ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
361 subscribers
1.3K photos
11 videos
146 files
169 links
Download Telegram
#ተአምራዊው_የትንሣኤ_ቅዱስ_እሳት
(Holy Fire)
ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ•••• የሚለው መዝሙር እናውቀዋለን ነገር ግን ሃይማኖታዊ ታሪካዊ ዳራውን ብዙዎቻችን በቅጡ የምናውቅ አይመስለኝም!!!

The Amazing Story of the Miracle of the Holy Fire in Jerusalem
አስደናቂው የትንሣኤው ብርሃን ከጌታችን ኢየሱስ መካነ መቃብር በድንቅ ተአምር የሚወጣ የማይዳሰስ ረቂቅ፣ የማይያዝ በተለያየ ኅብረ መልክ የሚታይ አስደናቂ እሳት ነው። ይኽ ብርሃን የሚወጣው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በሕማማት ዕለተ ቀዳሚት ነው። ይኽችን ቀዳሚት ዕለት ብርሃን የሚያሰኛትም ይኽ ተአምራዊ የትንሣኤው ብርሃን (እሳት) መውረድ ነው፡፡ ይኽ ብርሃን ጨለማ የማያሸንፈው፣ በሰው እጅ ያልተፈጠረና በልማድ ከሚታወቀው እሳት የተለየ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው መገለጫ ነው፡፡

The Holy Fire (Greek Ἃγιον Φῶς, "Holy Light") is described by Orthodox Christians as a miracle that occurs every year at the Church of the Holy Sepulchre in Jerusalem on Great Saturday, or Holy Saturday, the day preceding Orthodox Easter. However, many dispute the alleged miraculous descent of the Fire.

https://en.m.wikipedia.org › wiki
Holy Fire - Wikipedia

ይኽንን የትንሣኤው መገለጫ የኾነውን ብርሃን በተመለከተ የተለያዩ ጸሐፊዎች ብዙ ጽፈዋል፡፡
~~~~~~~~
በአገራችን በዐሥራ ዐራተኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንዲኹም በዐሥራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ የተጻፉ መጻሕፍት ስለ አስደናቂው የትንሣኤ ብርሃን አመጣጥ ይናገራሉ፡፡ ለምሳሌ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምሥጢር፣ ዐፄ ዘርኣ ያዕቆብ በመጽሐፈ ብርሃን፤ እንዲኹም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተአምር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል፡፡

በዐሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚኖሩ አበውም ስለ ትንሣኤው ብርሃን ምሥክርነታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ስለ ትንሣኤው ብርሃን (መብራት) መውረድ የጻፉት ምሥክርነት፤

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዐለ ልደት በሚነበበው ድርሳኑ(መጽሐፈ ምሥጢር) የትንሣኤው ብርሃን በኢትዮጵያውያን አባቶች እጅ ብቻ ይወርድ እንደ ነበር ሲናገር
እንዲኽ ብሏል ፡-

"ኢትዮጵያውያን ...ከፍጹም ልቅሶ ጋር (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ) በተቀበረበት ሥፍራ በጎልጎታ ይማልላሉ፣ ከዚያም የነበሩት ምሥክር የኾኑ አሉ፡፡ ከትንሣኤ በፊት በፋሲካ ዋዜማ ይኽችውም የሕማማት ቀዳሚት ሰንበት ናት፤ በጎልጎታ ሥፍራ የክርስቲያን ጉባኤ ይደረጋል፡፡

በየወገናቸውም መብራት ይሰቅላሉ፡፡ በመጀመሪያ የሮም ሰዎችና መልካውያን ይዞራሉ፣ ሲዞሩም ብርሃን አይገለጥም፡፡ የኢትዮጵያ፣ የግብጽ፣ የሶርያና አርመንያ፣ የማሮናም ካህናት) ይዞራሉ፡፡ ከነርሱ ጋር ኢትዮጵያዊ ከሌለ በመብራቶቻቸው ውስጥ ብርሃን አይታይም፡፡ ከነርሱ ጋር ኢትዮጵያዊ ቢኖር በኢትዮጵያዊው መብራት (በሻማው ላይ) ካልኾነ በቀር ብርሃን አይቀመጥም፡፡ በዓመቱም ከሀዲዎች ወደ ሌላ ሥፍራ ቢያዘዋውሩት እንኳን የእግዚአብሔር ፊት ይከተለዋል፡፡ በርሱም ላይ የሚያበራው መብራት ይታያል። ኢትዮጵያዊ መንገደኛ በጠፋበት ጊዜ ግብጻውያን ወደ አንድ ኢትዮጵያዊ መቃብር ሄደው አጥንቶቹን አውጥተው በልብሳቸው ቋጥረው የጌታችንን መቃብር ዞረዋል፡፡
(በዚኽን ጊዜ) የመብራቱ ብርሃን በቀንዲሉ ውስጥ ታይቷል፡፡"

ዐፄ ዘርኣ ያዕቆብ በመጽሐፈ ብርሃን ስለ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖት በተናገሩበት አንቀጽ ከሮም፣ ከጽርዕና ከቍስጥንጥንያ ሰዎች ያገኙትን መረጃዎች ምሥክር በማድረግ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መካነ መቃብር ላይ ለኢትዮጵያውያን የሚደረገውን ታላቅ ተአምር በተመለከተ እንዲህ ይላል:-

"••••ከኋላቸውም ከማርቆስ መንበር የኾኑት የኢትዮጵያ ሰዎች ሦስት ጊዜ ይዞራሉ፡፡ በዚኽን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ይወርዳል፤ ለኹሉም ይታያል፡፡ ከዚያም የጌታችን መቃብር በሚገኝበት የጣራ መስኮት ይገባል፡፡ በዚኽ ጊዜ መዓዛው እጅግ ያማረ ሽታ ያውጣል፡፡

ከማርቆስ መንበር በኾኑትና ሃይማኖታቸው በቀና ደጋግ የኢትዮጵያ ሰዎች ላይ ብርሃን ይወርዳል፡፡ ይኽ ለኢትዮጵያ ሰዎች የሚወርደው ብርሃን ክርስቲያኖች በሰውነታቸው ላይ በሚያደርጉት ጊዜ ለአንድ ሰዓት ያኽል አያቃጥልም፡፡ ይኽ ነገር ሐሰት አይደለም፤ እውነትና የተረጋገጠ ነው እንጂ••••" መጽሐፈ ብርሃን

የበዐለ ትንሣኤ ብርሃን (መብራት)
አወጣጥ ሥርዐት በኢትዮጵያውያን አበው መሪነት
~~~~~~~~
በኢየሩሳሌም እስከ ዐሥራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ፲፮፻፶፬ ዓ.ም) ድረስ ለኹሉም አብያተ ክርስቲያናት የትንሣኤ ብርሃን የሚወጣው በኢትዮጵያውያን አባቶች እንደ ነበር ጽፈዋል፡፡

