Dawit Dreams Official
22.5K subscribers
2.31K photos
41 videos
1 file
740 links
Dawit DREAMS Official Channel
Download Telegram
ማንያዘዋል እሸቱ በድንቅ ኢነርጂ ወደ ዳዊት ድሪምስ በመምጣት ያለህን በሙሉነት ስለሰጠኸን እና መንፈሳዊ አካላችንን ስላስታወስከን እጅግ በጣም እናመሰግናለን ክብረት ያድልልን።

ድንቅ የዳዊት ድሪምስ ቤተሰቦች ድንቅ ቆይታን ከማንያዘዋል ጋር ነበረን በቀጣይ ሳምንት በድንቅ እንግዳ እንጠብቃችኋለን። ያመለጣችሁን እንግዳ በ DAWIT DREAMS You Tube ቻናል ላይ ያገኙታል።
አራቱ የለውጥ ደረጃዎች
፫ ግጭት የለውጥ ደረጃ

ግጭት የለውጥ ደረጃ ወደ ሕልምህ የሚወስድህ ልዩ የለውጥ ደረጃ ነው። በማሰብ የለውጥ ደረጃ፣ በንቁ አዕምሮህ የምታስበው ድንቅ ሀሳብ በተደጋጋሚ በተራ ፓራዳይምህ ቢሸነፍም፣ ወደዚህ የግጭት የለውጥ ደረጃ ያደርስሀል። ነገር ግን በግጭት የለውጥ ደረጃም የድሮ ተራ ፓራዳይምህን የምታሽንፈው፣ በንቁ አዕምሮህ በምታስበው ድንቅ ሀሳብ ነው። አሁን የፓራዳይምን ተጽዕኖ በትክክል በመረዳት፣ በንቁ አዕምሮህ አሁን እያገኘህ ያለኸውን የማትፈልገውን ተራ ውጤት በመዝጋት፣ ስለምትፈልገው ውጤት ብቻ በማሰብ፣ በዚሁ ግጭት የለውጥ ደረጃ፣ ድንቅ ለውጥ ማምጣት ትችላለህ። የፓራዳይምን ትግል አልፈህ፣ አምስቱን የስሜት ህዋሶች ዘግተህ፣ በስድስቱ የአዕምሮ መሣሪያዎችህ የምትፈልገውን ውጤት ማሰብና መፍጠርህን በትግስትና በትኩረት ስትቀጥል፣ በድብቁ አዕምሮህ ድንቅ ፓራዳይም መገንባት ትጀምራለህ። ይህ ድንቅ ፓራዳይም ደግሞ በድብቁ አዕምሮህ ካለው ተራ ፓራዳይም ጋር ጦርነት ይከፍታል።

የግጭት የለውጥ ደረጃ ውስጥ የምትገባው፣ አዲስ የተፈጠረው ድንቅ ፓራዳይምህ፣ ከድሮው ተራ ፓራዳይምህ ጋር ሲጋጭ ነው። አዲሱ ፓራዳይም የድሮ ፓራዳይምህን ካሸነፈው፣ ወደ ነጻነት ሕይወት ትገባለህ፤ የድሮው ፓራዳይም አዲሱን ፓራዳይም ካሸነፈው ግን፣ ወደ ባርነት ሕይወት ትመለሳለህ።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ
ድንቅ የሆነ ቀን

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial
ዛሬ ሀሙስ ሰኔ 23/2014 ከ 11:30 ጀምሮ ዳዊት ድሪምስ ድንቅ በሆነ ልዮ ርዕሰ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ሊሰጠን ተዘጋጅቷል፣ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ማንም እንዳይቀር.

