ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
359 subscribers
1.3K photos
11 videos
146 files
169 links
Download Telegram
+መጻሕፍትንና አበውን ያናገረ መጽሐፍ+
#ጽንዐ_ተዋሕዶ

#መግቢያ

መፍቀሬ ሰብእ ክርስቶስ በኤማሁስ ሲያቀኑ የነበሩትን መንገደኞች መጻሕፍትን ተርጉሞ አእምሮ መንፈሳዊና እንደቸራቸው ሁሉ የራቀውን አቅርበው የረቀቀውን አጉልተው የሚያሳዩ በዘመን ሁሉ የተነሱ ሊቃውንትም መጸሐፍትን እየተረጎሙ የሳተውን እያረሙ የሰው ልጆች ጥራዝ ነጠቅ ፈቺ ሆነው እንዳይቀሩ ሲደርሱ ሲደጉሱ ኖረዋል።

ሃይማኖት እያቀኑ ብዙዎችን ስሁት ከሆነ ትምሕርት ነጥቀዋል በቃል የመጣውን በቃል በመጸሐፍ የመጣን በመጸሐፍ እያደረጉ ድል ነስተዋል። ዘመን የሚወልዳቸው ጸሐፍያን ደግሞ የሊቃውንቱን ትምህርት ማመሳከርያ እያደረጉ የቤተክርስቲያንን መሠረተ እምነት በጎልሕና በተረዳ አስቃኝተውናል። ከእነዚህም ውስጥ መምህር በዓማን ነጸር አንዱ ነው ብዬ አምናለው። የመስኮት ሰው ስላልሆን በመልክ ብዙዎቻችን ባናቀውም ቅሉ ባበጀው ክታበ ገጽ(fb) ላይ ጠንከር ያሉ ምን አልባትም ወተት ለለመድን ሰዎች እንደ አጥነት የጠነከሩ ጽሑፎችን ሲያጋረን እናቀዋለን። በጽሑፎቹ በጥበብ ሲገስጽ እና በብስለት ሲያስተምርም ተመልክተነዋል።

ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ ከአንጻሩ የሚያነጻጽር ጥንተ አብሶን ከነጓዙ የሚተነትን ቁንጸላዎችን የሚወድር ወለታ ጽድቅ በተሰኘው መጽሐፉ የተዋወቀን በአማን ነጸረ ተቀብዓ ተኮር መጽሐፋዊ ሐረጋት ጉባኤያት ታሪክና ዶግማ ከምክንያተ ጽሕፈት ከዘርዝር የነገረ ክርስቶስ ሐተታ ጋር የቀረበ ጽንዐ ተዋህዶ የተሰኘ መጽሐፍ በ2012 በገበያ ላይ አውሏል። ይሕን መጽሐፍ ባናነበው እንኳን ለብዙ ጥያቄዎች ምላሽ አንድም ማመሳከርያ ሊሆን የሚችል መጽሐፍ በመሆኑ ለትውልድ ቢሻገሩ ብዬ መምኛቸውው መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ሆኗል።

#የምዕራፎቹ_ጭብጥ ሐሳቦች

1👉በመጀመርያው ምዕራፍ በዘመነ ሊቃውንት የተዘጋጁ ተቀብዐ ተኮር ምንባባትን ከምክንያት ጽሕፈት ጋር ያትታል። በዚህ ክፍሉ የሄሬኔዎስን÷ የባስልዮስ ዘቂሳርያን÷የጎርጎርዮስ ዘኑሲስን÷ የአርጌንስን÷የአውሳብዮስ ዘቂሳርያን÷የአርዮስን የጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙን÷የአትናቴዎስን የዩሐንስ አፈወርቅን÷የንስጥሮስን÷የቅዱስ ቄርሎስን የቴዎዶስዩስ ዘእስክንድርያን÷የሳዊሮስ ዘአንጾኪያን÷ ተቀብዐ ተኮር ጽሑፎችን ያብራራል አንድም "ተቀብዐ" የሚለውን ቃል በምን መልኩ ለማን እና ለምን እንደተጠቀሙበት በጥልቀት ያስረዳል። ተቀብዐን በሁለቱ ጉባኤ ቤቶች ውስጥም ያለውን ፍቺ ይገልጣል። በምንፍቅና የተወገዙትን እንዲሁም የቅዱሳን ሊቃውንት የአበው መጻሕፍት እንዲናገሩ እድል ሰጥቷል።

