ناصر الدين(ናሲሩዲን)
477 subscribers
557 photos
87 videos
6 files
369 links
[[ وَجَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا ]]

{እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።}

ሼር add በማድረግ የበኩላችን እንወጣ


https://t.me/joinchat/jhrmqQH66YtiOGFk
Download Telegram
ሰይዲ ሙሀመድ ሙህዪዲን አብዱል ሀሚድ ረሒመሁላሁ ተዓላ🙏
በ1318 ሂጅራ በግብፅ ከፍሩል ሀማም በሚባል ቦታ ተወለዱ።
አባታቸው ዐ/ሀሚድ ኢብብራሂም በሚስር ቃዲ እንዲሁም በመጨረሻም ሙፍቲ ሆነው አገልግለዋል።

ሰይዲ ሙሀመድ ሙህዪዲን ዐብዱል ሀሚድ እቤታቸው የሙፍቲም ቤት አይደል ብዙ ዑለሞች ቤታቸው እየመጡ ከአባታቸው የተለያዩ ዒልች ላይ ሲያወሩ ይሰሙ ነበር።

በተለያዩ ዒልም ዘርፎ ላይ የተመሰከረላቸው ሙሀቂቅ ከሚባሉ አዝሀር ካፈራቻቸው ድንቅ ዑለሞች መካከል አንዱ ናቸው። በብዛት የሚነሱት በዒልመል መዋሪስ /ውርስ/ እንዲሁም በነህው እና በሰርፍ በሉገተል ዓረቢያ በአጠቃላይ።

ሱዳን ላይ መድረሳ ሲቋቋም በእሳቸው ታግዘው ነው። ፈራኢድ እና ሉغ ሲያስተምሩ ቆይተው ወደ አዝሀር ተመልሰው በአዝሀር ማስተማር ጀመሩ

ሰይዲ ሙሀመድ ሙህዪዲን በዙል ቃዕዳህ 25 በ1392 ሂጅራ ወደ ታላቁ ሀገር ተሸጋገሩ።
አላህ ቀብራቸው የጀነት ጨፌ ያድርግላቸው በዒልማቸው በበረካቸው የምንጠቀም ያድርገን🤲

https://t.me/ahlusunawelgema
ለምንድነው ግን ዘጠኙን የዙልሒጃ ቀናትን የማንፆመው???

💚የመጀመሪያው ቀን አላሁ ተዓላ ለነቢላሂ አደም ዐለይሂ ሰላም የማረበት ቀን ነው።
💚ሁለተኛው ቀን አላሁ ጀለ ወዓላ ለሰይድና ዩኑስ በአሳ ሆድ ውስጥ ሆነው ዱዓቸውን የተቀበለበት ቀን ነው።
💚ሶስተኛው ቀን አላሁ ሱብሓነ ወተዓላ ለነቢላሂ ዘከሪያ ዐለይሂ ሰላም ዱዓቸውን ሰምቶ ልጅ የረዘቃቸው ቀን ነው።

🖍የመጀመሪያ ሶስቱ ቀን ከልብህ ዱዓ የምታደርግበት ነው።

💚አራተኛው ቀን ነቢላሂ ዒሳ ዐለይሂ ሰላም የተወለዱበት ነው።
💚አምስተኛው ቀን ነቢላሂ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም የወለዱበት ቀን ነው።
💚ስድስተኛው ቀን ለነቢላሂ አዩብ አለይሂ ሰላም የኸይር በሮች በአጠቃላይ የከፈተበት ቀን ነው።
🖍እነዚህ ሶስት ቀናትም የዱዓ የሪዝቅ በር የሚከፈትበት ነውና አላህ ኒዕማችን ከነ ኒዕማው ይጠብቅልን ከመልካም ሲሳዮቹም ይለግሰን🤲
💚ሰባተኛው ቀን ጀሃነም የምትዘጋበት ቀን ነው። አስረኛው ቀን እስኪያልቅ አትከፈትም።
💚ስምንተኛው ቀን የተርውያ ቀን ነው።
💚ዘጠነኛው ቀን የዐረፋ ቀን ነው። ይን ቀን የፆመው ሰው ያለፈው አንድ አመት እና የሚመጣው አንድ አመት ወንጀሉ ይማርለታል። በዚሁ ቀን ነው
اليوم أكملت لكم دينكم …الخ
የሚለው አንቀፅ የወረደው።
💚አስረኛው ቀን የዒዱ ቀን የኡድህያ ቀን ነው። አንድ መቃረቢያ ያቀረበ ሰው ለሰራው ሃጥያት ሁሉ ማበሻ ይሆንለታል።
💚 ከዛ በኋላ ሶስት ተከታታይ ቀናት አያመ ተሽሪቅ ይባላሉ 11 ፣ 12 እና 13 የመብላት የመጠጣት የመደሰቻ ቀናቶች ናቸው።
🖍ማሳሰቢያ፦ ከአስረኛው ቀን ጀምሮ እስከ 13ተኛው ቀን ያሉ 4ቱም ቀናቶች መፆም አይቻልም ሀራም ነው።