መግቢያ 100 ብር
አድራሻ:- 22 ባታ ኮምፕሌክስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ድሪምስ ሲኒማ


የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial
https://t.me/DawitDreamsTelegram
፬ ነጻነት የለውጥ ደረጃ

“የሰው ልጆች የተፈጠርነው ሁሉንም ፈተናዎች በማሸነፍ የነጻነት እና የበረከት ሕይወት እንድንኖር ነው”

በሕይወትህ የሚያጋጥምህን ማንኛውም አይነት ፍራቻ በመለየት፣ በጥንቃቄ ካጠናኸው፣ ከተረዳኸውና ፊት ለፊት ገጥመህ ከተጋፈጥከው፣ ፍራቻን አሸንፈህ ወደ ነጻነት ትገባለህ። የነጻነት ሕይወት ደግሞ በጣም ደስ ይላል።

ሕይወቴን ለመቀየር ራሴን እየቀየርኩ ነው። ራሴን በመቀየር ሕይወቴን ስቀይርና ሕልሜን ሳሳካ ደግሞ፣ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ። ነገር ግን መቼም አልረካም። ምክንያቱም በመጀመሪያ ሕልሜ ሲሳካ፣ ሕይወቴንና የቤተሰቤን ሕይወት ቀይሬያለሁ። በዚህ ሳልረካ ግን፣ የተሻለ ሕልም በማስቀመጥ እና በማሳካት፣ በአገሬ ላይ ለውጥ በማምጣት ወገኖቼን እየረዳሁ ነው።

እኔ እያለሁ ለምንድን ነው ከሌላ አገር የመጡ ሰዎች አገሬን እስኪቀይሩና ወገኖቼን እስኪረዱ የምጠብቀው? በአገር ደረጃ ለውጥ ስናመጣ፣ ልባችን በደስታና በምስጋና ይሞላል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን አንረካም። በአፍሪካ ያሉ አገሮችን ለመርዳትና በዓለም ላይ ታሪክ ለመስራት ትልቅ ሕልም በማስቀመጥ፣ መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት በመክፈል፣ በዓለማችን ላይ ታሪክ እንጽፋለን። በዚሁ መንገድ ማደግና ራሳችንን መቀየር ስንችል ደግሞ፣ የት መድረስና ምን አይነት ተዓምር መፍጠር እንደምንችል፣ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ
ድንቅ የሆነ ቀን

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial
Dear Family,

Today, more than anyother day, Please remember to be happy, Joyful, pleasant, mindful, successful, conscious and and to live inside-out.

Stay blessed,

Dawit Dreams.
ውድ ቤተሰቦቼ

ዛሬ፣ ከማንኛውም ቀን በላይ፣ እባክዎን ደስተኛ፣ አስደሳች፣ አስተዋይ፣ ስኬታማ፣ ንቃተ ህሊና እና ከውስጥ ወደ ውጪ መኖርን ያስታውሱ።

ድንቅ የተባረከ ቀን

ዳዊት ድሪምስ.
ድንቅ አመለካከት

ህይወትህ የሚቀየረው ድንቅ አመለካከት ሲኖርህ ነው። በሕይወትህ ድንቅ አመለካከት እንዲኖርህ፣ በመጀመሪያ በንቁ አዕምሮህ ድንቅ ሀሳቦችን አስብ። በመቀጠልም በድብቁ አዕምሮህ ድንቅ ስሜቶችና ድንቅ እምነቶችን ገንባ። በሥጋዊ አካልህ ድንቅ የሆኑ ድርጊቶችን በመውሰድና አዳዲስ ልማዶችን በማዳበር፣ መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት ያለ ምንም ድርድር ክፈል። በአካባቢህ የምትፈልጋቸው ፈተናዎች፣ ችግሮች እና እንቅፋቶች ሲያጋጥሙህ ስለነዚህ ነገሮች በጭራሽ አትጨነቅ። ችግሮችና ፈተናዎች ሲያጋጥሙህ ማድረግ ያለብህ፣ በንቁ አዕምሮህ ችግሮቹንና ፈተናዎቹን መመልከት፣ ድንቅ የሆኑ መፍትሄዎችን መፍጠርና መፈለግ የሚያስችሉህን ዘዴዎች ማሰብ ነው። በንቁ አዕምሮህ በተደጋጋሚ የምታስበው ማንኛውም ሀሳብ ወደ ውጤትነት መቀየሩ ስለማይቀር፣ ስለ ችግሮችህ ሳይሆን ስለ ድንቅ መፍትሄዎቻቸው ብቻ አስብ።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ.
ድንቅ ምሽት ተመኘን