2👉በዘመነ ሊቃውንት ያሉትን ተቀብዕ ተኮር መጽሐፋዊ ሐረጋትና ካስቃኝ በኋላ "ተቀብዐ" በመካከለኛው ዘመን በኢትዮጵያ በተደረሱና የተተረጎሙ መጻሕፍተ ሊቃውንትን ከተጨባጭ ታሪኮች ጋር ያስቃኘናል። ሁለቱ ቤተ መነኮሳት ማለትም በቤተ ተክለሃይማኖት እና በቤተ ኤዎስጣቴዎስ የተደረገው የቅድምና ክርክርን ይተርካል። ተቀብዕ ከልሳነ ዐረብ ከተተረጎሙ ድርሰቶች ውስጥ በሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ÷ በሃይማኖተ አበው ዘሳዊሮስ ዘአንጾኪያ÷በሳዊሮስ ዘእስሙናይን ድርሳን÷ግብረ ሕማማት ዘሐሙስ ውስጥ ያሉትንም ሐረጋት ይመረምራል። "ተቀብዕ" ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ በተሰኘው በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሥራዎች ላይም እንዴት እንደተገለጠ ያስነብባል የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መጽሐፈ ሚላድንም ይዳስሳል።

3👉በመቀጠል ድኅረ ምጽአተ ካቶሊክ የተደረጉ ጎባኤያትን ከሥር መሠረታቸው ይተርካል። ሱታፌ መንፈስ ቅዱስ በነገረ ሥጋዌ የተነሣበት ከካቶሊካውያን ጋር የተደረገውን የመጀመርያውን ጉባኤ÷በዐፄ ዘድንግል ዘመን የተደረገውን ጉባኤ÷ በዓፄ ሱሲንዮስ የተደረጉ ተጨማሪ ጉባኤያትን እና የነገረ ክርስቶስ አለመግባባት የወለዳቸው አመፃዎችና ምዕላዶች ከፎገራ ጉባኤ ማግሥት እስከ ፋሲለደስ ንግሥና ድረስ ያለውንም ይተርካል። በዚሁ ሳያበቃ የነገረ ክርስቶስ ምዕላዳት መጀመርና ውስጣዊ የነገረ ክርስቶስ ክፍፍሎችንም እያስቃኘ ይሔዳል። የአልፎዝ ሜንዴዝ ወደ ሐገር መምጣት÷ተቀብዐ ተኮር ትምሕርቱና የተሰጠው ምላሽ÷ከሀገር በምን መልኩ እንደለቀቀና÷በእርሱ ምክንያት ስለተደረገው ጉባኤ÷እንዲሁም የሜንዴዝ እሾሆች የተባሉትን ይገልጻል። "የቅብዓት አስተምህሮ የት መጣ" በሚለው ንዑስ ርዕስ ምዕራፍ ሦስትን ይዘጋል።

4👉በቀጣዩ ምዕራፍ ማለትም በምዕራፍ አራት ከ1624-1762 የነበረውን ዘመን ያስቃኛል በዘመነ ጎንደር በነገረ ክርስቶስ ጉዳይ የተደረጉ ክርክሮችን ይዟል። በዘመነ ፋሲል÷በዘመነ አእላፍ ሰገድ÷በዘመነ አድያም ሰገድ ኢያሱ÷ በዘመነ ንጉሥ ተክለሃይማኖት÷በዘመነ ዐፄ ቴዎፍሎስ÷በዘመነ ዐፄ ዳዊት ሣልሳይ ÷በዘመነ ዐፄ በካፋና ብርሃን ሰገድ ኢያሱ÷በዘመነ ኢዩአስ በነገረ ክርስቶስ የተደረጉ ጉባኤያትና ያለ ጉባኤ የተደረጉ አዋጆችን ይዞ እናገኘዋለን።

