በክርስቶስ ( in christ)
684 subscribers
96 photos
34 videos
41 files
36 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
#መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር #ይቀሰቀቅሰኛል #ለስሙ እንድዘምር

@ownkin
@cgfsd
(እግዚአብሔራዊ አቆጣጠር)
     (ክፍል 1)


ብዙ አይነት በእጄ የሚያስብል የአቆጣጠር ስሌት አለ ደግሞ ይኖራል ።የእግዚአብሔር አቆጣጠር በእጅጉ አብዝቶ ይለያል እግዚአብሔርማ ይቁጠር በደንብ ይቁጠር እንጂ ከእግዚአብሔር ጀምሮ ምን የማያምር ነገር አለ?? ምንም ነዋ መልሱ ።

እሺ እግዚአብሔር ግን ምን ቆጠረ? 😁 ፅድቅ አዎን ፅድቅን ቆጠረ ። ፅድቅን ለመገንዘብ የእግዚአብሔር አቆጣጠር ሊገባህ ይገባል ካለ በለዚያ ፅድቅን እንደ ራስ ፣ እንደ ሀይማኖት፣ እንደ ሰው፣ እንደ አቅምህ ለመረዳት እና ለመቁጠር ትሞክርና ተራራ የመግፋት ያክል ሲገዝፍህ አርፈ ትቀመጣለህ ስለዚህ ፅድቅ በእግዚአብሔር አቆጣጠር ተመልከት ። ፅድቅ ስሌት ፣ቀመር ፣አሰራር አለው እሱ እግዚአብሔራዊ ነው እደግመዋለሁ የፅድቅ ቀመር እግዚአብሔራዊ ነው ።

ብዙ ሰው በአዳም በኩል ሀጢያት እደደረሰው ያምናል ። በክርስቶስ በኩል ደግሞ ፅድቅ እንደደረሰው ለማመን ለመቀበል ሲቸገር ይስተዋላል ። እግዚአብሔራዊን አቆጣጠር ለመገንዘብ ይሔን መንፈሳዊ እውነት ማመን ይጠይቃል በአዳም በኩል ሀጢያት  እንደገባ በክርስቶስ በኩል ፅድቅ እንደመጣ ሊቀበሉት ግድ ይላል። በአንዱ አዳም በኩል ሀጢያት ሞት በሰው እንደነገሰ በአንዱ በኢየሱስ በኩል ፅድቅ በፀጋው በኩል እንደነገሰ መንፈሳዊ እውነት ነው ይሔ እግዚአብሔአዊ አቆጣጠር ነው ።

መፀሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይናገራል " እኛ በእርሱ በኩል ሁነን የእግዚአብሔር ፅድቅ እንሆን ዘንድ ሀጢያት ያላወቀውን እሱን ሀጢያት አደረገው"         2ቆሮ 5:21
  እኛ በኢየሱስ ሁነን እርሱ ደግሞ በእኛ ቦታ ሁኖ የሚቆጠር ፅድቅ ነው ። ይሔ ምትክነት በመተካካት ወይም ቤዛነት ይባላል ።እኛ ፅድቅ አያውቀን ከፍጥረት የቁጣ ልጆች ነን እርሱ ደግሞ ሀጢያት አያውቀው ፃዲቅ ቅዱስ ነው ። የእኛ በደል በእርሱ ላይ በመስቀል ላይ ሊኖርበት ሀጢያተኛ ሳይሆን ሀጢያት ሊሆን እኛ ደግሞ የእርሱ ፅድቅ ልንወስድ ምትክነት ቤዛነት ሊደረግ የተሰራ ስራ ነው ። አቤት ግን እግዚአብሔር እንዴት ነው የሚቆጥረው ያውም በቤዛነት (ምትክነት ) የተደረገ ቆጠራ ነው ። በልጁ ኢየሱስ የቆጠረን ፣የተቆጠረን ፅድቅ ያስደምማል ምን አይነት ጌታ አለን ያስብላል ክብር ፅድቁን በልጁ ቤዛነት ለቆጠረን አባት ይሁን ።

   በቤዛነቱ የሆነው እግዚአብሔራዊ አቆጣጠር!!

