EECMY Children Ministry: MY Sunday School
736 subscribers
892 photos
14 videos
168 links
MY Sunday School is the official page of EECMY Children Ministry.

Wholistic Growth For Our Children!

Access Sunday School learning materials at www.mysundayschool.org
Download Telegram
EECMY Children Ministry: MY Sunday School
Photo
ለልጆች አገልጋዮች ስልጠና ተሰጠ
TAJAAJILTOOTA IJOOLLEETIIF LEENJIIN KENNAME!
***
የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ በሁለንተናዊ የልጆች እና ወጣቶች ዕድገት ላይ ያተኮረ ፡ ልጆች እና ወጣቶችን በሁለንተናዊ መልኩ ቀርጾ ለማሳደግ የሚረዳ ሁለንተናዊ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት ፓኬጅ ቀርጾ እየሰራበት ይገኛል፡፡ ከፓኬጁ የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ በሆነው የአገልጋዮች አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በጉዲና ቱምሳ በሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል ከሶስት ሲኖዶሶች:- ማለትም ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ: አዲስ አበባ ሲኖዶስ እና ፊንፊኔ እና አካባቢው ቤቴል እጩ ሲኖዶስ: እንዲሁም ፊንፊኔ ኦሮሞ ማ/ም ጨምሮ: ከአዲስ አበባና ከሸገር ከተማ ለተወጣጡ የልጆች አስተማሪዎችና አስተባባሪዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናው የተዘጋጀው በልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ሲሆን፡ በመምሪያው ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ እና በልጆች አገልግሎት ክፍል አስተባባሪ ዶ/ር ሊድያ ተፈራ አስተባባሪነት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል::

ስልጠናው 'ዘመኑን ማወቅ እና ትውልዱን መታደግ' በሚል ርዕስ የተሰጠ ሲሆን: በተለያየ ርዕሶች ላይ በቂ እውቀት እና ልምድ ያላቸው አገልጋዮች እንዲሳተፉ ተደርጔል::
1ኛ. 'በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ልጆቻችንን እንዴት እናስተምር' በሚል ርዕስ ከእህት ትዕግስት ገላጋይ ጋር (Children Development Specialist) ልጆችን ከማስተምራችን በፊት ልጆችን መረዳት እንደሚያስፈልግ እንዴትስ መረዳት እንዳለብን ከእግ/ር ቃል አንፃር እንዲሁም ከሳይንሳዊ ዕውቀት ጋር physiologically የጭንቅላት የዕድገት ልካቸውን በመረዳትና በማወቅ ማስተማር እንዳለብን አስተምረዋል እንዲሁም በተጨማሪ የመፅሀፍ ስጦታ "መወጣጫ ከራስ መገናኛ"በሚል ርዕስ በራሳቸው የተፃፈ መፅሐፍት ለአገልግሎት ክፍሉ አበርክተዋል::
2. 'ትውልድን መዋጀት' በሚል ርዕስ ዶ/ር ስዩም አንቶንዮስ-Medical Doctor and Educational Specialist :- Comprehensive Sexual Education ምን እንደሆነና በውስጡ ብዙ ለትውልዱ አደጋ የሆኑ ጉዳዮችን እንደያዘና ቤተክርስቲያን ይሄን ጉዳይ በግልጽ በመቃወም አቋሟን መግለፅ እንዳለባት: እንዲሁም አገልጋዮች ዘመኑን በማወቅ ትውልዱን በፀሎትና በማስተማር መጠበቅ እንዳለብን አበክረው አስተምረዋል:: እንዲሁም “Stand for the Family “በሚል ርዕስ የተፃፈ መፅሐፍት በስጦታ መልክ ለአገልግሎት ክፍሉ አበርክተዋል::