5👉ከዘመነ ጎንደር ወደ ዘመነ መሳፍንት ያቀናና የጸጋን አመጣጥ በአቡነ ዮሳብ ዘመነ ጵጵስና÷ጸጋ ከተዋህዶ ጋር÷የጸጋና የቅብዐት ዳግም ግንባር መፍጠር በዘመነ አቡነ ቄርሎስ÷ በስተመጨረሻም ከፕሮቴስታንታውያን ጋር የተካሄዱ የነገረ ክርስቶስ ንግግሮችን ይገልጻል።

6👉ጉባኤያት ድኀረ ዘመነ መሳፍንት እና መጽአተ አቡነ ሰላማ ሣልሳይ በምዕራፍ ስድስት ሠፍሯል። የአቡነ ሰላማ ምርጫበተመለከተ ወደ ሀገረ ኢትዮጵያ ሲመጡ ነበረውን ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ÷የአቡነ ሰላማና የዐፄ ቴዎድሮስ ጉዞ ከአምባ ጫራ እስከ መቅደላ ዘልቆ ካሳየ በኋላ ዐፄ ዮሐንስ መፍቀሬ ተዋህዶ አቋማቸውን እንዲሆም የቦሩ ጉባኤ እንዲሁም በተለምዶ ዘጠኝ መለኮት ስለሚባለው አስተምህሮ ይይዛል።

7👉ሰፊ ርዕሶችና በዛ ያሉ ንዑስ ርዕሶች የተካተቱበት ምዕራፍ ሰባት ሦስቶ የኢትዮጳውያን የነገረ ክርስቶስ ዘውጎች ካነሷቸው አርእስት ጋር ያብራራል። ተዋህዶ÷በተዋህዶ ከበር÷ሁለቱ የጸጋ አስተምህሮዎች÷ብሂለ ቅብዓት የተሰኙ ዐበይት ርዕሶች አሉት።

8 👉የመጸሐፉ የመጨረሻው ምዕራፍ ስምንት ከነገረ ክርስቶስ ጋር የተገናኙ ቅኔያትን ያስነብባል።

#ማጠቃለያ_{_የመጽሐፉ_አስፈላጊነት_}

👉መማርያ እና ማመሳከርያ

ይህ መጽሐፍ ጥናታዊ ስልትን የተጠቀመና ከሀገር ውጪ እንዲሁም ሀገር በቀል ድርሰቶች ተመርምረው የቀረቡበት ተቀብዐ ተኮር እና ነገረ ክርስቶስ የተዳሰሰበት በመሆኑ በቲዎሎጂ ላሉ መማርያ አልያም ማመሳከርያ ሊሆን የሚችል ክታብ ነው። በሀገራችን እንደነ አድማሱ ጀንበሬ አይነት ሊቃውንት የጻፏቸውን የመልስና የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የሸከፉ መጻሕፍትን ለትውልድ ከማስተላለፍ ባሻገር በመንፈሳዊ የትምሕርት ተቋማት ውስጥ እንደ ማመሳከርያ ሊቀርቡ ሲገባቸው ከግለሰቦች ውጪ ብዙ ምዕመናን እጅ ውስጥ መገኘት ተስኗቸዋል። እንዲህ ያሉ ችግር ፈቺ እና አንኳር ርዕሰ ጉዳዩች የያዙ መጽሐፎች ተመርጠው ለመማርያና ለማመሳከርያ ሊሆኑ ይገባል የሚል ቅናታዊ ሐሳብ አለኝ። ቢቻል ቢቻል የጥናትና የምርምር ማዕከል ተገንብቶ ዶግማቲክ ርዕሰ ጉዳዩች የሚዳሰሱበት መጽሐፋዊ ሐረጋትም ትንታኔ የሚሰጥባቸው ቢሆን እጅግ የተሻለ ይመስለኛል። በጥቅሉ ጽንዐ ተዋህዶ ከገበያ ሽያጭ ባለፈ ማጣቀሻ እና ማመሳከርያ ሆኖ ከቤተመዛግብት ሊቀመጥ የሚገባ ይመስለኛል።

