ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት🙏(ጫንጮ)
775 subscribers
84 photos
4 files
98 links
ሰንበት ትምህርት ቤት የመልካም ወጣት የመልካም ትውልድ መፍለቂያ ናት! ትውልድን ለበጎ ነገር የምታበቃ ናት፡፡


የጫንጮ ከተማ ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ቻናል
ለሀሳብ እና አስታየት @weldebirhanbot @ty1921 ይጠቀሙ

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
Download Telegram
ናፍቆናል መቅደስህ !!!


ያ የሚያምረው መቅደስ የታቦት ማደሪያው፣
የሕይወት እንጀራ ቃሉን መመገቢያው
የነፍስ መድኃኒት ቁርባን መቀበያው፣
የጥምቀት የተክሊል ምሥጢር መፈጸሚያው፣
የቀዳሽ ያስቀዳሽ ጸሎት ማሳረጊያው፣
የሰው ያለህ ይላል ጭር ብሎ ቤቱ፣
ምስጋና የሚያቀርቡት ቀርተው ሕፃናቱ ፡ሴት ወይዛዝርቶቹ ደግሞም አዛውንቱ ፣
ወጣቶች ጎልማሶች እንዲሁም መኳንንቱ ፡
ሁለት ወር ሆናቸው ከቀሩ ከቤቱ ፡ወንበሩ ባዶውን አቤት ማስፈራቱ
ዘንድሮስ ሞተናል በሕይወት የለንም
በደላችን በዝቶ ያውም በዓብይ ጾም
ቤቱ ዎና ሆነ ምዕመናኑ የሉም
ካህናት ዲያቆናት ተሟልተው አይታዩም።
አወይ ማሳዘኑ አወይ ማስለቀሱ በታላላቅ በዓላት ጭር ብሎ መቅደሱ
የምናከብራቸው በዓላቱ በሙሉ ሆኖ የማያውቀውን ዘንድሮ ታጎሉ
የትንሣኤው ደስታ ክብሩ ቢቀርብን በተደበቅንበት በቤታችን ሆነን
አባቶች በመቅደስ ሲላቀሱ እያየን ጡት እንዳስጣሉት ልጅ እኛም አለቀስን
መንበረ ጸባዖት ይድረስ ጩኸታችን
እንደወጣን አንቅር ከቤትህ መልሰን
ናፍቆናል መቅደስህ ዳግም ዕድል ስጠን
ይቅር በለንና በቤትህ ሰብስበን
ግድ ሆኖብን እንጅ ወደነው አይደለም
እንዲህ ያለ አምልኰት ልንለምደው አንችልም
በሞዐብ ምድር ላይ ሙሴ እንዳንቀላፋው፣
ምድሪቷን ሳይረግጣት ሳይገባ ከተስፋው፣
በሩቅ በዓይኑ እያየ መግባት ተመኝቶ፣
ሳይገባባት ቀርቷል ያቺን ምድር ከቶ።
አሁንም አባት ሆይ ሳንገባ ከመቅደስ፣
እንደ ወጣን ቀርተን ዳግም ሳንመለስ፣
ብርቱ ኀዘን እንዳይሆን እንደቸርነትህ
በይቅርታህና በምሕረት ደግፈህ
ከመአት ከመቅሰፍቱ ከክፉ ጠብቀህ፣
ለመቅደስህ አብቃን እንደ አባትነትህ ኤልሻዳዩ ንጉሥ አንተ ይቅር ባይ ነህ። አሜን
@yeberhanljoche
ወጣትነት
ወጣትነት ከሁሉም የእድሜ ክልል በሁሉም ነገር የሚበልጥ ኃይል የምናገኝበት ጊዜ ነው። አካላዊም ሆነ አዕምሯዊ አቅማችን ብርቱ የሚሆንበት ጊዜ ነው። ይህንን ጊዜያችንን ብንጠቀምበት ብዙ ነገር ለክርስቶስ ማድረግ እንችላለን። ዛሬ ያለን ኃይልም ሆነ ዛሬ ያለን ጊዜ ነገ ወደ ስራ ዓለም ስንገባ፣ ነገ ወደትዳር ዓለም ስንገባ እናጣዋለን። ስለዚህ ዛሬ ላይ ወጣትነታችንን ለክርስቶስ እንስጥ። እግሮቻችን ብርቱ ሳሉ ወደቤቱ ዘወትር እንገስግስ፣ አእምሯችን በሳል ሳለ ክርስቶስን እናገልግል፣ ወደ አገልግሎት እንግባ፣ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ ፈጣሪን እናስብ፣ ይህን በማህበራዊ ሚዲያ የምናጠፋውን ጊዜ ነገ ወደሥራና ትዳር ዓለም ስንገባ አናገኘውም። ስለዚህ በከንቱ ምንም ጥቅም በማይገኝበት ወሬ ብቻ ጊዜያችንን ከምናሳልፍ አይተናቸው የማናውቃቸውን ቁጥራቸው የተከመረውን መንፈሳዊ ገጾች እንመልከት፣ መንፈሳዊ ትምህርቶችን እናዳምጥ፣ ጽሁፎችን እናንብብ፣ ሰይጣን ይህን የሚጠቅመንን ነገር አሰልችቶን በማይጠቅም ከንቱ ነገር ጊዜያችንን እያስባከነ እንደሆነ ይግባን። ወጣትነታችንን ለክርስቶስ ኢየሱስ እንስጥ፣ ይህን ዕንቁ ጊዜያችንን በከንቱ አናባክን።
@yeberhanljoche
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል
"ሰኔ ፲፪"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ: ብኡላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ: እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ: ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ: ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።