3. እንዲሁም ሄላና ሳንድበርግ (Educational Specialist) ከፊንላድ ሀገር የመጡ አሰልጣኝ እና የትምህርት ባለሙያ ሲሆኑ :ከEELC ጋርም በጋራ ይሰራሉ::'እንዴት የትምህርት ዕቅድ/Lesson Plan ማዘጋጀት እንችላለን' በሚል ርዕስ በጣም ግልፅና ለልጆች በሚገባቸው መንገድ የሚጠቅም ስልጠና የሰጡ ሲሆን አስፈላጊ የስልጠና መጽሐፍት በስጦታ መልክ እበርክተዋል::
4. በጠዋት የፀሎት ሰዓታችን ላይ -በቄስ ሙላቱ ዘለቀ የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ የቤተሰብ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ 'ልጆችን በማሳደግ የወላጆች ድርሻ' በሚል ርዕስ ያስተማሩ ሲሆን : -ዶ/ር አስካለ አስፈው (Children Development Specialist) በወላጆች እና ልጆች መካከል ያለውን መራራቅ መሙላት 'Bridging Generations- Parent’s and Children' በሚል ርዕስ አስተምረውናል::

በአጠቃላይ በነበረው ጊዜ በልጆች እድገት ውስጥ ትልቁን ቦታ የሚወስዱት 1ኛ. ወላጆች 2ኛ.ቤተክርስቲያን 3ኛ. የልጆች አስተማሪዎች መሆናቸውን በመረዳት ሁሉም በመተባበር በትኩረት መስራት እንዳለባቸው መረዳት ተችሏል:: በመጨረሻም ከሉተራን ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለልጆች ማስተማርያነት የሚረዱ የተለያዩ መጽሐፍቶችን እና ጽሁፎችን ማዳረስ ተችሏል::
በአጠቃላይ ስልጠናው ውጤታማ የህብረት: የመማማር እና ልምድ የመለዋወጥ ጊዜ ነበረ::

ስለነበረን ጊዜ እግዚአብሔር ይባረክ!
እግዚአብሔር አገልግሎቱን ይባርክ::
***
BARSIISOTAA FI QINDEESSITOOTA TAJAAJILA IJOOLLEETIIF LEENJIIN KENNAME!
***
WKWWMYI'tti Qajeelchi Tajaajila Ijoollee fi Dargaggoo, guddina hundagaleessa ijoollee fi dargaggootaa waliigalaa irratti kan xiyyeeffate paakeejii hunda-galeessa qopheessee irratti hojjachaa jira. Qaama xiyyeeffannaa paakeejichaa keessaa tokko kan ta’e tajaajiltoota ijoollee leenjiidhaan guddisuu, hubannaa gaarii qabsiisuu irratti kan xiyyeeffate, leenjiin bal'aan Giddugala Leenjii Guddinaa Tumsaatti tajaajiltoota ijoollee sinoodoosota sadi, jechuunis: Sinoodoosii GidduGaleessa Itoophiyaa, Sinoodoosii Addis Ababaa fi Sinoodoosii Kaadhimamaa Beeteel Finfinnee fi Naannoo Isaa, akkasumas Waldaa Amantoota Oromoo dabalatee, waldaa amantootaa garagaraa Magaalaa Finfinnee fi Magaalaa Shaggar irraa walitta qabamaniif kennameera.
Leenjichi kan qophaa'e Qajeelcha Tajaajila Ijoollee fi Dargaggootaa waldattiitiin yoo ta'u, Daayireektara Qajeelchichaa Wondimmaagany Uddessaatii fi qindeessituu Tajaajila Ijoollee Waldattii Dr. Liidiyaa Tafarraatiin gaggeeffameera.
Leenjichi 'Baricha Beekuu fi Dhaloota Oolchuu' Mata duree jedhuun kan gaggeeffame yoo ta'u mata dureewwan garagaraa irratti tajaajiltoota beekumsaa fi muuxannoo cimaa qabaniin leenjichi akka kennamu godhameera.

