EECMY Children Ministry: MY Sunday School
723 subscribers
892 photos
14 videos
168 links
MY Sunday School is the official page of EECMY Children Ministry.

Wholistic Growth For Our Children!

Access Sunday School learning materials at www.mysundayschool.org
Download Telegram
ውድ ወንድማችን ፀጋሁን አሰፋ

የኢት/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ ዋና ጽ/ቤት የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት ዳይሬክተር በመሆን ከ2013-2021 እ.ኤ.አ በትጋት እና በታማኝነት እግዚአብሔርን እና ህዝቡን ስላገለገልክ የሥራው ባለቤት ጌታ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ! ቤተሰብህ አገልግሎትህ እና ቀሪው የሕይወት ዘመንህ ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም የተባረከ ይሁን፡፡ አሜን!

‹‹ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስካሁንም ስለምታገለግሉአቸው ያደረጋችሁትን ሥራ ስለ ስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና ::›› ዕብ.6፡10

የኢት/ወ/ቤ/ክ/መ/ ኢየሱስ የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት ዲፓርትመንት

ግንቦት 2022 አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

🙏🙏🙏

Jaalatamaa Obboleessa keenya Tsaggaahuun Asaffaa

WWW Makaana Yesuus Waajjira Olaanaatti Daarikteera Tajaajila Ijoollee fi Dargaggoo ta'uudhaan bara 2013-2021 ALA amanamummaa fi ciminaan Waaqayyoo fi saba Isaa waan tajaajilteef abbaan hojichaa Waaqayyo Gooftaan guddisee sihaa eebbisuu! Maatiinkee, tajaajillikee fi barri jireenyakee kan eebbifame haa ta'u!

''Waaqayyo hojii keessanii fi isa jaallachuu keessan... argisiiftan hin irraanfatu, hin jal'isus.'' Ibr. 6:10

WWW Makaana Yesuus Itoophiyaa- Tajaajila Ijoollee fi Dargaggoo

Caamsaa 2022, Finfinnee, Itoophiyaa


@MYSundaySchool
Forwarded from Wondmagegn Udessa Bidire
ከኢት/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ ፕረዚዳንቶች ጋር...

';የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።''  ዕብራውያን 13:7

እግዚአብሔር ቤተሰቦቻችሁን: አገልግሎታችሁን እና ዘመናችሁን አብዝቶ ይባርክ🙏!
===👇👇👇👇
''Warra isin geggeessanii, dubbii Waaqayyoo isinitti himanii turan yaadadhaa! Attamitti akka jiraatan akka du'anis, jireenya isaanii keessaa wanta argames ilaalaa, fakkeenya amantii isaanii fudhadhaa duukaa bu'aa!'' Ibroota 13:7

Pirezidaantota WWW Makaana Yesuus Itoophiyaa waliin...

Waaqayyo Gooftaan maatii, tajaajilaa fi bara keessan hundumaan dachaan haa eebbisuu, Nuuf Jiraadhaa🙏!
===👇👇👇👇
''Remember your leaders, who spoke the word of God to you. Consider the outcome of their way of life and imitate their faith.'' Hebrews 13:7
With EECMY Presidents since 1991
1. Rev. Yadesa Daba 1991-2001
2. Rev. Itefa Gobena 2001-2009
3. Rev. Dr. Wakseyoum Idossa 2009-2017
4. Rev.Dr. Yonas Yigezu, Since 2017

May God bless you, your family and your ministry abundantly! #Long_Live🙏!
Forwarded from EECMY Youth Ministry
Have you registered for the All Africa Youth Congress?
Here is how you do it;

Step 1: Application to show interest to attend AAYC

Step 2: Selection of applicants and shortlisting of participants

Step 3: Payment of registration fee

Step 4: Confirmation of participation to AAYC
click on the link to register https://allafricayouthcongress.org/register
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ_አይለያችሁ !

የ " FIAS 777 " ጉዳይ ከተነሳ በኃላ በርካታ የቤተሰባችን አባላት ልክ እንደ " FIAS 777 " ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን እየጠቆሙ ይገኛሉ።

እነዚህ አካላት ያለብንን የኢኮኖሚ ችግር ተገን አድርገው " በአጭር መንገድ ትርፋማ የሚሆኑበት የማለፋ ስራ " እያሉ በርካታ ወጣቶችን እየቀሰቀሱ ገንዘባቸውን ላፍ እያደረጉ ናቸው።

ውድ ቤተሰቦቻችን ተጠያቂ የምታደርጉት ሰው በሌለበት፣ ቢሮ ሆነ አድራሻ በሌላቸው ሰዎች ፣ ነገ ይቀጥል አይቀጥል የሚለውን በማታውቁት ሂደት በአሰቸጋሪ ሁኔታ ደክማችሁ ለፍታችሁ ያገኛችሁትን ገንዘብ፣ ተበድራችሁ ያገኛችሁትን ገንዘብ ፣ ተማሪዎችም ከቤተሰብ የተቀበላችሁትን ገንዘብ ለቀማኞች እንዳታውሉት አደራ እንላለን።