ዚቅ
ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይመክሮ: አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት: ኢየኀልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ: ወአልቦ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ: አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ: ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ።

ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል: እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ
አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ: ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ: ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ: ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ: ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ: ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ: ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ።

ወረብ
ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/
ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ: በእንተ ስጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ: ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ: ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ: በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ/፪/

ዚቅ
አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ: ዘኢይረክቦን ጥረስ: ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ: እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ: መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ።

ዚቅ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ: ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ: ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ።

ወረብ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/
ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ: ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ: ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ: ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ: እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ።

ዚቅ
ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ: ወእከስተ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን: ወእፈውስ ሎሙ ለቁሱላነ ልብ: ወእሰምዮ ለባሕራን ኅሩየ: ዝኬ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት: ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም: ወርእየቱ ከመ ተቅጻ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ።

ወረብ
"ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/
ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ: ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ: ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ: አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ: ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ።

ዚቅ
ቅዱሳት አጻብኢከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ: ወብጹዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ: ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ።

ወረብ
ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/
ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ "ሚካኤል መልአክ"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ: ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ: ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ: ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ: ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።

ዚቅ
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል: ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ: አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ።

ወረብ
መልአከ ሰላምነ/፬/
ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል በእንቲአነ/፪/

ምልጣን
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ: ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ: ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ: ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ።

አመላለስ
ወሪዶ እመስቀሉ/፪/
እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/

ወረብ
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/

እስመ ለዓለም
እምድኅረ ተንሥአ እሙታን ዓርገ ውስተ ሰማያት በስብሐት አምላከ ምሕረት: ወተቀብልዎ አዕላፋ አዕላፋት: ወሚካኤል ሊቀ መላእክት በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር: ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር።

ዓዲ (ወይም)
እስመ ለዓለም
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ: አዓርግ ሰማየ አቡየ ወአቡክሙ: ኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ: ዘንተ ይቤሎሙ ዓርገ ውስተ ሰማያት: ካዕበ ይመጽእ በዘዚአሁ ስብሐት: ሠርጎሙ ለሐዋርያት ብርሃኖሙ ለእለ ውስተ ጽልመት: መድኃኔ ነገሥት ክብሮሙ ለመላእክት ኖላዊሆሙ።

አመላለስ
በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር/፪/
ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር/፪/
ኦ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ዕቀብ ሕይወተነ ወሥረይ ኀጢአተነ፤
አድኀነነ ወባልሐነ ከመ ኢይርከብ ኃይለ ላዕሌነ ዝንቱ ደዌ ዘኮነ በመዋዕሊነ፡፡
ክፍለነ እምበረከትከ ቅድስት፡ በጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለ አሥመሩከ እምፍጥረተ ዓለም፡፡
@yeberhanljoche
#ቅዱስ_ላሊበላ

📖ሰኔ ፲፪
https://t.me/yeberhanljoche

ቅዱስ ላሊበላ የተወለደው በላስታ ሮሃ ቤተመንግሥት በዋሻ እልፍኝት ውስጥ ታህሳስ ፳፱ በ፲፩፻ወ፩ ዓ/ም ሲሆን በዛሬው ዕለት ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ያረፈበት ነው።
ይህ ቅዱስ ጌታችን የጠጣውን መራራ ሐሞት እያሰበ ዓርብ ዓርብ ኮሶ ይጠጣ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ ቅዱሳን መካናትን፤ ወደ ሰማይም ወስዶ የቤተ መቅደሶቹን አሠራር አሳይቶታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚሠራበትን እግዚአብሔር እንዲገልጥለት ሱባኤ ቢገባ ቤተ ማርያም ከተፈለፈለችበት ቦታ የብርሃን ዐምድ ተተክሎ አይቷል።
ቅዱስ ላሊበላ ጎጃም በመሔድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን ተምሯል። ላሊበላ ከወንድሙ ቀጥሎ እንደሚነግሥ ትንቢት ተነግሮ ስለነበር ንጉሡ ሊገድለው ምክንያት ይፈልግበት ነበር፡፡ በእናትም በአባትም እኅት የምትሆነው፣ ለላሊበላ ግን በአባት ብቻ እኅት የሆነችው ላሊበላን ለመግደል አጋጣሚ ትጠብቅ ነበር፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ጌታችን መራራ ሐሞት መጠጣቱን እያሰበ ዓርብ ዓርብ ከጾመ በኋላ ኮሶ ይጠጣ ነበርና እኅቱ አጋጣሚውን በመጠቀም መርዝ ጨምራ ሰጠችው።
ለቅዱስ ላሊበላ መርዝ ጨምራ የሰጠችውን እርሱ ከመጠጣቱ በፊት ያገለግለው የነበረ ዲያቆን ሲቀምሰው ወዲያው ሞተ፡፡ ዲያቆኑ ያስመለሰውን የጠጣው ውሻም ወዲያው ሞተ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም አገልጋዩ ለእሱ የተዘጋጀውን መርዝ ጠጥቶ እንደሞተ ባየ ጊዜ መርዙን ጠጣው፡፡ የጠጣው መርዝም ከሆዱ ውስጥ ሆኖ ያሰቃየው የነበረውን አውሬ አወጣለት። እሱም በተአምር ተረፈ።
በዚህ ምክንያት ቅዱስ ላሊበላ ለሦስት ቀናት አያይም አይሰማም ነበር። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ሰማይ ወስዶ ሰባቱን ሰማያት አሳየው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በመጀመሪያ አክሱም ከዚያም ኢየሩሳሌም ወስዶ በዚያ የነበሩትን ቅዱሳት መካናት አሳየው። ኢትዮጵያውያን ወደ ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉዞ ሲያደርጉ ይደርስባቸው የነበረውን መከራ እያሰበ ያዝን ነበርና በሮሐ ዐሥራ አንድ አብያተ ክርስቲያናትን ፈለፈለ።
ቅዱሱ አባት በሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በድፕሎማሲም የተዋጣለት ስለነበር በቱርኮች ተይዞ የነበረውና በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሡልጣን ገዳማችን እንዲመለስልን አድርጓል። ከውቅር አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ በርካታ ቤተ ክርስቲያኖችንም ሠርቷል፣ ንግሥናን ከክህነት፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አስተባብሮ የያዘው ቅዱስ ላሊበላ በዚች ሰኔ ፲፪ ቀን አርፏል።
🙏የቅዱሱ አባት የቅዱስ ላሊበላ ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን!!🙏

