Tsegaye R Ararssa
16.5K subscribers
1.66K photos
247 videos
162 files
2.48K links
TA
Download Telegram
ሲያድግ አማራ መሆን የሚፈልግ ኦሮሞ ሁሉ፣ ወደ ቤተ-መንግሥት ሲቀርብ የአማራ ልሂቃንን ፖለቲካ መጫወት (ሱሴ፣ ኢትዮጵያዬ፣ አድዋዬ ምናምን ማለት) ልማዱ ነው። አብይም ያደረገው ይሄንኑ ነው። ኦህ_deadም እንደዚሁ።
#ያዲያቆነ_ሳያቀስ_አይለቅ!
እንቀጥል እንዴ?
==========
አንዳንዱ፣ የራሱን መንበርከክ ለመሸፈን እራሱን አዋቂ አስመስሎ ካሜራ ፊት ተጥዶ የሰው ሥም ለማጥፋት ይፈልጋል። ለእነዚህ ዓይነቶች ወዶ-ገብ አፈ-ቀላጤዎች አንዳንድ ጥያቄዎችን ብቻ ማቅረብ በቂ ነው።

ለመሆኑ፣ ቄሮን demobilize ያደረገው ማን ነው? (ውጭ ያሉ ልሂቃን ናቸው?) "ነፃ ወጥተናል፣ አሁን ልማት ላይ እናተኩር" ያለው ማን ነው? ልሂቃኑ ነበሩ እንዴ? ጃዋርን እራሱን ከጥቃት ለመከላከል የወጣውን ወጣት እንኳን "በቃ ካሁን በኋላ፣ እቤት ግቡና አንድ ዓይናችሁን ገልጣችሁ (ሌላውን ጨፍናችሁ) ተኙ እያለ" ያስተኛው ማን ነው? (አንዳንዱ እስከዛሬም የተጨፈነ ዓይኑን አልከፈተም። ትዕዛዝ እየጠበቀ!)

WBOን ትጥቅ ለማስፈታት ሲንከራተት የነበረውስ ማነው? WBOን ትጥቅ ለማስፈታት የኳተነው ማን ነው?

የሕግ ማስከበር እርምጃ ይወሰድ ብሎ አብይን "ኃይልን የመጠቀም ብቸኛ ሥልጣን (monopoly over violence) ያለህ አንተ ነህ" ብሎ አደፋፍሮ በኦሮሚያ ላይ ጦርነት ያሳወጀውስ ማን ነው?

ለአራቱ የኦሮሞ ድርጅቶች 15 ሚሊዮን ብር አስመድቦ፣ ወደ ምርጫ ሲኬድ ከብልጥግና ጋር ለፌደራል ወንበር ለጥቂቶቹ በቀር እንዳይፎካከሩ፣ በኦሮሚያም በኮታ የCaffeeን ወንበር እንዲጋሩ ሲያመቻች፣ ሲያስማማ የነበረው ማን ነው?

ይሄ ነው፣ የሚቀናበት የትግል ሥልት? ይሄን ስልት ነው "የሚተካው ጠፋ" እየተባለ የሚንቆለጳጰሰው?

እሱን ከእስር ለማስፈታት ቄሮ ሲንቀሳቀስ (አንዴ ያልተጠራ ተቃውሞ በቄሮ ሥም እየጠራ፣ አንዴ የቄሮን የትግል ጥሪ እያፈነ፣ ሌላ ጊዜ የተቃውሞ መርሐ-ግብር እየቀያየረ) ያመከነው የማን ሚዲያ ነው? OMN አይደለምን? የእሱ የራሱ እልፍን አስከልካዮች አይደሉምን?

ሎሎች የኦሮሞ ሚድያ ተቋማት እንዳይጠናከሩ ጋዜጠኞቻቸውን አስፈራርቶና አባብሎ ያስኮበለለው ማን ነው? እነዚህ ሌሎች ሚድያዎች ድምጻቸውስ እንዳይሰማ ሲሯሯጡ የነበሩት የማን ሚድያ አለቆች ናቸው?

ለእሱ ድምጻቸውን ለማሰማት ብለው በOMN የቀረቡ እንግዶችን ድምጽ ("እንደ ጃዋር ተሰሚ ይሆኑና እሱን ይተኩታል" በሚል ፍርሃት ተነሳስቶ) ያፈነው ያሳፈነው ማን ነው?

ለዓለም-አቀፉ ማሕበረሰብ (እስር ቤት ሊጠይቁት በመጡ ዲፕሎማቶች በኩል) የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ስለ ኦሮሞ ነፃነት ታጋዮች ("ፖለቲካቸው brainless ነው:: እነርሱም የታጠቁ ቁጡ ወጣቶች /angry armed young men/ ” ናቸው":መንግስት ከፈረሰ የመንደር war lords ሆነው ኦሮሞን ያጫርሳሉ: ወዘተ እያለ) ያለውን አመለካከት ሁሉ ያዛባው ማንነው? የኦሮሞ ዲፕሎማሲያዊ ትግልም እንዳይሳካ ሲያሰነካክል የነበረው ማን ነው?

