ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
361 subscribers
1.3K photos
11 videos
146 files
169 links
Download Telegram
#ለምን_በኩረ_በዓል_ተባለ?#
ርዕሰ በዓላት (የበዓላት ራስ) መጋቢት 29 የበዓላት ሁሉ በኩር (የበዓላት ጥንት)፤ ይህች ቀን ለቅድስት ቤተ/ክ እጅግና ልዩ ናት፤ በየዓመቱ ከሚከበሩ ዓበይት በዓላትም ቀዳሚውን ሥፍራ ትይዛለች::

በዓለ ጽንሰት
ትስብእት ቃሉ ራሱ አምላክን ሰው መሆን ያስረዳል፡፡ ይህ በዓል መልአኩ ቅ/ገብረኤል ለቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክን ከእርሷ ሰው መሆን ያበሰረበት ፣አካላዊ ቃልም የዕለት ጽንስ ሆኖ በማኅጸኗ ያደረበት መታሰቢያ በዓል ነው፡፡ይህን በዓል ሊቃውንተ ቤተ/ክ የበዓላት ሁሉ በኩር (የበዓላት ጥንት)በማለት ስተምራሉ፡፡

#ለምን_በኩረ_በዓል_ተባለ?**
በዚህ ዕለት አምላካችን እግዚአብሔር:-
1.ሰማይና ምድርን ፈጠረ:: (ዘፍ. 1:1)
2.አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት በድንግል ማርያም ማኅፀን ተጸነሰ:: (ሉቃ. 1:26)
3.የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ:: ማቴ. 28:1
4.ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ በዚህች ቀን ይመጣል:: ማቴ. 24:1
በዚህ ዓበይት ምክንያትና ድርብርብ በዓላት ምክንያት ቀኑ"ርዕሰ በዓላት" (የበዓላት ራስ) "በኩረ በዓላት" እየተባለም ይጠራል፡፡

ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን!!!
አምላክ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን!
ተጻፈ:- መጋቢት29/2015 ዓ/ም

©መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
~•••••••~•••••••~•••••~
“ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤” ፩ኛ ዮሐንስ ፩፥፩!
••••••••••••••••••
የፌስቡክ ፔጃችንን ይቀላቀሉ ፤ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, እና Share ያድርጉ :-
~•••••••~•••••••~•••••~
የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/mikiyas.danail
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063973695479
https://www.facebook.com/mikiyas24/
የቴሌግራም ቻናል
: https://t.me/brana_Book