በክርስቶስ ( in christ)
694 subscribers
98 photos
34 videos
41 files
37 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
#ፀጋው በእምነት አድኖኝ ....
#ኢየሱስ ፅድቁን አልብሶኝ...
#ስለእኔ በአብ ፊት ታይቶ ....
#ፈፅሞታል ስራዬን ጨርሶ..
( ከማስታወሻዬ ማስታወሻ)

ከሰሞኑን በተደጋጋሚ የሰማኋቸውን የክርስቶስን የመዋጀት ስራ ላይ በማተኮር የተዘመሩን መዝሙሮች በማስታወሻዬ ፅፌ ነበር ።
................

( አስቴር አበበ)

#የአብን ቁጣ አበረድክልኝ #የቅጣቱን እጁን ተቀበልክልኝ #ለእኔ የተገባውን ሆኖ በአንተ ላይ #ሆንክልኝ ፅድቄ አብ ፊቱን እንዳይ
................
(ሰላም ደስታ)

#ፀጋው በእምነት አድኖኝ ....
#ኢየሱስ ፅድቁን አልብሶኝ...
#ስለእኔ በአብ ፊት ታይቶ ....
#ፈፅሞታል ስራዬን ጨርሶ..
..........

(ሰላም ደስታ)

........ #የበግ ደም አይደለም ያነፃኝ
#አብን እንዳየው ፀጋው ነው የረዳኝ

..............
(ህሊና ዳዊት )

#እኔም ኢየሱስን ለብሼ #አብ ፊት ሞገስ አገኘው !!
.................
(መስከረም ጌቱ)

#ኢየሱስ ያድናል #አዎን አድኖናል
ከፊት እየመራ 😍
ወደ ፅዮን ያደርሰናል

..............
(ዘመናይ ጎሳዬ)

#አባትነት ከሚሰየምበት #ከአብ ፊት እንበረከካለሁ #በልጁ ለሚያየኝ የልቤን አስታወቀዋለሁ
...................
( አዲሱ ወርቁ )

#እኔ በበኩሌ ከእኔ ነው የምለው
ምንም ታሪክ የለኝ
#በመስቀል ላይ ሁኖ ተጠማሁኝ
ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ

.........................
(በረከት መገርሳ)

#ከህይወቱ ብዙ መማሬ ሳያንሰኝ
#ትንሳኤ ድጋሚ ወደድኩት አነፀኝ
አቤት የኔ ረቡኒ .....

@ownkin
@cgfsd
#ከአባቱ እቅፍ እሰከ #አባቱ ቀኝ ያለው ርቀት በትኩረት ሲታይ #ሰው የሆነው #ስጋ የለበሰው ላይመለስ ለዘላለም ነው #በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ #ሳይቆጥር እንደተጣለ #ራሱን ባዶ ባዶ አድርጎ #ባሪያ መስሎ ወርዶ ወርዶ #ከፍ ከፍ አረገው አባቱ #ከስም ሁሉ በላይ ስም ሰጠው #የእኔ ነው የእኔ ነው የምለው #ኢየሱስ ብቸኛ ጌታ ነው ።


(በረከት ደጀኔ)
#ቀራንዬን ሳስብ ያንተን ነገር #ደግሞም ጎልጎታን ያን መቃብር #ይህ ሁሉ ለእኔ ነው ብዬ እልና #እባርክሃለሁ እንደገና#ከፍ አረግሃለሁ በምስጋና #ምወድህ ምክኒያት ኑሮኝ ነው #ኢየሱስ ማነባው የገባኝ ገብቶኝ ነው የማለቅሰው ...
(#ኢየሱስን መውደድ)

ሕይወት ማለት #ኢየሱስን መውደድ ነው

#ኢየሱስ እንደምንወደው መንገር ብቻ ሳይሆን መወደዱን ማየት ይፈልጋል... እንደተወደደ እንዲሰማው ይሻል

#ኢየሱስን የሚወድ ሰው እነዚህ ምልክቶች ይታዩበታል

1. ልዩ ትኩረት እና ልዩ መሰጠት #ለኢየሱስ ይሰጣል
2. አለምን እና ስራዋን ሁሉ ይጠላል
3. የጠፉትን ይፈልጋል

  kira
@ownkin
@cgfsd
#ሩጫ ሲበዛ ባክኜ እንዳልቀር #በማርታ ዘመን ላይ እንደ ማርያም ልኖር #ኢየሱስ አንተ ላይ እደላደላለሁ #መድኔ አንተ ጋር አብዝቼ ቆያለሁ

