ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት🙏(ጫንጮ)
775 subscribers
84 photos
4 files
98 links
ሰንበት ትምህርት ቤት የመልካም ወጣት የመልካም ትውልድ መፍለቂያ ናት! ትውልድን ለበጎ ነገር የምታበቃ ናት፡፡


የጫንጮ ከተማ ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ቻናል
ለሀሳብ እና አስታየት @weldebirhanbot @ty1921 ይጠቀሙ

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
Download Telegram
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ:-
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ::

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው የሐዲስ ኪዳን ደግሞ የመጀመሪያው ነቢይ ነው።

ስለ ወላጆቹም ስለ ካህኑ ዘካርያስና ስለ ቅድስት ኤልሳቤጥ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ብሎ ተመስክሮላቸዋል።

"በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበር፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስሟም ኤልሳቤጥ ነበረ። ሁለቱም በጌታ ትዕዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፉ እየሔዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።" ሉቃስ 1፡ 5-6።

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው::

ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው::

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች::

ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለ እርሷ ደስ አላቸው::

በ8ኛ ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት::

እናቱ ግን ዮሐንስ ይባል አለች::

ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት::

አባቱንም ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት::

እሱም ብራና ላይ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ:: ሁሉም አደነቁ::

ያን ጊዜ የአባቱ አንደበት ተፈታ እግዚአብሔርንም አመሰገነ::  

ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተነገረ::

ሄሮድስ ሕፃናትን ሊገድል አዋጅ ባወጀ ጊዜ አባቱ ወደ ቤተ መቅደስ ወስዶ ደበቀው።

በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው::

ሄሮድስ የላካቸው ጭፍሮች ዮሐንስን ባጡት ጊዜ ዘካርያስን ገደሉት::

ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ::

የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ነው::

ሚልኪያስም በፊትህ ጎዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ ብሎ ተናግሮለታል:: 

በአማላጅነቱ ተማምነን መታሰቢያውን እናድርግ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን::

የተባረከ የሰኔ ወር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈጸመ::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳዊያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን::

እንሆ ሰኔ ወር በሰላም ተፈጸመ::

በዚህ በሰኔ ወር በእምነታችን ታምነን ከኃጢአታችን ነፅተን በንሰሐ ሳሙና ታጥበን በቅዱሳኑ አማላጅነት ተማፅነን ወሩን ተጠቅመንበታል?

ሁሉ ነገራችን የሚያውቅ በቸርነቱ ለዚህ ቀን አድርሶናል::

አልረፈደም በዚህች በተሰጠች ቀሪ ዘመን መልካም እንድንሰራባት ከሃይማኖታችን በአፋ ከምታስወጣን ኃጢአት የምንርቅበት እንዲሆንልን እንግዲህ እንንቃ አምላከ ተክለ ሃይማኖት ቸርነቱን ያብዛልን የሁላችንም መጨረሻችን ያሳምርልን ለዘላለሙ አሜን::
https://t.me/yeberhanljoche
​​ወበዛቲ ዕለት ሐምሌ ፭ “ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ”

ክበር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር፤ (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”) መዝ. ፻፲፭/ ፻፲፮፡፲፭ (115/116፡15)

“ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።” ማቴ.፲፫፡፲፩

እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታቱ ለቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት ቀን በዓላቸው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ አሜን።

ቅዱስ ጴጥሮስ

ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው ቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴጥርስ ማለት ኰኩሐ ሃይማኖት ማለት ነው። ማቴ. ፲፮፡፲፰ (16፡18) በዕራይስጥ ኬፋ ይለዋል። ቀዳሚ ስሙ ስምዖን ነው። ዮሐ.፩፡፵፭ (1፥45)፡፡ የአባቱ ስም ዮና ሲሆን ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ ዮና ከነገደ ስምዖን የምትሆን አንዲት ሴት አግብቶ ቅዱስ ጴጥሮስን ወለደ፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስም ከተወለደ በኋላ እንደ ሕገ ኦሪት ትእዛዝ በስምንተኛው ቀን ወደ ግዝረት ቤት አግብተው ስሙን በእናቱ ነገድ ስም ስምዖን ብለው ሰይመውታል። እድሜው አምስት ዓመት ሲሆን እንደ አይሁድ ሥርዓት ሕገ ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በቤተ ሳይዳ አጠግብ ወደሚገኘው ወደ ቅፍርናሆም ሰደዱት፡፡ በዘመኑ በባህር ዳር በምትገኘውና ታላቅ የንግድ መነኸርያ በነበረችው ቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረችው በቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረው ኢያኢሮስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት አሰርቶት በነበረው ምኩራብ እየተማረ አደገ፡፡

ከዚያም በኋላ በዚያ ከተማ ቤት ሰርቶ ኮን ኮርድያ (ጴርጴቱዋ) የምትባል ሚስት አግብቶ እንደ አባቱ እንደ ዮና ይተዳደር የነበረው ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ ነበር። ዓሣ እያጠመደና እየሸጠ ይኖር ነበር፡፡ ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗለ። ማቴ. ፬፡፲፱ (4:19) ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከተቀበሉ በኋላ መዲናቸው ኢየሩሳሌም አንድ ዓመት ካስተማሩ በኋላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን ዕዳ በዕዳ ከተከፋፈሉ ጊዜ ርዕሰ ሐዋያ ነውና ሮምን ደርቦ ሰርቶታል።

በሮምም ፳፭ (25) አስተምሯል። ከዚያ በፊ ግን በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ጳንጦስ፣ በገላቲያ፣በቀጳዶያና በቢታኒያ አስተምራል። በትምህርቱም ጣቢታ ከሞት አስነስቷል። ሐዋ. ፱፡፴፪-፴፬ (9፡32¬-34) ያስተማራቸው ምዕመናም ከሃማኖታቸው እንዳይወጡ ፪ (2) መዕክታትን ጽፎላቸዋል። ንጉሱ ኔሮን ቄሳር ጣኦት አምላኪ ነበርና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር። ለጣዖትም እንዲሰግድ ባስገደደው ጊዜ ለጣኦ አልሰግድም በማለቱ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት።

አይሁድ ሲጣሉት ወደ ጌታ ቢያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር። ይዞ ዳግም ቢሰቅሉትም ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው። በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅሎታል። ሥጋውን ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቱ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንቦ እንዳይፈርስ በማረ በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል።

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
https://t.me/yeberhanljoche
​​​​ቅዱስ ጳውሎስ

ጳውሎስ ማለት ንዋይ ህሩይ ማለት ነው። ሐዋ. ፱፡ ፲፭ (9፡15) አንድም ብርሃን ማለት ነው። ዘዳ.፲፬፡፪ አንድም መድቅዕ ማለት ነው። ቀዳሚ ስሙ ሳዖል ነው። ሳዖል ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው። ትውልዱ ከነገደ ቢኒያም ነው። ፊሊ. ፫፡፭ አባቱ ዮስአስ ይባላል።

የተወለደው ጌታ በተወለደ በ፭ (5) ዓመት በጠርሴስ ነው። ከ፲፭ ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እህቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን ተምሯል። በወንጌል ያመነው ጌታ ባረገ በ፰ኛው ዓመት ነበር። ጌታም በደማቆ መብረቅ ጥሎበት ሳኦል ሳኦል ስለምን ታሳደኛለህ ብሎ ታርቆታል። ከ፸፪ (72) አርድእት አንዱ የሆነው ሐናንያ ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎን አስተምረህ አሳምነህ አጥምቀው አለው። እርሱም በእጁ ገና አይኑ በዳሰሰው ጊዜ አይኑን አሳውሮት የነበረው እንደ ቅርፊት ወድቆለታል። ሐዋ.፱፡፩-፲፱ (9፡1¬-19)

ከዚያ በኋላ በክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም አስተምዎ አጥምቋል። ሐዋ. ፲፬፡፰-፲፰ ብዙውንም አሳምኗል። በወይኒም ታስሮ በነበረበት ወቅት ብዙ ሰዎችን አሳምኗል። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱ፤ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።

ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤ ወደ ገዢዎችም አቅርበው። እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ። እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ አሉ።

ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።

የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው።
እነርሱም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።

ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው ፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። ሐዋ. ፲፮፡፲፰-፴፬ (16፡18-34) ሕሙማንንም ሕሙም መስሎ አስተምሯል። ፩ቆሮ.፱፡፳፪ (1ቆሮ.9፡22) ፲፬ መልዕክታትንም ጽፏል።