ያ አላህ አረፋን የመቆም ተውፊቁ ስጠን ያ ረቢ

ሼር 🙏
https://t.me/ahlusunawelgema
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሽርክ ሽርክ ሽርክ🙆‍♂🙆‍♂🙆‍♂🙆‍♂🙆‍♂🙆‍♂
አረብኛ የምታወሪ ሁላ አለቀልሽ😂😂😂

እከሌ ሆይ አትበል።😂 አላህ ሆይ በል። አንዳንድ ሰው አባቱን እናቱን ሲጠራ ያ አቢ ያ ኡሚ ይላል ይሄ ስህተት ነው። ሽርክ ውስጥ ይገባል ይሄ ሽርክ ውስጥ ይገባል።።😂😂😂

ሰውዬ ገደለኝ እኮ በአረብኛ ሁሩፉ ኒዳ የሚባሉ ቃላቶች አሉ። ሁሩፉ ኒዳ ማለት ሰውን ለመጥራት ስትፈልግ የምታስገባቸው ማለት ነው።

ልብ በሉ እነዚህ ቃላቶች በጥሪ ሰዓት ካልተጠቀምክ ከጥሪነት መቶ በመቶ ወጥቶ ትርጉሙ ሌላ ነው።
በቁርአንም
(يا أيها الناس) ! እናንተ ሰዎች ሆይ
(يا أيها النبي) ! አንተ ነብይ ሆይ
እና አላህም አሻርኮዋል ሊሉን ነው
ሱብሓነ አላህ…


እንኑር እንጂ ብዙ ጉድ እናያለን። እነዚህ መህማንን እየሰማቹ ገደል የምትገቡ አሳዘናቹኝ።።።።።

https://t.me/ahlusunawelgema
ለሀጅ የተዘጋጁ ሰዎች ተቃውሞ አሰሙ ምን ማለት ነው አንተ አንቺ የዛኔ በአለመል አርዋህ ለበይክ ብለህ ብለሽ ከሆነ አትቀርም ትሄዳለህ። አይደለም ዶላር ፕሌኑም ቢጠፋ ትሄዳለህ።

የዛኔ ያልመለስክ ከሆነ ግን አይደለም ዶላሩ ጠፍቶ እዛው መካም ብትሆን አታደርግም።

ወንድሜ ማላገጡ ተውና በዱዓ ወጥር አልቅስ አይኖችህ እንባ ያፍስሱ😢። ሰውን ተወውና ወደ አላህ ዙር፡ በየትኛው ወንጀሌ ይሆን ብለህ እራስህን መርምር። ሁሉሙ ነገር ተቃውሞ ሆነና ቀዳ እና ቀደር እየረሳን ነው። የሸሪዓ አካሄዱ ዘንግተን በፖለቲከኞች መስመር እየሄድን ነው።

{{ وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ}} (27)
[[(አልነውም) በሰዎችም ውስጥ በሀጅ ትዕዛዝ ጥራ። እግረኞች ከየ እሩቅ መንገድ የሚመጡ ከሲታ ግመሎች ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሀል።]]

አላህ ለነቢላሂ ኢብራሂም ዐለይሂ ሰለሰም ወደዚህ እንድትገነባው ወደ አዘዝንህ ቢት ሰዎች ሀጅ እንዲያደርጉ ተጣራ አላቸው። እሳቸውም ጌታዬ ሆይ ለሰዎች እንዴት ነው የማደርሰው ድምፄ ደካማ የማይደርሳቸው ሆኖ? አንተ ተጣታ ማድረሱ በኛ ነው ተባሉ።

