ناصر الدين(ናሲሩዲን)
477 subscribers
557 photos
87 videos
6 files
369 links
[[ وَجَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا ]]

{እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።}

ሼር add በማድረግ የበኩላችን እንወጣ


https://t.me/joinchat/jhrmqQH66YtiOGFk
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በድሩ ሁሴን የዛኔ በሰላማዊ ጊዜ የተናገረው
ባለቤትህ በፍቅር ቃላት ስታወራህ መንጠባረር ተውና ከሷዋ የበለጠ ፍቅር አሳያት። አንቺም ባልሽ ልቡን ከፍቶ ሲያወራሽ ከአንቺ ሌላ በምድር ሴት የሌለ አይምሰልሽ ተገቢውን ፍቅር ስጩ። ውጪ እኮ በንግግር በአለባበስ በተለያየ መልኩ የሚያማልሉት ብዙ ናቸው።።።።

ደግሞ እቤት ከባልሽ ጋር ስትሆኚ ድሪቶ ትለብሺና ከቤት ስትወጪ ተኳኩለሽ የምትሄጁ ሁለተኛ ለማግባት ነው ባልሽ ወደሌላ እንዲያይ አታድርጊው ተገቢውን ቦታ ስጩ

አብዛኛው ጊዜ ወንዶች ወደውጪ የሚያዩት ከሚስታቸው ተገቢውን ፍቅር ስለማያገኙ ነው። ከተቆጡ መከራ በፍቅር ቃላት ከመጡ መከራ ግራ ሲገባቸው ደጅ ይጠናሉ። ባልሽን አጥበቀሽ ያዢ❗️ አንተም ትዕግስት ይኑርህ እንደ ሸይጣን አትጣደፍ

@ahlusunawelgema
በወርቅ ቀለም የሚፃፍ ንግግር

አላህ የወደደው ወንጀሉ አይጎዳውም አላህ የጠላው ስራው አይጠቅመውም አሉ።

ሐፊዝ ሙራድ ሙሀመድ ሐፊዘሁላህ
​​➛➛ከመናገር ማሰብ ይቅደም➛➛

➲ በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል። ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት፡፡

አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፤

አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፤

አምስት መቶ ብር መክፈል፡፡

ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ "ሽንኩርቱን እበላለሁ" አላቸው፡፡
:
አንድ ኪሎ ሽንኩርት ቀረበለት፡፡ ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ታድያ ዓይኑ ማልቀስ ፣ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ፤ አልቻለም። ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና «መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡

ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ እንደደረሰ አልቻለም፡፡ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡

«እህሳ» አሉት ዳኛው፡፡

«አልቻልኩም» አላቸው፡፡

«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡

«በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡

«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት።

ብዙዎቻችን ከመናገራችን በፊት ማሰብ ሳንቸል ቀርተን በዘፈቀደ በተናገርነው ቃል እራሳችንን ፣ ቤተሰቦቻችንን ፣ ጎረቤታችንን አልፎም ሀገርን እረብሸናል፤ ጎድተናል፡፡ ሁሌም ከማውራታችን ከመፃፋችን በፊት የምናገረው ፣ የምፅፈው ነገር ሰዎችን ያስከፋል? እውነት ነው ብለን እንጠይቅ፡፡ እውነት እራሱ የብዙሀንን ሰላም ለመጠበቅ ሲባል ካለቦታውና ካለወቅቱ አይገለፅም፡፡
ሼር🙏
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
💖 @ahlusunawelgema 🌷
💖 @ahlusunawelgema 🌷
ما الفضلُ إِلا لأهلِ العلمِ إِنهمُ
على الهُدى لمن استهدى أدلاءُ
وقيمةُ المرءِ ما قد كان يحسِنُهُ
والجـــاهِلونَ لأهل العلمِ أعداءُ
فقمْ بعلمٍ ولا تطلبْ به بدلاً
فالناسُ مَوْتى وأهلُ العلمِ أحياءُ

https://t.me/ahlusunawelgema
አንድነት
እሸቱ ሲበላ… በተለይ አፍጥር ላይ 😋

እንደ እሸት ያማረ የማይከስም ሀያት አላህ ይስጠን

https://t.me/ahlusunawelgema
የዒልሙ ንጉስ ስለሆኑት ሰይዲ ሸህ ቃሲም ሸህ ታጁዲን ማንም እንዲነግረኝ አልፈልግም። ተገናኝተን ብዙ አውግተናል።

የዛኔ የተገናኘን ለታ ካወራንባቸው ጉዳዮች አንዱ የአቂዳ እና የመንጢቁ ፈን ነበር። በአቂዳው ከጀውሀራ አንስተን በሸርሀሑል ዓቃኢድ አድርገን እስከ መዋቂፍ እና መቃሲድ ሸርሆች ዳስሰናል።

በመንጢቁ ደግሞ ከኢሳغوጂ ፣ ሱለሙል ሙረውነቅ አንስተን በሸርሆቻቸው በኩል ጠይባን አስታከን ሸምስያን የቁጥቡዲን ራዚ ሸርህ ተደግፈን በሰይድ ጀርጃኒ እና በሰያለኩቲ በደሱቂ ሐሺያ ዞረን የሜራክል ቡኻሪን የኾነጂን ለመዳሰስ ሞክረናል።

ለካ ዒልም የሚባለው ነገር ከዋኙበት ሰዎች ጋር ስትሆን ነው የምታውቀው። ወይኔ እውቀት ትጠላለህ!

