AL-faruq-tube
6.17K subscribers
255 photos
88 videos
3 files
419 links
Download Telegram
(ኸሚስ ሙባረክ)😊

የለንበትም

እወቅ ብለናል ሳለህ ሳትሞት
የከጀልክ እንደሁ መራቅ ከሳት

ምህይምና ከሆን ጉዝጓዙ
ወደድክም ጠላህ አይቀርልህም
ውግዙን ፈቅዶ ፍቁድ ማውገዙ

መገን ምክራችን ሰምተህ ከመጣህ
ጥርት ያለውን እውቀት ከጠጣህ
ከስሁት መራቅ ይሆናል እጣህ

ግን ገላምጠኸን ግራ ስትኳትም
አጀልህ ደርሶ ኑሮህ ሲያከትም
ዐዛብ ቢያጣድፍህ ተገኝተህ የትም
የለንበትም!!!

ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ ድንቅ መንዙማ በሶላሁዲን ሁሴን
ለመጀመርያ ጊዜ በመዲነቱል ሙነወራህ የተሰራ

ልበሎ ዘላለም :- https://youtu.be/DeHUId2EZ5o
አበባማዋ ሌሊት»

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

«አበባማ» የሚል የማዕረግ ቅፅልንና ክቡር ቦታን ያገኘችው ሌሊት፤ የጁሙዐ ሌሊት (ሐሙስ ማታ) ስትሆን
ማለፊያ የሆነ ቅፅልን አውጪው ደግሞ ከአበባም በላይ የፈኩት የኛ ነቢይ ናቸው።

عن عمر بن الخطاب رضي الله عنه قال: قال رسول الله ﷺ أكثروا الصلاة علي في الليلة الزهراء واليوم الأغر فإن صلاتكم تعرض علي فأدعوا لكم وأستغفر

ዑመር ቢን አል ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዓንሁ) እንዳስተላለፉት የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል «በአበባማዋ ሌሊት ( ጁሙዐ ሌሊት) እና በብርሃናማዋ ቀን (በእለተ ጁሙዐ) በኔ ላይ ሶለዋት (ማውረድን) አብዙ፤ ያወረዳችሁት ሶለዋት ለኔ ይቀረባልና፤ እኔም ለእናንተ ዱአ(ጸሎትን) አደርጋለሁ ምህረትንም እለምንላችኋለሁ።»

የሐሙስ ማታው ክፍል በማዕረገ―ቅፅል የተጎናዘለበት ሚስጢር ከአዘቦት ሌሊቶች በተለይቶ «በነብያችን ﷺ ላይ አብዝተን ሶለዋት ማውረድን በመታዘዛችኑ ነው»

እውነትን ባነገሰው የረሱለሏህ ﷺ አንደበት «ጁሙዐ» ቀኑም ሆነ ማታው ከተቀሩት ቀናቶች እና ሌሊቶች በተለይቶ ልዩ ክብር ተሰጥቶታል።

ይህ ማለት «የጁምዐ ቀን» ከሌሎች ቀናቶች፣ ማታው ክፍልም ከሌሎች ማታዎች ይበልጣል ማለት ነው።
በኢስላም ቀንና ሌሊት አሰያየም ረገድ ከኛ ሐበሻዎች በተለይቶ ሌሊቱ ቀኑን ቀድሞት ይሰየማል።

በዚህ መሰረት የጁሙዐ ማታው ክፍል እኛ «ሐሙስ ማታ» ስንል የሰየምነው ነው። እና «የጁሙዐ ቀንና ሌሊት» ከሌሎች ቀናቶች የተለዩ መሆናቸውንና በዚህ የተከበረ ቀንና ሌሊትም ከሌሎች ቀናቶች በተለየ መልኩ በሳቸው ላይ ሶለዋት ማብዛት እንዳለብን ያስተማሩን የአሏህ ነቢይ ﷺ ናቸው።

የአዋቂዎች ሁሉ አዋቂ፣ የብልሆች ሁሉ ብልህ፣ የአዛኞች ሁሉ ቁንጮ፣ የርኅራኄ ጥግ የሆኑት የኛ ነቢይ ﷺ
ሐሙስ ማታን በሶለዋት እንድናስውባት ሲያዙን ለኛ ካላቸው ወደር የለሽ እዝነት ነው።

