AddisWalta - AW
45.5K subscribers
42K photos
208 videos
20 files
16.7K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
ፌዴራል ፖሊስ ለ21ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ምልምል የፖሊስ አባላት አስመረቀ

ሰኔ 25/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለ21ኛ ዙር በአዋሽ መሰረታዊ ፖሊስ ስልጠና አካዳሚ ያሰለጠናቸውን ምልምል የፖሊስ አባላትን በዛሬው እለት አስመርቋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ለተመራቂዎች የሥራ መመሪያ በሰጡበት ወቅት የሀገራችን ፖሊስ በየሥርዓቱ እየወደቀ እየተነሳ ሲያገለግል የቆየ ተቋም ሆኖ ቆይቷል ብለዋል።

በተለይም ባለፉት 27 ዓመታት ሙያዊ እና ተቋማዊ ሆኖ እንዲገነባ ሳይሆን የቡድኖችን ፍላጎት የሚጠብቅ ሆኖ እንዲያገለግል በአንፃሩ በዜጎች ዘንድ የሚፈራ እና የስጋት ተቋም ሆኖ አልፏል ማለታቸውን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ከትግራይ ልዩ ኃይል የመጡ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ሰኔ 25/2014 (ዋልታ) ከትግራይ ልዩ ኃይል የመጡ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የሽብር ቡድኑ ሁለት አባላት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ አካባቢ 11:00 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ዘመን ገ/እግዚአብሔር (የጥበቃ መምሪያ አባል የነበረ የፈንጂ ባለሙያ) እንዲሁም ገ/ኪዳን ገ/ጻድቅ የልዩ ኃይሉ አባል መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል።

አሁን ላይም በሽብር ቡድኑ አባላት ላይ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራ መጀመሩንም አስታውቋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ኮሚሸኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቅቆ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ መግባቱን አስታወቀ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የአገራዊ ምክክር ኮሚሸን የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎችን አጠናቅቆ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ መግባቱን የኮሚሽኑ ሰብሳቢ መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ገለጹ።

ኮሚሽኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ተቋቁሞ የኮሚሽኑ ሰብሳቢና አመራሮች ከተሾሙለት በኋላ በይፋ ወደ ቅድመ ዝግጅት ሥራ መግባቱ ይታወቃል።

በዚህም ኮሚሽኑ ከመንግሥት ኃላፊዎች፣ ከክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ትውውቅ አድርጓል።

በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ኮሚሽኑን የማደራጀት ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን የድርጊት መርኃ ግብር በማውጣትም ወደ ዝግጅት ምዕራፍ የሚያስገቡ ሥራዎችን አከናውኗል።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ኮሚሽኑ በአሁኑ ወቅት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቆ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ መግባቱን ተናግረዋል።

በዝግጅት ምዕራፉም ለሥራ የሚያስፈልገውን በጀትና ስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ ሲሆን በአጭር ጊዜ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸድቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

በዚሁ ምዕራፍ በአገራዊ ምክክሩ ሂደት የሚዘጋጁ የውይይት መድረኮችን የሚመሩና የሚያወያዩ ግለሰቦችንና ባለድርሻ አካላትን የመምረጥና ስልጠና የመስጠት ተግባራት እንደሚከናወኑ ጠቅሰዋል።

https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/photos/a.489214534492666/5570234093057326/?type=3&app=fbl
ጀግኖች ደማቸውን ሰጥተው ያስከበሯትን ሀገር በመስዋዕትነታችን እናስቀጥላለን - የመከላከያ ሰራዊት አባላት

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) ጀግኖች ደማቸውን ሰጥተው ያስከበሯትን ሀገር በመስዋዕትነታችን እናስቀጥላለን ሲሉ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ የሚገኙ ሜካናይዝድ እና የእግረኛ ክፍለጦር ሰራዊት አባላት ተናገሩ፡፡

አባላቱ የሀገርን ዳር ድንበር ከዉጭ ወራሪ ኃይልና ከውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ለመከላከል እና የሚሰጣቸውን ግዳጅ በድል ለመወጣት ሌት ተቀን ዝግጁነት የማረጋገጥ ሥራዎችን እየሰሩ አንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡

በክፍለ ጦሩ የሚገኘው የ2ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ አለምነው ተፈራ እንደተናገሩት ሰራዊቱ ተልዕኮውን እና አላማዉን በሚገባ የሚያውቅ፣ በወታደራዊ ዲሲፒሊን የተገነባ ስለሆነ ማንኛውንም ግዳጅ የሚፈፅመው አሰራሩን እና ደንቡን በመከተል ነው፡፡

የሻለቃው አዛዥ አክለውም ሠራዊቱ ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብን በሚገባ እንዲላበስ በስልጠና በማብቃት የሀገሩን ሉአላዊነት ክብር በመስዋትነቱ የሚያስከብር አመራርና አባላት ፈጥረናል ብለዋል፡፡

የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመድፈር የሚመጣ ጠላት እና ሰላማችንን ለማወክ የሚሯሯጡ የውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎችንም ይሁን ተላላኪ ባንዳዎች ለመደምሰስ ሰራዊቱ ከምንጊዜውም በላይ በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ሻለቃ አለምነው ተፈራ ተናግረዋል፡፡
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid02d1chorGDYnPjbg1EFnxtt15Vkvk8FVWcgPUezZTKsFxuWDhmQ71v8sd9egMDdVVil/?app=fbl
እያንዳንዱ ተመራቂ የተጠራለት ተግባር ለሀገሩ ዕድገት ምሰሶ መሆን ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) ''በባህላችን የተመረቀ ሰው ለበጎ የተጠራ ነው፤ እያንዳንዱ ተመራቂ የተጠራለት ተግባር ለሀገሩ ዕድገት ምሰሶ መሆን ነው'' ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት 'ፈጠራን ለማቀላጠፍ፣ ለማኅበረሰብ ተግዳሮቶች መፍትሔዎችን ለማግኘት እና ለብዙዎች የተስፋ ብርሃን ለመሆን ነው ሲሉም አክለዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
ለአብርኆት ቤተ መጻሕፍት ከ450 ሺሕ በላይ መጽሐፍ ተሰበሰበ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) “ሚሊዮን መጻሕፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ ለአብርኆት ቤተ መጽሕፍ ሲካሄድ በነበረው መጻሕፍት የማሰባሰብ ዘመቻ ከ450 ሺሕ በላይ መጻሕፍት መሰባሰቡ ተገልጿል።

ለአንድ ወር ሲካሄድ የነበረው መጻሕፍት የማሰባሰብ ዘመቻ የመጀመሪያ ዙር ማጠናቀቂያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመርኃ ግብሩ ላይ መጻሕፍትን የለገሱት ግለሰቦችና ተቋማት መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉና የተለያየ ይዘት ያላቸው እንደሆኑ ተጠቁሟል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በዘመቻው ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉና የተለያዩ ይዘት ያላቸው መጻሕፍት ማሰባሰብ ተችሏል ብለዋል።

ቤተ መጻሕፍቱ ሀሳብን በውይይት የሚፈታ ወጣት ለማፍራት ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል።

ወጣቱን አማራጭ ሳይቀርብለት መውቀስ ተገቢ አይደለም ያሉት ዲያቆን ዳንኤል አሁን ላይ የአብርኆት ቤተ መጻሕፍት በቀን እሰከ 10 ሺሕ ሰው እያስተናገደ ነው ብለዋል።

ቤተ መጻሕፍቱ የሚያስፈልገውን ያህል መጻሕፍት እንዲኖሩት አሁንም ዜጎች ልገሳቸውን ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬትን ጨምሮ በመጻሕፍት ማሰባሰብ ዘመቻው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የመገናኛ ብዙኃን እንዲሁም መጻሕፍት ያበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦችም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በመስከረም ቸርነት

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት መርቀው ከፈቱ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት መርቀው ከፍተዋል።

ከንቲዋ በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ፕሮጀክቱ የከተማዋን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር የሚያቃልል ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ይነሳ የነበረውን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ቅሬታን በመፍታት የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ውሃ ሰጥተው ውሃ የሚጠማቸው የሚያደርግ ሳይሆን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱ የተሳካ እንዲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባዋ ፕሮጀክቱ ተባብሮ፣ ተናቦ እና ተሳስቦ በመስራት የተገኘ ውጤት፤ ወደፊትም ሌሎች ፕሮጀክቶች በተመሳሳይ በትብብር ዕውን እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።

የከተማዋን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከመሰረቱ ለመፍታት የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለንም ነው ያሉት።

የውሃ ፕሮጀክቱ በፈተና ውስጥ የተሰራ ፕሮጀክት መሆኑን የገለፁት ከንቲባዋ ፈተና እንደማያስቆመንም ያሳየንበት ነውም ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በመደበው 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት የተሰራና በቀን 86 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችል ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል፡፡

https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid025qXv6UsVTtiRqdD4LqS56ceLDoBieTDFYvkEprQjVoUPgWrXkKwx86HAVmSG7M7Nl/?app=fbl
በርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በኢሉ አባቦር ዞን የሥራ ጉብኝት አደረገ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በኢሉ አባቦር ዞን የሥራ ጉብኝት አድርጓል።

ቡድኑ በኢሉ አባቦር ዞን በክላስተር በመልማት ላይ የሚገኘውን የጉመሮ ሻይ ተክል በመጎብኘት የዘንድሮውን የሻይ ችግኝ ተከላ በአሌ ወረዳ አስጀምሯል።

በቆይታውም የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመመልከት 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ያስቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢብኮ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW