذلك ... "

@ahlusunawelgema
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአላህ በየአውቃቱ ነፈሀት አለው። ያቺ ነፈሀት ያገኘቹ ከሸቅይነት ነፃ ይወጣል።

አላህ ከነፈሀቱ ያገናኘን በዘመናችን ታላቅ ዓሊም ዛሂድ ተቅይ ነቅይ ሙሀቂቅ በሆኑት ሰይዲ ሙሀመድ ከቢሩ💚 ስም ዒድ ሙባረክ🌷🌷

https://t.me/ahlusunawelgema
·





በድጋሚ ዒድ ሙባረክ🌷
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሰላችሁበት ሰላምና በረከቱ ይስፈንባቹ…

ዒድ ሙባረክ
እኛ እስልምናን በተግባር ያስተማሩን…

አደብን ተዋዱዕን መተነናስን መተዛዘን ፍቅርን ሁሉም የሞላቸው ሳዳቶቻችን…አላህ ያቆይልን

የኢትዮጵያ ኢማሞች ኢማም እና የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም ሰይዲ ሰይድ ሀጅ ጧሃ

https://t.me/ahlusunawelgema
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዛን ላይ ተምጢጥ ተው ብንል አልሰማ ብላቹ … ይሃው ዶሮም ጀመረው😂

ለማንኛውም ሰላቶቻችን ያለ አዛን እንደምንሰግድ ታውቃላቹ?

መልካም ዒድ… የዒዱን በረካ አላህ ይስጠን

https://t.me/ahlusunawelgema
ሆቴል ማለት በአጭር አገላለፅ የዝሙት መንደር በተጨማሪ የኸምር መጠጫ ነው። … ሆቴል አልህ ዘንድ የተጠላ ቦታ ለመሆኑ ከዚህ በላይ ምን ሊሰራበት ነው የምትሹት
ነብዩ ሰዐወ የሀላል ንግድ የሚፈፀምባቸው ቦታዎችን እራሱ… አላህ ዘንድ የተጠላ ቦታ ገበያ ነው ብለው ገልፀውታል። ታድያ የዝሙትና የኸምር ቦታዎችስ

የመጅሊሱ አዳራሾች ለኢስላማዊ ጉዳይ መወያያ መመካከሪ ካልሆኑ ለኮንሰርት ነው እንዴ የተሰሩት
ዒድ ሙባረክ በሞሪታንያ ሻይ

ከኸይራቱ የሚያገናኘን ዒድ ያድርግልን
ጫት የማትቅሙ ሰዎች አትጀምሩ:: የጀመራችሁም እጅግ በጣም ቀንሱ:: አደብ ከሌለው እንኳንስ ጫት ምግብም ሶላትም ያስቀይማሉ:: ሥርዓት የሚያስይዘንና ጸባያችንን የሚያስተካክልልንን ሶላት ስንሰግድ ሥርዓት ካስፈለገ ወትሮም ከሥርዓት የሚያስወጣንን ጫት እንዴት ሊሆን ነው? አቀራርቤ እያወዳደርኩ አይደለም::

ጫት ከመደበኛ የአስተሳሰብ ምሕዋር እንደሚያስወጣ ይታወቃል:: የቻለ አይቅረበው:: የቀረበው ግን ከምንም በላይ ለሥርዓት ይጨነቅ:: ከምሕዋር ይወጣላ! ፈታ ለማለት እየቃምን የምን መጨነቅ ነው ትሉ ይሆናል:: ወንድሜ ሁሌ ፈታ ማለት የለም:: ዱንያ ላይ ጨምደድ የምትልበት ወቅት ይበዛል:: ፈታ ለማለት የምትቅመው ጫት ደግሞ ብዙ ነገርህን ያጨማድድብሃል:: ማጨማደድ ባሕሪው ነው:: ሰተት ብለህ ከገባህለት ይገባልሃል:: አምጣ ባለህ ቁጥር የምትሰጠው አባትህ ወይም እናትህ ወይም ልጅና ሚስትህ አይደለም:: ጫት እኮ አያዝንልህም:: ምን ብትሰጠው አይጠግብም::

የቀድሞ አባቶቻችንን አቃቃም ከደረስክበት:- ቤት ለማሞቅ ይጎዘጉዛሉ:: ጥቂት ነው ቀመስ የሚያደርጉት:: ከሚቃመው ደርቆ የሚጣለው ይበልጣል:: ሲጀመር የሚጣልም ያህል አያመጡም:: እስኪመረቅኑ አይቅሙም:: እኛ አሁን በማኪያቶ ከምንመረቅነው አይዘልም ማለት ይቻላል:: በእርግጥ በዚያው ልክ አጋድመውና ተጋድመው የሚቅሙም ነበሩ::

ሰውነትህን ፕሮግራም ከሰጠኸው ወዲያው ይለምዳል:: ሽንት ባስለመድከው ፕሮግራም ብቻ ይመጣል:: እቤት ውስጥ መፍሳት ከለመድክ የትም ታንዛርጣለህ:: ከተውከውም ይተውሃል:: ምግብ ባስለመድከው ወቅት ብቻ ትበላለህ:: ሰውነታችን ችግር ይለምዳል, ሀብት ይለምዳል, ሀዘን ይለምዳል, መርሳት ይለምዳል, ብርድና ሙቀት ሳይቀር ይለምዳል:: ዋናው ከልብ መቁረጥ ነው::