በመቃማቸው ላይ ቆሙና እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታቹ ቤት አድርጎላቹኋልና ሀጅጁ አሉ። ተራራዎች ድምፁ በምድር አቅጣጫዎች ይተላለፍ ዘንድ ዝቅ አሉ ይባላል። በማህፀንም በጀርባም /አስላብ/ ውስጥ ላለው በሙሉ አሰማ።

ያንን ድምፅ የሰሙ ድንጋዮች አፈፀዋቶች ቤቶች በሙሉ ፤ እንዲሁም አላህ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ ሀጅ ያደርጉ ዘንድ የፃፈላቸው ሰዎችን እና ጋኔኖች ለበይከ አላሁመ ለበይከ በማለት መልስ ሰጥተዋል።

🖍አሁንም ደግሜ የማሳስበው እንዲህ ያሉ ነገሮች ሲከሰቱ ወደ አላህ ዞረን እናልቅስ። በሰራናቸው ወንጀሎች ከሀጅ ታገድን መንግስት ሳይሆን አላህ ነው። ወንድሞቼ እህቶቼ ይሄ ከአላህ የተላከልን ወደኔ አልቅሱ ወንጀላቹ በዝቶዋል የሚል ሚሴጅ ነው።።።።።።።።
አላህ መሀርታውን ይለግሰን

ሼር🙏
@ahlusunawelgema 🌱🌱

@ahlusunawelgema 🌱🌱
🖍በአይስላንድ በበጋ ወራት ቀኑ 22 ሰዓት ነው። ለሊቱ 2 ሰዓት ብቻ ነው ማለት ነው። ፀሐይ ከገባች ከ2 ሰዓታት በኋላ ትወጣለች። በፆምም በዓለማችን ረጅሙ ፆም የሚፆሙት እነሱ ናቸው።

እንደሚነገረው ከሆነ ከ21 ሰዓታት በላይ መፆሙ ይከብዳቸዋል። በጣም ከመጥናቱ የተነሳ አንዳንድ ሙስሊሞች ለአፍጥር 10 ደቂቃዎች ሲቀሩት ማለትም 21፡ 50 ላይ ያፈጥራሉ። በ2015 ወደ መቶ የሚጠጉ ሙስሊሞች አስር ደቂቃ ሲቀራቸው ፆማቸው ማፍረሳቸው ተወስቶዋል።

በክረምቱ ደግሞ ተቃራኒው ነው። ለሊቱ በብዛት 20 ሰዓታት ይሆንና ቀኑ 4 ሰዓት ብቻ ይሆናል።

ባነበበው ሰው ቁጥር አጅር ይፃፍልናል እና የገራልን የተስቢህ አይነት እንፃፍ🙏

ሰቡሀነ አላህ ዐደደ ኸልቂሂ ወሪዳ ነፍሲሂ ወዚነተ ዐርሺሂ ወሚዳደ ከሊማቲሂ🌷🌷

ሼር🙏
https://t.me/ahlusunawelgema
ኡዱሒያ ሲታረድ የሚደረግ ዱዓ
باسم الله والله أكبر اللهم هذا منك ولك، اللهم هذا عني وعن أهل بيتي
*ቢስሚላሂ አላሁ አክበር አላሁመ ሀዛ ሚንከ ወለከ አላሁመ ሀዛ ዐኒ ወዐን አህሊ በይቲ* ይህን ዱዓ ከአሁኑ ሀፍዙት…


ሰይደል ከውን ነብያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኡዱሂያ ሲያርዱ ያሉት
"باسم الله والله أكبر هذا عني وعمن لم يضح من أمتي" الترمذي
(በአላህ ስም አላህ የላቀ ነው። ይሄ ለኔ እንዲሁም ከኡመቶቼ ኡዱህያ ላላረዱት ነው።)

ሌለት እና ቀን ሳይረሱን የሁል ጊዜ ጭንቀታቸው እኛን በሆኑት ነብይ ሰላዋት ማውረድህ አትርሳ

اللهم صل على على سيدنا محمد عدد من يصلي عليه وصل على سيدنا محمد عدد من لم يصلي عليه