ብዙሃንን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራ በሚስጥር አይሰራምና ገንዘባችሁን ከሚያሳጣ ማንኛውም የአጭበርባሪዎች እንቅስቃሴ ራቁ።

ሌላው ደግሞ የስልክ ቀፎ፣ ቴሌቪዥን፣ ላፕቶፕ... የመሳሳሉ እቃዎችን በርካሽ ከደቡብ አፍሪካ ፣ ከኬንያ በሞያሌ በኩፓ እናስመጣለን እያሉ ቅድመ ክፍያ እየተቀበሉ እብስ የሚሉ አሉና ተጠንቀቁ።

ሰዎችን ማታለያ መንገዶች አይነታቸውን እየቀያየሩ እየበዙ ነውና ህጋዊ ተጠያቂነት ያለባቸው ስራዎች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጉ።

ሁሌም ጥንቃቄ ማደረጋችሁን አትዘንጉ።

@tikvahethiopia
With Lutheran World Federation General Secretary Rev. Rev. Anne Burghardt

The Lutheran World Federation is a global communion of 148 churches in the Lutheran tradition, representing over 77 million Christians in 99 countries. The LWF acts on behalf of its member churches in areas of ecumenical and interfaith relations, theology, humanitarian assistance, human rights, communication and the various aspects of mission and development.

The General Secretary of the LWF carries out the decisions of the LWF Assembly and Council.
Rev. Anne Burghardt is the first woman to hold this leadership position. (LWF)

Dear Rev. Anne Burghardt, may God guide you, & bless our communion so that it may be a blessing to the wider church and to the world.

(Photo: Wondmagegn Udessa, EECMY Children & Youth Ministry Director with Lutheran World Federation General Secretary Rev. Anne Burghardt in Addis Ababa, Ethiopia, @Elily Int'l Hotel, During the Africa Lutheran Church Leadership Consultation (June 28- July 01, 2022)
With Archbishop Dr Panti Filibus Musa, President of Lutheran World Federation
===
Currently Dr Panti Filibus Musa
serves as the Archbishop of  the Lutheran Church of Christ in Nigeria.
He was elected by the LWF Twelfth Assembly at its May 2017 meeting in Windhoek, Namibia. He is the thirteenth person to serve in the position of president since LWF’s founding in 1947.
The President is the presiding officer of the Assembly, the Council and the Executive Committee. He oversees LWF’s life and work in consultation with the General Secretary. (LWF)

(Photo: Wondmagegn Udessa, EECMY Children and Youth Ministry Director with Archbishop Dr Panti Filibus Musa, President of Lutheran World Federation in Addis Ababa, Ethiopia, @Elily Int'l Hotel, During the Africa Lutheran Church Leadership Consultation (June 28- July 01, 2022)
የመጀመሪያ ኃጢያት እና የተሰጠው የአዳኙ ተስፋ (ዘፍጥረት 3 )

👇👇👇
የመጀመሪያ ኃጢያት እና የተሰጠው የአዳኙ ተስፋ (ዘፍጥረት 3 )

ውድ ልጆች: ባላችሁበት የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ:: በዛሬው ትምህርታችን የመጀመርያው ሀጥያት ምን እንደነበረ: ሀጥያት ወደዚህ ዓለም እንዴት እንደገባ: እግዚአብሔርም የመዳኛ መንገድን እንዴት እንዳዘጋጀ እናያለን።
በኤደን ገነት ውስጥ የሚያፈሩ ብዙ ዛፎች ነበሩ ክፉውንና መልካሙን የሚለየው የእውቀት ዛፍ በኤደን ገነት መካከል ተተክሎ ነበር ። እግዚአብሔር ስለዚህ ዛፍ አዳምንና ሔዋንን እንዲህ ሲል አዝዞአቸው ነበር:  ‹‹በዚህ ገነት ውስጥ ካሉት ዛፎች ሁሉ የምታገኙትን ፍሬ መብላት ትችላላችሁ ነገር ገን በገነት መካከል ከተተከለው ከዚህ ዛፍ ፍሬ አትብሉ እነሆ እርሱን በበላችሁ ጊዜ ሞትን ትሞታላችሁ፡፡››

 