ለሌሎች መረጃዎች👇
https://t.me/@yeberhanljoche
“እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ” /ማቴ.10፡16/

እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን! አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡
@yeberhanljoche
ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይጸልያሉ። አንደኛው ጸሎቱ ተመለሰለት፣ አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ጸሎቱ ያልተመለሰለት፡- “ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ጸለይን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ የከለከልከኝ ለምንድን ነው?” አለው። እግዚአብሔርም፡- “ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ትጠፋለህ” አለው።

እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሣቱም ሁለቱም ለፍቅር ነውና ስለሆነልን ስለሚሆንልንና ስላልሆነልን ነገር ሁሉ ተመስገን ማለትን አንርሳ፡፡
@yeberhanljoche
ከቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ውድ ቃላት ውስጥ

"ሁሉን ነገር በኢየሱስ ክርስቶስ ታደርጋለህ"(Epistle Of Ephesians Chapter 8)

"ክርስትና የዝምታ ነገር ብቻ አይደለም ነገርግን ታላቅነት የሚገለጥበት ነው"
(Epistle Of Romans Chapter 3)

"የዓለም ተድላዎች ሁሉ እና የዚህች ምድር መንጎስታት ሁሉ ምንም አይጠቅመኝም በዓለም ዳርቻ ሁሉ ከመገዛት ይልቅ ለኢየሱስ ክርስቶስ መሞቴ ለእኔ ይሻላል"
(Epistle Of Romans Chapter 6)

"የእግዚአብሔርን እንጀራ፣የሰማይን እንጀራ፣የሕይወትን እንጀራ እፈልጋለሁ እርሱም ከዳዊት እና ከአብርሃም ዘር በኋላ የተገኘው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ ነው እና የማይጠፋ ፍቅር እና የዘለዓለም ሕይወት የሆነውን የእግዚአብሔር መጠጥ ማለትም ደሙን እፈልጋለሁ"
(Epistle Of Romans Chapter 7)

"ክርስቶስን አለማመን ከባድ ነው የሐዋርያትን ስብከት ውድቅ ማድረግ ከባድ ነው"
(Epistle Of Philadelphia Chapter 8)

"አንድ ክርስቲያን በራሱ ላይ ስልጣን የለውም ነገርግን ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ዝግጁ መሆን አለበት"
(Epistle Of Polycarp Chapter 7)

ይህ ቅዱስ እንዳውም ቴዎፎሮስ(ክርስቶስ የተሸከመው)ተብሎ የሚጠራ እና
ለክርስቶስ ሲል በሮም አደባባይ በትራጃን አማካኝነት ለአንበሶች የተጣለ እና በአንበሶች ተበልቶ ሰማዕትነቱን የፈፀመ ነው።

ወንጌሉንም በተግባር የኖረ ነው በሰባት መልዕክቶቹም በብዛት ለካህናተ ቤተክርስቲያን እንድንታዘዝ እና የካህናትን ክብር እንዲሁም ከተለያዩ የስህተት አስተምህሮዎች ስለመጠበቅ አስተምሮናል ባጠቃላይ ሐዋርያት ያፀኗት በክርስቶስ ኢየሱስ ራስነት የተመሰረተችው ቤተክርስቲያን በሐዋርያነ አበው ዘመን የነበራትን አቋም በመልዕክቶቹ ውስጥ መገንዘብ እንችላለን እንማራለን።

ይህ ቅዱስ ታሪኩ አስተማሪ ነው ደግሞም ታሪኩን ስናጠና ቤተክርስቲያን ስንት ፈተና አሳልፋ ለዚህ ጊዜ መድረሷን እና በዛ ጊዜ የነበረውን ማለትም የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ክርስትና ሒወት እናይበታለን።

ይህ ቅዱስ በሀገራችን ውስጥ ከጓደኛው ከቅዱስ ፖሊካርፐስ ጋር ሰላሌ ኦሮሚያ ውስጥ ቤተክርስቲያን አለው።
ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ሰማዕት የሆነበትም ቀን ሐምሌ ፯ ቀን በ፻፯ዓ/ም ነው።
በረከቱ ይድረሰን

ይህ ቅዱስ ለጓደኛው ለቅዱስ ፖሊካርፐስም ጭምር መልዕክት የፃፈ ሲሆን የፃፋቸው መልዕክታትም
፩ወደ ኤፌሶን ክርስቲያኖች
፪ወደ ማግኔዥያ ክርስቲያኖች (አሁን በዚህ ስም ለምትጠራው አገር ሳይሆን ጥንት የክርስቲያኖች መኖሪያ ለነበረችው እና ዛሬ በቱርክ ውስጥ ለምትገኝ ቦታ ነው)
፫ወደ ሮም ክርስቲያኖች
፬ወደ ትራሊያ ክርስቲያኖች
፭ወደ ፊላዴልፊያ ክርስቲያኖች
፮ወደ ሰርመኔስ ክርስቲያኖች
፯ወደ ጓደኛው ቅዱስ ፖሊካርፐስ ነው።
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
#አንተ_አንቺ_ማለት ...

