Dawit Dreams Official
22.9K subscribers
2.35K photos
43 videos
1 file
751 links
Dawit DREAMS Official Channel
Download Telegram
Follow our Facebook page
Channel name was changed to «Dawit Dreams Official»
መሀይም ስለሆንን ነው የፈለግነውን ውጤት የማናገኘው!

የምትፈልገውን ውጤት የምታገኝበትን ምስጢር ካላወቅክ፣ የፈለግከውን ውጤት ማግኘት ይከብድሀል። አስቀድመን ስለመሀይምነት ትርጉም ስንነጋገር እንዳነሳነው፣ መሀይምነት ማለት፣ ነገሮችን የማከናወኛ ምስጢርን አለማወቅ ነው። በዚህም በርካታ ሰዎች መሀይም ናቸው። ቀለም ለቆጠርነው እንኳ፣ እንዴት አድርገን ትልቅ ሕልም በማስቀመጥ፣ ሕይወታችንን መቀየር እንዳለብን፣ ትምህርት ቤቶቻችን አላስተማሩንም። ሕልሙን የሚያሳካበትን ምስጢር ያላወቀ ሰው፣ ስለ ትልቅ ሕልሙና ሕልሙን ማሳካት ስለሚችልበት መንገድ ሲያስብ ይጠራጠራል፤ ይፈራል፤ ይጨነቃል፤ ደግሞም ተስፋ ይቆርጣል። ሕልሙን የሚያሳካበትን ምስጢር ተምሮ መሀይምነቱን ሲያሸንፍ ግን፣ የማንንም ሰው መብት ሳይነካ፣ ትልቁን ሕልሙን በማሳካት የሚፈልገውን ሕይወት መኖር ይጀምራል።

ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
መልካም ቀን ተመኘን!
አሁኑኑ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
ዛሬ ሀሙስ ሰኔ 16/2014 ዳዊት ድሪምስ ድንቅ በሆነ ልዮ ርዕሰ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ሊሰጠን ተዘጋጅቷል፣ እናንተስ ይሄን ድንቅ የአዕምሮ ምግብ ለመታደም ዝግጁ ናችሁ?

መግቢያ 100 ብር
አድራሻ:- 22 ባታ ኮምፕሌክስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ድሪምስ ሲኒማ በመገኘት ይሄን ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ምግብ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
Dawit Dreams Official:
https://t.me/DawitDreamsOfficial 🤏ይህን አዲሱን የዳዊት ድሪምስ /Dawit Dreams public/ግሩፕ በመቀላቀል ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ምግብ ይወያዮ
እንዲሁም፣
https://t.me/DawitDreamsTelegram 🤏 አዲሱን የዳዊት ድሪምስ/Dawit Dreams official/ ቻናላችንን በመቀላቀል ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በአዳዲስ ምስሎች እና መልዕክቶች በትኩሱ ይከታተሉን።
Forwarded from ABRSH ALIVE (Abrsh)
ውሳኔ 4
መንፈሳዊነት
ከስጋዊና ቁሳዊ ነገሮች በመሻገር፣ መንፈሳዊነትን በመላበስ ራስህንና ቤተሰብህን ብቻ ሳይሆን፣ አገርህንና ዓለምን ለመቀየር ወስን።

ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
መልካም ምሽት ተመኘን!
አሁኑኑ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
ውሳኔ 5

ስር ነቀል ለውጥ፡

ሕይወትህን ለመቀየር፣ ስር ነቀል ለውጥ በማድረግ ራስህን ለመቀየር ወስን። ሕልምህን ለማሳካት፣ ስር ነቀል ለውጥ በማድረግ ራስህን ሕልሙን ማሳካት፣ ሕይወቱን፣ ቤተሰቡን፣ አገሩንና ዓለምን መቀየር ወደሚችል ድንቅ ሰውነት ለመቀየር ወስን።

ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
መልካም ቀን ተመኘን!
አሁኑኑ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዳዊት ድሪምስ
ወጣቱ የተረት አባት አብርሀም
አሁኑኑ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
አራት የለውጥ ደረጃዎች
የድሮ ፓራዳይም አንድ የማይፈልገው ነገር ቢኖር “ለውጥ” ነው። ሕልምህ እንደ እምነት እና ፓራዳይም በድብቁ አዕምሮህ ሲገነባ፣ ድብቁ አዕምሮህ ብቻ ሳይሆን፣ ሙሉ አዕምሮህ ጭምር ሕልምህን ማሳካት ወደሚችል ድንቅ አዕምሮነት ይቀየራል። አዕምሮህ ሲቀየር ደግሞ ራስህን ሕልሙን ማሳካት ወደሚችል ድንቅ ሰውነት ትቀይራለህ። ይህን ለማድረግ ግን በመጀመሪያ የድሮ ፓራዳይምህን ማሸነፍ አለብህ።
የድሮ ተራ ፓራዳይምህን አሸንፈህ በድብቁ አዕምሮህ አዲስ ፓራዳይም ለመገንባት፣ በአራት የለውጥ ደረጃዎች ማለፍ ይኖርብሀል። የድሮ ተራ ፓራዳይምህን በአዲስና ድንቅ ፓራዳይም ስትቀይረው፣ አዕምሮህ ሙሉ በሙሉ ይቀየራል። አዕምሮህ ሲቀየር ደግሞ፣ ራስህን በመቀየር ሕይወትህን ትቀይራለህ። ራስህን በዚህ ድንቅ መንገድ በእርግጠኛነት ለመቀየር፣ በአራት የለውጥ ደረጃዎች ማለፍ ያስፈልግሀል። እነዚህ ከስር የተዘረዘሩት አራት የለውጥ ደረጃዎች ምን እንደሆኑና እና እንዴት አድርገህ እነዚህን ደረጃዎች በትክክል በመጠቀም፣ ራስህን መቀየር እንደምትችል፣ ከነገ ጀምሮ በሚቀጥሉት አራት ቀናት እንመረምራቸዋለን።
፩. ባርነት የለውጥ ደረጃ
፪. ማሰብ የለውጥ ደረጃ
፫. ግጭት የለውጥ ደረጃ
፬. ነጻነት የለውጥ ደረጃ

ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
ድንቅ ምሽት ተመኘን!
አሁኑኑ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
አራት የለውጥ ደረጃዎች
፩. ባርነት የለውጥ ደረጃ

በባርነት ውስጥ እንዳልሆንክ ራስህን የምትፈትሽበት መንገድ፣ ምንም የማይሻሻልና የማያድግ ውጤት አለማግኘትህ ላይ ነው። በሕይወትህ ማደግ እና መሻሻል የነበረበት፣ ነገር ግን እድገቱ የቆመ ምን አይነት ነገር አለ?
ሁላችንም በሕይወት ያለን ሰዎች የሚቆም ወይም የማያድግ ነገር የለንም። ሁሉም ነገር ያድጋል፤ ካላደገ ደግሞ ይሞታል። ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ፣ በማደግ እና በመሞት መካከል ነው ያለው። ወይ እያደግክ፣ አልያም እየሞትክ ብቻ ነው የምትሄደው፤ በሕይወት እያሉ “አለማደግ” የሚባል ነገር የለም። በግንኙነቶችህ ያለህ ፍቅር፣ ደስታና ሰላም፣ በስራህ ያለህ ገቢ፣ ደሞዝና ትርፍ እየጨመረ ነው ወይስ እየቀነሰ? አሁን የምታገኘው ውጤት ከአምናና ካቻምናው የማይሻል ከሆነ፣ በሚቀጥለው ዓመት የምታገኘው ውጤትም ከያዝከው ዓመት የማይሻል ነው የሚሆነው። ስለዚህ በሕይወትህ ምንም አይነት ዕድገት የማያሳዩ ውጤቶች ካሉ፣ የባርነት የለውጥ ደረጃ ውስጥ እንዳለህ የሚያሳዩህ ሌሎች ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ።