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial
https://t.me/DawitDreamsTelegram
ሀሳብ

"አሁን ያለህ አመለካከት ድንቅ ነው ወይስ ተራ"? ይህንን የምትፈትሽበት የመጀመሪያው ደረጃ ሀሳቦችህን በመፈተሽ ነው። ሰሞኑን ያሰብካቸውን ሀሳቦች ሰከን ብለህ ስትፈትሻቸው፣ ድንቅ ናቸው ወይስ ተራ?

ድንቅ ሕይወት መኖር ከፈለግክ፣ በንቁ አዕምሮህ ስለ ትልቁ ሕልምህ እና ሕልምህን ስለምታሳካበት መንገድ ብቻ አስብ። በዚህ መንገድ ማሰብህን ስትቀጥል፣ ንቁ አዕምሮህ ሕልሙን ማሳካት ወደሚችል ንቁ አዕምሮነት ስለሚቀየር፣ ሙሉ ሕይወትህ ይቀየራል። እንደዚህ ስታደርግ፣ ነገሮች ሁሌም አልጋ በአልጋ ይሆናሉ ወይም ፈተናዎች እና ችግሮች አያጋጥሙህም ማለት አይደለም። በሕይወትህ ስለሚያጋጥሙህ ችግሮች ደጋግመህ ካሰብክ፣ የባሱ ችግሮች ነው የሚጨመሩልህ። ስለዚህ ማሰብ ያለብህ በሕይወትህ ውስጥ ስላሉ ችግሮች ሳይሆን ስለ ችግሮቹ መፍትሄዎች ብቻ ነው። በንቁ አዕምሮህ ለነዚህ ችግሮች መፍትሔ የሚሆኑ ሀሳቦችን ፈልግ፤ ፍጠር፤ ተቀበል፤ እንዲሁም በተደጋጋሚ አስብ።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.

መልካም ቀን

የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
የማክሰኞ እንግዶች
የሰኔ ወር የመጨረሻ እንግዶች ትዕግስት ዋልተንጉስ እና ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ የማክሰኞ ሰኔ 28/2014 እንግዳችን ናቸው፣ ከ 11፡00 ጀምሮ በ22 ማዞሪያ ባታ ኮምፕሌክስ 3ኛ ፎቅ ላይ ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ምግብ ሊመግቡን ተዘጋጅተዋል። ይህን ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ለመታደም ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ማንም እንዳይቀር።

መግቢያ በነፃ

ለበለጠ መረጃ በ +251938252525 ይደውሉ። ያመለጣችሁን እንግዳ በ Dawit Dreams You Tube channel ላይ በመግባት ታገኙታላችሁ።

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial
ድንቆች እና ዕድለኞች ነን!

በፈጣሪ ምስል የተፈጠረው የአዕምሯችን የማሰብና የመፍጠር ክህሎት ነው። ብዙ ሰዎች ተመራማሪዎች፣ አርቲስቶች፣ ደራሲዎች ወይም ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ድንቅ ስራዎችን ሲሰሩ በጣም ይደነቁና "እነሱ ዕድለኞች ናቸው፣ የፈለጉትን ነገር ያደርጋሉ፤ እኔ ግን ምስኪን ነኝ" ብለው ሊያስቡም ይችላሉ። እውነቱ ግን ሁላችንም ድንቆችና ዕድለኞች ነን። ጥያቄው፣ ዕድላችንን የእውነት እየተጠቀምንበት ነው ወይስ አይደለም?" የሚለው ነው። እኛ የሰው ልጆች፣ አፈጣጠራችንን ስንመለከት፣ ያለን ልዮነት ከውስጥ ሳይሆን ከውጪ ብቻ ነው። ወደ ውስጣችን ስንመለከት፣ እያንዳንዳችን መቶ ቢልየን ኒውሮኖች እና ሌሎች ለቁጥር የሚታክቱ ተዓምራዊ አወቃቀሮች ያሉን ድንቅ የፈጣሪ ልጆች ነን።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.