👉የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የገለጠ

የቤተከርስቲያኒቱን አስተምህሮ ያበራል።
አንድ አንድ መጽሐፉች ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻዎችን ከመስጠት ባሻገር የተለየ ድርሳናትነ እና ሐረጋትን እና ሐረጋትን አያትቱም። የሳተውን የሚመልሱ የመጸሐፍትን ምሥጢር እየመረመሩ እውነትን የሚገልጡ ጸሐፍት ባይኖሩ ኖሮ ለብዙ ዘመናት በተለይ በሐገራችን ሲያነታ
በዐቢይ ጾም ቢነበቡ የምላቸው ጠጠር ያሉና በአማርኛ የተዘጋጁ የነገረ ሃይማኖት መጻሕፍት
--
ጾም ሕሊናን ሰብስቦ ከፈጣሪ ጋራ ለመገናኘት፣ ለንባብ፣ ለማሰላሰል፣ ለመንፈሳዊ ተመስጦ ጊዜና አጋጣሚን ይፈጥራልና ተከታዮቹን መጻሕፍት እንጠቁማለን፡፡
--
1. ሃይማኖተ አበው፣ በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፡፡
2. ድርሳነ ቄርሎስ ወጳላድዮስ ምሰለ ተረፈ ቄርሎስ፣ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ፡፡
3. መጽሐፈ ምሥጢር፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፡፡
4. መድሎተ አሚን፣ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ (ዳግም ኅትመትና ሥርጭት ብራና መጻሕፍት)
5. ፍኖተ እግዚአብሔር፣ አለቃ ኅሩይ ፈንታ (ዝግጅትና አርትዖት መጋቤ ሐዲስ ልዑለ ቃል አካሉ)፡፡
6. ሥርወ ሃይማኖት፣ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ (ኅትመቱ ደካማ ቢሆንም ሊቀ ሊቃውንት ኃይለ መስቀል ውቤ ደግመው አሳትመውታል)፡፡
7. የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፣ አባ ጎርጎርዮስ የሸዋ ሊቀ ጳጳስ፡፡
8. ፍኖተ ሕይወት፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ (አሳታሚና አከፋፋይ ማኅበረ ቅዱሳን)፡፡
9.መሠረተ ሃይማኖት፣ ሊቀ ትጉሃን ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኘ (አሳታሚ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ሰ/ት/ቤት)፡፡
10. በትረ ሃይማኖት፣ ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሣ::
11 .የትምህርተ መለኮት መግቢያ፣ መ/ር ግርማ ባቱ::
12. ዝክረ ሊቃውንት ቁጥር ፩ እና በዐቢይ ጾም የሚወጣው ቁጥር ፪፣ መልአከ ብርሃን አድማሱ (የቁጥር ፪ቱ አሳታሚና አከፋፋይ ብራና መጻሕፍት)፡፡ ነገረ ሃይማኖት በቅኔያት እንዴት እንደሚገለጥ ለማወቅ ሁለቱ የመልአከ ብርሃን የዝክረ ሊቃውንት ቅጾች የግድ ያስፈልጋሉ፡፡

