ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
15.6K subscribers
616 photos
41 videos
1 file
79 links
ምንም አይነት መፅሀፍ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናመጣሎታለን፡
በሚያስገርም "ከ10-50%" በሆነ የዋጋ ቅናሽ ሞክረው ይዩን በአገልግሎታችን ይደሰታሉ

Free delivery
@Guramaylebooks

@Guramayelie 0912319263
Download Telegram
ጆርዳን ፒተርሰን "12 RULES FOR LIFE" የተሰኘ ልጨኛ(master piece) ስራው በተለይ በምዕራባውያኑ ዓለም በአሁኑ ወቅት እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ በመሆን ተደጋግሞ እየተነበበለት ደግሞም ብዕርክ ይለምልም እያሰኘለት ይገኛል።
ይህ ስራው ለሀገር ቤት ተደራስያን በገፀ ቅጠል 344 ብዛት ተቀንብቦ ለህትመት በቅቷል
ስለዚህ ዕውቅ ስራው፦
Camile Pagile እንዲህ ይላል
"ጆርዳን ፒተርሰን ከማርሻን ማክሉሀን ወዲህ የተፈጠረ እጅግ ወሳኙና አሳቢ ከሚባሉ ባለተፅዕኖ ካናዳዊ ፀሀፊ ነው። ዓለም አቀፍ ዝናው የናኘ ስነልቦና፣ የባህል ማህበረሰባዊ ጥናት(anthropology)፣ሳይንስ ፓለቲካ ንፅረታዊ ሀይማኖት ቀመስ እሳቤዎችን በማቀናጀት ሰብአዊ ሁለንተናዊነትን ለማንበር ሳያሰልስ ለማንበር የሚጥር ጉምቱ ፀሀፊ ነው።"
Howard Bloom በበኩሉ ይህን ስራ በተመለከተ በሰጠው አስተያየት የቃላትን ጉልበት ያገኘ አይመስልም።
"ይህ መፀሀፍ(12 Rules For Life)የእያንዳንዳችንን ጓዳ የሚጎበኝና የሚያስስ ብሎም በኑረታዊ ጉዘታችን ውሳኔዎቻችንን በተዋረዳዊ አመሳስልና መሰላል የሚያነቃቃ፤ ያልተለመዱና አይነኬ ርዕሰ ጉዳዮችንና እሳቤዎችን ለዛ ባለው አቀራረብ የሚደፍር የተሻለ የህይወት አቅጣጫን ጠቋሚ መፅሀፍ ነው ብሎታልደ
ይቀጥልናም ሆዋርድ የመጀመሪያዎቹን የመፅሀፋን 25 ገፆች እንኳን ብንመለከት የስነልቦናዊ ውቅር ጥናት ዘርፍን ቀንብቦ በማስረዳት በልብ አንጠልጣይ ለዘኛ አቀራረብ ሲነግረን እናነባለን ብሎለታል።
ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ
"ፒተርሰን አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው ያኔ አባቴ ሊነግረኝ የምመኘውን መንገድ ያመላከተኝ የቀደመ ፀሀፊ ነው ይላል።
በአሁን ዘመን ዓለማችን ከተፈጠሩላት ብርቅዬዎች አንዱ ነው ካለ በኋላም በተለይ ለአፍላ ወጣቶች ውሳጣዊ የአስተሳሰብ ጓዳቸውን በማፅዳት ለውጨኛው ዓለምና ለነፍስያ የሚፈይዱ ረብዕ ያላቸው ቁመሰ ነገሮችን የሚያጋራን ሰው ነው ይለዋል።
ገና ከበሩ ቆመን ስናንኳኳ (በሽፋን ገፁ) እንዲህ የሚል ቁም ነገር ሰፍሮ እናገኛለን፦
* ራስህን ከትላንትህ ጋር እንጂ ፈፅሞ ዛሬ ካለ ሌላ ሰው ጋር ለማነፃፀር አትፍገምገም*

#12 RULES FOR LIFE BY JORDAN B. PETERSON ብታነቡት ትወዱታላችሁ መልካም ንባብ ...
#12_RULES_FOR_LIFE በሚል በጆርዳን ፒተርሰን የተጻፈውን መጽሐፍ #የሕይወት_ቀመሮች በሚል ተተርጉሞ በገበያ ላይ ዋለ፡፡

#የሕይወት_ቀመሮች መጽሐፍ ለሕይወትዎ በሚጨነቅ ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት የታዘዘ በሕይወት ቀውስ ሁሉ ለሚከሰቱ ችግሮች መድኃኒት የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡
ደጋግመው ቢያነቡት የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው፣ ሱስ የሚያስይዝ መጽሐፍ፡፡
12 የሕይወት ቀመሮችን የያዘውን መጽሐፍ በአግባቡ ካነበቡት ከቀውስ ነጻ ሕይወት ከመምራትዎም ባሻገር ጤናማ፣ ደስተኛና ስኬታማ ያደርግዎታል፡፡
መጽሐፉ ለሕይወት ቀውስ ፍቱን መድኃኒት ነውና ሁሉም ሰው እንዲወስደው ይመከራል፡፡


የሕይወት ቀመሮች ጆርዳን ፒተርሰን
የገፅ ብዛት - የተለጠፈበት ዋጋ - 380 ብር
መሸጫ ዋጋ - 280 ብር  🇪🇹 >=3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie   0912319263