1ffaa: Jaarraa 21ffaatti Ijoollee Keenya Akkamitti Haa Barsiifnu?' mata duree jedhu irratti Leenjistuu Tigist Gelaagay wajjiin (Children Development Specialist),

2. 'Dhaloota Oolchuu' mata duree jedhu irratti Dr. Siyyuum Antooniyoos (Medical Doctor and Educational Specialist) fi haadha manaasaa waliin,

👇👇👇
@MYSundaySchool
EECMY Children Ministry: MY Sunday School
Photo
👆👆👆
👇👇👇

3. 'Akkamitti Qophoofnee Ijoollee  Barsiisna' mata duree jedhu irratti, Ms. Helena Sandberg (Educational Specialist) biyya Fiinlaandii irra kan dhufan waliin ta'uun leenjiin bal'aan hirmaattotaaf kennameera.
4. Yeroo kadhannaa fi Barumsa Dubbii Sagalee Waaqayyoo ganamaa irratti, mata duree 'Guddisa Ijoollee Keessatti Gahee Maatii' jedhu irratti Luba Mulaatuu Zallaqaa, Qajeelchaan Tajaajila Maatii Waldattii barumsa kan kennan yoo ta'u, guyyaa 2ffaatti immoo Dr. Askaalee Asfaaw (Children Development Specialist) biyya Ameerikaa (USA) irraa, walirraa fageenya Maatii fi Ijoollee Xiqqeessuu' 'Bridging Generations- Parent’s and Children' jedhu irratti barumsi bal'aan kennameera. Leenjicha irratti, guddina ijoollee keessatti gahee guddaa kan taphatan, maatii, Waldaa Kiristaanaa fi barsiisota ijoollee ta'uun isaanii hubatamee, hundumtuu tokkummaadhaan irratti akka hojjatuuf waamichi dhiyaateera. Dhumarrattis, Faawundeeshinii Heeriteejii Luteraanii waliin ta’uun kitaabotaa fi barruulee adda addaa ijoollee barsiisuu keessatti gargaaran hirmaattotaaf raabsuun danda’ameera.
Walumaagalatti, leenjichi yeroo milkaa'aa tokkummaa hafuuraa, yeroo barumsaa fi muuxannoo waliif jirjiiruu ture.

Yeroo bareedaa Waaqayyo nuuf kenneef galanni barabaraa Isaaf haa ta'u!
Waaqayyo Tajaajila Keenya Haa Eebbisuu!

📷: EECMY- YDCS Mekane Yesus TV ( 0911454205)
https://t.me/MYSundaySchool
Forwarded from EECMY Youth Ministry
'ሁለንተናዊ ዕድገት ለሁለንተናዊ ስኬት'
የ2016 ዓ.ም የወጣቶች በዓል መልዕክት

'Holistic Growth For Holistic Success'
EECMY 2016/2024 Youth Day Message

#EECMY #YouthDay #2016EC #2024
#መካነኢየሱስ #ወጣቶች #በዓል
https://t.me/eecmyyouthministry
The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus
Mekane Yesus TV
EECMY Youth Ministry
Forwarded from EECMY Youth Ministry
'GUDDINA HUNDA-GALEESSA MILKAA'INA HUNDA-GALEESSAAF'

Ergaa Ayyaana Dargaggootaa Bara 2016/2024

#EECMY #YouthDay #2016EC #2024
#MekaneYesus #Dargaggoo
https://t.me/eecmyyouthministry
@EECMY Youth Ministry
ኢትዮጵያ በቅርቡ ከአውሮፓ ህብረት ጋራ የፈረመችውን ስምምነት በመቃወም የተዘጋጀ የፊርማ ማሰባሰቢያ ቅጽ
        * ⚠️ አስቸኳይ⚠️  *
ባሳለፍነው ህዳር 5 ቀን 2016 ዓም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ ከካሪቢያንና ከፓሲፊክ የተውጣጡ ሀገራት ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የሚቆይ የንግድና ኢኮኖሚ ትብብር ስምምነትን ከአውሮፓ ህብረት ጋራ ሳሞዋ በምትባል ሀገር በፈረሙ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያም ይህንኑ ስምምነት ተቀማጭነታቸው ብራሰልስ በሆኑ አምባሳደV አማካኝነት በፊርማዋ አጽድቃለች፡፡ ይህ አደገኛ ይዘቶች ያሏቸውን አንቀጾች የያዘው ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ከሚቀጥለው ጥር ወር ጀምሮ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