ከላይኞቹ ጋራ ተደምራ መቈጠሯ ቀርቶ እንደ ኅዳግ ትወሰድና የኔዋ #ጽንዐ_ተዋሕዶ፣ በአማን ነጸረ (አሳታሚና አከፋፋይ ብራና መጻሕፍት)፡፡ … መቀጠል ይቻላል፡፡
--
ረዥም ጎዳና ስለላብን ከወዲሁ መልካም ጾመ ኢየሱስ፤ መልካም የንባብ፣ የጥሞናና የቀኖና ጊዜ ብለናል፡፡ በየዘውጉ መጻሕፍትን መጠቆማችንን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከጉዞ መልስ እንቀጥልበታለን፡፡ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፣ ላዘኑት መጽናናትን ይስጥልን፡፡ አሜን!
**ከበአማን ነጸረ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ
#በደብተራ_በአማን_ነጸረ
መሠረተ እምነት (ዶግማ) ለምን?
--
የምናምነውን እንጸልያለን፤ የምንጸልየውን እናምናለን የሚል ይዘት ያላት ጥቅስ በቀሲስ መብራቱ በኩል ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ ጸሎተ ሃይማኖት ትልቁ ጸሎታችን ነው፡፡ በምሥጢሩ የአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ፍጹም አምላክነት፣ አንድነትና ሦስትነት፣ የጌታ ከድንግል ሰው ሆኖ ዓለምን ማዳን፣ ምሥጢረ ጥምቀት፣ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን፣ ነገረ ቤተ ክርስቲያን ያለበት የእምነት መግለጫ ነው፡፡ የእምነታችን መግለጫ ጸሎታችንም ነው፡፡ አበው እንዲህ አድርገው አሠረጹብን፡፡ እምነታችን ዝርው እንዳይሆን መሰብሰቢያ ሠርተው ጸሎትም የእምነት መግለጫም በአንድ ላይ አቀበሉን፡፡ ይህ እምነትና ጸሎት በአንድ የተገለጡበት ድንጋጌ አማንያን በነጻ ፈቃድ የሚታሠሩበት የሚኖሩበት የሚገዙበት መንፈሳዊ ሕግ፣ ዘለዓለማዊ እውነት ነው፡፡
የቃል ሥጋ መሆን፣ የሥላሴ አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ መሆን፣ ያለወንድ ዘር በድንግልና ፀንሶ በድንግልና መውለድ እንዲሁ እንብለ ተኀሥሦ (ያለመመራመር) በእምነት የሚቀበሉት ምሥጢር ነው፡፡ ምሥጢሩን ለማወቅ ጭላንጭል የሚገኝ ተቀብለውት ሲያበቁ ነው፡፡ እግዚአብሔር ኢምክንያታዊ አምላክ አይደለም፡፡ ሆኖም በእርሱ ያለን እምነት በአመክንዮ የሚደረስበት አይደለም፡፡ እምነት ግላዊ ምናብና አስተያየት አይደለም፡፡ እምነት ተቀብለው የሚኖሩት ሕይወት ነው፡፡ ለማወቅ የሚሞከር ካመኑ በኋላ ነው፡፡ የማይመረመረውን ምሥጢር በድንግዝግዙ ለመግለጥ ሰብአዊ ቋንቋ እንጠቀማለን፡፡ የእምነታችን ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ቢሆንም ዝርውነት እንዳይኖር የመጽሐፉን ተርጓሚነት ሥልጣን በየግላችን አንቧጨቀውም፤ ሉዐላዊ የትርጓሜ ሥልጣኑ የቤተ ክርስቲያን እንደሆነ እናምናለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን ባሰመረችው መስመር፣ አበው ባኖሩት የዶግማ ቅጽር እንፀናለን፡፡ ለምን?