https://t.me/ahlusunawelgema
መከመሉ ነበር የኔማ ሙራዱ…
ያዛሎ ያአባዶ ኑሩል መጀረዱ

ማዲህ መህፉዝ🌷 በጉጉት እንጠብቃለን ክበርልን
ህልሟንም ቤተሰብዋንም በአንድ ላይ…💚

https://t.me/ahlusunawelgema
💧💧የኢማን ትርጉም ምንድን ነው?💧💧

የአህሉሱና ኡለሞች ኢማንን ቋንቋዊ ትርጓሜውን ጠብቀው ኢማን
#ተስዲቅ ብቻ ነው የሚል ገለጻ አስፍረዋል።

⚡️ሌሎች ደግሞ ኢማንን ሰፋ አድርገው ኢማን ማለት በንግግር በተግባር የሚገለጽ እምነት ነው ያሉ ሲሆን ኸዋሪጆች ደግሞ ኢማን ጀዋሪህ(አካላት ላይ ያለ ነው ስለሚሉ) ሶላትን በስንፍና የተወንና ወንጀል የሚሰራ ሁሉ በአካሉ ሲሰራው ከፍሯል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል ይህም የአህሉሱና የወጣ ተቀባይነት የሌለው ሐሳብ ነው!!

💠ኢማን ማለት ተስዲቅ ነው።ይህም ንግግር ከአራቱ መዝሐብ አኢማዎች አንጋፋው ከአቡሐኒፋና ከሳቸው ተከታዮች የማቱሪዲያዎች እንዲሁም የአንጋፋ የአሻዒራ ሙተከሊሞች የተወሰደ የአህሉሱና ንግግር ሲሆን አንዳንዶች ይሄን ንግግር የሙርጂአ አቂዳ ነው በማለት ሲያጣጥሉና ሌሎች ደግሞ ይሄ ንግግር የከፊል አሻዒራዎች ንግግር ነው በማለት ንግግሩ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነና እና ከቁርዐን ከሐዲስና እንዲሁም ከኢጅማእ የተጣረሰ ነው ሲሉ ኢጅማኡን ያልተረዱ ሰዎች በማክፈርም እንዲሁም ማሊኪያዎችም ላይ በመቅጠፍ ጭምር የፊትና ንግግር ጀምረዋል!!

💠ወደ ነጥቡ ስንመለስ
አንድ ሰው የእስልምናም እምነት ከያዘ በአንደበቱ ባይናገርም ሙስሊም ነው። በአንደበት መናገር አህካም ለማስፈር እንጂ ካልተናገረ ይከፍራል ማለት እንዳልሆነ እና በዚህ ነጥብ ኡለማዎች ልዩነት እንዳላቸው መንገዘብ ያስፈልጋል!!

⚠️ጀውሐረቱ ተውሂድ ላይ እንደተገለጸው
وفسر الايمان بالتصديق والنطق فيه الخلف بالتحقيق
#ኢማን_በተስዲቅ_ተተረጉሟል
#ይህም_በተህቂቅ_ኺላፍ_መኖሩን_ይጠቁማል!!

♻️ለዚህም ሁሉንም ተቀባይነት ያላቸውን የጀውሓራ ሽርህ ማየት በቂ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ኡለሞች እንደ ኢማሙል ገዛሊ ኢማሙል ሐረመይን የመሳሰሉ ሙጀዲድ ኡለማዎች የሰለፍን አቂዳ ነቅል ያደረጉት ኢማሙ ጦሃዊይ በአቂዳ ኪታባቸው ላይ በትክክል ያስገነዘቡት ጉዳይ ነው!!

🔰ሆኖም ግን መጤ አሳብ ለመዝራት የሚፈልጉ የጅምላ አክፋሪዎች ጀውሐረተ ተውሂድንና አቂደቱ ጦሐውያን ሲሸርሁ ይሄን ንግግር ከቁርዐን ከሐዲስና ከኢጅማእ የወጣ በማለት ጀውሐረተ ተውሂድን የሽረሁትን ዑለማዎች ሁሉ ኺታማቸው እንዳይበላሽ ስጋታቸውን ሁሉ በመግለጽ የኡለማዎች ላይ ጭምር አራጂ የሆነ ትችትን በመሰንዘር ከብዙሐኑ አህሉሱና ውጭ የሆነ አዳዲስ እይታዎች እያስገቡም ጭምር መሆኑን ልንገነዘብና ልንጠነቀቅ ጭምር ይገባናል!!