ፀሀይዋን ተመልከታት አታምርም ? ጨረቃዋስ ከዋክብቱስ ዛፎቹ ወንዙና ተራራውስ አያምሩም ? ያምራሉ እኚ ሁሉ ግን ያልፉሉ አንተ ግን በሞት ከዚህ አለም ብትለይ እንኳን በሰማይ ለዘላለም ትኖራለህ ፈጣሪ ፍጥረታትንን ሁሉ በቃሉ በመናገር እና በሀሳብ (በሀልዮ) ሲፈጥር አንተን ግን በእጁ አሽሞንሙኖ ፈጥሮሀል አንተ ማለት ክርስቶስ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለው ማንም ሚከፍትልኝ ቢኖር ገብቼ እራቴን ከእርሱ ጋር እበላለው ብሎ የተናገረልህ ነህ ፈጣሪ አለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ አለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል ተብሎ የተነገረልህ ዋጋ የከፈለልህ የመንግስቱ ወራሽ ውድ ልጁ ነህ ምን አልባት ዛሬ በተለያየ ሱስ ተይዘህ ይሆናል ምን አልባት ስራ በማጣት ፍቅረኛ በማጣት ትሰቃይ ይሆናል ምን አልባት ቤተሰብህ ወገንህ ተስፉ ቆርጦብህ ይሆናል ምን አልባት ሞትህን እየተመኘህ ይሆናል ግን አይዞህ ፈጣሪ በአንተ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ አትሞትም

ሰው ተስፉ ቢቆርጥብህ እራስህም ተስፉ ብትቆርጥ የፈጠረህ በአንተ ላይ ተስፉ አይቆርጥብህምና አይዞህ 1 ጠጠር አንስተህ ተራራ ላይ ብትወረውር ተራራው ምንም አይሆንም ጠጠሩ ተንከባሎ እግሩ ስር ይሆናል ያን ጠጠር አንስተህ መስታወት ላይ ብትወረውረው ግን መስታወቱ ይሰባበራል ጠጠሩን በችግር እንመስለውና ችግር ወዳንተ ሲመጣ እንደ መስታወቱ አትሰባበር እንደ ተራራው በቁጥጥር ስር አውለው 1 የተለኮሰ የክብሪት እንጨት ጭድ ላይ ብትጥለው ይቀጣጠላል ውሀ ላይ ብትጥለው ግን ውሀው ያጠፉዋል የሚያቃጥሉ ነገሮች በህይወትህ ውስጥ ሲከሰቱ እንደ ጭድ አትቀጣጠል እንደ ውሃው አጥፉቸው

እህቴ ምን አልባት ለስራ ጉዳይ በተለያየ ሀገር ውስጥ ሆነሽ ይሆናል ያለሽው መፈጠርሽ ሴትነትሽም አስጠልቶሽ ይሆናል። ግን ክርስቶስ ወደ አለም ሲመጣ ምድራዊ እናት እንጂ አባት አላስፈለገውም የሴት ልጅ ተብሎ እስኪጠራ ድረስ ማርያም ብቻዋን ነው ያሳደገችው። በኛ ቤተክርስቲያን ህንፃ ቤተክርስቲያኑ ተሰርቶ አለቀ የሚባለው ጉልላቱ ተሰርቶ ሲያልቅ ነው ። ፈጣሪም ፍጥረትን ሁሉ ፈጥሮ ሲጨርስ አዳምን ፈጠረ በመጨረሻም ከጎኑ ሄዋንን ወይም አንቺን የስነ ፍጥረት ጉልላት አርጎ ፈጠረሽ ስለዚህ እህቴ ክብርት ፍጥረት ነሽና ደስ ይበልሽ
@yeberhanljoche
✥ የተቆለፈ ሳጥን

#ልዩ_ልዩ

አንድ በተቆለፈ ሳጥን ላይ ተቀምጦ የሚለምን ለማኝ ነበር። ከእለታት በአንዱ ቀንም በዚያ መንገድ የሚያልፍ ሰው ወደሱ ጠጋ ብሎ ለመሆኑ የተቀመጥክበትን ሳጥን ከፍተህ ውስጡን አይተህ ታውቃለህን ? ብሎ ጠየቀው። ለማኙም አረ አላቅም አለና ከፍቶ ቢያየው ሳጥኑ በወርቅ በብር የተሞላ ነበር። እኛም እንደዛ ነን እኔ ዋጋ የለኝም አልረባም ብኖር ባልኖር። አልጠቅምም እንላለን። ግን አንድም ቀን ውስጣችንን አይተን አናውቅም። ውስጣችን ግን ወርቅ በመሰሉ አላማዎች እንቁ በመሰሉ በጎ ሀሳቦች የተሞላ ነው። ማይልስ እንዳለው የአለም ውድ ሀብት ያለው በአረብ ሀገራት የነዳጅ ቦታ ውስጥ አይደለም የአለም ውድ ሀብት ያለው በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ቦታዎች ውስጥም አይደለም ።የአለም ውድ ሀብት ያለው የመቃብር ቦታዎች ውስጥ ነው።

ምክኒያቱም ብዙዎች ወደዚህ አለም ይዘው የመጡትን አላማና ራዕይ አውጥተው ሳይኖሩትና ለአለም ሳያበረክቱት ስለሚሞቱ ነው። ማግኘት ማጣት የጊዜ ጉዳይ ነው። ማንም ባዶ የለም ምንአልባት አሁን ባዶ እጃችንን እንሆን ይሆናል ነገር ግን ባዶ ልባችንን አልተፈጠርንም። ለዝች አለም የምናበረክተው አንዳች ነገር በውስጣችን አለ። እኛ ምን አልባት ለቤተሰቦቻችን በስህተት የተወለድን ይመስላቸው ይሆናል። ነገር ግን በስላሴ ዘንድ መለኮታዊ አጀንዳ ተይዞልን ለአለማ ተወልደናል። አለም ላይ ላሉ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ የያዝን አለን: ለተዘበራረቀው ፖለቲካችን የተስተካከለ የአመራር ብቃት ያለን አለን ፡ እየጠፉ ላለው ስነፅሁፋችን የተባ ትንቱግ ብዕር የጨበጥን አለን ፡ ብቻ ሁላችንም ውስጥ ውድ ሀብት አለ። እኛ ግን ቆልፈንበት ተቀምጠናል እናውጣው እንጠቀምበት
@yeberhanljoche
😃አስደሳች ዜና ለጫንጮ ነዋሪዎች በሙሉ😃
የጫ/ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲና ቅ/ኪዳነ ምህረት አብያተ ክርስትያናት ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ክረምት ክረምት ከ4ኛ ክፍል እስከ 9ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ላለፉት አስርት አመታት ሲያስተምር መቆየቱ ይታወቃል በዘንድሮ አመትም ተማሪዎችን ሰብስቦ ለማስተማር ዝግጅቱን ጨርሷል
ታዲያ መማር የምትፈልጉ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን እንዲሁም የማስተማር ችሎታው እና ፍላጎቱ ያላቹም በ#0968057940 ላይ በመደወል ማስተማርና ከቅዱስ እግዚአብሔር አብ በረከት እረዴት መካፈል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የትምህርቱ ፍፃሜ ላይም የትምህርት ቢሮ ማህተብ ያለበትን የምስክር ወረቀት እንደምንሰጥ ልናሳውቅ እኖዳለን።
እንዳያመልጦት!!!!

😃 Oduu gammachiisaa jiraattota magaalaa Caancoo hundaaf 😃
Mana Dilbata Caancoo waqaa abaa fi qulquleetii waadaa araaraa Waggoota kurnan darbaniif barattoota kutaa 4ffaa hanga 9ffaatti jiran barnoota gannaa barsiisaa akka ture ni beekama.
Baranas qophii barsiisuu xumure barsiisuu jalqabe jira.
warri barachuu barbaaddan galmaa'uu ni dandeessu,
akkasumas warri dandeettii fi fedhii barsiisuu qabdan immoo #0968057940 iratti bilbiluun barsiisuu fi eebba qulqulluu waqaa abbaa irra argachuu ni dandeessu.

Iddoo barumsicha itii kenamuu giibii mana amantaa waqaa abbaa keessa

Xumura barumsa kana irratti waraqaa ragaa chaappaa Waajjira Barnootaa qabu akka kenninu ni beeksifna.
Carraa kun akka isin Hin darbiinee!!!!
"እየጠላን የምናደርገው"

ብዙ ሰው ‹‹እኔ ሐሜት አልወድም፡፡ ግን ማማት የሚወዱ ጓደኞች አሉኝ›› ይላል፡፡ አሁን እርሱ ምን እያደረገ ነው? ‹‹ወዳጆቼ ሐሜተኞች ናቸው›› ሲል እያማቸው አይደለምን? ወይስ ለእርሱ ሲሆን ሐሜቱ ተለውጦ የመረጃ ቅብብል ይሆናል?! በነገራችን ላይ ይህ የዚህ ጽሑፍ መግቢያ ራሱ ሐሜት ነው።

የማንወደው ነገር ግን እየጠላንም ቢሆን የምናደርገው ኃጢአት ሐሜት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሜተኛ ሆኖ የተጠቀሰው በእባብ ያደረው ሰይጣን ነው፡፡ በመጀመሪያ የታማው ደግሞ እግዚአብሔር ሲሆን፣ ሐሜቱን ሰምታ ሳትመረምር የተቀበለችውና ለስሕተት የቸኮለችው ሴት ሔዋን ነበረች፡፡(ዘፍ 3፥1-5)

የሰይጣን ሐሜት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አንደኛ "አትሞቱም፤ እንደ እርሱ እንዳትሆኑ ነው የከለከላችሁ" በሚለው ንግግሩ "እግዚአብሔር ዋሽቷችኋል" እያለ ፍቅሩን እንድትጠራጠር እያደረገ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ከዛፉ ብትበሉ እንደ እርሱ ትሆናላችሁ በማለት የእግዚአብሔር አምላክነት "የዛፍ ፍሬ" በመብላት የተገኘ መሆኑንና እርሱም እንደ እነርሱ የነበረበት ጊዜ እንዳለ እንድታስብ እየገፋፋት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስም ማጥፋት (Character assassination) ከየት ሊገኝ ይችላል? ሰይጣን በነገር ሁሉ ፍጹም የሆነን አምላክ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሐሰት ፈጥሮ ለማማት ወደ ኋላ ካላለ፣ አንዳች ጉድለት የማያጣብን እኛማ ከሐሜቱ ጅራፍ ልናመልጥ እንደማንችል ሊታወቅ ይገባል፡፡

