ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
15.5K subscribers
616 photos
41 videos
1 file
79 links
ምንም አይነት መፅሀፍ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናመጣሎታለን፡
በሚያስገርም "ከ10-50%" በሆነ የዋጋ ቅናሽ ሞክረው ይዩን በአገልግሎታችን ይደሰታሉ

Free delivery
@Guramaylebooks

@Guramayelie 0912319263
Download Telegram
የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ አራት አዳዲስ መጽሐፍት በአንድ ላይ የታተሙበት!

የደስታ ቀናት እንደ ሰማይ ሲርቁ…
ክፉ ቀናት እንደ አጀብ ሲከቡን…
ሞት አንድ አማራጭ ሆኖ ሲቀርብ…
ውስጣዊ ሰላማችን ሲረበሽ…
እርጋታ ፈጽሞ ሲጠፋ….

…ያን ጊዜ “ጌታ ሆይ እስከመቼ?” እንላለን፡፡ ደግሞም በልጅነት ሰቆቃ በአባቶቻችን አንደበት
#እስከማዕዜኑ? እንላለን፡፡

“እንደ ልጄ እንደ ዳዊት ቀና ሁን፣ እንደ ታላቁ ታጋሽ እንደ ኢዮብ ሁንልኝ፣ የቀጠርኩልህ ቀን ሲደርስ የመከራህን ቀናት አስረሳሃለሁ! እንደ ተወዳጁ ልጄ እንደ ወልድ ትንሳኤህ እስኪገለጥ እርጋታን ገንዘብህ አድርግ!” ይለናል፡፡ በቃሉ ያባብለናል፡፡

የህማማት ቀናቶቻችን እንደ ግዮን ወንዝ የረዘሙ ሲመስሉ፣ የህዝባችን እፎይታ፣ የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት እንደ ጌታችን መምጫ ቀን ሲርቁብን፣ ህይወት ከንቱ መኖርም ምናምንቴ መስሎ ሲታይ… የስጋ ድካም ከዘለዓለማዊው እጣ ፈንታችን ሊያናጥበን ሲል… ያን ጊዜ የታላላቅ አባቶች ምክር፣ የቅዱሳን ጥበብ፣ የታጋሾች ምስክርነት ያስፈልገናል፡፡

የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ አራት መጽሐፍት በአንድ ላይ
#እስከማዕዜኑ በሚል ርእስ የተዘጋጁትም ለዚሁ ዓላማ ነው፡፡

በሕይወታችን ያሉ እስከመቼ የምንልባቸውን መከራዎች እንዴት እንደምንወጣቸው የሚያስተምር ድንቅ መጽሐፍ ነው-
#እስከማዕዜኑ!

እስከማዕዜኑ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
የገፅ ብዛት - 304 የተለጠፈበት ዋጋ - 254 ብር
መሸጫ ዋጋ - 230 ብር 🇪🇹 >= 3 Free delivery 🇪🇹
Contact us
@Guramayelie 0912319263