💠 ኡለማዎች ተስዲቅን የተቀበሉት ብዙ ማስረጃዎች የጠቀሱ ሲሆን ለዚህም ሐዲሱ ጁብሪል ላይ ጂብሪል ዐለይሒ ሰላም ረሱልን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን ሲጠይቃቸው ተስዲቅ ብቻ መጠቀሱን ለማስረጃነት ያቀርባሉ ከዚህም በተጨማሪ ረሱል ዐለይሒ ሶላቱ ወሰላም በሐዲሳቸው ላይ ቅንጣት ታክል ኢማን ያለው ሰው ከጀሐነም ይወጣል (ዘላለም አይቀጣም) ማለታቸውን እንደ ማስረጃነት ይጠቅሳሉ!!

🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁

❗️ታዲያ ኢማሙ ነወዊ በልቡ አምኖ ያልተናገረ በኢጅማእ ካፊር ነው ዘላለምም እሳት ይገባል ያሉት ንግግር እንዴት ይታያል

ይህ የኢማሙ ነወዊይ ንግግር ለአንዳንዶች እንደመረጃ የሚያዩት ሲሆን
#ሳይረዱት ግን ሰውን #ለማደናበር የሚሞክሩበት ስለሆነ በግልጽ መተንተን ያስፈልጋል!!

ኢማሙ ነወዊይ ይህንን የገለጹት ቃዲ ኢያድን ተከትለው ሲሆን ሁለቱም የተለያየ ገለጻ አስቀምጠዋል!!
አሺፋ ኪታባቸው ላይ ቃዲ ኢያድ እንዲህ ብለዋል፦
((فهذا اختلف فيه ايضا…والشهادة من جملة الاعمال فهو عاص برتكها غير مخلد))
🔸በማለት
#ኺላፍ መኖሩን ሲገልጹ ኢማሙ ነወዊ በበኩላቸው አልሚንሐጂ በሚባለው የሶሂህ ሐዲስ ሙስሊም ሽርሐቸው ላይ
((اذا اعتقد دين الاسلام اعتقادا جازما لا تردد فيه كفاه ذلك وهو مؤمن))
🔸በኢእቲቃዱ ብቻ
#ሙእሚን እንደሚሆንና ያበቂ ሆኖ #ሙእሚን_ተብሎ_እንደሚገለጽ_አስረድተዋል!!

አሁንም በሽርህ ሙስሊማቸው ላይ
((فان المراد التصديق الجازم قد حصل لان النبي صلى الله عليه وسلم اكتفى بالتصديق) )
🔸ሲሉ አስረድተዋል ይህም ነብያችን በተስዲቅ ብቻ መብቃቃታቸውን ሲያስረዱ ኢጅማኡም ያለው አንድ ሰው ኑጥቅ እንዲያደርግ ሲጠየቅ
#እምቢ ካለ መሆኑን ኡለማዎች ገልጸዋል!!
الفقيه ملا علي القاري فى مرقاة المفاتح
وفى هذا دلالة ظاهرة لمذهب أهل الحق ان اعتقاد التوحيد لا تنفع دون النطق عند القدرة أو عند الطلب ولا النطق دون الاعتقاد
#بالاجماع بل لا بد منهما عايته ان #النطق فيه #خلاف أنه شطر أو شرط وقد #يسقط #بعذر))

🔸ሙላ ዐልዩኒልቃሪእ ሚርቃቱል መፋቲሕ ኪታባቸው ላይ ኺላፍ መኖሩን አስረድተው ኑጥቅ የሚወድቅበትም ሂደት አብራርተዋል!!


💦قال التفتازاني فى شرح العقائد النسفية
((وذهب جمهور المحقيقين إلى انه التصديق بالقلب وانما الاقرار شرط لاجراء الاحكام فى الدنيا))
🔸አል ኢማም ተፍታዛኒ የብዙሐኑ ሙሐቂቆች ንግግር (ኢማን)በልብ ተስዲቅ ማድረግ መሆኑን ገልጸው ኢቅራሩ በዱንያ ሑክም ለመስጠት መሆኑን አስደርተዋል።

♦️ኢማሙ ተፍታዛኒ ከጠቀሳቸው ብዙሐን ሙሐቂቆች በላይ ሙሐቂቅ ነን የሚሉን ሰዎች መኖራቸው ጉዳዩን አስቂ ያደርገዋል

#ይቀጥላል
https://t.me/sufiyahlesuna
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ

ውድ የዳሩልሂጅራተይን ቻናል ቤተሰቦች ከዚህ ቀደም በጀመርነው መሠረት መማማራችን የምንቀጥል ይሆናል።

የደርስ ቀናቶች እቅድ

1️⃣ ሰኞ ፦ ኡሱሉል ፊቂህ ወረቃት
[ በሸይኽ ኻሊድ ሸይኽ አሊ ]