በነገራቹ ላይ የአቂዳ እና የመንጢቅ ዒልም ሲነሳ ሁለት በአንድ ዘመን የነበሩ ታላላቅ ዓሊሞችን ማንሳት የማይቀር ነው። የፈለገ ጀማ ይሁን የሁለቱን ኪታብ ካልከፈተ ወላሂ በአቂዳም በመንጢቁም የሚያቀው ጉዳይ የለም።

ሰዕደዲን አል_ታፍታዛኒ ነሰፊያን ሸርህ አድርገው ከኋላ የመጡትን ሁላ አጡዘዋል። ስሙ ሸርሀል አቃኢድ ተብሎ እንደመትን ነው የሚቀራው። በዚህ ላይ የተፃፉ ሀሺያዎችን በአጠቃላይ የነ ሰይዲ ኸያሊ፣ ረመዳን፣ ከስተሊይ፣ ባጁሪይ ለሌሎችም እንደ ጉድ ነው የዋኙበት።
በመንጢቁ የሸምስያ አስደናቂው ሸርህ የቁጥቡዲን ራዚን ኪታብ ሸሪፍ ሰይድ አል_ጀርጃኒይ መተው ሀሺያ አድርገው ባይፈቱት ኖሮ ቁጥቡዲንን መረዳት ያዳግት ነበር።

ሰይዲ ሸይህ ቃሲም ጋር ኪታቦቹን እያወሳን በውስጣቸው የተጠቀሱ ወሳኝ ነጥቦችን ለማየት ችለናል። አላህ ከእሳቸው ለመቀመጡ ይወፍቅህ እንጂ ጊዜው አያሳስብህ አላህ በበረካ ነው የሚሞላልህ። ቀላል ነው ያላመነ በንፁህ ልብ ይጠጋቸው አኼራን ከፈለገ በፍፁም ከሳቸው መራቅን አይመኝም።
ሀያተን ጠይባ🙏
https://t.me/ahlusunawelgema
አሏህን የማየው ብሆን እንጂ>>ያሉበት ተሰውፋዊ ቅኔ ሙሐመዲይ ምሉዕ ስብዕናዎች እንጂ አልተቃኙትም.......እዚህ መንደር ለመድረስ ነው የሃቂቃ ሱፊዎች ዙህድ የተጠነሰሰ!

የዙህድ ዛፍ መካን እንደሆነች አትዘልቅም...የሶብር ውሃ ጠጥታ በኢኽላስ ፍሬዎች የደመቀች ዕለት ጣፋጯ እንደ ጡባ በየአይነታው ይቆረጠማል።

የፋጤ አባት የዙህድን ፈዋኪህ ሲያቀምሱን <<አንድ ሠው የዱንያን ቸልተኝነት እና ዝምታን ተሰጥቶ ካየከው ተጎዳኘው....ከእርሱ ልብ ላይ የጥበብ ምንጭ ትፈልቃለችና>> ብለውናል!.....የሙሪድ እና ሙርሺድን መግነጢሳዊ ፍልልጎሽ ሲጠቁሙ!

በየትኛው የዙህድ ማዕዘን ሥር እንዳለን ነፍሳችንን እንጠይቅ? ሙእሚን ተጓዥ ነው።መራመድ ባይችል እንኳ ይንፏቀቃል!

ከዐሪፎቹ ማዕድ ላይ እንደተነሳው ዙህድ በተሰበከበት የጌታዬ ቃል ቀለሜን ገታሁ!

لِّكَيْلَا تَأْسَوْا عَلَىٰ مَا فَاتَكُمْ وَلَا تَفْرَحُوا بِمَا آتَاكُمْ ۗ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ

(ይህ ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑ አላህም በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው፡፡ አላህም ኩራተኛን ጉረኛን ሁሉ አይወድም፡፡(አል ሐዲድ 23)

ይህ የአውሊያኦች ሲፋ ነው - እጃቸው ላይ ባለው ሲተማመኑ ፡ባመለጣቸውም ላይ ሲቆዝሙ አልታዩም!