  ይቀጥላል....

ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ


#በመወለዱ አብሪያችሁ ነኝ አለ

#በመሰቀሉ ወዳችኋለው አለ

#ከሙታን በመነሳቱ አብራችሁኝ ናችሁ አለ


@ownkin
@cgfsd
ዘፀአት ውስጥ ግብፅ ትንሳኤ ውስጥ እኔነት የለም ።


Barbi
@ownkin
@cgfsd
መሲሃዊ አገዛዝ
     (ንጉሱ ኢየሱስ)
  

#የእግዚአብሔር መንግስት በኢየሱስ ማንነት የተብራራ ፣የተገለጠ፣የተበሰረ፣የታወጀ ፣የታየ ፣የተነገረ ነው ።
  


  በፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
እናት :- በጣም ስጨናነቅ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ በእጅ መሃል የፈሰሰውን ደም  አያለው አስባለሁ እፅናለለሁ

ልጅ :- እንደተሰቀለ ሁኖ ስላየሽው ብቻ ?

እናት:- እኔን እይኝ እያለኝ እኮ ነው ።

@ownkin
@cgfsd
(#ኢየሱስን መውደድ)

ሕይወት ማለት #ኢየሱስን መውደድ ነው

#ኢየሱስ እንደምንወደው መንገር ብቻ ሳይሆን መወደዱን ማየት ይፈልጋል... እንደተወደደ እንዲሰማው ይሻል

#ኢየሱስን የሚወድ ሰው እነዚህ ምልክቶች ይታዩበታል

1. ልዩ ትኩረት እና ልዩ መሰጠት #ለኢየሱስ ይሰጣል
2. አለምን እና ስራዋን ሁሉ ይጠላል
3. የጠፉትን ይፈልጋል

  kira
@ownkin
@cgfsd
ልመርቃችሁ ዝቅ በሉ...

ኢየሱስ ኢየሱስ እንዳላችሁ መሞት ይሁንላችሁ! እሱን ባከበራችሁት አፍ ስለእርሱ በተናገራችሁትና በዘመራችሁት አፍ ሌላን ነገር መዘባረቅ አይሁንላችሁ! ወደ እርሱ በሮጣችሁበት እግር ወደሌላው መገስገስ አይሁንላችሁ! ኢየሱስ ኢየሱስ ስትሉ ዘመናችሁ ይለቅ!
አሜን🙏😍
ቀና በሉ በቃ...!


Tsegaab-daniel

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ በእኛ ላይ ገኖ መታየት በሌላ ጎኑ የእኛ መሞት ነው ።ኢየሱስ በእኛ ላይ መገለጥ የእኛ መሸፈን ነው ።

@ownkin
@cgfsd
Audio
ታላቁ ሊቀካህናት ኢየሱስ !!!

እንዲህ ያለ ሊቀካህናት ተገብቶናል ። ከወርቅ ይቅል አብዝት የነጠረ ወድ የሆነ ሊቀካህናት ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ።


በፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመኖር የግድ ኢየሱስን ማየት አስፈላጊ ነው ምክኒያቱም የእግዚአብሔር ፈቃድ በሙላት የኖረው ኢየሱስ ብቻ ነው ።

(ኢየሱስን በማየት በእግዚአብሔር ፈቃድ መመላለስ)

@cgfsd
@ownkin
እነሆ የተሰቀለው ክርስቶስ! እነሆ ለሁሉ በመስቀል የተገለጠው እግዚአብሔር !! 'እነሆ ሰውየው!' [ዮሐ.19፥ 6]

እግዚአብሔር ለማዳን የተገለጠበትን መንገድ ማጤን ግድ ይለናል ይላል ማርቲን ሉተር ። የቅዱሳት መጻሕፍትን ታሪክ ፍሰት ማመሳከሪያ በማድረግ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ለማዳን [ሰውን ከጠፋበት መንገድ ለመመለስና ለመታረቅ] ሲገለጥ ልክና ወሰን የለሽ ክብሩን በማሳየት አይደለም፤ ይልቅኑ በተቃራኒው ነበር ይለናል።

