AddisWalta - AW
45.2K subscribers
41.8K photos
204 videos
20 files
16.6K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
ፋሲል ከነማ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ፋሲል ከነማ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ደማቅ አቀባበል ተደረገለት፡፡

አምና የሊጉ ሻምፒዮን የነበረውና በዚህ የውድር ዓመት ከሁለተኛው የውድድር አጋማሽ ጀምሮ ምርጥ ፉክክር ሲያደርግ የቆየው ፋሲል ከነማ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

በሊጉ ባደረጋቸው 30 ጨዋታዎች 61 ነጥብ በመያዝ ያጠናቀቁት አፄዎቹ ዛሬ ወደ ጎንደር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ክለቡ በውድድር ዘመኑ ላስመዘገበው ውጤትም የከተማ አስተዳደሩ 7 ሚሊየን 462 ሺሕ 500 ብር፣ ከክለቡ 2 ሚሊየን 487 ሺሕ 500 ብር በድምሩ 9 ሚሊየን 950 ሺሕ 500 ብር ለክለቡ ተጫዋቾችና ለአሰልጣኞች እንዲሁም ለአጠቃላይ ሰራተኞችና የቦርድ አመራሮች የማበረታች ሽልማት ተበርክቷል።

በአቀባበሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ከንቲባ ዘውዱ ማለደና ሌሎች የጎንደር ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ክለቡ በቀጣዩ የውድድር ዓመት በአፍሪካ መድረክ በክለቦች የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናልም ነው የተባለው፡፡

በሀብታሙ ገደቤ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
የማታ 1፡00 ዜና በቀጥታ ከዋልታ ቴቪ ሰኔ 26/2014
https://fb.watch/e1tPv7s0cv/
በሊጉ ጨዋታዎች ላይ የተፈጠሩ ክስተቶችን ተከተሎ ለጨዋታ ታዛቢዎች፣ ዳኞችና የቡድን መሪዎች ጥሪ ተደረገ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ የተፈጠሩ ክስተቶችን ተከተሎ ለጨዋታ ታዛቢዎች፣ ዳኞችና የቡድን መሪዎች ጥሪ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በተጫዋቾች ዳንኤል ተሾመ (አዲስ አበባ ከተማ)፣ አብዱልባሲጥ ከማል (ሃዋሳ ከተማ) እና ጀማል ጣሰው (አዳማ ከተማ) በ5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከቱ 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት 1 ሺሕ 500 ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል።

በ30ኛ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ የተፈጠሩ ክስተቶችን ተከተሎ ለጨዋታ ታዛቢዎች፣ ዳኞችና የቡድን መሪዎች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ለማነጋገር በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ጽ/ቤት እንዲገኙ ጥሪ ተላልፏል።

በዚህም ለሦስት የጨዋታ ታዛቢዎች ሻለቃ በልሁ ኃይለማሪያም፣ ሰላሙ በቀለ እና አበጋዝ ነብየልዑል ሲሆን ከዳኞች ለኢንተርናሽናል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው (ፒኤችዲ)፣ ለኢንተርናሽናል ዳኛ አሸብር ሰቦቃ፣ ለፌዴራል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ፣ ለፌዴራል ዳኛ ባህሩ ተካ ለፌዴራል ዳኛዮናስ ካሳሁን እና ለፌዴራል ዳኛ እያሱ ፈንቴ ጥሪ ቀርቧል።

https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/photos/a.489214534492666/5571310619616340/?type=3&app=fbl
በሶማሌ ክልል በሙስና በተጠረጠሩ 168 የመንግሥት ሰራተኞች ላይ ክስ ተመሰረተ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊነትን ለግል ጥቅም በማዋልና በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩ 168 የመንግሥት ሰራተኞች ላይ ክስ መሰረተ፡፡

የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አህመድ ሃጂ እንደገለጹት በገቢ ማሰባሰብ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ላይ በተደረገ የኦዲት ምርመራ 93 ሚሊየን ብር ጉድለት እንደተገኘ የሶማሌ ክልል ጠቃላይ ኦዲት ጽ/ቤት ለአቃቤ ህግ በላከው ሪፖርት አረጋግጧል። ይህን ተከትሎም በገንዘብ ምዝበራው ተሳትፎ አላቸው በሚል በተጠረጠሩ 168 የመንግሥት ሠራተኞች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡

ቢሮው ከፖሊስ ጋር በመተባበር በወሰደው እርምጃም እስካሁን ከተለያዩ ግለሰቦች 15 ሚሊየን ብር ተመላሸ ሆኖ ወደ መንግሥት ካዝና መግባቱን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ የሶማሌ ክልል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሰራተኛ ሆነው የመንግሥትና የሕዝብ ሃብትን ለግል መጠቀሚያ በማድረግና በሙስና በተጠረጠሩ 14 ሠራተኞች ላይ ክስ የመሠረተ ሲሆን ከተከሳሾቹ መካከል ሁለቱ ዳይሬክተሮች መሆናቸውን ኃላፊው ገልፀዋል።

ከነዚህ 14 ግለሰቦች መካከል 4ቱ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ የቀጠለ ሲሆን ቀሪዎቹን ለህግ ለማቅረብ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በግብረአብረነት ተሳትፎ እንዳላቸው በተጠረጠሩ 17 ነጋዴዎች ላይም ክስ መመስረቱን ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/photos/a.489214534492666/5571417646272304/?type=3&app=fbl
የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ሕዝቦች ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ይገባል ተባለ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያን እና የሱዳንን ሕዝቦች ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚገባ በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ደፋኣላ አልሃጅ ጋር በኢትዮጵያና በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለቱ አገራት ሕዝቦች መካካል ያለው ግንኙነት ለዘመናት የዘለቀና በመልክዓ ምድር፣ ባህል፣ ታሪክ እና ሃይማኖት የተሳሰረ መሆኑን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ አውስተዋል።

በሁለቱ መንግሥታት መካከል ልዩነቶች ቢከሰቱም እንኳ ዘላቂና ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻችንን ግምት ውስጥ በማስገባት በሰከነና በሰላማዊ መንገድ ልዩነቶችን ለመፍታት መስራት አስፈላጊ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

አምባሳደር ደፋኣላ አልሃጅ በበኩላቸው የሁለቱን አገራት ሕዝቦች ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር በሁለቱ መንግሥታት መካካል የሚነሱ ልዩነቶችን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሱዳን ዝግጁ ናት ማለታቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቢሮው ከመንግሥት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ የጣሱ 8 የነዳጅ ቦቴዎችን ወረሰ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከመንግሥት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከሕግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ስምንት የነዳጅ ቦቴዎች መውረሱን አስታወቀ፡፡

ሆን ብለው የነዳጅ እጥረት እንዲከሰትና ከመንግሥት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከሕግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ ያደረጉ ስምንት የነዳጅ ካምፓኒዎች ቦቴዎች በዛሬው እለት በፀጥታ ኃይሎችና በኅብረተሰቡ ጥቆማ ተወርሰዋል፡፡

የተወረሰው ነዳጅም በነዳጅ ማደያዎች በኩል እንዲከፋፈል ማድረጉን ቢሮው አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ መስፍን አሰፋ ሕግ አክብረው በማይሰሩና በትክክል ስራቸውን በማይወጡ የነዳጅ ካምፓኒዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ኢዜማ ብርሃኑ ነጋን (ፕ/ር) በድጋሚ የፓርቲው መሪ አደርጎ መረጠ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ አመሻሽ ባካሄደው አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው በየዘርፉ ተፎካካሪ እጩዎች ቀርበው የምረጡኝ ቅስቀሳ ካደረጉ በኋላ አሸናፊዎቹን እኩለ ሌሊት ገደማ አሳውቋል፡፡

በዚሁ መሰረት ፓርቲው ብርሀኑ ነጋን (ፕ/ር) መሪ እና ዮሐንስ መኮንንን ምክትል መሪ አድርጎ መርጧል፡፡

ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) እና አማኑኤል ኤርሞ (ዶ/ር) ደግሞ የፓርቲው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ኢዜማ አበበ አካሉን ዋና ፀሀፊ አድርጎ የመረጠ ሲሆን በሚስጥር በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት በሌሎችም ዘርፎች ፓርቲውን የሚመሩ አባላትን ጭምር መርጦ መሰየሙን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ ከዋልታ ቴቪ ሰኔ 27/2014
https://fb.watch/e2e_4aFzJW/
ጠ/ሚ ዐቢይ መሰናክሎች የዕድገት እና የመሻሻል ዕድሎች ናቸው አሉ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) በመንገዳችን ላይ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ተቋቁመን ማለፍ ከቻልን መሰናክሎች የዕድገት እና የመሻሻል ዕድሎች ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ባለፍንባቸው ጊዜያት ጎን ለጎን በጎ ነገሮችንም መፍጠር ችለናል ብለዋል።

የተለያዩ መሰናክሎችን በመቋቋም ጭምር በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች የጠንካራ ሥራ ውጤቶች ናቸው ሲሉም አክለዋል።