ከዚህ በኋላ በ69 ዓ.ም ሮም ሲያስተምር ኔሮን ቄሣር አስጠሩት ሲል በንጉሱ ፊት ሲቀርብ መስቀሉን ይዞ ቀረበ። ንጉሱ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ። በመጎናጸፊያም ሸፍኖ ሰይፎታል። ደሙም ሰማየ ሰማይ ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል። ሲያልፍም የ72 ዓመት አረጋዊ ነበር። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የሞቱት በአንድ ቦታ በአንድ ቀን ነበር። ይህም ሐምሌ ፭ ነው።

ምንጭ፡- ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር ፪፣ መዝገበ ታሪክ

የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
https://t.me/yeberhanljoche
ማንም ኋለኛ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ
(በቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ)

ከመጀመርያ ጀምሮ መልካም ነገርን መምረጥ ክፉ አይደለም፤ በመልካምነት አለመቀጠል ግን ብዙ ወቀሳን ያመጣል፡፡ የብዙ ሰዎች ክፉ መሆን በዚሁ የሚመደብ ነው፤ ብዙዎች ሕይወታቸውን በመልካም ጀምረው በኋላ ግን በክፋት መርዝ ተጠምቀው ሲሰክሩ ተመልክቻለሁና፡፡
እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ፡፡ ምንም እንኳን አሁን ወደ ክፋት ጥልቅ ወርዳችሁ ቢሆንም “ከዚሁ ተመልሰን መነሣት አይቻለንም፤ መለወጥም አይሆንልንም” በማለት ተስፋ የምትቈርጡ አትሁኑ፡፡እናንተ ስትፈቅዱ እግዚአብሔርም ሲረዳችሁ ከክፋት ዐዘቅት መውጣት በእጅጉ ቀላል ነውና፡፡ ከሁሉም በላይ አመንዝራ ተብላ በከተማው ዘንድ ትታወቅ የነበረችውን ሴት በመልካምነቷ እንዴት እንደምትወደስ አልሰማችሁምን? እየነገርኳችሁ ያለሁት በዮሐንስ ወንጌል ላይ ስለተጠቀሰችው ሴት አይደለም፡፡ በእኛ ዘመን ስላለችውና ፍኒሳ ከተባለችው ጋጠ ወጥ ከተማ ስለተገኘችው ሴት እንጂ፡፡ ይህች ሴት አስቀድማ በመካከላችን በአመንዝራነቷ ትታወቅ ነበር፡፡
በክብር ቦታ ሁሉ የመጀመርያን ስፍራ የምትይዝ ሴት ነበረች፤ ስሟ በሀገሩ ሁሉ የገነነ ነበር፤ በእኛ ከተማ ብቻ ሳይሆን በሲልስያ እና በቀጰዶቅያም ጭምር እንጂ፡፡ ይህች ሴት ብዙ ከተሞችን አፍርሳለች፤ የብዙ ወላጅ አልባ ሕፃናትን ንብረት በልታለች፡፡ ብዙዎችም “መተተኛ ናት” ይሏታል፤ ውበቷን ብቻ ሳይሆን መድኃኒትም ጭምር ትጠቀም ነበርና፡፡ ከዚሁ የተነሣ በአንዱ ቀን የንግሥቲቱን ልጅ እስከ ማማለል ደርሳለች፡፡ ጭካኔዋ የክፉ ክፉ ነበር፡፡
ከዕለታት በአንዲቱ ቀን ግን ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ሆኖም ግን በዓይኔ ፍጹም ተለውጣ ራሷን በእግዚአብሔር የጸጋው ዙፋን ፊት ድፍት አድርጋ ስታለቅስ አየኋት፡፡ አሁን የቀድሞ ክፉ ሥራዎቿን ሁሉ እርግፍ አድርጋ ትታለች፤ በእርሷ ላይ ከነበሩት
የአጋንንት ጭፍራ ተፋትታ አሁን የክርስቶስ ሙሽሪት ሆናለች፡፡