ሐዋርያቱም በአደባባይ የሰበኩት 'ንጉሡንና ወሰን የለሽ ክብር የተጎናጸፈውን' አይደለም። የተሰቀለውን እንጂ። አዚማሞቹንም የገላቲያ ማሕበራት 'ክርስቶስ በክብሩ በፊታችሁ ተስሎ አልነበረም ወይ?' አልተባሉም። 'እንደ ተሰቀለ' ተባሉ እንጂ። የተሰቀለውን ማሳየት ይቻላል፤ በመስቀል የደከመውን መስበክ የቤተክርስቲያን ኃላፊነት ነው። ዓለም ሞኝነት ያለችውን የማዳንና የመታደግ መንገድ ቤተክርስቲያን ጥበቤ ነው ትላለች። በክብር #እስኪገለጥ ሞቱን ትመሰክራለች።

'እነሆ ንጉሥሽ' የተባለውን ካላየን ሲሉ 'ከምድር ከፍ ከፍ ስል ሁሉን ወደኔ እስባለሁ' ብሎ ነበር ክርስቶስ። እነሆ መስቀሉ ለሁሉ የሚታይበት መንገዱ ነበረና።

ነገር ግን ባለጠጎችና 'ጸጋ ሞል' ነን የሚሉቱ መስቀል ጠል ናቸው። መስቀል ጠሎች ደግሞ 'እነሆ አምላካችን' ቢሉም የሚያሳዩት ወርቃቸውንና ብራቸውን ነው። ይዋሻሉ፤ ዋሾ ናቸው። መስቀል የተሰወረባት ማሕበር 'እነሆኝ' ብትል ታዳጊውንና በመስቀል የሞተውን አዳኝ አታሳይም፤ ሌላ ክርስቶስን ካልሆነ በስተቀር።

ማኀበራትም ሁለት ናቸው:- አንደኛይቱ በዚህ ዓለም የቆሰለውን አዳኝ ሳያፍሩ- የሚመሰክሩና ፈለጉን የሚከተሉ ያሉባት ናት። ኹለተኛይቱ ግን እንደ ዓለም ሁሉ በመስቀል ሞቱ የሚያፍሩ ያሉባት ናት።

እና የ'እነኾኝ' ጥሪዎች 'እነኾኝ መስቀል' ካላሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጥበብ ይሰውራሉ። አጀንዳቸውም ሌላ ነው። ይኸው ነው።

#የተሰቀለው_ክርስቶሰ #የእግዚብሔር_ክርስቶስ #እግዚአብሔር_የሾመው_ንጉሥ


tegegn mulugeta

@ownkin
@cgfsd
በቃ መድህናችን እንዲህ ነው በመስቀል ላይ የተንጠለጠለ !!ተልዕኮው አድህኖት የነበረ በሰው ልብ፣ ያልታሰበው ግን በምክረ መለኮት የተበጀውን ታላቅ የሆነ የመስቀል ስራ ፈፀሞ በእጄ ያለን አዎ ጌታችን የተሰቀለው ነው በእርግጥም ነው ምንም የማናወላዳበት የማንዘነጋው የነፍስ ምስላችን ይሔው ነው ። እኛም መላልሰን ቤዛነቱን እንዘክራለን...ያ የተወጋው ጎኑ የተጠገንበትን፣ የፈሰሰው ደሙ የተሰማንበትን፣ በተቸነከረው እጁ ራሱ ቆርሶ ያጎረሰን ስጋ ሁሌ እንመለከታለን

መሲሁን ኢየሱስ እርሱ ዘወትር እንደተሰቀለ እንድናስብ መንፈስ ቅዱስ ይርዳን ።


@ownkin
@cgfsd
(ኢየሱስ ታዛዬ )