ፕሮጀክቶቹ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተሰነቀው ራዕይ ማሳያ ምልክቶች ናቸውም ነው ያሉት።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተሰጠ ይገኛል።

በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም ችግር እየወሰዱ ሲሆን ፈተናው ለ3 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።

የፈተና ደኅንነት ለመጠበቅ እና የፈተናውን ሂደት ለመከታተልም ቀደም ሲል የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት 10 የፀጥታ አካላት ማሰማራቱ ተጠቁሟል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን በዚህም 71 ሺሕ 832 የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ ከከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ኢንስቲትዩቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል አሳሰበ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ እርጥበት አዘል አየር በአጭር ጊዜ ተጠናክሮ በሚቀጥሉት ቀናት ከባድ ዝናብ በመፍጠር ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

በኢንስቲትዩቱ የአየር ሁኔታና የአየር ጸባይ ትንበያ ዳይሬክተር ጫሊ ደበሌ እንደገለጹት ከደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው እርጥበት አዘል አየር ካለፉት ሳምንታት በበለጠ በቀጣዮቹ ሳምንታት ሊጠናከር እንደሚችል ትንበያዎች ያሳያሉ።

በዚህም የጎርፍ አደጋ ሥጋት ያለባቸው አካባቢዎች ላይ አደጋ እንዳይፈጠር ከወዲሁ የመከላከል ሥራ ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተለይ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ ወንዞችና ተዳፋታማ አካባቢዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተጠናከረ የጥንቃቄ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በተለይ በከፍተኛ ቦታዎችና፣ በደጋ አካባቢ የሚዘንበው ዝናብ በዝቅተኛ አካባቢዎች ላይ የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid02WehphEmXX2bTU9SHHVRWH9QNTc6r88p7VDwA7a1rbm3sdttdvKbzyYjPP3SwDovSl/?app=fbl
ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን አስጀመሩ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን አስጀመሩ።

በክልሉ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው ፈተና 4 ሺሕ 900 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ፈተናውን ባስጀመሩበት ወቅት በክልሉ ለፈተናው አስፈላጊው ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸው በተለይም በተማሪዎች መካከል ኩረጃ እንዳይኖር፣ ፈተናው እንዳይሰረቅ እና የፈተናው አሰጣጥ ውጤታማ እንዲሆን ከማስቻል አንፃር በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ለትምህርት ጥራት በተለይም የተማሪዎች ውጤት እንዲጎለብት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተው የሚመለከታቸው አካላትም የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በክልል ደረጃ በከተማና በገጠር በሚገኙ 24 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
የቀን 6፡00 ዜና በቀጥታ ከዋልታ ቴቪ ሰኔ 27/2014
https://fb.watch/e2pAZiNlAP/
በገላን ከተማ በ613 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ናቸው

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) በገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ፒኤችዲ) የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ገላን ከተማ የተሰሩትን ፕሮጀክቶች እየመረቀ ይገኛል።

በገላን ከተማ በ613 ሚሊየን ብር የተገነቡ ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የሆኑና የከተማይቱ መሰረተ ልማት የሆኑ 52 ፕሮጀክቶች ናቸው እየተመረቁ የሚገኙት።

በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝን ጨምሮ ከፌዴራልና ከክልል የተወጣጡ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለረጅም ዓመታት ስንጠይቅ የነበረ ጥያቄያችን ዛሬ ምላሽ ማግኘቱን የገለጹት የገላን ከተማ ነዋሪዎች ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው በመመረቃቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።

በታምራት ደለሊ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ሊጉ የበጎ ፈቃድ መርኃ ግብሩን በደብረ ብርሃን ከተማ ጀመረ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የ2014/15 ዓ.ም በጎ ፈቃድ መርኃ ግብሩን በደብረ ብርሃን ከተማ ጀምሯል።

''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' የሚል ስያሜ ያለው መርኃ ግብር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳና ሞዴል የከተማ ግብርና ሥራዎች መጎብኘትን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል ዓለሙ ስሜን (ፒኤችዲ) ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ካሳሁን እምቢአለ አባቶቻችን ነጻነቷ ሳይደፈር ያስረከቡንን ሀገር ወጣቱ ዘመኑ በሚጠይቀው መስዋዕትነት ሀገሩን በመተባበር ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል።

ወጣቶች ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊና ዘላቂ ግንባታ ያላቸውን ሚና መወጣት እንደሚኖርባቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአየር መዛባትን ለመከላከል የአረጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን በመተግበር ላይ ነች ብለዋል።

ወጣቶችም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ላይ ተሳትፎ በማድረግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW