EECMY Children Ministry: MY Sunday School
746 subscribers
894 photos
14 videos
169 links
MY Sunday School is the official page of EECMY Children Ministry.

Wholistic Growth For Our Children!

Access Sunday School learning materials at www.mysundayschool.org
Download Telegram
እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረ (ዘፍጥረት 1)
🌎🌒🌞🌛🐦🦚🦜🦆🦄🦋🐅🐏🐄🌴🌾🍃🍇🍓🍃🌻🍉👫👨‍👩‍👧‍👦

ቀጥላችሁ አንብቡ!👇
እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረ (ዘፍጥረት 1)
🌎🌒🌞🌛🐦🦚🦜🦆🦄🦋🐅🐏🐄🌴🌾🍃🍇🍓🍃🌻🍉👫👨‍👩‍👧‍👦
ውድ ልጆች በያላችሁበት የእግዚአብሔር ሰላም ይብዛላችሁ! ከብዙ ዘመናት በፊት ይህ ዓለም አልነበረም፡፡ ወፎች፣ ንቦች ሜዳና አበቦችም አልነበሩም፡፡ ሐይቆች ወንዞች ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትም  አልበሩም ሰዎችም አልነበሩም ሰዎችም አልነበሩም ምንም ነገር አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር ብቻ ነበር፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ምድርን ፈጠረ፡፡ ሰማይና ምድርን ፈጠረ ሁሉን ነገር ከማይታይ ነገር ፈጠረ እግዚአብሔር ዓለምን በውስጧ ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ ፈጠራቸው አንዳንዱን በአንድ ቀን ፈጠረ እግዚአብሔር ማኛውንም ነገር ሲፈጥር ‹‹ እንዲህ ይሁን››ይል ነበር፡፡ ያም ነገር ይሆናል፡፡

በመጀመሪያ ጨለማ በሁሉም ስፍራ ነበር ስለሆነም እግዚአብሔር ‹‹ ብርሃን ይሁን አለ›› እግዚአብሔር ይህንን እንዳለ ሆነ፡፡ ብርሃኑም የቀን ብርሃን ነበር ይህም የመጀመሪው ቀን ነው፡፡ በሚቀጥለው ቀን እግዚአብሔር ሰማዩን ከእኛ በላይ ከፍ እንዲል ተናገረው እርሱም ሆነ  ይህም ሁለተኛ ቀን ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ውሃ በአንድ ስፍራ እንዲሰበሰብ አዘዘ በዚህም መንገድ ወንዞችን ባሕሮችን እና ውቅያኖስን ፈጠረ፡፡ በመካከላቸውም ደረቅ ምድረ በዳ ሆነ፡፡

ነገር ግን በምድር ላይ አንዳች ነገር አልበቀለም ነበር፡፡ ዛፎችና ቁጥቋጦዎች ወይም አበቦች በየትኛውም ሥፍራ አልነበሩም፡፡ እግዚአብሔር ተናገረ እፅዋትን ፈጠረ፡፡ ሜዳዎች ሁሉ አረንጓዴ ሣር ለበሱ፡፡ የሚያማምሩና ብዙ ዓይነት ቀለም ያላቸው አበባዎች በመሬት ላይ በቀሉ ቁጥቋጦዎችና ዛፎች በየዓይነቱ ነበሩ፡፡ ብዙዎቹ ቁጥቋጦዎችና ዛፎችም ፍሬዎች ነበሩአቸው፡፡እግዚአብሔር ለእፅዋቶቹ ዘርን ሰጣቸው ስለሆነም ሁልጊዜ ብዙ እፅዋት ያድጋሉ፡፡እግዚአብሔር እነዚህን ሁሉ በሦስተኛው ቀን አደረገ፡፡

እግዚአብሔር ከዚህ የበለጠ ፈጥሮአል እግዚአብሔር ተናገረ ሰማይም በአንድ ግዜ በብርሃን ተሞላ ፀሐይና ጨረቃን በሌሊትም የሚያብለጨልጩትን ከዋክብት ፈጠረ፡፡ ይህም በአራተኛው ቀን ሆነ፡፡ ምድር አሁን የምታምር ሆነች እግዚአብሔር ከዚህም የተሸለች አድርጓታል እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ደግሞ ተናገረና ዓሣንና በባሕር ውስጥ የሚኖሩትን ልዩ ልዩ ወፎች ሞላቸው እግዚአብሔር እነዚህን ሁሉ በአምስተኛው ቀን አደረገ፡፡

በስድስተኛው ቀን እግዚአብሔር እንደገና ተናገረ፡፡ ንቦች ከአንዱ አበባ ወደ ሌላው እንዲበሩ አደረገ፡፡ ድመቶችና ውሾች በሜዳ ላይ ይጫወታሉ ፈረሶችና ላሞች ምግባቸውን እየፈለጉ ወዲያና ወዲህ ይሉ ነበር፡፡