የጌታ ኢየሱስን ፍለጋ እንደመከተል ለልብ አንጀት የሚያደርስ ጥም ቆራጭ ህይወት ከወዴት ይገኛል ??
ኢየሱስ ምድር ላይ የረገጠ አንድ ተራ ሰው ብቻ አልነበረም መለኮትም እንጂ ። ምናልባት ባደገበት አውራጃ የማያውቁት ከማርያም ቤት የቀደመ በኩር ልጅ ብቻ አድርገው የሚመለከቱ አይጠፉም ሌሎችም ደግሞ በሙያው አናፂ የሆነ አንድ ወጣት የሚያደርጉት አይታጡም ።. አገልግሎቱን ሀ ብሎ ከዩሀንስ ጥምቀት በኋላ አስከትሎ ሲጀምር ነቢይ ፣መምህር ግፋ ቢል የአይሁድ የተበላሸ ፖለቲካ የሚያስተካክል መሲህ አድርገው ያስቡት ነበር ። እርሱ ግን ያነገበው ተልዕኮ ፣ የመጣበት መምጣት ፣ ራሱን ያስኬደበት ማስኬድ በእጅጉ አብዝቶ የብዙዎች ቀልብ ያሽፍታል ።

ኢየሱስ ታዛ ነው !!!! ታዛ መጠለያ ፣ መሸሸያ ፣መኖሪያ ፣ ማረፊያ የሚል ትርጓሜ አለው ። ጌታ ደቀመዛሙርቱን ወደራሱ ጠራቸው ይላል ቅዱስ ቃሉ ። በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ወደ ማንነቱ ጠራቸው እንደማለት ነው ። ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ሲጠራቸው እነሱን ለማኖር ወደሚሆን ቅንጡ ፣ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ፣ ቤተመንግስት ፣ ሰፋፋ ወዳለው ክፍሎች አይደለም ወደራሱ የጠራቸው ወደ እሱነቱ ወደ ክርስቶስነቱ ፣ ወደ አሳራፊቱ ነው የጠራቸው የሚያርፉት በኢየሱስ ላይ ነው ኑሮአቸው የተመሰረተው በእሱነቱ ላይ ነው ።

ደቀመዛሙርቱን ሲጠራቸው ሆድ ያዝ ያዝ የሚያረጉ አሉ የተባሉ ምግቦችን ሜኑ እያስነባባቸው አለነበረም ..ዲዘርት ፣አቢታይዘር ፣ስጋ ፣አትክልት እያማረጡ እንዲበሉት አልነበረም ።እሱ ግን የጠራቸው ወደ ማንነቱ ነበር የህይወት እንጀራ ወደ ሆነው ማንነቱ ቢበሉት ወደማያልቀው አንዴ አይደለም ዘላለም የሚያጠግብ ስጋው በመስቀል ላይ ቆርሶ ደሙን አፍስሶ እንኩ ብሉኝ ወዳለበት የህይወት ጥሪ የው የተጣራው ።

ደቀመዛሙርት ኢየሱስ ሲከተሉት በወቅቱ እስራኤል ላይ የፖለቲካ ስጋት ነበር ኑ ሲል ወታደር መድቦላቸው ከፖለቲካ ሊከላለከላቸው ከሞት ሊያስመልጣቸው ሳይሆን ራሱ ጠባቂ፣እረኛ ሊሆናቸው ህይወት፣ ትንሳኤ ሁኗቸው ሞት እንዲያሸንፉ ነበር ።

ታዛ ኢየሱስ ነው!!ማንነቱ መጠለያ !!በማንነቱ የተጠለልን ማንነቱ ጥላ የሆንነ ሰዎች ነን!!


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
(ለጌታ መቸኮል)