💚💜ሶላት እና ሰላም በአህመድ በኑር አበባው በቤተሰቦቹም ላይ ይስፈን ! አሚን
ወንድም አይመን ሐፊዘሁላህ

https://t.me/ahlusunawelgema
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለሰላም ለውይይት ሁሌም ዝግጁ ነን
ግን ዲናችን አሳልፈን አንሰጥም።

#ክቡር_ዶክተር_ተቀዳሚ_ሐጅ_ዑመር_ኢድሪስ 🙏
ــ {ألا بذكر الله تطمئن القلوب}
ـ سبحان الله🍁
ـ ‏الحمدلله🌿
ـ ‏لا اله الا الله🌾
‏ـ الله أكبر🍂
🖊አስቸኳይ ማሳሰቢያ

የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማሕበር
በነገው ዕለት ሐምሌ 11 በሸራተን አዲስ ሊደረግ የታሰበውን ስብሰባ የነባሩ ሙስሊም መሻይኾች ዛሬ ባወጡት መግለጫ በስብሰባው እንደማይገኙ መግለፃቸው ይታወቃል። ሆኖም ግን አንዳንድ የመንግስት አካላት የሱፍያ ተወካዮች ጋር እየደወሉ በማስፈራራት በግድ በስብሰባው መሳተፍ አለባቹህ የሚል ጫና ለመፍጠር እየሞከሩ በመሆኑ ህዝባችን መሻይኾቹ ሳይደናገጡ በአቋማቸው እንዲፀኑ እና ወደ ስብሰባው እንዳይገቡ እያበረታታን የዛሬው መግለጫ መልእክት ያልደረሳቸው ተሳታፊዎች ካሉም መረጃውን በማድረስ እንተባበር። በተጨማሪም ይህን ሁሉ አልፎ በስብሰባው የሚገኝ የነባሩ ሙስሊም የሱፍያው ተወካይ ነኝ የሚል ካለ ግለሰቡ እራሱን እንጂ ሌላ ማንንም የማይወክል መሆኑንን ህዝብና መንግስት ማወቅ አለባቸው።

ይህን መልእክት ሼር እናድርገው!
ነገ ቢሰበሰቡም ባይሰበሰቡም ወሃ^ቢዮች ከስረዋል:: ብቻቸውን አለመሆናቸው ያሳዝናል እንጂ!

ዑለሞቻችን ቢገቡ ኖሮ ግን እንደ ቴኒስ ኳስ ያንቀረቅቧቸው ነበር:: ሚያዝያ 23/2011 ላይ የወ^ሃቢ ተንኮል አልገባቸው ኖሮ ሄዱ:: ከሸይኾቹ ጠንካራ አቋም አለው የሚሉትን ሸይኽ ሁሉ ስሙን ሰርዘው ለሸራተን አዳራሽ አስተናባሪ ሰጡት:: ሸይኾቹ በጥሪው መሠረት ሲሄዱ በር ላይ ታገቱ:: ሁከት ተፈጠረ:: ያኔ ዐብይ እየገባ ነበርና <<ግርግሩን ተውትና ሁሉም ይግባ >> ብሎ ግን እጅግ ክብር የሚነካ ቃል ጣል አደረገባቸው:: ዑለሞች ተከፉ:: የመንግሥት አልጋይቷም አልረጋ አለች::

አሁንም የሀምሌ 11ዱን ልክ እንደ ያኔው ድፍንፍን አድርገውት ቆዩ:: ያው በቅርቡ ከዐብይ ጋር ተሰብስበው ይዘውት የነበረውን የሰነድ አጀንዳ ገልብጠው ሌላ አጀንዳ ይዘው መጥተው ጭራሽ ማስፈራራት ሁላ ያዙ:: በተለይ አደን ፋራህ ድን ድንበር ሁላ አለፈ::

=========

አንዳንዴ ያደግክበት ለየት ያለ ባሕል ይኖርሃል:: ሌላ ቦታ ስትሄድ ግን የሌላውም ባሕል ማክበር ያስፈልጋል:: አደን ፋራህ ባደገበት አካባቢ መሪ ስትሆን የተመሪውን ታዛዥነት ለመለካት ፈስህን ደርርርር አድርገህ ትፈሳና

አያ ዱሴይ - ማነው የፈሳው? ብለህ ትጠይቃለህ
ተመሪው:- አኒ ጋ ዱሰይ (እኛ ነን የፈሳነው) ብሎ ኃላፊነት ይወስድልሃል:: ለሁሉ ነገርህ ኃላፊነት የሚወስድ ታዛዥ ማግኘት ጥሩ ባሕል ነው:: ደጋው ላይ ግን እንዲህ ያለ experiment አልተለመደም::
=======


በዚህ ላይ የወ^ሃቢ ሸፍጥ ተጨምሮበት የሚፈጠር ነገር በሽ ነው:: እና ዑለሞቻችንን ለምሳ ሲያስቧቸው ለቁርስ አደረሷቸው:: ከእንግዲህ ዑለሞቻችን ምንም ቢመጣባቸው ድል አድርገዋል:: ባይሆን መንግሥት የድሉ ተካፋይ ቢሆን ያዋጣዋል::
# ጋሽ አብራር
✍️አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ
የክረምት ኮርስ ምዝገባ ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን ተመዝግባቹህ ክፍያ ያልጨረሳቹህ እድሉ ሳያመልጦ ከወዲሁ ክፍያዎን ያጠናቅቅቁ።

🟢 ለመመዝገብ፦ @Darulhigratein
ዳሩልሒጅረተይን ምዝገባ ክፍል

@DaralHijrataynIslamicSchool