AddisWalta - AW
45.4K subscribers
42.2K photos
208 videos
20 files
16.7K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
ፓርላማው ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ልዩ ስብሰባ በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሐሳብ አሳለፈ

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ልዩ ስብሰባ ፤ በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሐሳብ አስተላለፈ።

የዕለቱን መርኃ-ግብር በግፍ ለተጨፈጨፉት ዜጎች የአንድ ደቂቃ የኅሊና ጸሎት በማድረግ የጀመረው ምክር ቤት፤ የሚከተሉትን የውሳኔ ሐሳቦች አስተላልፏል፡፡

በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ እጅግ የኮነነው ምክር ቤቱ በሀገሪቱ በየትኛውም ክልልና አካባቢ በሲቪል ዜጎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ያስከተሉ እና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ እንዲደረግ ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

በየደረጃው ያለው አመራር አካል፣ የጸጥታ አካል እና የፍትሕ ተቋም የሕዝቡን ደኅንነትና ሠላም በጥብቅ እንዲያስከብር፣ አጥፊዎች ለሕግ ተጠያቂነት እንዲቀርቡ እንዲደረግ ወስኗል።

ከመንደራቸውና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በአስቸኳይ እንዲሰራ የወሰነው ምክር ቤቱ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት ከየትኛውም ጊዜ በላይ በወንድማማችነት፣ በአብሮነት እና በአንድነት እንዲቆሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ለሕዝብ ተጠቃሚነት በላቀ ቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል አሉ

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) ለሕዝብ ተጠቃሚነት በላቀ ቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ አስታወቁ፡፡

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) በ2014 ዓ.ም የሴክተር መስሪያ ቤቶች አፈፃፀም እና የ2015 በጀት ዓመት አማራጭ የበጀት ድልድል ላይ ተወያይቷል።

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የክልሉ መንግሥት ለሕዝብ የገባውን ቃል ከመፈፀም አንፃር የተለያዩ ተግባራት ቢከናወኑም በቀጣይ በላቀ ትኩረት መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

በክልሉ የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አንፃር እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ማጠናከርና ቀጣይነት ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ከቅጥርና ከደረጃ እድገት ጋር በተያያዘም የህግ ጥሰት በሚፈፅሙ እና በኢንቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ባላለሙ አካላት ላይም በአፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid0tzA5JDFcnituPrpSpcnsBS4KY7Uq4uwLJfHa5UVurEmtVA4VNFxEFtrLjs6ibSVZl/
ከሐምሌ 1 - 10 ቀን ከፍተኛ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል በተዳፋት አካባቢዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ አሳሰበ

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) በሐምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ከፍተኛ ጎርፍ ስለሚኖር በተዳፋትና ገደላማ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከሐምሌ 1 እስከ 10 ቀን 2014 ዓ.ም የሚኖረውን የአየር ፀባይ ሁኔታ ትንበያ በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም በሐምሌ ወር የመጀመሪያዎች አስር ቀናት በሀገሪቱ መደበኛ እና በአንዳንድ አካባቢዎች ነጎድጓዳማ እና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ይጠበቃል ብሏል።

በትንበያው መሰረት በሚቀጥሉት አስር ቀናት የሚኖረው የዝናብ ሁኔታ ከባድ እና ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል መሆኑን ገልጿል።

በዚህም በምዕራባዊ የሀገሪቱ አካባቢዎች አጋማሽ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከ100 እስከ 200 ሚሊ ሜትር፤ በተወሰኑ ቦታዎች ከ200 ሚሊ ሜትር በላይ ዝናብ እንደሚጠበቅ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

በሐምሌ ወር በመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ እና በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይጠበቃል ብሏል።

በአብዛኛው የአባይ፣ ባሮ-አኮቦ፣ ተከዜ፣ አዋሽ፣ ስምጥ ሸለቆ፣ ኦሞጊቤ፣ አፋር-ዳናከል፣ የላይኛውና መካከለኛው ዋቢ-ሸበሌ እንዲሁም ገናሌ-ዳዋ ተፋሰሶች ከፍተኛ እርጥበት ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በታችኛው ገናሌ-ዳዋ፣ ስምጥ ሸለቆ እና ...
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid02ztXiMb61dneWUTfdou1RVecH6ZjQktBdq2HyqJGNPz4UaU4YCB1MBN42RrQTy6NAl/
ከስደት ተመላሽ ዜጎች የተሻለ ኑሮን ለመፍጠር ከዓለም ዐቀፉ የፍልሰት ድርጅት የላቀ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) ከፍልሰት ጋር የተገናኙ ተግዳሮቶች በዘላቂነት ለመፍታት እና ለተመላሽ ዜጎች የተሻለ ኑሮን ለመፍጠር ከዓለም ዐቀፉ የፍልሰት ድርጅት የላቀ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት የምስራቅ አፍሪካና እና አፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ዳይሬክተር መሀመድ አብዲከር ጋር በፍልሰት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሊኖር ስለሚገባ የጋራ ትብብር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸው አምባሳደር ብርቱካን ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እና በትብብር በመስራት ለሀገሪቱ የፍልሰት አስተዳደርና በተመላሸ ዜጎች ዙሪያ የሚደረገውን ጥረት እያደረገ ያለውን ያልተቋረጠ ድጋፍ አድንቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ አገር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስና ህገ-ወጥ ስደትን ለመቀነስ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid0Y6nykWorhwST1pFMAmBVzWytA2vmY7oafkaKZZDCyyrPmFbL6f2ZqfnmngBAsoml/
የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ ያሉ የ65 አመቷ አዛውንት

