AddisWalta - AW
45.3K subscribers
41.9K photos
204 videos
20 files
16.7K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
ጀግኖች ደማቸውን ሰጥተው ያስከበሯትን ሀገር በመስዋዕትነታችን እናስቀጥላለን - የመከላከያ ሰራዊት አባላት

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) ጀግኖች ደማቸውን ሰጥተው ያስከበሯትን ሀገር በመስዋዕትነታችን እናስቀጥላለን ሲሉ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ የሚገኙ ሜካናይዝድ እና የእግረኛ ክፍለጦር ሰራዊት አባላት ተናገሩ፡፡

አባላቱ የሀገርን ዳር ድንበር ከዉጭ ወራሪ ኃይልና ከውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ለመከላከል እና የሚሰጣቸውን ግዳጅ በድል ለመወጣት ሌት ተቀን ዝግጁነት የማረጋገጥ ሥራዎችን እየሰሩ አንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡

በክፍለ ጦሩ የሚገኘው የ2ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ አለምነው ተፈራ እንደተናገሩት ሰራዊቱ ተልዕኮውን እና አላማዉን በሚገባ የሚያውቅ፣ በወታደራዊ ዲሲፒሊን የተገነባ ስለሆነ ማንኛውንም ግዳጅ የሚፈፅመው አሰራሩን እና ደንቡን በመከተል ነው፡፡

የሻለቃው አዛዥ አክለውም ሠራዊቱ ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብን በሚገባ እንዲላበስ በስልጠና በማብቃት የሀገሩን ሉአላዊነት ክብር በመስዋትነቱ የሚያስከብር አመራርና አባላት ፈጥረናል ብለዋል፡፡

የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመድፈር የሚመጣ ጠላት እና ሰላማችንን ለማወክ የሚሯሯጡ የውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎችንም ይሁን ተላላኪ ባንዳዎች ለመደምሰስ ሰራዊቱ ከምንጊዜውም በላይ በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ሻለቃ አለምነው ተፈራ ተናግረዋል፡፡
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid02d1chorGDYnPjbg1EFnxtt15Vkvk8FVWcgPUezZTKsFxuWDhmQ71v8sd9egMDdVVil/?app=fbl
እያንዳንዱ ተመራቂ የተጠራለት ተግባር ለሀገሩ ዕድገት ምሰሶ መሆን ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) ''በባህላችን የተመረቀ ሰው ለበጎ የተጠራ ነው፤ እያንዳንዱ ተመራቂ የተጠራለት ተግባር ለሀገሩ ዕድገት ምሰሶ መሆን ነው'' ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት 'ፈጠራን ለማቀላጠፍ፣ ለማኅበረሰብ ተግዳሮቶች መፍትሔዎችን ለማግኘት እና ለብዙዎች የተስፋ ብርሃን ለመሆን ነው ሲሉም አክለዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
ለአብርኆት ቤተ መጻሕፍት ከ450 ሺሕ በላይ መጽሐፍ ተሰበሰበ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) “ሚሊዮን መጻሕፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ ለአብርኆት ቤተ መጽሕፍ ሲካሄድ በነበረው መጻሕፍት የማሰባሰብ ዘመቻ ከ450 ሺሕ በላይ መጻሕፍት መሰባሰቡ ተገልጿል።

ለአንድ ወር ሲካሄድ የነበረው መጻሕፍት የማሰባሰብ ዘመቻ የመጀመሪያ ዙር ማጠናቀቂያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመርኃ ግብሩ ላይ መጻሕፍትን የለገሱት ግለሰቦችና ተቋማት መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉና የተለያየ ይዘት ያላቸው እንደሆኑ ተጠቁሟል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በዘመቻው ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉና የተለያዩ ይዘት ያላቸው መጻሕፍት ማሰባሰብ ተችሏል ብለዋል።

ቤተ መጻሕፍቱ ሀሳብን በውይይት የሚፈታ ወጣት ለማፍራት ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል።

ወጣቱን አማራጭ ሳይቀርብለት መውቀስ ተገቢ አይደለም ያሉት ዲያቆን ዳንኤል አሁን ላይ የአብርኆት ቤተ መጻሕፍት በቀን እሰከ 10 ሺሕ ሰው እያስተናገደ ነው ብለዋል።

ቤተ መጻሕፍቱ የሚያስፈልገውን ያህል መጻሕፍት እንዲኖሩት አሁንም ዜጎች ልገሳቸውን ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬትን ጨምሮ በመጻሕፍት ማሰባሰብ ዘመቻው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የመገናኛ ብዙኃን እንዲሁም መጻሕፍት ያበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦችም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በመስከረም ቸርነት

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት መርቀው ከፈቱ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት መርቀው ከፍተዋል።

ከንቲዋ በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ፕሮጀክቱ የከተማዋን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር የሚያቃልል ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ይነሳ የነበረውን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ቅሬታን በመፍታት የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ውሃ ሰጥተው ውሃ የሚጠማቸው የሚያደርግ ሳይሆን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱ የተሳካ እንዲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባዋ ፕሮጀክቱ ተባብሮ፣ ተናቦ እና ተሳስቦ በመስራት የተገኘ ውጤት፤ ወደፊትም ሌሎች ፕሮጀክቶች በተመሳሳይ በትብብር ዕውን እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።

የከተማዋን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከመሰረቱ ለመፍታት የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለንም ነው ያሉት።