--
1.እንዲህ እናምናለን ብሎ ለመቆም!
ደጋግሜ እንደምለው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አካሄዳችን አጸፋዊ (reactive) የሆነ መስሎ ይሰማኛል፡፡ በሚቀረጽልን አጀንዳ ዙሪያ ብቻ መሽከርከር፡፡ አልፎ አልፎም በተጋነነ ቀናዒነት በሚሰጥ የደም ፍላት ምላሽ ከመጽሐፍ እስከ መጋጨትና መሠረታዊ ዶግማን እስከ ማድ እንደርሳለን፡፡ ‹‹እንዲህ እናምናለን›› ማለትን ሳያስቀድሙ ‹‹እንዲህ ይሉናል፣ እንዲህ ይላሉ›› ከሚል ደመ ነፍሳዊ ስሜት የሚነሣ የአፀፋ አካሄድ ማነፁ ያጠራጥራል፡፡ ዕቅበተ እምነት (እምነትን መጠበቅ/መከላከል) አስቀድሞ እምነትን ማወቅን ይፈልጋል፡፡ የተጻፈ የተተረጐመ ዶግማ አለን፡፡ ክብ … ድ አድርገን በ‹‹ፊዚክስ›› ዐይን አንየው፤ ቅል …ል አድርገንም በደመ ነፍስ የሚነበነብ ጸሎት አናድርገው፡፡ ጊዜ ሰጥተን፣ ከቀልባችን ሆነን ዶግማውን እንወቀው፡፡ ‹‹እንዲህ እናምናለን፣ እንታመናለን›› እስክንል ድረስ፡፡
--
2.የኅብረትና አንድነታችንን መሠረት ለማወቅ!
አንድ ምዕመን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመን ሲባል ወደ አንድ ዐቢይ መንፈሳዊ ኅብረት እየተጨመረ ነው፡፡ ዕድር፣ ዕቁብ፣ አክሲዮን ስንገባ መተዳደሪያ ሕጉን እናውቃለን፡፡ ያሰተሳሰረንን አንድነት እናውቀዋለን፡፡ የእምነታችን መጠሪያ የሆነውን ‹‹ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ›› ትርጓሜ ማወቅ እየተቻለን ዕውቀትን ለካህን ብቻ የተሰጠ ግብር ማድረግ ስንፍና ነው፡፡ ያስጠይቃል!
--
3.እንዲህ ነን ለማለት!
‹‹እንዲህ ናችሁ›› ባዩ ብዙ ነው፡፡ የእምነቱን መሠረታውያን ያወቀ ሰው ‹‹አይ እንዲያ ሳይሆን እንዲህ ነን›› ለማለት አያፍርም፡፡ በማይጠራበት ስም ሲጠሩት በስሜ ጥሩኝ ይላል፡፡ ራሱን መግለጥ በሚገባው ቦታ ይገልጣል፤ ይመሰክራልም፡፡ አውቆ መመስከር ያጸድቃል፡፡
--
4.እምነቱን ለልጅ ለማውረስ!