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) የ2014 ዓ.ም የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መስጠት ከትናንት በስቲያ መጀመሩ ይታወቃል።

በደቡብ ክልልም ፈተናው ከትናንት ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል።

በክልሉ ደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ኔሪ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማታው ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን በመከታተል የሚገኙት የ65 ዓመቷ ወርቅነሽ ወንበራ የስምነተኛ ክፍል ፈተናን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ከዓለም ዐቀፉ የስደተኞች ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

ሰኔ 29/2014(ዋልታ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም ዐቀፉ የስደተኞች ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሙሀመድ አብዲከር ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሯ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢነቱ እየጨመረ በመጣው ቀጣናዊና ሀጉራዊ በሆኑ የሠራተኞች ፍልሰት ጉዳዮች ላይ ፣ በቀጠናው የክህሎት ልማት እና የወጣቶች የሥራ ዕድለ ፈጠራን፣ የሰራተኞች ተዘዋውሮ የመስራት፣ የዜጎችን ሰብዓዊ እና ማህበራዊ መብቶችን ማስጠበቅን በተመለከተ መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቀጠናው የሰራተኞች ፍልሰት ጉዳይ የሚኒስትሮች ፎረምን የምትመራ ሀገር እንደመሆኗ ድርጅቱ ድጋፉን አጠናክሮ ስለሚቀጥልበት ሁኔታም መምከራቸውን ከትስስር ገጻቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከቀጠናው ባለፈ ከሌሎች ሀገራት እና አህጉራት ጋር ህጋዊ የሆነ የሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ የሰው ኃይል ዝውውር ሥርዓት መዘርጋት እና በትብብር ለመስራት በሚደረገው እንቅስቃሴ ድርጅቱ ድጋፉን እንደሚጠናክር ማረጋገጡን ጠቁመዋል፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል ከ650 ሺሕ በላይ ለሆኑ ወገኖች የምግብ እርዳታ እያደረገ መሆኑን ገለጸ

ሰኔ 29/2014(ዋልታ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል ከ650 ሺሕ በላይ ለሆኑ ወገኖች የምግብ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ።

የድርጅቱን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሰሜናዊ አፋር ኮኔባ አካባቢ ዛሬ መድረሳቸውን እና ወደ መጋዘን እየተራገፈ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል።

በየስድስት ሳምንት ልዩነት “በአፋር ክልል በግጭትና በድርቅ ምክንያት” ለተፈናቀሉ ከ650 ሺሕ በላይ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ጠቁሟል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት በክልሉ ለ80 ሺሕ ዜጎች የሚሆን የምግብ እርዳታ ማድረሱን ጠቁሞ አሁንም የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ገልጿል።
1ሺሕ 24 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺሕ 24 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 1ሺሕ 19 ወንዶች እና አምስት ህጻናት መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 47,408 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
ዋልታ ምሽት በቀጥታ ሰኔ 29/2014
https://fb.watch/e5qW6HZZv4/
ርላማው ነገ ጠ/ሚ ዐቢይ በተገኙበት በአዲሱ የ2015 በጀት ድልድል ላይ ይወያያል

ሰኔ 29/2014(ዋልታ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ በሚያካሂደው 16ኛ መደበኛ ጉባዔ፤ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በነገው ዕለት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ይወያያል።

ፓርላማው በዚህ መደበኛ ጉባዔው፤ ሰሞኑን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ላለው የዜጎች የፀጥታ እና ደኅንነት ጉዳይ ዐቢይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ ይጠበቃል።

እንደዚሁም ለሌሎች ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ-ሀብታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቶ፤ ምክር ቤታዊ ውይይት ይካሄዳል።

በተጨማሪም በአዲሱ የ2015 የበጀት ድልድል ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቀውም ተመላክቷል፡፡

የፌዴራል መንግስት አጠቃላይ ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትም የሚቀርብ ሲሆን፣ በዚሁ ሪፖርት ላይም ምክር ቤቱ ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጋር እንደሚወያይ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር እንደማይቻል ተገለጸ

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስኪሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ ይህንን ያሉት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ነው።

በከተማ አስተዳደሩ በየሦስት ወሩ የሚታደስ ለቤት ኪራይ ደንብ እና መመሪያ እንዳለው ይታወቃል።

ሆኖም በከተማዋ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በዜጎች ላይ ጫና እያስከተለ በመሆኑ ደንቡ እስኪሻሻል ድረስ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።

የኑሮ ውድነቱ እስካልተስተካከለ ድረስ በምንም አይነት መልኩ አከራዮች የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይችሉ መሆኑን ተከራዮችም አከራዮችም ሊያውቁት እንደሚገባ በአፅንኦት አብራርተዋል።

አስተዳደሩ ክልከላውን ተላልፈው በሚገኙ አከራዮች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም ከንቲባዋ አሳስበዋል።

በአመለወርቅ መኳንንት
ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

ሰኔ 30/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን በወቅታዊ ጉዳዮች እና በ2015 የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እያካሄደ ነው።

በአሁኑ ወቅትም የምክር ቤቱ አባላት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ።

ምክር ቤቱ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየተወያየ ነው።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በ2015 የፌደራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ - በቀጥታ
https://fb.watch/e6coN2XSGT/