ይህ የትብብር ስምምነት በውሥጡ የያዛቸውን አስራ ሁለት ዋና ዋና አደገኛ ይዘቶችን ጠቅልለው የሚይዙ የተወሰኑ ሀሳቦች ለመጥቀስ ያህል ፡-

ሀ) የሀገር ሉዓላዊነትን የሚጥሱ አንቀጾች በግልጽ መቀመጣቸው፣

ለ) ግብረሰዶማዊነት፣ የጾታ መቀየርና፣¸ውርጃና ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን የመሳሰሉ እኩይ አጀንዳዎች በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በሌሎች አሳሳች ሀረጎች ተሰውረው የገቡበት መሆኑ፣

ሐ) ግብረሰዶማዊነት በርካታ ቀውሶች ማለትም በአካል፣ በሥነልቦናና በማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያስከትልና ለሀገር ደህንነትም አደጋ መሆኑ፣

መ) የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን የሚንድ መሆኑ፣

ሠ) የሀገራችንን ሀይማኖት፣ባህልና እሴቶች የሚንዱ ጸያፍ ልምምዶችን እንድንቀበል በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በእርዳታ ስም የምንገደድበትና ለዘመናዊ ባርነት ወይንም ቅኝ አገዛዝ ታልፈን የምንሰጥበት መሆኑ፣

በአጠቃላይ ይህ አዲስ የአጋርነት ስምምነት ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡና ትውልድንና ብሎም ሀገርን እጅግ የሚጎዱ በርካታ አንቀጾች የተካተቱበት መሆኑ ለሀገራችን ህዝብ ዕድገትን ሳይሆን ውድቀትንና ከፍተኛ የሞራል ዝቅጠትን የሚያስከትል መሆኑን በሚገባ ተረድተናል፡፡

በተጨማሪም ከተጠበቀው ውጭ ሀገራችን ይህንን ስምምነት በመፈረJ የተጋረጠብንን እጅግ አሳሳቢ አደጋ ለመቀልበስ አስፈላጊ የሆኑ ሰላማዊና ህጋዊ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም መንግስት ትኩረትን እንዲሰጠው ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

በመሆኑም ይህ የመንግስት ውሳኔ እንደገና ተጠንቶ ውሳኔው እንዲቀለበስ ማለትም ስምምነቱ አስፈላጊው ሁሉ ማስተካከያ እስኪደረግበት ድረስ ወይንም እጅግ አደገኛ የሆኑት አንቀጾች ተነቅሰው ወጥተው የማንቀበላቸው መሆናችንን በይፋ ማሳወቅ (Submission of an Interpretive Declaration) እስከምንችል ድረስ የምንወዳት ሐገራችን ኢትዮጵያ ፊርማዋን በመሰረዝ ከስምምነቱ ራሷን እንድታገልል በሐገራችን ከፍተኛው የሥልጣን አካል ለሆነው ለተከበረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለሐገሪቱ መሪ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በታላቅ አክብሮት እጅግ አስቸኳይ ጥሪን እናደርጋለን፡፡

የዚህንም ስምምነት አደገኛ አንቀጾችንና በኤክስፐርቶች የተሰጠውን ትንታኔ የያዘ ዶኩመንት በአባሪነት ያቀረብን መሆናችንንም በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን፡፡