አንድን ስራ ብቻ የሙጥኝ ብለን በመያዝ (በሰይዳችን ላይ ሶለዋት ማውረድን በማብዛት) ነገር ግን ያ ስራችን

ወንጀልን የሚያስምር፣ ደረጃንና ምንዳን የሚያስጨምር፣ ሪዝቅን (ሲሳይን) የሚያሰፋ፣ ድንገተኛና መጥፎ ችግሮችን የሚያጠፋ፣ በአሏህ የሚያስወድድ፣ የነቢዩን ﷺ ፍቅር የሚጨምር ፣ እሳቸውን በህልም እንድናይ የሚረዳ፣ እሳቸው ዘንድ በመልካም የሚያስወሳን እና እልቆ መሳፍርት የሌላቸው ማለፊያ ሰጤዎችን የሚያስቸረን መሆኑ ነው።

ነብያችን ﷺ እንዳሉት

«አሏህ የፍጥረታትን የስም መዝገብ ዶሴ የሰጠው መላኢካ አለ፤ እኔ በሞትኩ ጊዜ አንድ ሰው በኔ ላይ ሶለዋት ባወረደ ጊዜ መላኢካው ከቀብሬ በመሰየም ሙሐመድ ሆይ! እገሌ የእገሌ ልጅ ባንቱ ላይ ሶለዋትን አውርዷል ይለኛል፤ አሏህም ለዛ ሰው በየ አንዷ (ሶለዋት) ዐስር ምንዳን ሰጥቶ፣ ዐስር ወንጀሉን አፅድቶ፣ ዐስር ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።»

((ሓሪስ ኢብኑ አቢ ኡሳማህ፣ በዛር፣ ጦበራኒይና ሌሎቹም ዘግበውታል))

የተከበረው መላኢካ ስሙን ነቢዩ ዘንድ እንዲያደርስለትና አንዷ ስራው በአሏህ ዘንድ ከአስር እጥፍ ጀምሮ እንዲባዛለት የሚሻ
በትልቁ ሰዋችን፣ ነቢያችን፣ በሰይዳችን፣ በአይነታችን፣ በአዛኛችን፣ በአማላጃችን ሙሐመድ ﷺ ላይ ኒያውን ለጀሊሉ ያጠራ ሆኖ ሶለዋት ማውረድን ያብዛ።

የሶለዋቱ ፍሬ የሚገኘው ሶለዋቱ በጠራና በተስተካከለ መልኩ ሲባል ብቻ በመሆኑ የስራው ልከኛነት ሊያሳስበን ግድ ይላል።

ነቢዩ ﷺ በህልማችን ሃሴት ከሚዘራው ከዚያ አበባማ ፈገግታቸው ጋር መጥተው ያበሽሩን፤
( ኸሚስ ሙባረክ )

ሁሌም ከመሻይኾቻችን ጎን በመሆን ዲናችንን እንጠብቅ !!!

" ወይ ጎራ ሁን ወይ ከ ጎራ ተጠጋ "
አባባሉም የሚለዉ እንደዛ ነዉና ወይ በዒልም እንደ ተራራ መግዘፍ ወይ ደግሞ እንደ ተራራ ዒልማቸዉ የገዘፈ ዑለሞች ጎን መሆን ነዉ የሚያዋጣዉ ።

روى الإمام أحمد وأصحاب السنن عن أبي الدرداء -رضي الله عنه- أنه قال: قال رسول الله، صلى الله عليه وسلم: "إن العلماء ورثة الأنبياء، وإن الأنبياء لم يورثوا دينارا ولا درهما، إنما ورثوا العلم، فمن أخذه أخذ بحظ وافر"

የአሏህ መልዕክተኛ ነብያችን ሙሐመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል :-
" ዑለማዎች የነብያቶች ወራሾች ናቸዉ ነብያቶች ደግሞ የወርቅም ሆነ የብር ገንዘቦችን አላዎረሱም ይልቁንስ እዉቀትን ነዉ ያወረሱት ያንን የያዘ ደግሞ እድለኛ ነዉ "

( አል ኢማም አሕመድ ዘግበዉታል )

ሁሌም በዒልማቸዉ ከጎራ የገዘፉ ዑለማዎቻችን ጋር እንሁን ።

ከአመት በፊት ገደማ ስለ አባታችን ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ኢደሪስ ይሄንን ብለን ነበር :- 👇👇

( አሁንም ወደፊትም ከዑለማዎቻችን ጎን ነን )

Al- Faruq TUBE አል- ፋሩቅ ቲዩብ
አሚን

ያ አሏህ የወለጋ ሙስሊሞችን ነስሩን ወፍቅልን::
አሏህ ሶብሩን ይወፍቅህ ወንድሜ::
የሞቱትንም አሏህ ይማራቸው


የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎችን እንጋራ
በፌስ ቡክ ላይክ እናድርግ
https://www.facebook.com/Abu-sualih-أبو-صالح-አቡ-ሷሊህ-111677811568911/