አንተስ ትቅማለህ ወይ? ካልከኝ አልቅምም ብል ይቀላል:: ከማኪያቶ ሙቀት እንዲዘል አልፈቅድለትም:: ከምቅመው ይልቅ የምጥለው ያስደስተኛል:: አሁን ላይ ባለ 70 የሚሉት ላይ 1/5ኛውን አልፈጅም:: ቤት ያሞቅና እንጥለዋለን:: እርሱም ከዕለታት ባንዱ ቀን:: ለ25 ዓመታት ያቆምኩ ሰው ነኝ:: ከዚያ ለ25 ቀናት ወይም ለ25 ወራት ላልነካ እችላለሁ::

በእስልምና ስም መቃሙን እንኳ ተውት:: እስልምና ንጽሕና ነው:: ለጡሃራ ደግሞ ከውሃም ውስጥ ውሃ ይመረጣል:: ጫትም እስኪያቆሽሽህ ከቃምክ ስተሃል:: ወላሂ!

Hassan injamo
https://t.me/Haseniye

https://t.me/mneyuredulahe
ምን ትላላቹ
ጫት ስለበላህ ሱፍይ አትባልም። ስላልበላህም ውሃብይ አትባልም። በቀላሉ ከሀገር ውስጥ ሀረር ድሬዳዋ ብትሄድ ከሱፍያው በላይ የሚቅመው ውሃብዩ ነው። አዲስም ውስጥ የምናውቃቸው የሚቅሙ ውሀብዮች አሉ። ድሬ ወይም ሀረር ሄደህ ጫት ሀራም ነው ብትል ውሃብዩ ነው አፈር ድሜ የሚያስበላህ።

ወንድሞች ሲጀመር ጫት አይደለም ከሱፍይነት ከእስልምና ጋር ምንም አያገናኘውም። ስለቃመ ሙስሊም አይባልም። ስላልቃመም ክርስቲያን አይባልም።

ጫት ልክ እንደ ሻይ ማክቶ ቡና ነው። ሌላ ምንም ለውጥ የለውም። ቡና ስለጠጣህ ሱፊ ሰለፊ አትባልም። ሻይም ማክያቶም ጫትም እንደዛው። ጫቱ ለአባቶች እንተወው። ዑለሞቹ ሲቅሙ ኪታብን ያቃራቸው ዘንድ አንድ ሁለት ነው የሚዙት።

አንተ የምትቅመው ቅራ ስንልህ ጊዜ የለኝም ያልከን ስትቅም የሚባክነው ጊዜስ ዑለሞች እኮ ያለ እውቀት የሚሰራ ዒባዳ ባጢል ነው። ተቀባይነት የለውም ብለዋል። እንደውም በፊቅህ በሻፊዕዮች ባፈድልን በሌሎች መዝሀቦችም በባፈድል ደረጃ ያለን ኪታብ ካልቀራ ሰላቱ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።❗️

👌ነገ የመጀመሪያ ሂሳብ የሚደረገው ሰላት ነው። ሰላቱ የተበላሻ ሁሉም ስራው ይበላሻል። ሰላቱ የተስተካከለ ሁሉም ስራው ይስተካከላል። ታድያ ሳትቀራ እንዴት ነው ሰላትህ የሚስተካከለው

አንዳንዱ ስለቃመ አረንጓዴ ስለለበሰ ሙስበሃ አንገቱ ላይ ስለደራረበ ወልይ ሱፍይ የሆነ ይመስለዋል። አትሸወድ ሱፍይነት በአጭር አገላለፅ
محاربة النفس لا سلم فيها
{ከነፍስያ ጋር ስምምነት የሌለው ጦርነት መክፈት ነው።}
አንተ ጃሂል ከሆንክ በመቅራት ነፍስያህ ጋር ጦርትነት መጀመር። በቀራሀው ለመስራት መታገል። ውስጥህም ውጭህም ለአላህ አሳልፈህ ለመስጠት የምታደርገው ጦርነት።

ብጣሽ ወረቀት ቀርተህ አፍህን በአላህ ባሮች እየከፈትክ ሱፍይነኝ ስትል አታፍርምተሰውፍነት ወሬ ሳይሆን ስራ ነው። ስራ ደግሞ የሚጀምረው ከዒልም ነው። ሰይዲ ኢማም ማሊክ
من تفقه ولم يتصوف فقد تفسق، ومن تصوف ولم يتفقه فقد تزندق
ዒልም ከስራ ጋር ስናገናኘው ውጤቱ ተሰውፍ ጋር ያደርሰናል። ዒልም እና ዐመል መነጣጠል የሚይችሉ የተሰውፍ መሰረቶች ናቸው።

የፈለገ ይቃም የፈለገ አይቃም መብቱ ነው። ቡናም የፈለገ ይጠጣ የፈለገ አይጠጣ መብቱ ነው። ሻይም ማክያቶም። ነገርግን ስለ ቃምክ ሱፍይ ሱፍይ አይሰራራህ።

https://t.me/ahlusunawelgema
ፕሮፍይል በማድረግ ላልደረሳቸው እንዲዳረስ ሰበብ ይሁኑ

https://t.me/DaralHijrataynIslamicSchool
በመጨረሻ ሰዓት