ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
15.6K subscribers
616 photos
41 videos
1 file
79 links
ምንም አይነት መፅሀፍ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናመጣሎታለን፡
በሚያስገርም "ከ10-50%" በሆነ የዋጋ ቅናሽ ሞክረው ይዩን በአገልግሎታችን ይደሰታሉ

Free delivery
@Guramaylebooks

@Guramayelie 0912319263
Download Telegram
Can't hurt me - David Goggins

ለዴቪድ ጎጊንስ ልጅነት ቅዠት ነበር -- ድህነት፣ ጭፍን ጥላቻ እና አካላዊ ጥቃት ቀኖቹን ቀለም ቀይረው ሌሊቱን አስጨናቂ ነበር። ነገር ግን እራስን በመግዛት፣ በአእምሮ ጥንካሬ እና በትጋት በመስራት ጎጊንስ ራሱን ከጭንቀት ከተጨነቀ እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ካለው ወጣት ወደፊት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሃይሎች ተምሳሌትነት እና ከአለም ከፍተኛ የጽናት አትሌቶች ተርታ ተቀየረ። እንደ Navy SEAL፣ Army Ranger እና Air Force Tactical Air Controller በታሪክ ውስጥ የላቀ ስልጠናን የጨረሰ ብቸኛው ሰው በተለያዩ የጽናት ዝግጅቶች ላይ መዝገቦችን በማስመዝገብ የውጪ መፅሄቶችን በማነሳሳት ስሙን በአሜሪካ ውስጥ በጣም ጥሩ (እውነተኛ) ሰው ብሎ እንዲሰይመው አድርጓል

አልችልም በሚለው ውስጥ፣ አስደናቂ የህይወት ታሪኩን ያካፍላል እና አብዛኞቻችን 40% አቅማችንን ብቻ እንደምንጠቀም ገልጿል። ጎጊንስ ይህንን የ 40% ህግ ብሎ ይጠራዋል እና የእሱ ታሪክ ማንኛውም ሰው ህመምን ለመግፋት ፣ ፍርሃትን ለማጥፋት እና ሙሉ አቅሙን ለመድረስ የሚፈልገውን መንገድ ያበራል...
ሞትን ትደፍረዋለህ!
የሰው ልጅ አእምሮ ትልቁ መከራ ሞትን መቃወም ነው። ሞትን በተቃወምክበት ቅጽበት ሕይወትንም ትክዳለህ። ሕይወት ትክክል ሞት ደግሞ ስህተት ነው ብለው ታስባለህ፥ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ሕይወት እንዲህ የሆነችው ሞት ስላለ ብቻ ነው። ወንዝ ሁልጊዜ የሚከሰተው በሁለት ዳርቻዎች መካከል ነው። አንተ ግን በቀኝ ባለው ዳርቻ ቆመህ፣ “በግራ በኩል ያለውን ዳርቻ አልወደውም፣ መጥፋት አለበት” ትላለህ። እንደሱ አይሰራም… አሁን በዚህ መጽሐፍ ሞትን እንድትደፍር ትሆናለህ… ለምን ቢባል… ሕይወትን በአግባቡና በትክክል ለመኖር!

እምነትህን ታስተካክላለህ!
በዓለም ላይ ያሉትን ፀሎቶች ተመልከት፡፡ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑት ፀሎቶች፣ “ይህንን ስጠኝ፣ ያንን ስጠኝ፤ አድነኝ፣ ጠብቀኝ፡፡” የሚሉ ናቸው፡፡ ይህ እምነት ሳይሆን ስምምነት ነው፡፡ የማይረባ ስምምነት ለማድረግ እየሞከርክ ነው፡፡ አሁን ትክክለኛው ስምምነት ምን እንደሆነ ስታውቅ… እምነትህም በአስደናቂ ሁኔታ ይስተካከላል!

