Tsegaye R Ararssa
16.5K subscribers
1.66K photos
247 videos
162 files
2.48K links
TA
Download Telegram
የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ግብ (Abbaa biyyummaa)፣ እና ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ የማድረግ ፕሮጀክት ግብ አንድና ያው ናቸው ከሚል ሰው ጋር ምን የምትነጋገረው ነገር አለ?
#safuu
Titiisni titisumaa
Huursun amalumaa!
Forwarded from KMN
በጋምቤላ ክልል የእኝዋክ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ፖሊሶች እና ወጣቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ ፈፀሙ
KMN:- June 19/2022
=================================
ባለፈዉ ሳምንት ማገባደጃ ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ርዕሰ ከተማ በሆነችዉ ጋምቤላ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያነጣጣር የጅምላ ግድያ መፈፀሙን ነዋሪዎች ከበርካታ የምስል ማስረጃ ጋር ለሚዲያችን አድርሰዋል::

በዚሁ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል በጥምረት የሚንቀሳቀሱት የኦነሠ እና የጋምቤላ ነፃ አዉጪ ግምባር በጥምረት በጋምቤላ ከተማ ሰፍሮ በነበረዉ የመንግስት ሰራዊት ላይ በወሰዱት ጥቃት በርካታ የመንግስት ሰራዊት አባላት ተገድለዋለዋል ያሉት ምንጫችን "ይህን ጥቃት ምክንያት በማድረግ የአኝዉክ ወጣቶች ከከተማዉ ተሰብስበው መሳሪያ ከመንግሥት መጋዘን ታድሏቸዉ ከክልሉ ልዩ ሀይል ጋር በመሆን በከተማይቱ ለረጅም አመት በኖሩ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ንፁኃን ነዋሪችን ከመኖሪያ ቤት እና ስራ ቦታ እየሰበሰቡ በጅምላ ገድሏል"

በምስሉ ላይ የምትታየዉ ሟችን እንደምሳሌ ያነሱልን የመርጃ ምንጫችን በጋምቤላ ከተማ ለዉዝ በመሸጥ የምት ተዳደር እና የረጅም ግዜ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ እና የሶስት ልጆች እናት እንደሆንችም ገልፆልናል::

አሁን በጋምቤላ ያለዉ ጥቃት መከላከያ ስለገባ ቆሟል የሚለዉ የመረጃ ምንጫችን ሆኖም ግን ጥቃቱን ያደረሱት ወጣቶችም ሆኑ ፖሊሶች አሁንም እንደታጠቁ ስላሉ የህዝቡ ስጋት ከፍተኛ ነዉ ብሏል::

ተጨማሪ የተጎጂዎች ምስል ከቴልግራም ቻናላችን ያገኛሉ