የውሃ ፕሮጀክቱ በፈተና ውስጥ የተሰራ ፕሮጀክት መሆኑን የገለፁት ከንቲባዋ ፈተና እንደማያስቆመንም ያሳየንበት ነውም ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በመደበው 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት የተሰራና በቀን 86 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችል ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል፡፡

https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid025qXv6UsVTtiRqdD4LqS56ceLDoBieTDFYvkEprQjVoUPgWrXkKwx86HAVmSG7M7Nl/?app=fbl
በርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በኢሉ አባቦር ዞን የሥራ ጉብኝት አደረገ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በኢሉ አባቦር ዞን የሥራ ጉብኝት አድርጓል።

ቡድኑ በኢሉ አባቦር ዞን በክላስተር በመልማት ላይ የሚገኘውን የጉመሮ ሻይ ተክል በመጎብኘት የዘንድሮውን የሻይ ችግኝ ተከላ በአሌ ወረዳ አስጀምሯል።

በቆይታውም የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመመልከት 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ያስቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢብኮ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
በክልሉ በሁሉም ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በሲዳማ ክልል የሁለት ዓመት ጉዞ በሁሉም ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡ ተገልጿል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 2ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የፓናል ውይይት ላይ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የታደሙ ሲሆን ክልሉ በሁለት ዓመታት ውስጥ ያከናወናቸውን አስተዳደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የመሰረት ልማት ሥራዎች ለታዳሚው ቀርቧል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ባደረጉት ንግግር ልማታችንን ለማፋጠን ሕዝብን ያሳተፈ ሥራ መስራት ከፍተኛ ዋጋ እንዳለውና በዚህም ባለፈው ሁለት ዓመት ብዙ ውጤቶችን ያየንበት ነው ብለዋል።

በአገልግሎት ዘርፉ እና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ደካማ አፈፃፀም መታየታቸውንም ገምግመናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ ሕዝቡ ችግርም መፍትሄም በእጃችን መሆኑን አውቆ በንቁ ተሳትፎ ከጎናችን መቆም አለበት ብለዋል።

የፓናል ውይይቱ ላይ የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡት አራርሶ ገረመው (ፒኤችዲ) ውይይቶች በግልፅነት ላይ የተመሰረተ ሥራን ለማከናወን እና በሕዝብ እና በአስተዳደሩ መካከል ያለውን የጋራ መግባባት የሚያጠናክሩ ስለሆነ ፋይዳቸው የጎላ ነው ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በመንግሥት የተሰሩትን የመሰረተ ልማት ሥራዎች ቦታው ድረስ በመሄድ መጎብኘታቸውን ጠቅሰው ከልማቱ ጎን ለጎን የፀጥታና ደኅንነት ሥራ እንዲጠናከርም ጠይቀዋል።

የክልሉ መንግሥት 2ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል በነገው እለትም በተለያዩ ሁነቶች መከበር እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

አንተነህ ደጀኔ (ከሀዋሳ)
በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው አለመኖሩን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

"የዝንጀሮ ፈንጣጣ" በመባል የሚታወቀው እና በተለያዩ ሀገራት የተከሰተው ተላላፊ በሽታ በሀገራችን ተከስቶ ሁለት ሰዎች ተለይተዋል (ኳረንቲን ገብተዋል) የሚል መረጃ በሪፖርተር ጋዜጣ ወጥቶ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ እንደሚገኝ የገለጸው ሚኒስቴሩ “በሽታው በሌሎች ሀገራት ቢከሰትም በሀገራችን እስከ አሁን በበሽታው የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን እናሳውቃለን” ብሏል።

ኃላፊነት የሚሰማቸው የሚዲያ ተቋማት ይህን መሰል ያልተረጋገጠ እና በሚመለከተው አካል ያልቀረበ መረጃን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡም አሳስቧል።

ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን እንዲሁም የማኅበረሰቡ የጤና ስጋት የሚሆኑ ወረርሽኞችን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ከጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማግኘት የሚቻል መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አስጀመሩ

ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ‘‘አረንጓዴ አሻራችን ለትውልዳችን’’ በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደውን አራተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በጋምቤላ ወረዳ ቀርሚ ቀበሌ አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመርኃ ግብሩ ላይ እንዳሉት በአራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከ9 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ታቅዷል።

ዕቅዱን እውን ለማድረግ አመራሩ መላውን የክልሉን ነዋሪ በማስተባበር ውጤታማ ሥራ ማከናወን እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

ባለፉት ሦስት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሮች በተሰራው ሥራ በርካታ የተራቆቱ አካባቢዎችን በእጽዋት ማልበስ መቻሉን ገልጸዋል።

ዘንድሮም ካለፈው መልካም ተሞክሮ በመውሰድ እንደሚሰራ ጠቅሰው እስከ መስከረም አጋማሽ በሚዘልቀው የችግኝ ተከላ ሁሉም ሰው ቢያንስ 100 ችግኝ በመትከል ለዕቅዱ መሳካት የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አጃክ ኡቻላ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ተራቁቶ የነበረ ከ15 ሺሕ ሄክታር መሬት በላይ ወደ ቀድሞ ይዘቱ መመለሱን ተናግረዋል።

በዘንድሮ መርኃ ግብር የአካባቢውን ሥነ-ምህዳር በማሻሻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሴ ጋጂት በመርኃ ግብሩ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ተማሪዎች በስፋት እንደሚሳተፉ አመልክተዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

የአኝዋሃ ዞን አስተዳዳሪ ኡቦንግ ኡጁሉ በበኩላቸው የሽብር ቡድኖችን እኩይ ሴራ በመመከት የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስኬታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።