የሕይወት ማዕበልን ታሸንፋለህ!
ሕይወት የራሷ ማዕበሎች አሏት፡፡ በማዕበል ላይ መጓዝ ከተማርክ፣ አንድ ቀን ህልምህ ከሱናሚ ጋር መጋጠም ይሆናል፡፡ በማዕበሉ ላይ በመጓዝ ጎበዝ ከሆንክ፣ ቀጥሎ የምትፈልገው ትልቁን ማዕበል ይሆናል፡፡ በማዕበል ላይ መጓዝ ካልተማርክ ግን፣ ማዕበሉ በመጣ ጊዜ ትወድቃለህ፡፡ ችግሩ ከማዕበሉ ነው? አይደለም፡፡ የሕይወት ማዕበልን በትክክል ባለመማርህ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ሲያስተምርህ ደግሞ… ትላልቅ ማዕበሎችን ታሸንፋለህ!!!


የሕይወት ኬሚስትሪ ተርጓሚ ሀኒም ኤልያስ
የገፅ ብዛት - 206 የተለጠፈበት ዋጋ - 260 ብር
መሸጫ ዋጋ - 190 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
እልልታ የዋጠው እሪታ
▬▬▬▬▬▬▬

➔ከሥልጣን ሽግግሩ ዋዜማ አንስቶ እስካለንበት ጊዜ ድረስ በመንግሥታዊ እልልታዎች የተዋጡትን ሕዝባዊ እሪታዎች በወግና በስንኝ የሚተርከው...
➔እንደ ሕዝብ ያከሸፍናቸውን መልካም አጋጣሚዎች፣ የቀበርናቸውን ወገኖች፣ ያስተናገድናቸውን ማንነት ተኮር ወረራዎችና ጥቃቶች፣ የተከፈሉልንን መስዋዕቶች እንዳጠቃላይም ባለፉት አራት ዓመታት ተከስተው የዘነጋናቸውን አበይት ክስተቶች፣ ከምሥልና ከቃል ማስረጃ ጋር የሚያወሳው 4ኛ መጽሐፋችን ለአንባቢያን ቀርቧል
አሳየ ደርቤ።


እልልታ የዋጠው እሪታ አሳየ ደርቤ
የገፅ ብዛት - 248 የተለጠፈበት ዋጋ - 300 ብር
መሸጫ ዋጋ - 270 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
"ካፖርቱ
የመጨረሻው ቅጠል
ሽማግሌውና ባሕሩ"
እጅግ በጣም ተወዳጅነትን ያተረፉ በተርጓሚ መስፍን ዓለማየሁ የተተረጎሙ ሶስት መጽሐፍትን በአንድ ላይ