2️⃣ማክሰኞ ፦ አቢ-ሹጀዐ እና ሙተሚ
[ በሸይኽ ሪድዋን ዑመር ]

3️⃣ ረቡዕ ፦ ሙቀዲመቱ አስ - ሰኑስያ
[ በሸይኽ ካሚል ]

4️⃣ ሐሙስ፦ ተንቢሁል አናም ሰለዋት
[ በወንድም ኢብኑ ሰልማን ]

5️⃣ ጁሙዐ ፦ ነህው ሙተሚማ
[ በሸይኽ ሪድዋን ]

6️⃣ ቅዳሜ ፦ ፊቂህ ዑምደቱ ሳሊክ
[ በሸይኽ ፈኽሩዲን ]

7️⃣ እሁድ ፦ አቂዳ ጠሀዊያ
[ በሸይኽ ፈኽሩዲን ]

👌በቅርቡ ሌሎች ተጨማሪ ኪታቦች በተጨማሪ ኡስታዞች እንደምንጀምር ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

💜አስተያየት ተቀባይ
@Darulhigratein

ሼር እናድርገው ባረከላሁ ፊኩም 🙏 @DaralHijrataynIslamicSchool
@DaralHijrataynIslamicSchool
እየተሳበ እንዲጓዝ የተፈጠረ መብረር አይችልም !

ውሸት የተለያየ ገፅታ ቢላበስም ጠፊ ነው ! ሊጠፋም ነው የተፈጠረው ..

የሀቅ ባለቤት ደሞ እራሱን አል'ሐቅ ብሎ የሰየመው አሏህ ነው ፣ እሱ ጠባቂው የሆነው ደሞ ማንም አያሸንፈውም !

የሐቅ ባለቤት አሸናፊነት ከገንዘብ ከስልጣንም ሆነ ከምክንያቶች ጋር የተያያዘ አይደለም !

አሸናፊነቱ የሁሉም የበላይ ከሆነው ከአሏህ ብቻ የሚመጣ ስለሆነ ነው

አሏህ የሀቅ አሸናፊነት ሰበብ ያድርገን
ኸይር ኸይሩን ያሰማን
ከሸረኛና ከሴረኞች ይጠብቀን

https://t.me/mededulhabib
ተሙጥጥ በርቸ ሰላም ዀት ሶስት ግዝየ ድረድግ
አላሁ ተዓላ 99 ስሞች አሉት። እነዚህን የሀፈዛቸው ሰው ጀነት ገባ አሉ ነብዩ (ሰዐወ)

በቀን አምስት ስሞች እንኳን ብትሀፍዝ በ20 ቀን የጀነት ትኬት ትቆርጠሰለህ።

ወንድሞቼ አንዘናጋ የስት ሙፍሲዶች ስም ሀፍዘናል። የአንተ የጌታህ ካነበርክበት በዚህ በአማረ አፈጣጠር ያስገኘህ፣ ሳትጠይቀው እስልምናን የሰጠህ ጌታህ ስም አላቀውም ብት ሼም አይደለም

ለዛሬ አምስቱን በጋራ አብረን እንሀፍዝ
۞ الله ۞ الرحمن ۞ الرحيم ۞ الملك ۞ القدوس ۞ السلام ۞
አላህ * አርረሕማን * አርረሒም * አልመሊኩ * አልቁዱሱ * አስሰላሙ*

ይቀጥላል…
@ahlusunawelgema
اللهم اجعل أمي

سيدة من سيدات أهل الجنة واجعل الحوض موردا لها والرسول شافعا لها والولدان المخلدون خدما لها والسندوس لباسا لها والقصور سكنا لها 🤲🤲🤲
አሚን በሉማ 🙏
አንድ ባላገር ለሰይድና ዓልይ (ረ) የነብዩን ሰዐወ አኽላቃቸውን ቁጠሩልን አላቸው። እሳቸውም መቁጠር ታውቃለህን? አሉት። እሱም አዎ አላቸው። ሰይድና ዓሊይም የዱንያ መታዕን /መጠቃቀሚያዋን/ ቁጠርልኝ አሉት። እሱም ኧረ አይቆጠርም አላቸው።