በተለይ በአሁን ጊዜ ሐሜት በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሥሩን ሰድዷል። እንደውም ባልንጀራን ማማት እንደ ምግብ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን በዚህች ደሃ አገር ከመጠን በላይ ወፍረን እንቸገር ነበር። ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን የሐሜት አውድማዎች ሆነዋል። በየገጾቻችን ከሽነን የምናቀርባቸው ጽሑፎች ጠረናቸው የሰው ሥጋ የሰው ሥጋ ይላሉ። ፊታችን በሐሜት ወይቦ ሁለት መልክ ካወጣን ቆየን። ይኸው ሳንባችን በማማት አየር ተመርዞ ሳሉ ከበረታብን ሰነባብተናል። ወዳጃችንን የማናማበት ብቸኛው ጊዜ ከእርሱ ጋር የምንሆንበት ሰዓት ነው። ያውም ደግሞ ያንኑ ጊዜ ሌላኛውን ሰው ለማማት ካልተጠቀምንበት ማለቴ ነው።

ሊቁ ዮሐንስ ካዝያን እንደሚናገረው ሰው ከሚጠቅመው ቃለ እግዚአብሔር ይልቅ የማይጠቅመው ሐሜት ያጓጓዋል። የአምላክ ቃል ሲነገር እንቅልፍ እንቅልፍ የሚለው ሁሉ፣ የሐሜት ነገር ሲሆን ግን እንደ እርሱ ንቁ የሚሆን የለም። በጥፍሩ ቆሞ ይሰማል። ሌሊቱን ሁሉ ሳይተኛ ቢያድር ደስ ይለዋል።

ለመሆኑ ባልንጀራችንን ስለ ምን በቀስታ እናማዋለን? የወዳጃችንንስ ውድቀት በማውራት በእኛ ላይ የምንጨምረው ምን በጎ ነገር አለ? በሰው ፊት መልካም እየመሰልን ከኋላው ግን ስለ እርሱ ውድቀት በማውራት የራሳችንን ደረጃ ከፍ ማድረግ አይቻልም። ስለ ሌሎች በማውራት የምናጠፋውን ሰዓት ራሳችንን ለማሳደግ ብንጠቀምበት ኖሮ "መኖራችንን ትርጉም እንዲኖረው" ማድረግ ይቻለን ነበር።

"ንጹሕ ወዳጅነት" ሐሜትና ማሾክሾክ የሌለባት የታማኞች ጌጥ ናት። የሐሜት ስለታቸውን ያልጣሉ ሰዎች "እውነተኛ ባልንጀርነት"ን አያውቋትም። አንተ በፍቅር ወዳጅ አድርገህ ከፊትህ ስታቀርባቸው እነርሱ ከኋላህ ሆነው የሚያሙህን አትጥላቸው፤ አትጣላቸው። ነገር ግን የሐሜቱ እርሾ እንዳያገኝህ ቶሎ ተለያቸው። ከፊትህም አድርገህ አታሰቃያቸው። የእነርሱ ቦታ ከኋላህ መሆን ነው።

ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።

ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።

"ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" ገላ 5፥15

@yeberhanljoche
††† እንኳን ለእናታችን ቅድስት መሪና ሰማዕት እና ቅዱስ ለንጊኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ታላቋ ቅድስት መሪና ሰማዕት (SAINT MARINA THE GREAT) †††

††† እናታችን ቅድስት መሪና ስም አጠራራቸው ከከበረ : ተጋድሏቸው ካማረ ታላላቅ ሴት ሰማዕታት አንዷ ናት:: ተወልዳ ያደገችው ከዋናው ዘመነ ሰማዕታት በፊት በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን ሶርያ አካባቢ ነው:: አባቷ ዳኬዎስ የሚባል ጣዖት አምላኪ ቢሆንም እናቷ ግን ክርስቲያን ነበረች::

ነገር ግን እናቷ ገና በ5 ዓመቷ ሞተችባትና ለሞግዚት ተሰጠች:: የእግዚአብሔር ጥበብ ሆኖ ሞግዚቷ ደግ ክርስቲያን ነበረችና ለ10 ዓመታት ሃይማኖተ ክርስቶስን እና ምግባረ ጽድቅን አስተማረቻት:: ዕድሜዋ 15 ዓመት ሲሆን አባቷ ዳኬዎስ አረፈ::

በዘመኑ ዳኬዎስ የሚሉት (ቅዱስ መርቆሬዎስን የገደለው) ክፉ ንጉሥ ነበርና ክርስቲያኖችን አሳደዳቸው:: ይህን ዜና ቅድስት መሪና ስትሰማ ደስ አላት:: እጅግ ባማረ ንጽሕና እንደ ኖረች ሁሉ በክርስቶስ ስም ደሟን ለማፍሰስ አስባ ወደ ንጉሡ መኮንን ሔደች::

††† አበው እንዳስተማሩን ከሴቶች ሰማዕታት በውበትና ደም ግባት እንደ ቅዱሳት:-
*መሪና
*አርሴማ እና
*ጣጡስ የሚያክል የለም:: ዐይንን ማፍዘዝ የሚችል ውበት ነበራቸው::

መኮንኑ መልኩዋን ዐይቶ ሰውነቱ ተናወጠ:: "ጣዖት አምልኪና የእኔ ሚስት ሁኚ" አላት:: እርሷ ግን መኮንኑን ከነ ጣዖቱ አቃለለችው:: "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ" አለችው::