አንገቱን በፍጥነት ወደኋላ ጠምዝዞ ሲመለከት፤አሮጌ የደንብ ልብስ ያጠለቀ አንድ ትንሽ ሰው አለ።አካኪይ አካኪየቪች መሆኑን ሲረዳ ይህ ነው የማይባል ድንጋጤ፤መሐል አናቱን ሲበረቅሰው ተሰማው።የሽማግሌው ጸሐፊ ገጽ እንደ በረዶ ነጭ ሆኖ አስከሬን ይመስላል።መንፈሱ በበቀል ስሜት አፉን ማጣመምና ማጩማደድ ሲጀምር፤ትልቁ ሰው ገደብ በሌለው የሽብርና የፍርሃት ማጥ ውስጥ ዘቀጠ።የአካኪይ አካኪየቪች ኤኬራ ከመቃብር ሽታ ጋር የሚመሳሰል ትንፋሽ እየተነፈሰ“ታዲያስ፤ጌታው!በመጨረሻ ተገናኘን አይደለም?አንገትህ በመዳፌ ውስጥ ገባ!አሁን ካንተ የምፈልገው ካፖርትህን ብቻ ነው። ካፖርቱ
“አንድ የምነግርሽ ነገር አለኝ”አለቻት።ወዳጃችን በኸርማን ዛሬ በሆስፒታል ውስጥ ዐረፈ።የሳንባ ምች ነው ይባላል ጠንቁ።ለሁለት ቀናት ብቻ ነው የታመመው።ሕመሙ በያዘው ቀን ማለዳ ቤት ውስጥ ተኝቶ ሲሠቃይ በቅድሚያ ደርሶ ያገኘው የሕንፃው ጠባቂ ነው ይባላል።ኃይለኛው ዶፍ ሲወርድ ባደረ ማግሥት መሆኑ ነው።ከእግር እስከ ራሱ ጫማና ልብሱ ሳይቀር በውኃ ሾቆ ሁለመናው በረዶ ሆኖ ነበር።በመጀመሪያ ያንን የመስለ አስፈሪ ሌሊት የት እንዳሳለፈ ያወቀ ሰው አልነበረም። የመጨረሻዋ ቅጠል
ድንገት የቀኝ መዳፋቸው ከፊታቸው ጋር ሲጋጥና ገመዱ ቀኝ እጃቸውን እንደ እሣት እየለበለበ ሲጎተት ተሰማቸውና ከእንቅልፋቸው ነቁ።የግራ እጃቸው የት እንዳለ ፈጥነው ለማወቅ አልቻሉም።በከፍተኛ ፍጥነት እየተፈተለከ ወደ ባህሩ በመንጎድ ላይ ያለውን ገመድ ጨምድደው ለመግታት ቢሞክሩም አልተሣካም። ሽማግሌውና ባሕሩ


ካፖርቱ፣ የመጨረሻው ቅጠል፣ ሽማግሌውና ባሕሩ የተለጠፈበት ዋጋ - 450 ብር
መሸጫ ዋጋ - 380 ብር 🇪🇹
በብዙ የኢትዮጵያ አንባቢያን ዘንድ አልኬሚስት በተሰኘው ስራው የምናውቀው ፓውሎ ኩዌልሆ ያለምንም ጥርጥር በቅርብ ዘመናት ውስጥ ሊጠቀስ የሚችል እጅግ ስኬታማው ደራሲ ነው። መጽሐፍቱ በመቶ ሚሊዮን ቅጂዎች ከመሸጣቸውም በላይ ወደ 150 በሚደርሱ የዓለም ቋንቋዎች ተተርጉመውለታል። በዚህም የጊነስ ድንቃ ድንቅ መዝገብ "ጽሑፎቹ በብዙ የአለም ቋንቋ የተተረጎሙለት በሕይወት ያለ ደራሲ!" ሲል ስሙን አስፍሮለታል።

የስሜት ነጻነት ፓውሎ ኮሆልዮ
የገፅ ብዛት - 224 የተለጠፈበት ዋጋ - 250 ብር
መሸጫ ዋጋ - 200 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
አንድ ለማኝ ከሰላሳ አምስት አመታት በላይ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር። አንድ ቀን አንድ እንግዳ ሰው ወደ እርሱ መጣ፤ ለማኙም ገንዘብ መቀበያ ኮፍያውን እያሽከረከረ ለእንግዳውን ሰው "ገንዘብ ስጠኝ" አለው። "እኔ የምሰጥህ የለኝም" አለ እንግዳው ሰው። ለማኙንም ጠየቀው
"ምን ላይ ነው የተቀመጥከው?"
"ምንም አይደለም" አለ ለማኙ "አንድ ተራ ሳጥን ነው። እስከማስታውሰው ድረስ እዚህ ላይ ለብዙ አመታት ተቀምጬያለሁ።"
"ውስጡንስ አይተኸው ታውቃለህ?" እንግዳ ሰው ጠየቀ
"አይ" አለ ለማኙ "ምን ይፈይድልኛል ብለህ ነው። ምንምም አይኖረውም"
"እስኪ ውስጡን ክፈትና ተመልከት" እንግዳው ለማኙን እንዲመለከት ገፋፋው።
ለማኙ እንደምንም ታግሎ የሳጥኑን ክዳን ከፈተው። በአግራሞት እና ባለማመን ፈዞ ቀረ። ሳጥኑ በወርቆች ተሞልቷል።
እኔ እንግዳ ሰው ነኝ፤ ወደ ውስጥ እንድትመለከትም እገፋሃለሁ።
"እኔ ለማኝ አይደለሁም" ስትል ይሰማኛል።
እነዚያ ምን እንደሚፈልጉ የማያውቁ፣ የሚወዱትንም ህይወት የማይኖሩ - ለማኞች ናቸው። ገንዘብ ቢኖራቸው እንኳ ለማኝ ናቸው። ሁሌም ቢሆን ውጪያዊ ከሆነው አለም የሆነ ነገርን ይፈልጋሉ። ፍቅርን፣ ደህንነትን ተቀባይነትን፣ ደስታን ወዘተ የማይፈልጉት የለም። እኔ ግን እልሃለሁ፤ የማያልቅ እልፍ ዋጋ ያለው ወርቅ በውስጥህ አለ፤ ወደ ውስጥም ተመልከት።