በቴሌግራም ጆይን እንበል
https://t.me/abusualih5595

ሸር በማድረግ ሌሎችን እንጥቀማቸው::
ባረከሏሁ ፊኩም::
( ኸሚስ ሙባረክ )

"لبيكَ اللهمَّ لبيك لبيكَ لا شريكَ لك لبيك إنَّ الحمدَ والنّعمةَ لكَ والمُلك لا شريكَ لك"
ጌታየ ሆይ በዚህ አመት እንዲሁም በየ አመቱ ያላቅከዉን ቤትህን ናፋቂዎች ነን እና ወፍቀን 😥
ورد في حديث رسول الله صلى الله عليه وسلم "من حج
فلم يرفث ولم يفسق خرج من ذنوبه كيوم ولدته أمه". رواه البخاري
የአሏህ መልዕክተኛ ነብያችን ሙሐመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል :- "አንድ ሰዉ ሀጅ ካደረገ እናም በዚህ ሀጁ ላይ ግብረ ስጋ ግንኙነት ካልፈፀመ እንዲሁም ፍስቅናን የሚያስከትሉ ወንጀሎችን ካልፈፀመ ሙሉ በሙሉ ከወንጀሉ ፀድቶ እናቱ ሆድ እንደወጣበት ቀን ንፁህ ይሆናል " ቡኻሪ ዘግበዉታል

( ሀጅ እና ዑምራን አሏህ ይወፍቀን ሙሉ በሙሉ ወንጀላቸዉ ከሚማርላቸዉ ባርያዎች ያድርገን )

Al- Faruq TUBE አል- ፋሩቅ ቲዩብ
( የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች )

قال سيدنا علي رضي الله عنه :-
" حين سكت أهل الحق عن الباطل توهم أهل الباطل أنهم على الحق "
ሰይዱና ዓልይ ረድየሏሁ ዐንሁ እንዲህ አሉ:-

" እዉነትን የያዙ ሰዎች ዝምታ ሲያበዙ ስህተት ላይ ያሉ ሰዎች እዉነትን የያዙ መስሎ ተሰማቸው "

- እዉነት ሁሌም እዉነት ነዉ -
ስህተት ላይ ያሉ ሰዎች ዉሸት ብለዉ ቢሰይሙት እንኳን

-ዉሸት ደግሞ ሁሌም ዉሸት ነዉ -
ስህተት ላይ ያሉ ሰዎች እዉነት ብለዉ ቢሰይሙት እንኳን

ሁሌም ከ እዉነት ጎን እንሁን ሀቅ ከያዙ ሰዎች ጋር እንሁን ።

የእምነት ቦታቸዉን እንዲሁም ተቋማቸዉን ለሌላ ሀይማኖት ተከታይ አሳልፈን አንሰጥም ማለታቸዉ ስህተት አይደለም ።

አሁንም በእስር ላይ ያሉ ወንድሞቻችን ሁሉም እንዲፈቱ ስንል እንጠይቃለን 🚫

Al- Faruq TUBE አል- ፋሩቅ ቲዩብ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#እኔ_አንደበት
አዲስ የመንዙማ ከቨር በኢሳም አል ሙነወር
በቅርብ ቀን 👇👇👇
https://youtu.be/McmEcvcevlE

ዘወር በልልኝ የሀድራዉጠላት
አይበቃም አትበል ነብዩን መጥራት
ጠላት አንፈራም ወሏሂ እርሶን ለመጥራት
አንሸነፍም

Al- Faruq TUBE አል- ፋሩቅ ቲዩብ
#በኔ_አንደበት!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመምጣት ለመንዙማዉ አፍቃሪያን ድንቅ ችሎታዉን እያሳየ ያለዉ ታዳጊዉ ማዲህ #ኢሳም_አል_ሙነወር አሁን ደግሞ #በኔ_አንደበት በሚል በአይነቱ ለየት ባለ መልኩ ዉብ እና ማራኪ የሆነ በታላላቅ ወጣት ማዲሆች የተሰሩ መንዙማዎችን በራሱ ይዘት ቀምሞ አዲስ #የመንዙማ #ከቨር ይዞ ታዳሚዉን ሊያስደምም ከተፍ ብሏል!!!

ኸሚስ ምሽት ባማረ ቪድዮ ክሊፕ በ ተወዳጁ #አል_ፋሩቅ_ቲዩብ ወደ እናንተ ይደርሳል!