Tsegaye R Ararssa
16.4K subscribers
1.67K photos
248 videos
163 files
2.49K links
TA
Download Telegram
#Inbox #Alert #OromoPoliticalPrisoners

"የኦነግ አመራሮችን በህግ በማይታወቁ ማጎርያ ካምፖች ሲያዞሯቸው ከቆዩ በኋላ መልሰው ወደ ቡራዩ ካመጧቸው 11 ቀን ሆኗቸዋል።

"ከታሰሩት መካከል ለምሳሌ:- ለሚ ቤኛና ዳዊት አብደታ እስከ መጨረሻው የሀገሪቷ የህግ አካል ድረስ ቀርበው ምንም ወንጀል አልተገኘባቸውም ብሎ ነፃ ቢላቸውም በማን አለብኝነት ዛሬም ታጉረው እንዳሉ ነው። መቼም የአንድ ሀገር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነፃ ያለውን አካል አስሮ በማቆየት ይህ መንግስት የመጀመርያው መሆን አለበት

"የጃል ሚካኤልና የነኬነሳ ደግሞ አቃቤ ህግ ክስ የለኝም ብሎ ቢያሰናብታቸውም ያው ታግተው እንደተቀመጡ ናቸው።

"ጃል በቴ ኡርጌሳ ደግሞ እስካሁን ከተያዙበት ግዜ አንስቶ ያለ ክስ እንደተቀመጡ ናቸው።

"ይህ ሁሉ እንዳለ ሆኖ፣ The Silent Killer በመባል በሚታወቀው በ Hepatitis B ጃል በቴ ኡርጌሳ ተይዟል። ጉበቱ ላይ ጠባሳ በመገኘቱና ሀኪምም በግዜ ካልታከመው ወደ ካንሰር ሊቀየር ስለሚችል ተኝቶ እንዲታከም ቢያዝም፣ ፖሊስ ግን ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

"ይህ ህመም ተላላፊ በመሆኑ ከአንድ አመት በላይ አብረው የታሰሩ ጓዶቹ ባለቤቱና ልጆቹ ጭምር ወደ ህክምና እንዲመጡ የታዘዘ ቢሆንም እስካሁን ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ አልተደረገም። የጣብያ ሀላፊዎቹ ሲጠየቁም ከበላይ አካል አልታዘዝንም የሚል ምላሽ እየተሰጠ ነው።

"ጃል በቴ ኡርጌሳ ተኝቶ ካልታከመ በማንኛውም ሰዓት ህይወቱ ሊያልፍ እንደሚችል ሀኪሞች ተናግረዋል። አንድ ነገር ከሆነ ተጠያቂው መንግስት ብቻ መሆኑ ይታወቅ!!!"