‹‹እምነት እንደ ፍሻሌ ሽጉጥ አይወረስም›› የሚልህን ዝርው ቧልተኛ እርሳው፡፡ ይወረሳል፡፡ የይስሐቅ እምነት ከአብርሃም የተወረሰ ነው፤ ከነግዝረቱ ነዋ! በነሐሴ 3 ስንክሳር የምትዘከረውን የሶፍያ ንግሥት ደናግል ልጆች እምነት ታውቃለህ! ቅዱስ ያሬድ ‹‹መተወት ደቂቃ ለስምዕ›› የሚላት እርሷን ነው፡፡ በየትም አገር ልጅ የአባቱን እምነት ተቀብሎ አብዛኛው በዚያው እምነት ኖሮበት ያልፋል፡፡ ብልጣብልጡ እንኳ ልጁ እምነቱን እንዳይወርስ ያደርጋል ብለህ እንዳትገምት፡፡ አራዳውን እርሳው! ሕገ መንግሥቱም ወላጅ ልጁን በሚያምንበት እምነት አንጾ የማሳደግ መብት እንዳለው ይደነግጋል፡፡ እንደ ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖተ አበውን መጠበቅ ግዴታችን ነው፡፡ ቄርሎስን እንደ ቄርሎስ እንዲሠራ አጎቱ ቴዎፍሎስ ደክሟል፡፡ ቈስጥንጢኖስ የእናቱ ልጅ ነው፡፡ ከአባትህ የተቀበልከውን ለልጅህ ማቀበል ግዴታህ ነው፡፡ የምታቀበልው እንዳታጣ የቤተ ክርስቲያንህ ዶግማ ሰንቅ! ልጅህን በእምነትህ ቅረጸው! ቢላዋ የሚሳል ለራ ባልተሳለ ሞረድ ነው ብለህ ግን እንዳትዘናጋ፡፡ ማወቅና ማሳወቅ እየቻሉ አለማወቅና አለማሳወቅ አያጸድቅም!
--
5.አፈንጋጮችን ትቈጣጠርበታለህ!
ዐውደ ምሕረት ላይ እምነት የሚያጎድፍ፣ ምሥጢር የሚያፋልስ ሰብከት ቢሰበክ፣ በመጻሕፍት ተጽፎ ብታገኝ፣ በግል ውይይት ሲነገር ብትሰማ ጋላቢው ላይ ልጓም ትስብበታለህ፡፡
--
6.ማን፣ ለምን፣ ከምን፣ በምን፣ እንዴት እንዳዳነህ ትረዳበታለህ!
ቤተ ክርስቲያን አንዲት ዘለላ የድኅነት ፎርሙላ አትሰጥህም፡፡ ‹‹አመንክ ጸደቅህ›› ብላ አታዘናጋህም፡፡ ነገረ ድኅነት ጌታ ከፅንሰት እስከ ምጽአት ያለው ጉዞ የሚካተትበት፣ የምግባርና የምሥጢራትም ጉዳይ ያለበት ሁለንተናዊ ጉዞ መሆኑን ትረዳበታለህ፡፡ ዝርዝር ጥያቄዎችህ በዚያ ሂደት መልስ ያገኛሉ፡፡ ያመንከውን ለማወቅ አንብብ፣ ጠይቅ፣ ተረዳ፣ የተረዳሀትን ለመኖር ጣር፣ በምሥጢራት ተሳተፍ፣ ቸርነቱን በእምነት ተስፋ አድርግ፡፡
--
ንባብህን እንደ #ኦርያሬስ ካሉ የጉባኤን ምሥጢር ሳይገድፉ የዘመንህን ቋንቋ የዋጀ አቀራረብ ካላቸው የነገረ ሃይማኖት መጻሕፍት አታርቅ፡፡ ያንጊዜ ባለፀጉረ ጉንጉን ሐሳዊም ሆነ የፌርማ አወናባጅ አያወናብድህም፡፡ እምነትህ እንደ መገበሪያ ሰንዴ የተለቀመች ናት፡፡ አትሰነፍ! የጉባኤ ሰዎች ቸርነት ሳይነጥፍ፣ ያንተም የጉብዝና ወራት ሳያልፍ፣ ኦርያሬስ ሳትጠልቅ (ጀምበር ኦርያሬስ/ ሳለች ሩጥ እንዲሉ አበው) ምሥጢሯን አስስ! ኦርያሬስ ከሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ #ተንከተም ና ከእነ መ/ር ገብረ መድኅን #ምሥጢረ_ምሥጢራት በኋላ የመጣ ግሩም የነገረ ሃይማኖት መጽሐፍ ነው፡፡ የብሔራውያኑን ሊቃውንት ረቂቅ የነገረ ክርስቶስ ተዋሥኦ ካሻህ እንዳቅማችን በአማተራዊ ብርዕ የደከምንባት #ጽንዐ_ተዋሕዶ መስፈንጠሪያ ትሆንህ ይሆናል፡፡

#ኦርያሬስ_በአርጋኖን_መጽሓፍት_መደብር_እየተከፋፈለነው