መጽሐፉ አስተሳሰባችንን ልከኛ ያደርገዋል
ተግባራችንን ውጤታማ ያደርገናል
ምስቅልቅላችንን አስተካክሎ ቅርጽ ይሰጠዋል
በዘፈቀደ መኖር አቁመን በተግባር በተፈተኑ የስኬት መርሆዎች አማካይነት በልኬት ወደ ስኬት የምንሻገርበት መጽሐፍ ነው፡፡
መለኪያውም፣ ማሳኪያውም መንገድ በመጽሐፉ ውስጥ ተቀምጧል፡፡ እንለካለን፣ እናሳካለን!!


በልኬት ወደ ስኬት
የተለጠፈበት ዋጋ - 260 ብር
መሸጫ ዋጋ - 190 ብር 🇪🇹
የመዝጊያ መልዕክት ከእረኛየ!!!
ይገርማል ሁሌም ድክም ብሎኝ ስቀር ምርኩዝ ይልክልኛል፤ አንቺም የበቃልዬ ምርቃት ይድረስሽ ሲል ምርኩዝ አርጎ አመጣሽ። በቃልዬ አብነትን የመረቃትን ሰምተሻል? "እውቀት እንደ ምንጭ ይፍለቅብሽ፣ እንደጅረት ወርዶ ለዓለም ሁሉ ይድረስ ብሎ ነው የመረቃት" ። ለአንቺም ከምርቃቱ ይድረስሽ። አሜን፤ ጎሽ ልጄ አዎ፤

እማማ እንመለስ? ደከመዎት?
አየ ልጄ መመለስማ የለም፤ ወደኋላ ዞሬ መመልከቴ ከመነሻየ ምን ያህል ርቀት ተጉዤ እንደመጣሁ ለማወቅ፣ ወደፊት ለመጓዝ ተስፋ እንዲሆነኝ ነው፤ መመለስማ የለም።

ብዙ መከራ አይቻለሁ፣ ብዙ መከራና ስቃይ ፈትኖኛል ልጄ፤ ያኔ ከአበባየ መርገፍ በኋላ ጉልበት ተስኖኝ እቤት ቀርቼ ነበር።

ሰው የጭረት ጠባሳውን እየገለጠ፣ የሌላውን ቁስል እየወጋ፣ በቂም መከፋፈሉን አይታ፣ መቁሰሌ ሌላውን ሰው ወደ ሞት የሚወስድ አይሁን፣ ለእርቅና ለይቅርታ ይሁን ብላ የመንደሩን ሰው በአደራ መራችው። ወደኋላ መመለስ የለም ብላ ሁሉን በአንድነት አስተሳስራ የኔ ልጅ ወደፊት መራችው። ለወደደችው፣ ላመነችበት ዋጋ ከፈለች፤ ዋጋ ከፈለች እኔ ግን እሷ የከፈለችውን ዋጋ ከንቱ ለማስቀረት እቤቴ ቁጭ አልኩ፣ እቤት ቀረሁ፤ ግን ትውልድ አይጥፋ፣ ተስፋ አይጥፋ ይሄው አንቺ መጣሽልኝ እና ምርኩዝ ሆነሽ ይዘሽኝ ወጣሽ።