መኮንኑ ካነጋገሯ የተነሳ ተቆጥቶ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ:: መሬት ላይ ጥለው በብረት ዘንግ ቢመቷት አካሏ እየተቆረጠ ብዙ ደም ፈሰሰ:: ወስደውም ጨለማ ውስጥ ጣሏት:: ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ አድኗት: አጽንቷትም ዐረገ::

በማግስቱ በመጋዝ አካሏን ቆራርጠው ጣሉ:: ዳግመኛ ሊቀ መላእክት አዳናት:: ወደ ጨለማ ክፍል ወስደው ሲጥሏት ትልቅ ዘንዶ መጣባት:: እጆቿ ተዘርግተው እጸለየች ዋጣት:: እርሷ ግን ጸሎቷን ቀጠለች:: ከደቂቃዎች በሁዋላ ግን ዘንዶው ለ2 ተሰነጠቀና እጆቿ እንደተዘረጉ ወጣች::

በሌላ ቀን ግን ሰይጣን ፊት ለፊት መጥቶ ታገላት:: ከሰማይ ነጭ ርግብና መስቀል ወርዶላታልና አልቻላትም:: ከእግሯ በታች ጥላ ደጋግማ ረገጠችው:: ሰይጣንም በሐፍረት እየጮኸ ሔደ::
"ለሰይጣን ኬደቶ ከመ አሣዕን በእግር" እንዲል:: (እንዲህ ነበሩ የቀደመው ዘመን እናቶቻችን)

መኮንኑ ከክርስትና ያስወጣት ዘንድ በትልቅ ጋን ውሃ አስፈልቶ "በዚያ ላይ ቀቅሏት" አለ:: ድንገት ግን ከሰማይ ነጭ ርግብ ወርዳ: ውሃውን አቀዝቅዛ: 3 ጊዜ በውሃው አጠመቀቻት:: (እስከዚህ ሰዓት ድረስ አልጠመቀችም ነበርና)

ርግቧ የብርሃን ልብስ አልብሳ: አክሊለ ክብር ደፋችላት:: መኮንኑ ተስፋ ስለ ቆረጠ "አንገቷን በሰይፍ ምቱ" አለ:: በዚያች ሰዓት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ "ብጽዕት መሪና ብጽዐን ይገባሻል" አላት::

"ስምሽ በሚጠራበት: መታሰቢያሽ በሚደረግበት ሁሉ በዚያ ረድኤት: በረከት ይበዛል:: አንቺን ያከበረውን አከብረዋለሁ:: ከርስትሺም አስገባዋለሁ" ብሏት ጌታችን ዐረገ::

ወታደሮቹ አንገቷን በሰየፉ ጊዜ ታላቅ መነዋወጽ ሆነ:: ድውያን ተፈወሱ: ዕውሮች አዩ: አንካሶች ረቱ: የማይሰሙትም ሰሙ:: ቅዱሳን መላእክትም ከሰማያት ወርደው የቅድስት መሪናን ነፍስ በዝማሬ አሳረጉ::

††† ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት †††

††† ለንጊኖስ ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው:: ስለ ጌታችን ተአምራት በየጊዜው ይሰማ ነበር:: ሔዶ እንዳያገኘው ግን አይሁድን ይፈራ ነበር:: እነርሱ "በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይባረር" ብለው ነበርና:: (ዮሐ. 9:22)

ጌታችን በተሰቀለባት ዕለተ ዐርብ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጌታን እንዲሰቅሉ ከታዘዙ ወታደሮች እንደ አንዱ ተመርጦ ነበርና በዘዴ "አሞኛል" ብሎ እስከ 9 ሰዓት ድረስ ቆየ::

በሁዋላ ግን አይሁድ "በክርስቶስ ሞት ያልተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው" የሚል አዋጅ በማስነገራቸው እየፈራ ቀራንዮ ሲደርስ "ጐኑን ውጋው" ብለው ረዥምና ጥቁር ጦር ሰጡት:: ለንጊኖስ ወደ ጌታችን ዐይን ተመለከተ:: እያየው እንዳልሆነ ገመተ::

ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷልና ጦሩን ጨብጦ ወደ ጌታ ጐን ልኮ ወጋው:: ከጌታ ቀኝ ጐንም በ"ለ" አምሳል ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ:: አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዐይኑን አበራች::

ለለንጊኖስ ታላቅ ደስታ ሆነ:: ለእኛ ግን ማየ ገቦና ደመ ገቦ ፈለቀልን:: የጌታችን ትእግስቱና ቸርነቱ ግን ይደንቃል::
"ከመ ኢየሐስብ ቦቱ ዘኩናተ እዱ ርግዘቶ::
በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ::
ምሕረቶ እሴብሕ ወዐዲ ትዕግስቶ::" እንዳሉ ሊቃውንት::

ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት : ስለ ሃይማኖትም ተማረ:: ተጠምቆ: ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ:: ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ::

በመጨረሻም በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት: አንገላቱት:: የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት:: የጽድቅ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና:: በዚህች ዕለትም አይሁድ አንገቱን ቆርጠውት ለሰማዕትነት በቃ:: ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል::

††† እግዚአብሔር በቸር ጥሪው ሁላችንም ወደ ቀናው የጽድቅ ጐዳና ይጥራን:: ከሰማዕታቱም ረድኤት በረከት ይክፈለን::

††† ሐምሌ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት መሪና እናታችን (ታላቋ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ለንጊኖስ ሐራ (ሐዋርያና ሰማዕት)
3.ቅዱስ አብጥልማዎስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል

††† "ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም:: ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው:: ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ:: ያየውም መስክሯል : ምስክሩም እውነት ነው:: እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ : እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል:: ይህ የሆነ:-
"ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው:: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:-
"የወጉትን ያዩታል" ይላል::" †††
(ዮሐ. 19:33)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

https://t.me/yeberhanljoche
ቅበላ ዓላማው ምንድን ነው?