ችኩሉ ጴጥሮስ ......... ችኮላ መቸም ከሰው ልጅ አብራክ የተፈበረከ ባህሪ ነው ። የሰው ልጆች በሞላ የጋራ የሚያረገው ባህሪ ችኮላ አንዱ ነው ፤ ምን ለማለት ነው ጴጥሮስ ብቻ ችኩል ያደረገው ማን ነው ?? በእርግጥ ጴጥሮስ ችኩል ለመሆኑ መፀሀፍ ቅዱሳችን ገልጦ ያሳየን ሀቅ ነው ። አንዳንዴ የጴጥሮስ ችኮላ ሲያጠፋ ቢስተዋልም ግን መቸኮሉ ለጌታ ነው ። ለጌታ ነው የቸኮለው የሚያሰኙን አንድ ሁለት ብለን የምንጠቅሳቸው ስራዎቹ እናያለን ።
ምናልባትም ጌታን ከተከተሉት አስራ ሁለቱ ሐዋሪያት በእድሜ ገፋ ያለው እሱ ሳይሆን አይቀርም ቢሆንም ግን ያለው ትኩስነት ልጅ ነው እንዴ ያስብላል ።
ኢየሱስ ጴጥሮስ በተደጋጋሚ ገስጿታል በተደጋጋሚም ደግሞ በተቀራኒው ምላሽ ሰጥቶታል ግን አንድ ነገር ጴጥሮስ ላይ ይስተዋላል መቸኮል አዎ ግንም ደግሞ ለጌታ መቸኮል ።

የመፀሀፍ ቅዱስ አስተማሪዎች በጴጥሮስ ታሪክ ዙሪያ የተሰራውን አፈ ታሪካ እንዲህ ይናገራሉ " ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ድንጋይ ይዛችሁ ተከተሉኝ ይላል ሁሉም ትላልቅ ድንጋይ ይዛሉ ጴጥሮስ በተራው ጠጠር ይይዛል ረጅም ከተጓዙ በኋላ ትንሽ እንዲያርፉ ያረግ እና የያዙትን ድንጋይ ወደ ዳቦ ይይረዋል የሁሉም በያዙት ድንጋይ ልክ ትልልቅ ዳቦ(ድፎ ዳቦ) ሲሆን የጴጥሮስ ጠጠር ስለነበረች ዳቦ ቆሎ ትሆናለች ። ሁሉም ይበሉና ይጠግባሉ ጴጥሮስ ግን ያዝናል ከእንደገና ጌታ ድንጋይ ይዛችሁ ተከተሉ ይላል ሁሉም ስለጠገቡ በተራቸው አነስተኛ ጠጠር ይይዛሉ ጴጥሮስ ግን ትልቅ ይይዛል በኋላ ከተቀየረ ካሳ እንዲሆነው ከብዙ ጉዞ በኋላ ጌታ በሉ የያዛችሁት ድንጋይ ወርውሩ ይላቸዋል ይወረውራሉ ጴጥሮስ እንደተጨበቀው ሳይሆንለት ይቀራል ያዝናል ። "
(ልብ በሉ ይሔ ታሪክ ለማስተማር ብቻ የሰራ ነው )

ከዚህ አፈ ታሪክ ጠቅሰው ጴጥሮስ ችኩል ነው ይተላለፋል በርካቶች ይላሉ ጌታ ግን እንደዚህ የሚለው ይመስለኛል ጴጥሮስ ለኔ ነው የቸኮለው ።

3 ጊዜ የካደው ክህደት ካሃዲነቱ ትዝ ይለናል ጌታ ደግሞ ለመመለስ አብዝቶ ያነባውን እንባ ያስታውሳል ። የማልኮስ ጆሮ እንደቆረጠ እናስታውሳለን ጌታ ግን ለቤተክርስቲያን መሪነት ያየዋል ።

አጎል መቸኮል ሳይሆን ለጌታ መቸኮል ግን እንዴት ያስደስታል ስለ ጌታ ተልዕኮ ፣ ስለ ጌታ የልብ ሃሳብ መቸኮል ግን እንደምን ያረካል !!
እንደዚህ አይነት ችኮለ ይብዛልን ጌታን ከመውደድ፣ ለአካሉ ለቤተክርስቲያን ከማሰብ ፣ወንጌል ከማድረስ፣ ክርስቶስ እንደተቆረሰ እንደ እሱ ለሌሎች ለመቆረስ ይብዛልን።

ለጌታ መቸኮል


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
መስቀሌ በገዘፈብኝ ጊዜ ሁሉ መስቀልህን አሳየኝ ጌታዬ

jonny afework

@ownkin
@cgfsd