ፊርማውን ለመፈረም ሊንኩን ይጫኑ; አስፈላጊውን መረጃ ከሞላችሁ በኃላ 'አስገባ' የሚለውን ትጫናላችሁ... 'አስገባ' የሚለው ቀይ የነበረው ቀለም ወደ አርንጓዴ ሲቀየር ፈረማችሁ ማለት ነው::

ለሌሎችም እንዲደርስ #Share #Forward በማድረግ ተባበሩ!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ: ይጠብቃትም!

https://keap.page/gq193//landing-page.html#appId=gq193;siteRef=bd460600-7d31-466c-8ab1-0f3f3cbd6ed0;pageRef=edad85db-899a-4ca1-a1ba-bf5db45dda57

#Ethiopia #Children #Youth #SaveGeneration #SaveTheChildren #SaveTheYouth
Forwarded from EECMY Youth Ministry
“ሁለንተናዊ ዕድገት ለሁለንተናዊ ስኬት”

የኢት./ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ የወጣቶች በዓል
መጋቢት 29፤ 2016 ዓ.ም (April 07, 2024)

መሪ ጥቅስ: "ኢየሱስም... በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።" ሉቃ. 2:52

#ዓላማ:- ወጣቶቻችን በሁለንተናዊ መልኩ እንዲያድጉ እና ለስኬት እንዲበቁ፤ ለእግዚአብሔር መንግስት አገልግሎት አልፎም ለትዉልዱ በረከት እንዲሆኑ፡ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን መንፈሳዊ ጸጋ እና የተፈጥሮ ችሎታ አውቀው እና አሳድገው እንዲጠቀሙበት...

EECMY Youth Ministry
Telegram:https://t.me/eecmyyouthministry
Forwarded from EECMY Youth Ministry
“Guddina Hunda-Galeessa Milkaa'ina Hunda-galeessaaf”

Ayyaana Dargaggootaa WKWWMYI
Bitootessa 29/2016 ALI (April 07, 2024ALA)

Luqqisii Duree: "Yesuus...Waaqayyoo fi namoota duratti ayyaana argachaa, namummaadhaa fi ogummaatti in guddata ture." Luqaas 2:52

Kaayoo: Dargaggootni keenya bifa hundagaleessaan guddatanii akka milkaa’aniif; hojii babal’isuu Mootummaa Waaqayyoo keessatti gahee isaanii akka bahanuuf, dabalataan ofirra darbanii dhalootaaf eebba ta’uu akka danda’aniif, ayyaanaa fi kennaa addaa Waaqayyo biraa isaaniif kenname adda baafatanii, guddisanii akka itti fayyadamaniif ciminaan isaanirratti hojjachuu...

EECMY Youth Ministry
Telegram:https://t.me/eecmyyouthministry
Forwarded from EECMY Youth Ministry
'Holistic Growth For Holistic Success'

EECMY Youth Day, Megabit 29, 2016/ April 07, 2024

"Jesus grew in wisdom and stature, and in favor with God and men." Luke 2:52

#Purpose:- To equip our youth in a holistic way and help them to be successful; to serve God's kingdom and be a blessing to the generation, to know and develop the spiritual gifts and natural talents given to them by God...

EECMY Youth Ministry
Telegram:https://t.me/eecmyyouthministry
Forwarded from EECMY Youth Ministry
የወጣቶች በዓል መልዕክት
Ergaa Ayyaana Dargaggootaa...
EECMY Youth Day Message, 2024

#ComingSoon #staytuned
📷 📹 Olif Jira Dhufera, EECMY Digital Media Head
https://t.me/eecmyyouthministry
Forwarded from EECMY Youth Ministry
የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ ካለንደር: ሚያዚያ 2016

Kaalandarii WKWWMYI, Ebla 2016/2024

(Source: EECMY- Yemisrach Dimts Communication Service)


@eecmyyouthministry
@MYSundaySchool