ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
15.6K subscribers
616 photos
41 videos
1 file
79 links
ምንም አይነት መፅሀፍ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናመጣሎታለን፡
በሚያስገርም "ከ10-50%" በሆነ የዋጋ ቅናሽ ሞክረው ይዩን በአገልግሎታችን ይደሰታሉ

Free delivery
@Guramaylebooks

@Guramayelie 0912319263
Download Telegram
#የሰመረ_ሕይወት_እንዲኖርህ_3ቱን_አድርግ!

#1_ስህተትህን_ተሸክመህው_አትዙር!

ያለፈው ስህተትህ አስደናቂ የወደፊት ጊዜን እንድትፈጥር ሊያስተምርህ እንጂ እንድትፈራው ሊያደርግህ አይገባም፡፡ ስህተትህን ተሸክመኸው አትዙር፡፡ ይልቁንም ከእግርህ ስር አድርገኸው እንደ መውጫ ደረጃ ተጠቀምበት፡፡ በፍጹም እንዳትጸጸት፡፡ ጥሩ ከሆነ ቆንጆ ነው፡፡ መጥፎ ከሆነ ደግሞ ልምድ ነው፡፡ ስኬት አንድ ጊዜ በቆምክበት ቦታ አይለካም፤ ይልቁንም ምን ያህል ተማርክ እና እዚያስ ለመድረስ ምን ያህል ርቀት ተጓዝክ በሚለው ይለካል፡፡

#2_አስፈላጊ_የሆነው_ነገር_ላይ_ብቻ_አተኩር

ለአንተ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ነገር ለይ፡፡ ሌላውን ነገር በምትችለው አቅም ሁሉ አስወግደው፡፡ ጊዜ አታባክን፣ በማይረቡ ነገሮች ላይ ጉልበትህን አትጨርስ፤ መጸጸትም አቁም፡፡ ያለፈው አልፏል፤ የሚመጣውም ምን ይዞ እንደሚመጣ አይታወቅም፤ አሁን ላይ ብቻ ሁን! አሁን ላይ በጣም አስፈላጊው ነገር ላይ ብቻ አተኩር፡፡

#3_ለሁሉም_ሰው_ሁሉንም_ነገር_መሆንህን_አቁም

ከሁሉም ጋር ጓደኛ ለመሆን አትሞክር፡፡ ከጥቂት ሰዎች ጋር የቅርብ ግንኙነቶችን መስርት፡፡ ለሆነ ሰው ሁሉንም ነገር መሆን ላይ ማተኮር ጀምር፡፡ ሁሉንም ሰው መርዳትና ማስደሰት የማይቻል ነው፡፡ አንድን ሰው እንዲስቅ ማድረግ መቻል ግን ዓለምን ሊቀይር ይችላል፡፡ ምናልባት መላውን ዓለም ባይቀይር የእነርሱን ዓለም ግን ይቀይርላቸዋል፡፡ ስለዚህ ትኩረትህን አጥብብ እና እራስህን ሁን፡፡

በተረፈ ደግሞ #የስኬት_አቡጊዳ_መጽሐፍን አንብብ፡፡ የሰመረ ሕይወት ይሁንልህ!