ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
15.5K subscribers
617 photos
41 videos
1 file
79 links
ምንም አይነት መፅሀፍ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናመጣሎታለን፡
በሚያስገርም "ከ10-50%" በሆነ የዋጋ ቅናሽ ሞክረው ይዩን በአገልግሎታችን ይደሰታሉ

Free delivery
@Guramaylebooks

@Guramayelie 0912319263
Download Telegram
#7ቱ_ሕይወትህን_በኃያልነት_የምትመራባቸው_ሕጎች

48 Laws of POWER የተሰኘው አነጋጋሪ መጽሐፍ #የኃያልነት_ሕጎች በሚል ተተርጉሞ በገበያ ላይ ውሏል፡፡ ከመጽሐፉ በርካታ ትምህርቶች መካከል ሕይወታችንን በኃያልነት የምንመራባቸውን ሰባት ሕጎች ለቅምሻ እነሆ ብለናል፡-

#አንድ
በወዳጆችህ ብዙ አትታመን፣ ጠላቶችህን መጠቀም ተማር፤ ወዳጆችህን ቅርብ፣ ጠላቶችህን ግን የበለጠ ቅርብ አድርግ፡፡ 

#ሁለት
ሁልጊዜ ከሚያስፈልገው ያነሰ ተናገር፤ ትንሽ ብቻ በመናገር ሌሎች ችሎታህን አሳንሰው እንዲያዩት አድርግ፡፡  

#ሶስት
ብዙ ነገር በመልካም ስም ላይ የተመሰረተ ነው፤ ስምህ ሁሉ ነገር ነው፤ ስለዚህ የትኛውንም ዋጋ ከፍለህ ልትጠብቀው ይገባል፡፡ 

#አራት
በምንም መንገድ ይሁን ትኩረት አግኝ፤ ሌሎችን ለማሳመን ውዳሴና ግርማ ሞገስ ተጠቀም፡፡ 

#አምስት
ሌሎች ለአንተ እንዲሰሩልህ በማድረግ ሁልጊዜ ምስጋናውን አንተ ውሰድ፤ የሌሎችን ጥረት ለአንተ መጠቀሚያ አድርግ፡፡  

#ስድስት
በክርክር ሳይሆን በድርጊቶችህ አሸንፍ፤ ከቃላትህ ይልቅ ድርጊቶችህ ይናገሩ፡፡  

#ሰባት
ፍጹም ወይም እንከን የለሽ ሆነህ አትታይ፤ ይህ በሌሎች ውስጥ ቂምና ቅናት ይፈጥራል፡፡

ይህ ኃያልነትን የሚያቀዳጀው #የኃያልነት_ሕጎች መጽሐፍ
#ጄዚ
#ካንዬ_ዌስት
#ፊደል_ካስትሮ
#ጆርዳን_ፒተርሰን
#ባራክ_ኦባማ
#ኤለን_መስክን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ እና ኃያል ግለሰቦች ለስኬታቸው እንደምክንያት የሚጠቅሱት ነው። እናም አንተም ያቀድከውና ያሰብከው የስኬት መዳረሻ ላይ ለመውጣት ይህን መጽሐፍ እንደ መሰላል ተጠቀመው፡፡