ራስህን ስትፈትሽ፣ በባርነት ሕይወት ውስጥ ካገኘኸው፣ አሁኑኑ ከዚህ የፓራዳይም እስር ቤት ውስጥ ለመውጣት ተዘጋጅ። የመጀመሪያው የለውጥ ደረጃ፣ በሕይወትህ የገባህበትን እስር ቤት ለይተህ ማወቅ ነው። ነገ በምንለጥፈው ሁለተኛ በሆነው የማሰብ የለውጥ ደረጃ፣ እንዴት አድርገህ ከባርነት ሕይወት በመውጣት ወደ ነጻነት ሕይወት መግባት እንደምትችል እንመረምራለን።


ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
ድንቅ ቀን ተመኘን!
አሁኑኑ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
በራስ መተማመን

አንተ ማን እንደሆንክና ምን ማድረግ እንደምትችል በትክክል ስታውቅ እና ስትረዳ፣ በራስህ መተማመን ትጀምራለህ። በውስጥህ ያለውን ዕምቅ አቅም በመጠቀም፣ ምን ማድረግ እንደምትችል ስትረዳ፣ አሁን ያለህ "ትልቅ ነው" ብለህ ያስቀመጥከው ሕልምህ፣ እንደሚያንስብህ እርግጠኛ ነኝ። ለማመን ይከብደኛል ብለህ የፈራኸው ፓራዳይም እና ለመልመድ ይከብዱኛል ብለህ የፈራሀቸው ልማዶችም በጣም ቀላል ይሆኑልሀል፣ አሁን ላይ ምናልባትም ከአስር ሰዎች ጋር ተወዳድረህ፣ እንድታሸንፍ ስትጠየቅ፣ "ከአቅሜ በላይ ነው!" ብለህ በራስህና በአቅምህ ትጠራጠር ይሆናል። ከመወለድህ አስቀድሞ፣ ዘር ከነበርክበት ማንነትህ አንስቶ እስከ አሁን፣ በሕይወትህ ያለፍካቸውን ፈተናዎች እና ችግሮች እንዲሁም የፈጠርካቸውን ተዓምሮች አንዴ መለስ ብለህ ካሰብክ፣ ማን እንደሆንክ እና ምን ማድረግ እንደምትችል በትክክል ትረዳለህ።

ትልቅ ሕልም አለኝ!
አንድ ብር ከአንድ ዶላር እኩል ነው!
ዳዊት ድሪምስ
ድንቅ የሆነ ምሽት🙏

የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናላችንን በመቀላቀል ይወያዩ ድንቅ የአዕምሮ ምግብ በምስልና በፅሁፍ ይከታተሉ።
ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/DawitDreamsOfficial
https://t.me/DawitDreamsTelegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሸናፊ ሰዎች በቅዝቃዜም በሙቀትም ያሸንፋሉ! ተሸናፊ ሰዎች ተኝተው ያሳብባሉ!

መልካም የማሸነፍ ቀን

ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ
ድንቅ ቀን ተመኘን!
አሁኑኑ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
https://t.me/DawitDreamsTelegram
የማክሰኞ እንግዳችን

ድንቁ እና ተዓምረኛው የስብዕና ልህቀት አሰልጣኝ ማንያዘዋል እሸቱ የማክሰኞ ሰኔ 21/2014 ልዩ እንግዳችን ነው፣ ከ 11፡00 ጀምሮ በ22 ማዞሪያ ባታ ኮምፕሌክስ 3ኛ ፎቅ ላይ ድንቅ የሆነ የአዕምሮ ምግብ ሊመግበን ተዘጋጅቷል።

መግቢያ በነፃ:-ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ማንም እንዳይቀር።

ለበለጠ መረጃ በ +251938252525 ይደውሉ። ያመለጣችሁን እንግዳ በ Dawit Dreams You Tube channel ላይ በመግባት ታገኙታላችሁ።

join us
https://t.me/DawitDreamsTelegram