በክርስቶስ ( in christ)
694 subscribers
98 photos
34 videos
41 files
37 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
እነሆ የተሰቀለው ክርስቶስ! እነሆ ለሁሉ በመስቀል የተገለጠው እግዚአብሔር !! 'እነሆ ሰውየው!' [ዮሐ.19፥ 6]

እግዚአብሔር ለማዳን የተገለጠበትን መንገድ ማጤን ግድ ይለናል ይላል ማርቲን ሉተር ። የቅዱሳት መጻሕፍትን ታሪክ ፍሰት ማመሳከሪያ በማድረግ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ለማዳን [ሰውን ከጠፋበት መንገድ ለመመለስና ለመታረቅ] ሲገለጥ ልክና ወሰን የለሽ ክብሩን በማሳየት አይደለም፤ ይልቅኑ በተቃራኒው ነበር ይለናል።

ሐዋርያቱም በአደባባይ የሰበኩት 'ንጉሡንና ወሰን የለሽ ክብር የተጎናጸፈውን' አይደለም። የተሰቀለውን እንጂ። አዚማሞቹንም የገላቲያ ማሕበራት 'ክርስቶስ በክብሩ በፊታችሁ ተስሎ አልነበረም ወይ?' አልተባሉም። 'እንደ ተሰቀለ' ተባሉ እንጂ። የተሰቀለውን ማሳየት ይቻላል፤ በመስቀል የደከመውን መስበክ የቤተክርስቲያን ኃላፊነት ነው። ዓለም ሞኝነት ያለችውን የማዳንና የመታደግ መንገድ ቤተክርስቲያን ጥበቤ ነው ትላለች። በክብር #እስኪገለጥ ሞቱን ትመሰክራለች።

'እነሆ ንጉሥሽ' የተባለውን ካላየን ሲሉ 'ከምድር ከፍ ከፍ ስል ሁሉን ወደኔ እስባለሁ' ብሎ ነበር ክርስቶስ። እነሆ መስቀሉ ለሁሉ የሚታይበት መንገዱ ነበረና።

ነገር ግን ባለጠጎችና 'ጸጋ ሞል' ነን የሚሉቱ መስቀል ጠል ናቸው። መስቀል ጠሎች ደግሞ 'እነሆ አምላካችን' ቢሉም የሚያሳዩት ወርቃቸውንና ብራቸውን ነው። ይዋሻሉ፤ ዋሾ ናቸው። መስቀል የተሰወረባት ማሕበር 'እነሆኝ' ብትል ታዳጊውንና በመስቀል የሞተውን አዳኝ አታሳይም፤ ሌላ ክርስቶስን ካልሆነ በስተቀር።

ማኀበራትም ሁለት ናቸው:- አንደኛይቱ በዚህ ዓለም የቆሰለውን አዳኝ ሳያፍሩ- የሚመሰክሩና ፈለጉን የሚከተሉ ያሉባት ናት። ኹለተኛይቱ ግን እንደ ዓለም ሁሉ በመስቀል ሞቱ የሚያፍሩ ያሉባት ናት።

እና የ'እነኾኝ' ጥሪዎች 'እነኾኝ መስቀል' ካላሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጥበብ ይሰውራሉ። አጀንዳቸውም ሌላ ነው። ይኸው ነው።

#የተሰቀለው_ክርስቶሰ #የእግዚብሔር_ክርስቶስ #እግዚአብሔር_የሾመው_ንጉሥ


tegegn mulugeta

@ownkin
@cgfsd