ሰይድና ዐልይም አንተ የዱንያን መታዕ መቁጠር አቃተህ። ነገር ግን አላህ በጣም ቲንሽ መሆንዋ መስክሮዋል።
{قل متاع الدنيا قليل}
እንዴት አድርጌ ነው የነብዩን ሰዐወ ባህሪ የምገልፅልህ? አላህ እኮ የነብዩን ሰዐወ አኽላቅ ትልቅ ነው ብሎ መስክሮዋል።
{{وإنك لعلى خلق عظيم}}
አቦ ሰላዋት አብዙባቸው
አላሁመ ሰሊ ዐላ ሰይድና ሙሀመድ ወዐላ አሊሂ ወሰህቢሂ ወሰለም

https://t.me/ahlusunawelgema
አንዳንድ የቁርአን ቃላቶች እዲሁም ስንቴ እንደተጠቀሱ።

ዱንያ 115 አኼራ 115
መላኢካ 88 ሸይጣን 88
ሙሀመድ 4 ሸሪዓህ 4
ሰዎች 50 ነብያቶች 50
ኢብሊስ 11 ከሱ መጠበቅ 11
ወንድ 24 ሴት 24
ህይወት 145 ሞት 145
መልካም ስራ 167 መጥፎ ስራ 167
ግልፅ ማድረግ 16 መደበቅ 16
ሙሲባ 75 ሹክር 75
ቅናቻ 79 ራህማ 79
እነዚህ ቃላት ካያቹዋቸው ተቃራኔዎች ናቸው። በሰው ችሎታ ሊደረግ የማይችል ኢላህይ ስራ።

ችግር العسر በቁርአን 12 ሲጠቀስ መግራራት اليسر ደግሞ 36 ጊዜ በሶስት እጥፍ ተጠቅሶዋል። አንድ ችግር ሁለት መግራት ሊያሸንፍ አይችልም አይደለም ሶስት።

ከሚያጅቡ ነገሮች ሰላት الصلاة የሚለው ቃል በቁርአን 5 ቦታ ነው የተጠቀሰው። እንደዚሁም ሰላቶች الصلاوات የሚለውም 5 ጌዜ ነው። በቀን ግዴታ የሆነብን ሰላትም 5 ነው።
ቀን يوم የሚለው ቃል በቁርአን 365 ጊዜ ተጠቅሶዋል። በአመት ያሉ ቀናቶች ብትም 365።

መሬት أرض የሚለው ቃል በቁርአን 13 ጊዜ ተጠቅሶዋል። በተቃራኒው ባህር ደግሞ 32 ጊዜ ተጠቅሶዋል። ይህን በፐርሰንት ስንሰራው መሬት 29% ባህር ደግሞ 71% ነው። ይህ ወደ ነባራዊ ሁኔታ ስናመጣው መሬት ከባህር አንፃር የሚሸፍነው እና ባህርም ከመሬት አንፃር ያለውን ይዘት ነው።

https://t.me/ahlusunawelgema
ኡዱሒያ የምታርዱ ሰዎች እርዱን እስከትፈፅሙ ድረስ ፀጉራቹንም ሆነ ጥፍራቹ ከመቆረጥ ተቆጠቡ
عن أم سلمة رضي الله تعالى عنها أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: [إذا رأيتم الهلال] وفي لفظ [إذا دخل العشر وأراد أحدكن أن يضحي فليمسك عن شعره وأظفاره] رواه مسلم وأحمد

ከኡሙ ሰለማ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልክተኛ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል። {የዙልሒጃ ወር ጨረቃ ካያችሁ} በሌላ ቃል ደግሞ {የዙልሒጃ አስሩ ቀናቶች ከገቡ ከእናንተ መካከል አንዱ ኡዱሒያ ማድረግን ካቀደ ፀጉሩንና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ}። ሙስሊም እና ኢማም አህመድ ዘግበውታል

وفي رواية [فلا يأخذ من شعره وأظفاره شياء حتى يضحي ]
በሌላ ዘገባም፤ {ኡዱሒያ እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩና ከጥፍሩ ምንንም አይቁረጥ} ብለዋል።

መልካም የዒባዳ ቀናቶች ይሁንልን። ከመልካም ሰሪዎችም አላህ ያድርገን።🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

https://t.me/ahlusunawelgema
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ውሀብያ የሚለው ስያሜ

ያወጣው ማን ነው


https://t.me/ahlusunawelgema