ዛሬ እግሬ እንዲቀጥልና እንድበረታ ያጸናኝ ተስፋ ነው።

የኔ ልጅ በዚህ እድሜሽ የደረሰብሽን እናትሽን ማጣትሽን ሰምቻለሁ ልጄ ግን ወደኋላ መመልከቱ ምን ያህል ትተሽው እንደመጣሽ ለማወቅ እንጂ ወደኋላ ለመመለስ አይሁን፤ አይሁን ልጄ።

ከመጣንበት ይልቅ ገና የምንሄድበት ብዙ ነው።

አሁን ምንድን ነው የሚመረቀው?
ዛሬ ሸክላ በመስራት ነው የሚያስመርቁት ብለዋል።
ጎሽ ጥሩ አድርገዋል የሰው ልጅስ ከመነሻው እንዲሁ አይደል እንደሸክላ ከአፈር፤ ሁሉም የሰው ልጅ እኮ ከአፈር ተነስቶ ወደ አፈር ነው።

ከአፈር እስከ አፈር!!!
በደራሲ እና የፍልስፍና መምህር ደሳለኝ ስዩም ጥንቅቅ ብሎ የተዘጋጀው አዲስ የፍልስፍና መጽሐፍ  የፍልስፍና መግቢያ

የሰው ልጅ ነገሮችን መመርመር እንዲጀምር፣ አዳዲስ ፈጠራዎችን እንዲያስብ ወይም በህይወት ላይ እንዲያምጽና በጎጅ ነባራዊ ልማዶች ላይ እምብኝ ማለትን እንዲለምድ ካነሳሱት ጥያቄዎች ዋነኛው ‹ማነኝ› የሚው ጥያቄ ነው፡፡ ማነኝ በሚለው ጥያቄ ውስጥ ፈርጀ ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ፤ በዋነኝነት የሚመጣው ግን ‹የህይወት ትርጉሙ ምንድን ነው› የሚለው ነው፡፡
በእርግጥም የህይወት ትርጉም ጥያቄ ጠቅለል ባለ መንገድ ‹ሳይንሳዊ› ብለን በተደራጀ መንገድ ከምናጠናው ተጠኝነት ሁሉ ያለፈ ጥያቄ ነው፡፡ ሳይንስ በአጠናን ባህሪው የነገሮችን ምንነት እና ተፈጥሮ ለማወቅ ይታትራል፡፡
በዚህም በውጤቱ ተፈጥሮም ሆነች ህይወት እንደምን (how) እንደሚሰሩ ይገልፅልናል፡፡ የህይወት ትርጉም ጥያቄ ግን ከዚህ የተሻገረ ነው፡፡ የህይወት ትርጉም ምንድን ነው? ስለምንስ ይሄ ሁሉ ነገር ተፈጠረ (ኖረ) የእኔስ ህይወት መፈጠር (መኖር) ሰበቡ ምንድን ነው? እያልን ስንጠይቅ በጥያቄያችን ውስጥ የምንፈልገው ህይወት አልያም ተፈጥሮ እንዴት እንደምትሰራ አይደለም፡፡
ይልቁንስ ስለምን (why) እንደተፈጠረች (እንደኖረች) እና ተፈጥሮዋንም ለምን ሳይንስ እንደሚገልፅልን - እንዳገላለጹም የሆነው ለምን እንደሆነ ለማወቅ እንፈልጋለን፡፡
እንግዲህ የህይወት ትርጉም እንዲህ ያለ ጥያቄ ነው፡፡ በየትኛውም ማብራሪያ (description) የማይረካ የለምን (why) ጥያቄ ነው፡፡ ከመጽሐፉ የተወሰደ