@ownkin
@cgfsd
ዉዴ ለእኔ ያለዉን የፍቅር መግለጫ የጻፈው በስጋና በደሙ ቀራኒዮ ነበር ፍቅሩ ደግሞ ከመቃብር በላይ ነው።

#ኢየሱስ

sharona

@ownkin
@cgfsd
ለዘላለም እንጂ ለዛሬ አልሰራም #ስለ ህይወት እንጂ ለመበል አልሰራም #ኢየሱስ እውነቴን መቼ አላስነካም።

🎼

@ownkin
@cgfsd
የመስቀሉን ሊሻን አርገን #የደሙን ሀብል አጥልቀን #በቀዩ ምንጣፍ ላይ በእምነት #ተራምደን ገብተናል ገነት #ድል ነስቶ ድል አልብሶናል #ኢየሱስ ማዕረግ ሁኖናል ።



🎼
@cgfsd
@ownkin
#ኢየሱስ -በምድር በነበረበት ዘመን አለመኖሬ ኢየሱስ እንዲያመልጠኝ አላደረገኝም....በምድር አይኑር እንጂ እሱ ወዳለበት መንፈስ ቅዱስ አድርሶኛል......እርሱ ካልገለጠልን በቀር ኢየሱስን ማወቅም መንካትም አንችልም 😇😘

Ariel

@ownkin
@cgfsd
እንጀራ ልንበላ አልተከተልህም ሀብት ብልጥግና ወደ አንተ አልጠራንም #ለምድር በረከት ታይቶ ለሚጠፋው #መች ደምህ ፈሰሰ ለሚያልፍ ተስፋ #የዘላለም ህይወት ማግኘታችን ጉዳይ ሁሌ ብርቃችን ነው #ህይወት ያካፈልከን #ኢየሱስ አንተ ነህ #ሌላ አላየንም በነፍሱ የጨከነ ...


🎼 መስኪ

@ownkin
@cgfsd
( ከማስታወሻዬ ማስታወሻ)

ከሰሞኑን በተደጋጋሚ የሰማኋቸውን የክርስቶስን የመዋጀት ስራ  ላይ በማተኮር የተዘመሩን መዝሙሮች  በማስታወሻዬ ፅፌ ነበር ።
    ................

    ( አስቴር አበበ)

#የአብን ቁጣ አበረድክልኝ #የቅጣቱን እጁን ተቀበልክልኝ #ለእኔ የተገባውን ሆኖ በአንተ ላይ #ሆንክልኝ ፅድቄ አብ ፊቱን እንዳይ
        ................
        (ሰላም ደስታ)

#ፀጋው በእምነት አድኖኝ ....
#ኢየሱስ ፅድቁን አልብሶኝ...
#ስለእኔ በአብ ፊት ታይቶ ....
#ፈፅሞታል ስራዬን ጨርሶ..
            ..........
       
           (ሰላም ደስታ)

........ #የበግ ደም አይደለም ያነፃኝ
#አብን እንዳየው ፀጋው ነው የረዳኝ

              ..............
         (ህሊና ዳዊት )

#እኔም ኢየሱስን ለብሼ #አብ ፊት ሞገስ አገኘው !!
       .................
          ( ታምራት ሃይሌ)

በዛ ታሪካዊ መስቀል ላይ
ዘምር ዘምር አለኝ የሰራልኝ ሳይ
  
       ..............
(ፀጋዬ)

እዩት ኢየሱስን መስቀሉ ማማሩ
ለተመራመረው ብዙ ነው ሚስጥሩ

                ...................
           ( አዲሱ ወርቁ )

#እኔ በበኩሌ ከእኔ ነው የምለው
         ምንም ታሪክ የለኝ
#በመስቀል ላይ ሁኖ ተጠማሁኝ                    
         ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ

.........................
           (በረከት መገርሳ)

#ከህይወቱ ብዙ መማሬ ሳያንሰኝ
#ትንሳኤ ድጋሚ ወደድኩት አነፀኝ
     አቤት የኔ ረቡኒ .....