እግዚአብሔር ሁሉንም ዓይነት እንሰሶች በምድር ላይ የሚመላለሱ ፍጥረታትን ሁሉ እንዲሁም የምድር አራዊትን ሁሉ ፈጠረ፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሔር ሰዎችን ፈጠረ፡፡ እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ሰውን ከምድር አፈር አበጀው እንዲሁም በአፍንጫው እፍ አለበት፡፡ እግዚአብሔር ቀጥሎ የመጀመሪያውን ሴት ለመጀመሪያው ሰው እረዳት እንድትሆን ፈጠራ፡፡ እግዚአብሔር የመጀመሪያዋን ሴት የፈጠራት ከአዳም የጎድን አጥንቶች አንዱን በመውሰድ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከፈጠራት በኋላ ሚስት እንድትሆነው ወደ አዳም አመጣት አዳምም ሔዋን ብሎ ስም አወጣላት፡፡ እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ሁሉ ተመለከተ እንሆ ሁሉም መልካም ነበር በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አረፈ ሰባተናውንም ቀን ባረከው ቀደሰውም፡፡

1. እግዚአብሔር ዓለምን በስንት ቀናት ውስጥ ፈጠረ?
2. በየቀኑ የፈጠራቸውን ጥራ?
3. እግዚአብሔር የፈጠራቸው የመጀመሪያው ወንድና የመጀመሪያው ሴት እነማን ነበሩ?

መልሳችሁን በሃሳብ መስጫ ቦታው ላይ ጻፉ!

መልካም እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!

http://www.mysundayschool.org
https://t.me/MYSundaySchool
Waaqayyo Biyya Lafaa Uume (Seera Uumamaa 1)
🌎🌒🌞🌛🐦🦚🦜🦆🦄🦋🐅🐏🐄🌴🌾🍃🍇🍓🍃🌻🍉👫👨‍👩‍👧‍👦

Itti fufaatii dubbufadhaa👇!
Waaqayyo Biyya Lafaa Uume (Seera Uumamaa 1)
🌎🌒🌞🌛🐦🦚🦜🦆🦄🦋🐅🐏🐄🌴🌾🍃🍇🍓🍃🌻🍉👫👨‍👩‍👧‍👦
Jaalatamoo ijoollee keenya, nageenni Waaqayyoo isiniif haa baay'atuu!
Durii, durii biyyi lafaa hin turre. Simbirroommii fi kannisonni, dirreewwanii fi daraaronni, bishaan ciisaa fi lageen, biiftuun, ji'aa fi urjoonni hin ture. Namoonni iyyuu hin ture. Homti tokko iyyuu hin turre. Waaqayyo qofaatu jira ture. Ergasii Waaqayyo lafa uume. Inni waaqaa fi lafa uume. Hundumaa iyyuu waan hin jirre irraa uume. Waaqayyo guyyoota ja’a keessatti biyya lafaa kana uume. Guyyaa guyyaatti wantoota murtaa’oo uume. Waaqayyo yeroo wantoota sana hunda uume, “Kun haa ta’u” jedhee dubbate, innis ni ta’e.

 

Jalqabatti bakka hundumaa irra dukkanatu ture. Waaqayyo, “Ifni haa ta’u!” Jiedhe. Battala Waaqayyo kana dubbatetti, ifnis ni ta’e. Ifichi akka guyyaatti ifa ture. Kunis guyyaa tokkoffaa ture.

 

Guyyaa isa itti fufutti Waaqayyo dubbatee waaqa (samii) nuun ol jiru kana uume. Kunis guyyaa lammaffaa ture.

 

Iffi fufees, Waaqayyo akka bishaan bakkawwan murtaa’anitti akka walitti qabamuuf itti dubbate. Akka Kanatti, lageen, haroo fi garba/bishaanota ciisaa uume. Lafti gogaan gidduu gidduu isaanii ture.

 

Garuu wanti tokko iyyuu laficha irratti hin biqille. Mukeetin, bosonni, yookiis daraaronni eessayyuu hin turre. Ergasii Waaqayyo dubbatee biqiltuuwwan taasise. Margi magariisi dirree uffise. Daraarawwan babbareedoon haalluu hedduu qaban lafa irratti guddatan. Daggalaa fi mukeetiin qomoo hundaas ni jiraatan. Daggaloonni hedduun sanyii qabu, mukeetiin hedduunis ija/firii qabu. Akka isaany yeroo hundumaa baayyataniif Waaqayyo biqilaawwaniif sanyii kenneef. Kana hundaa waaqayyo guyyaa sadaffaatti hojjate.

 

Waaqayyo ittuma fufee hojjete. Inni ammas ni dubbate, si’a tokkichatti waaqni ifawwaniin guute. Inni biiftuu fi ji’a,akkasumas urjoota halkan ifan uume. Kun guyyaa afuraffaatti ta’e.

 

Amma lafti ni miidhage, waaqayyo garuu kana irra akka wayyaa’u taasise. Waaqayyo ammas dubbatee qurxummii fi uumamawwan bishaan daakan qomoo hundaa uume. Qilleensaa fi mukeetiis qomoo simbirrootaa hundumaan guute. Waaqayyo kana hundaa uume. Qilleensaa fi mukeetiis qomoo simbirrootaa hundumaan guute. Waaqayyo kana hundumaa gaafa guyyaa shanaffaa hojjete.

 

Guyyaa ja’affaatti, Waaqayyo ammas ni dubbate. Kanniisommi daraaraa irraa gara daraaraa isa kaaniitti barrisan.  Adurreewwanii fi saroonni dirreewwan irra taphatan. Fardeenii fi loon nyaata isaanii barbaaduuf adeeman.

 

Waaqayyo beeyladoota hundumaa, loon, uumama Iafa irra adeeman, fi beeyladoota bosonatti galan hundaa uume.  Hundumaa booda, Waaqayyo nama uume. Waaqayyo nama isa jalqabaa biyyoo lafaa irraa tolche. Hafuuras funyaan isaatti in baafate, akkasitti namni uumama lubbuu qabaatee jiraatu ta’e. Waaqayyo namicha Addaam jedhee moggaase. Itti dabalees akka nama isa jalqabaa kana waliin jiraattuuf dubartii ishee jalqabaa uume. Waaqayyo lafee cinaachaa Addaam tokko irraa ishee tolche. Akka isheen haadha manaa isaaf taatuuf Waaqayyo gara namichaatti ishee geesse. Addaamis Hewwaan jedhee moggaase.

 

Waaqayyo waanuma hojjete hundumaa in ilaale, innis baay'ee gaarii ture. Guyyaa torbaffaatti Waaqayyo boqonnaa fudhate. Inni guyyaa torbaffaa ni qulqulleesses.

 

1.       Waaqayyo guyyaa meeqatti biyya lafaa kana uume?

2.       Wantoota Inni guyyaa guyyaatti uume dubbadhu?

3.       Dhiiraa fi dubartiin Waaqayyo jalqabatti uume eenyu fa’i?

👇👇👇

Deebii keessan nuuf barreessaa!
Guyyaa gaarii eebbaan guutuu isiniif haa ta'u!

http://www.mysundayschool.org
https://t.me/MYSundaySchool

 
TRAINING TIME FOR EMERGING LEADERS (Children and Youth)
===@EECMY Tullu Ejersa Saris Congr.
👉Children are the hope of the day after tomorrow, and youth are the hope of tomorrow and adults are the only hope of today.
👉A Church without children and young people is dead.
👉Therefore, the Church should be concerned about children and youth in their congregation and beyond.

#EquipChildrenandYouth!
#EquipEmergingLeaders!
ትውልድ በዕውቀት የምታነጽበት ቤተ መጻሕፍት ተመርቆ ተከፈተ...

EECMY- South West Bethel Synod:
Mizan Teferi Bethel Mekane Yesus

ቀጥለው ሙሉውን ያንብቡ

@MYSundaySchool
ቤተመጻሕፍት ተመርቆ ተከፈተ
#አንባቢዎች_መሪዎች_ናቸው
====
''የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል'' እንደሚለው ቃሉ (2ጢሞቴዎስ 3:16): በቤተክርስቲያኒቱ የልጆች እና ወጣቶች ሁለንተናዊ አገልግሎት ፓኬጅ መሰረት: ልጆች እና ወጣቶች: እንዲሁም አገልጋዮች እና መሪወች አንባቢዎች እንዲሆኑ: አንብበው እንዲማሩ: ተምረው እንዲያስተምሩ: ታድሰው ትውልዱን እንድያድሱ በማሰብ በእያንዳንዱ ማ/ምዕመናን መጠነኛ ቤተመጻሕፍት (Mini Library) እንዲደራጅ ታስቦ እና ታቅዶ እየተሰራበት ይገኛል።
ይኼንንም ራዕይ ተቀብለው ከግብ በማድረስ በደቡብ ምዕራብ ቤቴል ሲኖዶስ የምትገኘዋ የሚዛን ተፈሪ ቤቴል መካነ ኢየሱስ ማ/ምዕመናን ቀዳሚ ሆናለች።በሲኖዶሱ በነበረው የልጆች እና ወጣቶች የመሪዎች ስልጠና ወቅት የተደራጀውን ቤተመጻሕፍት ለእግዚአብሔር ክብር እና ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲሆን በጸሎት መርቀን ከፍተናል።
ይሄንን ራዕይ ተቀብለው በቀዳሚነት ስላስፈጸሙት
የሚዛን ተፈሪ ቤቴል መካነ ኢየሱስ ማ/ምዕመናን የልጆች እና የወጣቶች አገልግሎት አስተባባሪዎችን: የማ/ምዐሰመናኗን ሽማግሌዎች: ቄሶች እና በወንጌላውያንን: መጽሐፍትን በመለገስ አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ የሥራው ሁሉ ባለቤት እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ ይባርካችሁ ለማለት እንወዳለን።