ብርሃን በሚወጣበት ቅዳሜ ዕለት በሚሰበሰቡበት ከኹሉ አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀብሮ ወደ ነበረበት የመቃብር ቦታ ነጭ ልብስ ለብሶ የሚገባው የኢትዮጵያው መምህር ነበር፡፡ በዚኽን ዕለት ጳጳሳቱና መነኰሳቱ በአንድነት ወደ መካነ መቃብሩ ሲሄዱ ከፊት ለፊት የሚሄደው ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የሚላከው ኢትዮጵያዊ አባት ነበር፡፡ ይኽ አባት ይኽንን የትንሣኤውን ብርሃን ለማውጣት ብቻ ከኢትዮጵያ የሚመጣ ነበር፡፡

የሌሎች አብያተ ክርስቲያናት መምህራን የሮም፣ የአርመን፣ የኩርጅ፣ የሶርያና የቅብጥ አብያተ ክርስቲያናት መምህራን በተቀመጠላቸው ቅደም ተከተል መሠረት ከርሱ በኋላ ወደ መካነ መቃብሩ ይገባሉ፤ ብርሃን በሚወጣበት ቅዳሜ በአንድነት ጧፍ አብርተው ከመካነ መቃብሩ ይወጣሉ፡፡

የትንሣኤውን መብራት ለማብራት ይኽ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መምህር ነጭ ልብስ ለብሶ፣ ዘይት የተመላበት ያልተቃጠለ ፈትል ያለበት የብርጭቆ ቀንዲል ይዞ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መካነ መቃብር ይገባል፡፡ ወደ መካነ መቃብሩ ገብቶ መዝጊያውን ዘግቶ ይቆማል፡፡ የሌሎችአብያተ ክርስቲያናት መምህራን ደግሞ ከሕዝባቸው ጋር ጧፍ ይዘው ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ (ትንሣኤኽን ለምናምን ለእኛ፣ ብርሃን ላክልን ወደ እኛ፡፡)" በማለት እየዘመሩ በደጁ ላይ ይጠብቁታል፡፡ ይኽ በመቃብሩ ሥፍራ ያለው የኢትዮጵያ መምህር ብርሃን ከወጣለት በኋላ ሌሎቹ ገብተው መካነ መቃብሩን እንዲሳለሙ መዝጊያውን ያንኳኳል፡፡ ከዚኽ በኋላ ኹሉም መምህራን በኢትዮጵያዊው መምህር ከተያዘው የትንሣኤ መብራት በእጃቸው የያዙትን ጧፍ በፍጥነት በማብራት ወደ ራሳቸው አብያተ መቃድስ ቤተ መቅደሶች) ሄደው ብርሃነ ትንሣኤውን ያከብራሉ፡፡

ስለ ትንሣኤው ብርሃን መውረድ