@ownkin
@cgfsd
( #ኢየሱስ እውነተኛ የሰው ልጅ )



ወደ ከተማዋ መግቢያ በር ሲደርስም፣ እነሆ፤ ሰዎች የአንድ ሰው አስከሬን ተሸክመው ከከተማዋ ወጡ፤ ሟቹም ለእናቱ አንድ ልጅ ብቻ ነበር፤ እናቱም መበለት ነበረች፤ ብዙ የከተማውም ሕዝብ ከእርሷ ጋር ነበረ።  ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፣ “አይዞሽ፤ አታልቅሺ” አላት።
ሉቃስ 7:12-13


ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረብ ከተማዋን አይቶ አለቀሰላት፤  እንዲህም አለ፤ “ሰላምሽ የሚሆነውን ምነው አንቺ ዛሬ በተረዳሽ ኖሮ! አሁን ግን ከዐይንሽ ተሰውሮአል፤ ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሠርተው፣ ከየአቅጣጫውም ከበው አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣልና፤”
ሉቃስ 19:41-43

ኢየሱስም እርሷ ስታለቅስ፣ ተከትለዋትም የመጡት አይሁድም ሲያለቅሱ ባየ ጊዜ መንፈሱ በኀዘን ታውኮ፣  “የት ነው ያኖራችሁት?” ሲል ጠየቀ።
እነርሱም፣ “ጌታ ሆይ፤ መጥተህ እይ” አሉት።
ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።
አይሁድም፣ “እንዴት ይወደው እንደ ነበር አያችሁ” አሉ።
ዮሐንስ 11:33-36

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አድርጎ እንዲህ አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ፤ አባት ሆይ፤ ይህን ሁሉ ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን፣ አባት ሆይ፤ ይህ የአንተ በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።”
ሉቃስ 10:21


#ኢየሱስ እውነትም የሰው ልጅ በመሆኑ ለሰዎች ሁሉ እውነተኛ ወገን ሁኗል ። በምድር በነበረበት ጊዜ የሰዎችን ደስታ እና ሀዘን ይጋራል ። ከልቡ ደስ ይለዋል ፣ ከልቡም ያዝናል ።  ራሱን ከህዝቡ መካከል አርቆ አይመለከትም፤ ራሱን የሰው ልጅ እያለም ይጣራ ነበር ። አብሮአቸው ይራባል ፣ አብሮአቸው ይበላል ፣ አብሮአቸው ሰርግ ይታደማል ፤ ትልቅ ማንነቱ ከእነርሱ ጋር እንዳይሆን አልከለለውም ፣  አምላክነቱ አብሮ ችግራቸውን እንዳይከፈል አልገደበውም ። ኢየሱስ የሰው ልጅ መስሎ አልነበረም በምድር ቆይታው ያለፈው እውነተኛ የሰው ልጅ ሁኖ ነው ያለፈው ።

@cgfsd
@ownkin
(ክርስቶስ በየትኛው ልብ ውስጥ የሚኖረው ?)


#በክርስቶስ ደም በተረጨ ልብ ውስጥ

#በመንፈስ ቅዱስ በኩል የእግዚአብሔር ፍቅር በፈሰሰበት ልብ ውስጥ

#የእግዚአብሔር ታላቅ ምህረት ያረፈበት ልብ ውስጥ

#ክርስቶስ ኢየሱስ ይመጣል በሚል ግሩም ተስፋ በተሞላ ልብ ውስጥ

#በእግዚአብሔር የህልውና መአዛ በታወደ ፤ በታጠነ ልብ ውስጥ

#ኢየሱስ የሚለውን ስም ሁልጊዜ እንዲጠራ ፈቃድ በሰጠው ልብ ውስጥ

#ክርስቶስ ኢየሱስ  በራሱ ለራሱ በዋጀው ልብ ውስጥ


        ክርስቶስ ኢየሱስ የሚኖርበት ልብ ራሱ ክርስቶስ ባፈሰሰው ደም የደመቀ፣ በቅዱስ መንፈሱ የተዋበ፣ በጥልቅ ፍቅሩ ያሸበረቀ ፣ በድንቅ ስሙ ያበራ፣ በአስደናቂው ፀጋ የተጥለቀለቀ፣ በተባረከው ተስፋ ኢየሱስ በኩል የታወደ፣ ውድ በሆነው ምህረቱ የሚያብረቀርቅ ልብ ውስጥ ክርስቶስ ይኖረናል ።

     " ኢየሱስ ሌላ ምንም አላለንም ደም ባፈሰስኩበት ልብ ውስጥ ልኑር "

@cgfsd
@ownkin