ከዚህ በመቀጠል በከተማ ደረጃም ትውልዱን ወደ ዕውቀት ጎዳና የሚመራ ቤተመጻሕፍት ለማደራጀት የድርሻችሁን እንደምትወጡ ተስፋ እናደርጋለን። እኛ የዓለም ብርሃን እና የምድር ጨው እንድንሆን ተጠርተናልና ብርሃናችን ለሰው ሁሉ እንዲበራ ወደ ትውልዱ ወጥተን በመልካም ምግባራችን ብርሃን በመሆን እና ለምድሪቱም ጨው በመሆን ለእግዚአብሔር ክብር እና ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲሆን መስራት አለብን።

👉የወጣቱ ትልቁ ሀብት አዕምሮው ነው: አዕምሮ ደግሞ የሚገነባው እና የሚበለጽገው በእውቀት ነው: ከእውቀት ምንጮች ዋነኛው ደግሞ መጽሐፍ ነው። አንባቢ ትውልድ መሪ ነው (Readers are Leaders) እንደሚባለው ልጆች እና ወጣቶች መሪ ሆነው እንዲያድጉ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል።

👉ውድ ወጣቶች: መሪዎች: (አገልጋዮች)... በዚህ አጋጣሚ ሌሎች ማ/ምዕመናናትም ይሄን መልካም ተሞክሮ በመውሰድ: ትውልዱን ወደ ዕውቀት ጎዳና ለመምራት የሚፈይደውን በእያንዳንዱ ማ/ምዕመናን መጠነኛ ቤተመጻሕፍት (Mini Library)
ማደራጀት አለብን ብለን የጀመርነውን ራዕይ ከግብ እንድታደርሱ በጌታ ፍቅር አደራ ልንላችሁ እንወዳለን።በሚዛን ተፈሪ ቤቴል መካነ ኢየሱስ ያለውን እንቅስቃሴ አይተን ደስ ብሎናል። ትምህርቱ: ስልጠናው: ጉብኝቱ ይቀጥላል።

#ቤተ_መጽሐፍትን በማ/ም ደረጃ ለማደራጀት:
👉በየ ማ/ም ካሉት መጠነኛ ክፍል (ቢሮ) መጠቀም ይቻላል (የግድ አዲስ ግንባታ አያስፈልግም)
👉መጽሐፍትን የማሰባሰብ እንቅስቃሴን በመጀመር ሰዎች መጽሐፍትን እንዲለግሱ ማድረግ ይቻላል።
👉የገቢ ማሰባሰቢያ በማድረግ ተጨማሪ አዳዲስ መጽሐፎችንም በየጊዜው አቅዶ መግዛት ይቻላል።
👉መጽሐፎቹ ለመንፈሳዊም እንዲሁም ለጠቅላላ እውቀት የሚረዱ ሳይንሳዊ መጽሐፎች: ለሁለንተናዊ አገልግሎት የሚረዱ እንዲሆኑ መስራት:
👉ኮሚቴ በማዋቀር አገልግሎቱ ፈጣን: ምቹ እና ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል።

#ቤተመጽሐፍቱ ተደራጅቶ ሲራ ሲጀምር:.
👉ልጆች ያነባሉ...
👉ወጣቶች ያነባሉ...
👉አገልጋዮች ያነባሉ...
👉መሪዎች ያነባሉ...
👉ምዕመኑ ያነባል...
👉አንባቢ ትውልድ ይፈጠራል; በዕውቀት ህይወቱን; ቤቱን: ቤተሰቡን: አገልግሎቱን: ድርጅቱን: ሀገሩን ይመራል።

''መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤...'' (ሉቃስ 24:45); የምታነቡትን እንድታስተውሉ አእምሮአችሁ በኢየሱስ ስም የተከፈተ ይሁን!
===
ይህ መልዕክት ለሌሎችም እንዲደርስ #Share በማድረግ ይተባበሩን።

የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት የሚከተለውን አድራሻችንን ይጠቀሙ👇!

http://www.mysundayschool.org
https://t.me/MYSundaySchool
https://t.me/eecmyyouthministry