"አብይ ከወደቀ፣ WBO የኦሮሞን ሕዝብ በwar lord መልክ በመከፋፈል የኦሮሞን ሕዝብ ያባላል" በሚል ተራ ሃሜት ፈረንጆቹ ከአብይ ጎን እንዲቆሙና ዕድሜውን እንዲያራዝሙ ያደረገው ማን ነው? ለሥልጣንና ላጋበሰው ንግድ በመሳሳት ብቻ፣ የሕዝቡን የመከራ ዘመን እስከዛሬ እንዲራዘም ያደረገው ማን ነው?

ከእነ ጻድቃንና ደብረ-ጽዮን ጋር መልዕክት እየተለዋወጠ በእነሱ አዲስ የአገዛዝ ዘመን የሥልጣን ፍርፋሪ እንዲሰጠው (በዲፕሎማቶች በኩል ጭምር) ሲለማመጥ የነበረው ማን ነው? (ከዚህ በላይስ ለሥልጣን መንጠራወዝ ከወዴት ሊገኝ ነው?) በአቋራጭ TDFን ተጠቅሞ ሥልጣን ላይ ፊጥ ለማለት ሲያሶመሱም የነበረው ማን ነበረ? (ደሞ እኮ "ከወያኔ ጋር አዲስ አበባ ለመግባት ይፈልጋሉ" ምናምን እያሉ ሊያሸማቅቁን ይዳዳቸዋል! ለመሆኑ እነሱ ተግተልትለው ሲገቡ ያላማለለን አዲስ አበባ ዛሬ የሚያማልለን ይመስላቸዋል? አዲስ አበባቸው መንግሥተ-ሰማይ ቢሆን እንኳን ገሃነምን እንደምንመርጥ ቀደም ብለን ለራሳቸው ያልነገርናቸውና የማያውቁ ይመስል! ለማያውቁ ተረኛ ዝንቦች ይሄንን ለምን አይነግሯቸውም? ያው ሁሉንም ሰው በራሳቸው የምኞት ልክ መገመት እውቀት ሆኖላቸው መሆኑ ነው ሰውን በዚህ የሚገምቱት!)

ተዉ፣ አትነካኩን። ተዉ፣ ትተነው እንለፈው ስንል እየተነኳኮሳችሁ ወደኋላ አትመልሱን።

አብይን ተለማምጣችሁ፣ በእምብርክክ ሄዳችሁ ለማግኘት የጓጓችሁለትን ሥልጣን ለመቀራመት መሯሯጥ መብታችሁ ነው። በሌላው ሰው መብት፣ ሥም፣ እና ክብር ላይ ተረማምዳችሁ እንድታደርጉት ግን አንፈቅድም።

#Gantummaa_ofii_dhoksuuf_ololli_hin_fayyadu!
#ሂሳብ_እያወራረድን_እንቀጥል?
የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ግብ (Abbaa biyyummaa)፣ እና ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ የማድረግ ፕሮጀክት ግብ አንድና ያው ናቸው ከሚል ሰው ጋር ምን የምትነጋገረው ነገር አለ?
#safuu
Titiisni titisumaa
Huursun amalumaa!
Forwarded from KMN
በጋምቤላ ክልል የእኝዋክ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ፖሊሶች እና ወጣቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ ፈፀሙ
KMN:- June 19/2022
=================================
ባለፈዉ ሳምንት ማገባደጃ ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ርዕሰ ከተማ በሆነችዉ ጋምቤላ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያነጣጣር የጅምላ ግድያ መፈፀሙን ነዋሪዎች ከበርካታ የምስል ማስረጃ ጋር ለሚዲያችን አድርሰዋል::

በዚሁ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል በጥምረት የሚንቀሳቀሱት የኦነሠ እና የጋምቤላ ነፃ አዉጪ ግምባር በጥምረት በጋምቤላ ከተማ ሰፍሮ በነበረዉ የመንግስት ሰራዊት ላይ በወሰዱት ጥቃት በርካታ የመንግስት ሰራዊት አባላት ተገድለዋለዋል ያሉት ምንጫችን "ይህን ጥቃት ምክንያት በማድረግ የአኝዉክ ወጣቶች ከከተማዉ ተሰብስበው መሳሪያ ከመንግሥት መጋዘን ታድሏቸዉ ከክልሉ ልዩ ሀይል ጋር በመሆን በከተማይቱ ለረጅም አመት በኖሩ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ንፁኃን ነዋሪችን ከመኖሪያ ቤት እና ስራ ቦታ እየሰበሰቡ በጅምላ ገድሏል"

በምስሉ ላይ የምትታየዉ ሟችን እንደምሳሌ ያነሱልን የመርጃ ምንጫችን በጋምቤላ ከተማ ለዉዝ በመሸጥ የምት ተዳደር እና የረጅም ግዜ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ እና የሶስት ልጆች እናት እንደሆንችም ገልፆልናል::

አሁን በጋምቤላ ያለዉ ጥቃት መከላከያ ስለገባ ቆሟል የሚለዉ የመረጃ ምንጫችን ሆኖም ግን ጥቃቱን ያደረሱት ወጣቶችም ሆኑ ፖሊሶች አሁንም እንደታጠቁ ስላሉ የህዝቡ ስጋት ከፍተኛ ነዉ ብሏል::

ተጨማሪ የተጎጂዎች ምስል ከቴልግራም ቻናላችን ያገኛሉ