     ድንቅ ምሽት🙏

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
ምሁርነት

ምሁር የሚባለው ሰው፤ ፊደል መቁጠር የቻለ ሰው ብቻ አይደለም። ድንቅ የክፍለ ዘመናችን ምሁር፣ የአዕምሮ መሣሪያዎቹን በመጠቀም፣ የሌሎች ሰዎችን መብት ሳይነካ፣ የሚፈልገውን ውጤት ማግኘት የሚችል ሰው ነው። በሕይወታችን ከሚገጥሙን የመሀይምነት ችግሮች በመውጣት ወደ ነፃነት ሕይወት ለመግባት፣ የሚያስፈልገን ዐብይ ጉዳይ "ትክክለኛ ዕውቀት ነው" ትክክለኛውን እና እውነተኛውን ዕውቀት ማወቅ መረዳትና መጠቀም ስንችል፣ ከማንኛውም የመሀይም እና የፓራዳይም እስር ቤት ነፃ መውጣት እንችላለን፣ ስለዚህ የክፍለ ዘመናችን ምሁር፣ በሕይወቱ የሚፈልገውን ውጤት ለማግኘት ጠቃሚ የሆነውን ዕውቀት የሚያውቅ የሚረዳና የሚጠቀም ነው።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
ኢትዮጵያን እና አፍሪካን እየቀየርኩ ነው!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ.
     መልካም ምሽት

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsTelegram
እንዲሁም ለአዲሱ 30ኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ +251938252525 በመደወል ይመዝገቡ
ተመስገን ዛሬ ከራሴ ጋር መሀላ ገብቻለሁ። 🖐🖐🖐
ትልቁ ህልሜ እስኪሳካ ከህልሜ ጋር ተጣብቄያለሁ። ሁሉንም የውስጥ ሀብቴን አውጥቼአለሁ። እምነቴ ሁሌም ከስበት ህግ ጋር አንድ ነው፤ ተገጣጥሟል። ሀሳቤ፣ስሜቴ፣ደስታዬ፣እምነቴ፣መንፈሴ፣እንቅስቃሴዬ ወደ ትልቁ ህልሜ ዘወትር ያመራል። ለትልቁ ህልሜ የሚያስፈልገኝ ሁሉ እዚህ አለ። የእኔ ስራ ማገጣጠም ብቻ ነው። በውስጤ ሰላምና መረጋጋት አለ። በጣም ደስተኛ ነኝ። ፊቴና መላ ሰውነቴ በደስታ ተሞልቷል። ትልቁ ህልሜ የእኔ ሆኗል።

ተመስገን!! ድንቅ፣ በስኬት የተሞላ፣ በማስተዋል በጥበብ የታጠረ ቀን ተመኘሁ!!!
የማክሰኞ እንግዶች
የሰኔ ወር የመጨረሻ እንግዶች ትዕግስት ዋልተንጉስ እና ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ የማክሰኞ ሰኔ 28/2014 እንግዳችን ናቸው፣ ከ 11፡00 ጀምሮ በ22 ማዞሪያ ባታ ኮምፕሌክስ 3ኛ ፎቅ ላይ ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ምግብ ሊመግቡን ተዘጋጅተዋል። ይህን ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ለመታደም ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ማንም እንዳይቀር።

መግቢያ በነፃ

ለበለጠ መረጃ በ +251938252525 ይደውሉ። ያመለጣችሁን እንግዳ በ Dawit Dreams You Tube channel ላይ በመግባት ታገኙታላችሁ።

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial