በክርስቶስ ( in christ)
697 subscribers
98 photos
34 videos
41 files
37 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
ራስህን ከፍለህ ኢየሱስ
በራስ ገዛኸኝ ኢየሱስ

ሊሊ

@ownkin
@cgfsd
Audio
Part 5
የሐዋሪያት ስራ ዳሰሳ

ሐዋሪያት ስራ 4:13-29

በፊሊሞን ነጋ

@cgfsd
@ownkin
#የጌታ ኢየሱስ ውልደት በመከራ የታጀበ ነበር ።


* በተወለደ ጊዜ የእንግዳ ማረፊያ ስለጠፋ በበረት(በግርግም)ተኛ ። ሉቃ 2:7

* ሔሮድስ ስለፈራ ሊገድለው አሰደደው ወደ ግብፅ ሸሸ (ማቴ 2:13)

* ከግብፅ ሲመለስ የሔሮድስ ልጅ ስለነገሰ በምሪት ወደ ገለሊ ወደ ናዝሬት እንዲሄድ ተደረገ ። (ማቴ 2:21-23)

  #በበረት በመከራም ህፃን ሁኖ ግን ኢየሱስ ጌታ ስለሆነ በመከራው መካከል ይመለካል !!

* መላዕክት አበሰሩ የሰማይ ሰራዊት ስለ ተወለደው ህፃን አመሰገኑ ክብር በአርያም ሰላም ለሰው ልጅ እያሉ (ማቴ 2:13-14)

* ሰባአ ሰገን በኮከብ ተመርተው መጡ ሰገዱለት ያላቸውን ወርቅ እጣ ስጦታ አድርገው ሰጡት ። (ማቴ2:10-11)


የበረቱ እንግዳ የአለም ባለቤት ነው !!

@ownkin
@cgfsd
በማዕበል በምትናጠዋ ጀልባ ላይ የተኛው ማነው? ኢየሱስ ወይስ ዮናስ? ኢየሱስ ከሆነ ይቀስቀስ! ዮናስ ከሆነ ግን #ይወርወር


ከገፅ የተወሰደ

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ላይብረሪ ነው ይጠናል !!

habte..silo

@ownkin
@cgfsd
ግን ምን አይነት ጌታ ይሁን ይሔ ኢየሱስ ??

  ኢየሱስ አሳ አጥማጆችን ጠርቶ የሰው አጥማጅ አረጋችኋለው አለ። የሚያጠምዱበት መረብ ሞቱ እና ትንሳኤው እንዲሆን የገዛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ ።


@ownkin
@cgfsd
በበረት አድረህ..ምድር ላይ ቆይተህ..መስቀል ላይ የዋልከው ኢየሱስ ልቤን፣ሀሳቤን፣ቀልቤን፣እኔነቴን ወስደከኸዋል ።

@cgfsd
@ownkin
ብዙዎች  ወዳጅነት መስርተው ከዛም  ሚስጥራቸውን ይከፋፈላሉ እግዚአብሔር ግን ሚስጥሩን አካፍሎ ነው ወዳጅነት የመሰረተው ።

   ሚስጥሩም ኢየሱስ ነው!!

@ownkin
@cgfsd
“ቤተክርስቲያን አለም ፊቷን ያዞረችባቸው ሰዎች ህብረት ሳትሆን ፊታቸውን በአለም ላይ ያዞሩ ሰዎች ህብረት ናት”

"ንቀነው እንጂ ንቆን የተለየነው የአለም ክብርም ይሁን ተድላ የለም"

"ሳናገኘው ቀርተን ሳይሆን ሳንገኝለት ቀርተን ያፈረስነው የአለም ኪዳን እልፍ ነው"

በኢየሱስ ቆፍጠን ያልን አለምን የካድን ህዝቦች ነን🫡


ከገፅ የተወሰደ
Haniel
@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ ብቻውን ነው ድል የነሳው ድሉ ግን የተቆጠረው ለእኛም ጭምር ነው ።

@ownkin
@cgfsd
በ1970 ዓ.ም በዚሁ ከተማ Wilmore - Asbury university ታላቅ መነቃቃት ሆኖ ነበር ይላሉ ታሪኩን የሚያውቁ ሰዎች። በወቅቱ ለ144 ሠዓታት የጸሎት፣ የዝማሬ፣ የቃል ትምህርትና የንስሓ ጊዜ እንደነበር ያስታውሳሉ። ከዚያም በኋላ ታላቅ የወንጌል ሥርጭት ተካሂዶ በርካታዎች ወደ ጌታ የመጡበት ጊዜ ነበር ይላሉ።

ባለፈው ረቡዕ ዕለት ጠዋት Feb. 8, 2023 በተለመደው የዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ጸሎት ወቅት (regular chapel) በHughes መታሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነበር የመንፈስ ቅዱስ እሳት በወጣት ተማሪዎች ውስጥ የተቀጣጠለው። ከጠዋቱ 10:00AM በተለመደው ሁኔታ አምልኮውን የሚመሩ ወጣቶች ለአገልግሎት ቆሙ። ማቆም ተሳናቸው። ሰዎች ያለቅሳሉ፣ ንስሓ ይገባሉ፣ አንዱ ሌላው ላይ እጁን እያኖረ ይጸልያል በቃ ቀጠለ። ዘመሩ፣ በየመሐሉ ጸለዩ፣ ቀጠሉ ቀጠሉ። ያልተገኙ ተማሪዎችና ፕሮፌሰሮች ተጨመሩ፣ የቤተ ክርስቲያን መጋቢዎች የሌላ ከተሞች አገልጋዮች ወደ አዳራሹ መግባት ጀመሩ። የሚገባ እንጂ የሚወጣ ሳይኖር መሸ። ነጋ፣ መሸ፣ ሌላም ቀን ነጋ ይኼው ዛሬ ሳምንት ሆኖታል። ❤️

ሰዎች ከተለያዩ ከተሞች ከተለያዩ ግዛቶች ይመጣሉ። ይቀጣጠላሉ። አንዱ ይሄዳል ሌላው ይመጣል… አንዱ ያለቅሳል፣ ሌላው ይደሰታል፣ … ሌላው ይመሰክራል፣ ሌላው ይንበረከካል፣ ሌላው ይያያዛል፣ ሌላው ይዘምራል፣ ሌላው እጁን ወደ ላይ ያነሳል፣ ሌላው ዝም ብሎ ይቀመጣል፣ ሌላው ይነሳና መድረክ ላይ ወጥቶ መልዕክት ያስደምጣል። የጊዜ ጉዳይ የሥራ ጉዳይ የሌክቸር ጉዳይ የሪሰርች ጉዳይ ማን ያስባል? “Lord I need you every hour I need you” ይላሉ። “Way maker, miracle worker, promise keeper” ይላሉ። የክፍል ጓደኞቼ ሲነግሩኝ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ነው። ነገ ሄጄ እስክሳተፍ ልቤ ቸኩሏል። 😲😲

ቤተ ክርስቲያን ትንቃ ትነቃቃም።

werkneh koyera

@ownkin
@cgfsd
መቼ ነበር ልገልፀው በማልችለው የእግዚአብሔር አብሮነት እያለቀስሁ በጉልበቴ የወደቅሁት?

መቼ ነበር ከተንበረከክሁበት መነሳት የሞት ያህል ከብዶኝ የነበረው?

መቼ ነበር ፍፁም በሆነ የእግዚአብሔር ፍቅር ልቤ የተሞላው?

መቼ ነበር . . .

የሰሞኑ የ Asbury University የመንፈስ ቅዱስ "እንቅስቃሴ" ራሴን እንዲህ እንድጠይቅ አስገድዶኝ ነበር: በእኔ ቁጥጥር ስር እንዳልሆነና በመፍጨርጨር እንደማላመጣው አውቃለሁ፣ ነገር ግን ምን ያህል የዚህ ንፋስ ርሃብተኛና ጥማተኛ ነኝ ብዬ ከመጠየቅ አልታቀብሁም::

ሰሞኑን በፖለቲካና በሃይማኖት በሰከርንበት ወቅት Asbury University ውስጥ ሰዎች በመንፈስ "ይሰክሩ" ነበር::

ክርስትና ከእግር ጥፍር እስከራስ ጠጉር ድረስ በዶክትሪን ጢም ብሎ መሞላት ብቻ ከሆነ How boring would it be. እንደዛ አይነት ክርስትና የሰው ጥበብ እንጂ የእግዚአብሔር ጥበብ የሚገለጥበት አይደለም:

What we missed is not theology as such but God - about whom our theology is all about.

እግዚአብሔር ሲፈቅድልን ብቻ የምንገባበት የላቀና የሰው እጅ ያልነገሰበት ሕይወት አለ: ከጅረቱ ስር ነፍሳችን በውሃ ጥም እንዳትሞት እግዚአብሔር ወደዛ ጅረት ያስገባን::

Yilu danu
@ownkin
@cgfsd
በጎቹ የበሉት ብቸኛ እረኛ ኢየሱስ ይባላል ።

  melos

@ownkin
@cgfsd
ከAsbury ሪቫይቫል 2023 ምን ተማርኩ?

1. Revival እግዚአብሔር በወደደው ጊዜና ቦታ ከወደዳቸው ሰዎች ጋር የሚሠራው ነገር መሆኑን ነው። እንደ እኔ ከየአገሮች የሥነ መለኮት ትምህርታቸውን ለመከታተል የመጡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ለሌላ የአገልግሎት ኃላፊነት ራሳቸውን የሚያዘጋጁ “አዋቂም ታዋቂም” የሆኑ ማስትሬታቸውን ዶክትሬታቸውን የሚያጠኑ ትጉሃን የሰሚነሪ ተማሪዎች ከመንገዱ ማዶ አሉ። አልፎአቸው ሄደና ከመንገዱ ወዲያ በሚገኙ “ገና ምናቸውንም አልለዩም” በሚባሉ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ሊሠሩ በመጡ ለግላጋ ወጣቶች መካከል ነው ይህንን ያልተጠበቀ እሳት ጌታ የጣለው። የኛ ጸሎት ትጋት ያመጣው፣ የኛ መንፈሳዊ ልምምድ ያስከተለው፣ የኔ ቅድስና ያወረደው፣ የኔ የስብከት ብቃት ያመጣው የሚል ተጠሪ ማንም እንዳይኖር አድርጓል። የተለየ ሰው እንዳይጠራ ሌላው ይቅርና የአንድ ቤተ እምነትም ብቻ (የሜቶዲስት የባፕቲስት) ምናምን እንዳይሆን ለአገርና ለዓለም እንዲሆን university ውስጥ ማድረጉን መረጠው የሚል ትምህርት አግኝቼበታለሁ።

2. እውነተኛ revival የመንፈሳዊ ረሃብና የመንፈሳዊ ጥማት ምላሽ መሆኑን ነው። መጠማት ጌታን ነው። መራብ ጽድቅን ነው። ሕልውናውን አብሮነቱን ራሱን ጌታን ነው። ያ ሲሆን ጌታ የሚሰጠው ምላሽ እንዲህ ያለ revival ነው። አሁን በአገሪቱ ያለውን አምላክ ጠል የክህደት አካሄድ፣ የሥነ ምግባር አንጻራዊነት፣ የግብረገብ ብልሽት የተጸየፉ ልቦች በዙሪያቸው እየሆነ ያለው ከንቱነት ያንገሸገሻቸው ጌታንና ክብሩን ብቻ የሚጠሙ ቃሉን የሚራቡ ፊቱን የሚፈልጉ በእውነት በመንፈስ ጌታን የሚያመልኩ ሰዎች የሚያገኙት ምላሽ ነው ሪቫይቫል። እንዲህ ያሉ ሰዎች የተጠሙትን የጌታን ክብር የሚያዩበት ቀን መቼና እንዴት እንደሆነ ባይታወቅም ጌታ ለእንዲህ ዓይነቶቹ ራሱን የሚገልጥ መሆኑን ተማርኩ። ማንም ይሁን የትም ይሁን ጉዳዩ ጌታንና ክብሩን የመጠማት የመራብም ጉዳይ ነው። የአንዳንድ ወጣቶችን ምስክርነት ስሰማ ከሪቫይቫሉ በፊት የምድረ በዳ ጥም ዓይነት ነገር ወጣቶቹ ውስጥ እንደነበር ተረድቻለሁ።

ጊዜ ሳገኝ እመለሳለሁ።

Workneh d.koyera