አንድ ቀን አዳምና ሔዋን በገነት ውስጥ እንዳሉ ዲያቢሎስ በእባብ ተመስሎ ወደ አዳምና ሔዋን መጣ። ከዚያም ‹‹እግዚአብሔር በገነት ውስጥ ካሉት ዛፍ ሁሉ ፍሬ እንዳትበሉ አዝዞአችኋልን?››አላቸው፡፡  ሔዋንም እንዲህ አለች፡- ‹‹በገነት ውስጥ ካሉት ዛፎች ከየትኛውም የሚገኘወን ፍሬ መብላት እንችላለን፡፡ ነገር ግን በገነት መካከል የሚገኘው ዛፍ ፍሬ እንዳንበላ እንዳንነካውም እግዚአብሔር ከልክሎናል: አለበለዚያ እንሞታለን፡፡››

 

ዳያቢሎስም ሲያታልላቸው ‹‹ይህ እውነት አይደለም አትሞቱም እኔን ስሙኝ : ከዚህ ዛፍ ፍሬ ከበላችሁ እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ  መልካሙንና ክፉውንም ታውቃላችሁ›› አላቸው፡፡ ሔዋንም የዛፉን ፍሬ ተመለከተች ሲያዩት ያምራል: ስለሆነም አንዱን ፍሬ ቀጠፈችና በላች ሌላውንም ፍሬ ቀጥፋ ለአዳም ሰጠችው: እርሱም ደግሞ በላ፡፡ አዳምና ሔዋን ለእግዚአብሔር አልታዘዙም: ይህ የመጀመሪያው ኃጢአታቸው ነበር፡፡ ታላቅ ፍርሃት ፈሩ፡፡ እግዚአብሔር እንደሚቆጣ አወቁ ስለሆነም በገነት ውስጥ ከእግዚአብሔር ፊት ተሸሸጉ፡፡

 

አዳምና ሔዋን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን አደረጉ፡፡ እግዚአብሔር ግን አሁንም በጣም ይወዳቸዋል፡፡ በሀጥአታቸው ምክንያት ለዘላለም እንዲቀጡ አልፈለገም፡፡ ስለሆነም የሚያስደንቅ ቃል ኪዳን ገባላቸው፡፡ እንዲህ አላቸው ‹‹ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ ልጄን ወደ ዓለም እልከዋለሁ: እርሱ ከሴት ይወለዳል ሰውም ይሆናል፡፡ እርሱ ኃጢአታችሁን ያስወግዳል›› አዳምና ሔዋን ይህን አስደናቂ ቃል ኪዳን ስሙ፡፡ ቃል ዲሳኑንም አመኑ። እግዚአብሔር እንደሚወዳቸው አዳኙም የእርሱን ኃጢአት ለማስወገድ እንደሚወለድ አወቁ፡፡ እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ጠበቀ: ከብዙ ዓመታት በኋላ የእግዚአብሔር ልጅ በቤተልሄም ተወለደ ስሙም ኢየሱስ ተባለ:  ኢየሱስም ሰው በሆነ ጊዜ ፍጽምና ያለውን ሕይወት ኖረ አንዳችም ስህተት አላደረገም፡፡ የህዝብ ሁሉ ኃጢያአት የሚያስተካክለውን ቅጣት በራሱ ላይ ወስዶ በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ለዚህ ነው ኢየሱስን የዓለም አዳኝ ነው የምንለው፡፡

 

እግዚአብሔር ሁሉንም አዳምና ሔዋንን ይወዳል ከገነት ውሰጥ እነሱን ማስወጣት ነበረበት እንደገና ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ በልተው ኃጢያታቸው ጋር ለዘላለም እንዲኖሩ አልፈለገም፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር የእሳት ነበልባል የሆነ ሰይፍ የያዘ መልአክ ወደ ገነት ልኮ ከዚያ እንዲወጡ አደረገ፡፡ አዳምና ሔዋን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በረጅሙ የህይወት ዘመናቸው ኃጢያት በማድረግ ቀጠሉ ከዚያም በኋላ ሞቱ፡፡ እግዚአብሔር አዳኝ እንደሚልክላቸው የገባላቸውን ተስፋ አመኑ፡፡ ኢየሱስ ኃጢያት ወደሌለበት ከእርሱ ጋር እንዲኖሩ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይወስዳቸዋል፡፡

#የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጥቅስ : ሮሜ 5:14-21 (ከወላጆቻችሁ/ከታላላቆቻችሁ ጋር አጥኑ)።

ጥያቄ

1.       አዳምና ሔዋንን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ ምን አደረጉ?

2.      እግዚአብሔር ለእነርሱ የገባላቸው የተስፋ ቃል ምንድን ነበር?   አዳኛቸው ማን ነው?

3.   ከዚህ ክፍል ምን ተማራችሁ?

መልሳችሁን በሃሳብ መስጫ ቦታው ላይ ጻፉ! በተከታታይ የ5 ትምህርቶችን መልስ በትክክል ከመለሳችሁ የመጽሐፍ ሽልማት ይኖራችኋል።

መልካም እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!

http://www.mysundayschool.org
https://t.me/MYSundaySchool