Tsegaye R Ararssa
16.4K subscribers
1.67K photos
248 videos
163 files
2.49K links
TA
Download Telegram
Forwarded from KMN
#ሰበር_ዜና_BreakingNews

መንግስት የወለጋ ዞን ወረዳዎችን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሬያለሁ ባለ ማግስት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ ተገሉ::
KMN:- July 05/2022
==========================
የፌድራሉ መንግስት, የኦሮሚያ እና የአማራ ሀይል በጥምረት በመሆን የወለጋ ዞን ወረዳዎችን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሬያለሁ ባለ ማግስት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ መገደላቸዉን ነዋሪዎች ገለፁ:: የተገደሉት ነዋሪዎች በመቶዎች የሚቆጥሩ ናቸዉ ያሉት ነዋሪዎቹ በመንግስት የፀጥታ ሀይል በጅምላ የተገሉ ሲሆን "ሸኔን ትደግፋላችሁ" እየተባሉ እንደተገደሉ ተናግረዉ ግዳዮቹ ህፃን ሽማግሌ እና ወጣት ሳይሉ እንደረሸኑ አብራርተዋል::

የሟቿቹ ቁጥር አሁን በዉል አይታዋቅም ያሉት ነዋሪዎቹ በግምት ከምቶ ሰዉ በላይ አልቋል ሲሉ ገልፀዋል:: በአከባቢዉ የተሰማሩት የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሞ ጥላቻ የሰከሩት እና በትግራይ ክልልም የዘር ማፅዳት ወንጀል የተሳተፉት የአማራ ክልል ታጣቂዎች መሆናቸዉን ከዚህ ቀደም በቪዲዮ ጭምር ለህዝቡ ስናቀርብ የነበረ ሲሆን ወደ ወለጋ የዘሙትም ህገ ለማስከበር ሳይሆን ወለጋ የአማራ ርስት ነዉ ብለዉ ለርስት ማስመለስ እንደ ዘመቱም ጭምር የተናገሩትን በዋቢነት በቪዲዮ አቅርበን ነበር::

ይህን ጅምላ ግድያ የአለም ጤና ድርጅት ፕረዘዳንት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ያወገዙ ሲሆን ኦሮሚያ ላይ በተፈፀመዉ የንፁኃን ግድያ ማዘናቸዉን ገልፀዉ በመላዉ በሀግሪቱ እየተፈፀመ ስላላዉ የንፁኃን ግድያ መፍትሔዉ ወደ ሰላም ማምራት መሆኑን ጠቁመዋል::

የሞቾችን ትክክለኛ ቁጥር እና የደረሰዉን ዉድመት እንደ ደረሰን የምናሳዉቅ ይሆናል::