የፍልስፍና መግቢያ
በደሳለኝ ስዩም
የገፅ ብዛት - 224 የተለጠፈበት ዋጋ - 300 ብር
መሸጫ ዋጋ - 230 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
የዮሴፍ ታሪክ በአምስቱ የሙሴ መጻህፍት (ዘፍጥረት፣ ዘጸአት፣ ዘሌዋውያን፣ ዘኁልቁ እና ዘዳግም) ውስጥ ረዥም ስፍራ የሚሸፍን ብቸኛ የአንድ ሰው ታሪክ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቃቸው ታላላቅ አባቶችም አዳም፣ ሄኖክ፣ አብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ የዮሴፍን ያህል የግለ ታሪክ ሥፍራ በኦሪት መጻሕፍት ውስጥ የላቸውም። ለምን? ነው ጥያቄው። ሙሴ ከዮሴፍ በኋላ ለእስራኤል የተነሣ መሪ ነው። በዮሴፍ ሞት እስራኤል ተጎድተዋል። እርሱ ከሞተ በኋላ የተነሡ ነገስታት ለእስራኤል መልካም አልነበሩም። በዚህ የተነሳ የዮሴፍ ታሪክ ለእስራኤላውያን መጽናኛቸው ነበር። ሙሴም ይሄንን ታሪክ እያጠና ያደገ ነው በሌላም በኩል ዮሴፍ የእስራኤልን ታሪክ ወደ ሌላ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው። የዮሴፍ ሕይወት የእስራኤልን ታሪክ በስድስት መልኩ ቀይሮታል። ከመጽሐፉ የሽፋን ገጽ የተወሰደ።

ፍቅር ወደ ጥላቻ የአደረገው ጉዞ (የያዕቆብ ልጅ የዮሴፍ ታሪክ) ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
የገፅ ብዛት - 270 የተለጠፈበት ዋጋ - 450 ብር
መሸጫ ዋጋ - 400 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
"THE POWER OF NOW" በተሰኘው መጽሐፉ አንባቢዎቹን አሁንን በአግባቡ በመኖር ደስተኛ መሆን እንደሚቻል በአግባቡ መረዳት እንዲችሉ ያደረገው ኢካርት ቶሌ "A NEW EARTH" በተሰኘው በዚህ መጽሐፉ ደግሞ ከሚገባው በላይ ለራሱ ማድላት የሚያመጣብንን ቀውስና ይህንኑ ተከትለው የሚመጡ ንዴት ፣ ቅናትና ደስታ ማጣትን የመሰሉ ነገሮችን መንስኤና ውጤት አሰናስኖ ለአንባቢው ፍንትው ብሎ በሚታይ መልኩ ያሳያል።

ራስን የመለወጥ መንገድ ኢካርት ቶሌ
የገፅ ብዛት - 237 የተለጠፈበት ዋጋ - 280 ብር
መሸጫ ዋጋ - 220 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263
የስልጣኔ አየር ከከበደ ሚካኤል
የገፅ ብዛት - 171 የተለጠፈበት ዋጋ - 320 ብር
መሸጫ ዋጋ - 230 ብር  🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie   0912319263  

Telegram :
t.me/guramaylebooks
Twitter :
twitter.com/guramaylebooks
Facebook :
facebook.com/guramaylebooks
IG :
Instagram.com/guramayle_books
Email :
guramaylebooks@gmail.com
የአለም ታሪክ ከከበደ ሚካኤል
የገፅ ብዛት - 420 የተለጠፈበት ዋጋ - 450 ብር
መሸጫ ዋጋ - 350 ብር  🇪🇹 >=3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie   0912319263  

Telegram :
t.me/guramaylebooks
Twitter :
twitter.com/guramaylebooks
Facebook :
facebook.com/guramaylebooks
IG :
Instagram.com/guramayle_books
Email :
guramaylebooks@gmail.com