ስለ ቅበላ ያለን አመለካከት በልማዳችን ውስጥ የተንሸዋረረ ነው። ከጾም ጋር ተያይዞ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ከሚፈጸሙ ተግባራት መካከል በአጽማት መግቢያ የሚደረገው የአቀባበለ ሥነ ሥርዓት ነው። ይህ ሥርዓት በራሱ መጸሐፍ ቅዱሳዊ ይዘት ያለውና በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያንም የተለመደ ትውፊታዊ ቅብብሎሽ ያለው ሥርዓት ነው። ይህ ግን አሁን ከምንፈጽመው የቅበላ ሥርዓት የተለየ ነበር። ጥቂት ማሳያዎችን እንመልከት።

1:- በመጸሐፍ ቅዱስ አይሁድ ቀዳሚት ሰንበት ከመግባቷ በፊት በዋዜማው የተለየ አቀባበል ያደርጉ ነበር። ዓርብ ፀሐይ ሲገባ ካህኑ ደውል
ይደውላሉ አሊያም በቤት ያለ የቤቱ አባወራ የሰንበት
መግቢያ ሰዓት መቃረቡን ድምጽ በማሰማት ያሳውቃል፡፡ በአካባቢው ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በአንድ ላይ ሆነው ወደ ፀሐይ መውጫ ይሰግዳሉ፡፡ ጸሎት ይደረጋል፡፡ ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል፣አሥርቱ ቃላት ሌሎችም ንባባት ይደገማሉ፡፡ ማብራት ተይዞ “ዕለተ ሰንበት እንኳን
ደህና መጣሽ” ብለው ያከብሯታል፡፡ ከሦስት ሰዓት በኋላእራት ይበላሉ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ እግዚአብሔርን
ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡" ከዚህም ጎን ለጎን ከግብጽ ባርነት መውጣታቸውን ምክንያት በማድረግ ለሚያከብሩት የፋሲካ ሏዓል በታዘዞት መሠረት ጠቦት አዘጋጅተው አቀባበል ያደርጉለት ነበር። ኦዘጸ 25:12

2:- ትክለኛው ቅበላ ግን ከሕሊና ዝግጅት ጋር ተያያዥነት ያለው ነው። ቀደምት አበው አጽዋማት ከመግባታቸው በፊት ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚሆኑ መገልገያዎችን ያዘጋጃሉ እነርሱም እራሳቸውን ለአገልግሎት ያዘጋጃሉ። ምእመኑም ሱባኤውን የሚያሳልፍበትን ቦታ መርጦ ይጠብቃል ንሰሐ ገብቶ እራሱን ለቅዱስ ቁርባን ያዘጋጃል። የቀማውን ይመልሳል የበደለውንም ይክሳል። ማጠናቀቅ ያለበትን ተግባረ ሥጋ ፈጽሞ ይጠብቃል። በጥቅሉ በጾም ወቅት ሊሟሉ የሚገቡ ውጫዊና ውስጣዊ ዝግጅቶችን በዋዜማው ይፈጽማሉ። ካገኙ በመጠኑ መቀበያ የፍስክ ምግብ ይመገባሉ ካላገኙ ግዴታ ስላልሆነ ጥሬ ቆሬጥመው ውሀ ተጎንጭተውም ቢሆን ይቀበሉታል።

3:-አሁን ያለው ደግሞ ፍጹም የተለየ አቀባበል ነው። በጾሙ ላይ ተሳትፎ የሌለውም ያለውም በጠቅላላ የህሊና ዝግጅት የለውም አቀባበል ሲባል ቀጥታ ግንኙነት ያለው ከመብላትና ከመጠጣት ጋር ይመስለዋል።


በየቦታው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲበላ ሲጠጣ ሲያልፍም ወዳልተገባ ሥጋዊ ስሜት ውስጥ ይገባል። ብዙ ነዳያን የሚቀምሱት ባጡበት ዘመን ከገደብ ያለፈ የአመጋገብ ሥርአት በቅበላ ወቅት የተለመደ ነው። ይህ ከክርስትናው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ሰው ለፈቃደ ስጋው ሲያደር የፈጠረው እንጂ። እግዚአብሔር ለቅበላው ስለበላነው እና ስላልበላነው ጉዳይ ሳይሆን ሚያሰበው የእኛ በኃጢአት መኖር መሆኑን ልብ እንበል። ስጋ በልቶ የተቀበል ቆሎ በልቶ ከተቀበለው ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ብልጫ የለውም። ከሁሉ ሚያሳዝነው በቅበላውም በፍቺውም የፍስከ ምግቦች ለመብላት የሚሰለፉት ማይጾሙት መሆናቸው ነው። ስለዚህ በቅበላ ጊዜ "የግድ እነዚህን ካለበላችሁ የሚል ህገ የለም ያገኘም በመጠኑ እና በማያስነውር መልኩ ቢመገብም ነውር የለውም። በአጽማት ስጋ መብሊት አለመብላት ግዴታ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ዝግጅቶች ምናደርግበት ነው።

JOINE JOINE

👇👇 👇👇
https://t.me/yeberhanljoche