በእውነት ከእርሷ የሚከፋ ሰው በዐይኔ አላየሁም፡፡ በኋላ ግን ራሷን ከእንደዚህ ዓይነቱ ክፉ ሥራ ከለከለች፡፡ ከዚህ በፊት ስትለብሳቸው የነበሩት የምንዝር ጌጦች ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ አሁን ግን እነዚህ ሁሉ በእርሷ ዘንድ ቦታ የላቸውም፡፡ እነዚህን ሁሉ አወላልቃ ጥላ ለእግዚአብሔር በሚገባ የማቅ ልብስ ለብሳ ራሷን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር አድርጋለች፡፡ ይህችን ሴት ወደ ቀድሞ ሕይወቷ ለመመለስ የሀገሪቱ መኳንንት ከዙፋናቸው ወርደው ለምነዋት ነበር፤ ወታደሮች ትጥቃቸውን ታጥቀው በመምጣት አስፈራርተው ሊወስዷት ሞክረው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ወደ ቀድሞ ሕይወቷ ሊመልሷት አልተቻላቸውም፤ ከተቀበሏት ደናግላን በዓት ሊያስወጧት አልተቻላቸውም፡፡ ይህች ሴት ከዚያ አስነዋሪ ሕይወቷ ተመልሳ ለቅዱስ ቁርባን በቅታለች፤ ለእግዚአብሔር ጸጋ የተገባ ሆና ተገኝታለች፤ ኃጢአቷን ሁሉ በጸጋው አጥባለች፤ ከተጠመቀች በኋላ ራሷን መግዛት ችላለች፡፡ ይህች ሴት የቀድሞ ሕይወቷን፣ ገላዋን ለብዙ ወዳጆቿ ያሳየችበትን ሕይወት “የእስር ቤት ሕይወት” ብላ ትጠራዋለች፡፡ በእውነት “ኋለኞች ፊተኞች ይሆናሉ፤ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ” የሚለው የከበረው የጌታ ቃል በእርሷ ሲፈጸም አየነው፤ መለወጥ ከፈለግን እኛን ማሰናከል የሚቻለው ኃይል እንደሌለ አወቅን ተረዳን፡፡
እንግዲያስ ተወዳጆች ሆይ! ተስፋ በመቁረጥ በኃጢአት ዐዘቅት ሰምጠን የምንቀር አንሁን፡፡ ከእኛ መካከል በጽድቅ በረሀነት የሚኖር ማንም አይገኝ፡፡ ፊተኛ ነኝ የሚልም ከቶ አይኑር፤ ብዙ አመንዝሮች እርሱን አልፈዉት ሊሄዱ ይችላሉና፡፡ ማንምም ኋለኛ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ፤ ከልቡ ከተጸጸተና ከተመለሰ ፊተኛ መሆን ይቻለዋልና፡፡
የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፡- “ይህም ሁሉ ካደረገች በኋላ ወደ እኔ ትመለሳለች ብዬ ነበር፡፡ ነገር ግን አልተመለሰችም፡፡ አታላይ እኅትዋም ይሁዳ አየች” /ኤር.3፡7/፡፡
ወደ እግዚአብሔር ስንመለስ የቀድሞ ኃጢአታችንን
አያስበውም፤ እግዚአብሔር እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለምና፡፡ በእውነት እርሱ በቀድሞ ኃጢአታችን የሚወቅሰን አይደለም፡፡ እርሱ እንደ ሰው አይደለምና፡- “እስከ አሁኑ ሰዓት ወዴት ነበርክ?” የሚለን አይደለም፡፡ ብቻ እኛ እንመለስ እንጂ እርሱ እንዲህ ያለ አምላክ አይደለም፡፡
ይህን እንደናደርግ ሰውን በመውደድ ሰው የሆነው ክርስቶስ ይርዳን አሜን!!
https://t.me/yeberhanljoche
Forwarded from ተዋህዶ
መንፈሳዊ መማማሪያ ግሩፕ ይፈልጋሉ
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ ቶሎ join ያድርጉ
​​​​🌼 ልጄ ሆይ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ

ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ።

ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት  እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ

ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ።

በንስሐ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼       🌼       🌼      🌼
🌼        🌼      🌼      🌼
🌼🌼🌼         🌼🌼🌼

🌼
🌼
🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼                   🌼
🌼                   🌼
🌼🌼🌼          🌼
🌼      🌼         🌼
🌼🌼🌼          🌼

🌼
🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
    🌼               🌼
     🌼              🌼
                        🌼
                        🌼
                        🌼

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼     🌼     🌼      🌼
🌼     🌼     🌼      🌼
🌼🌼 🌼     🌼🌼🌼
          🌼
        🌼
      🌼

🌼
🌼
🌼🌼
       🌼
         🌼🌼🌼🌼
      🌼             🌼
      🌼             🌼
      🌼             🌼
      🌼              🌼    
   
     🌼🌼🌼🌼
      🌼          🌼
         🌼🌼🌼
           🌼
              🌼
    🌼🌼🌼🌼🌼
    🌼                🌼
     🌼                🌼🌼🌼

            🌼
               🌼
   🌼🌼🌼🌼🌼 🌼
   🌼                    🌼
   🌼                    🌼
   🌼                    🌼
   🌼                    🌼
   🌼                    🌼

    🌼🌼🌼🌼
    🌼          🌼
    🌼          🌼
    🌼🌼 🌼 🌼🌼
                             🌼
                             🌼
                             🌼
                             🌼

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼      🌼     🌼         🌼
🌼       🌼     🌼        🌼
🌼🌼 🌼      🌼🌼 🌼

          🌼 
          🌼🌼🌼
                      🌼
                      🌼
       🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
                      🌼
                      🌼
                      🌼
                      🌼

                #መልካም #በዓል!
​​​​እንኳን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ

ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ6 የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: #ቅዱስ_ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "#ዘካርያስ ካህኑና #ቅድስት_ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

¤የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!

¤እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::

¤ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

¤ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል #እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

¤የአምላክ እናቱ ስትደርስና "#ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

¤ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ #ሰብአ_ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

¤እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና #ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

¤ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ #ድንግል_ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

¤ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በሁዋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

¤ከዚህ በሁዋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

¤ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ #መንፈስ_ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

¤ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ:: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነ ልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

¤"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "#መጥምቀ_መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::

¤በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)

¤ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት #ደብረ_ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: #ቅዱሳን_ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::

¤ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ በዚህች ቀን ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

<<¤ አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ (የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች) ¤>>
1.ነቢይ
2.ሐዋርያ
3.ሰማዕት
4.ጻድቅ
5.ካሕን
6.ባሕታዊ/ገዳማዊ
7.መጥምቀ መለኮት
8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)
9.ድንግል
10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ)
11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)
12.መምሕር ወመገሥጽ
13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ)

=>ጌታችን #መድኃኔ_ዓለም የመጥምቁ ዮሐንስን ምትረት አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን::
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
https://t.me/yeberhanljoche
ዜና እረፍት

መስከረም ፲፰ቀን፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
*********************
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
*****************************

ጸሎተኛው፣ደጉ፣ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን
Forwarded from ተዋህዶ
መዝሙር እንዴት ማግኘት እችላለው ብለው ተጨንቀዋል። 🤔
እንግዲያው ከታች ካሉት ውስጥ መርጠው ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
❝በአገልግሎት መመረጥ መበርታት እንዲህ ነው!❞

አየህ አገልግሎት ገደብ የለውም! ዕድሜ፣ ቦታ፣ ስራ፣ ትዳር፣ ሁኔታ፣ ሌላውም ምክንያት አይገድበውም። ይህን መልዕክት የምትመለከተው ወንድሜ ሆይ ያኔ በልጅነት ሰንበት ትምህርት ቤት ያሳለፍከውን ጊዜ አስብ፤ መልዕክቱን የምታነቢውም እህቴ፣ ያን የማይረሳ የአገልግሎት ዘመን አስቢው! ዝማሬ ለመቆም፣ መዝሙር ለማጥናት፣ ያሬዳዊ ዝማሬን አጥንቶ ለማቅረብ፣ ድራማ እና ጭውውት ለመስራት፣ አልባሳት ለብሶ ለመዘመር፣ በየበዓላቱ በአልባሳት ደምቆ ቄጤማ እና ዘንባባ ይዞ በየከተማው እየዘመሩ ለመሄድ፣ በየወርሃዊ የዝክር መርሐግብሮች ላይ ጸበል ጸድቅ ለመቃመስ፣ በየልቅሶው ቤት አጽናኝኝ እመአምላክ እያሉ እየዘመሩ ሐዘንተኞችን ለማጽናናት፣ የታመሙትን ድውይ ነኝ አንተ አድነኝ እያሉ እየዘመሩ በሽተኞች በሽታቸውን እንዲረሱ ለማድረግ፣ በየሰርጉ ላይ መርአዊ ሰማያዊ እያሉ ለማጀብ፣ በየንግሱ ታቦታቱን በአልባሳት አሸብርቆ ለማጀብ ያለህን ፍቅር እና ፍላት ቅናት እና መነሳሳት አስበው ወንድሜ። እስኪ ትዝ ይበልሽ እህቴ!

ዛሬስ? ዛሬማ ትልቅ ሆንና! መንግስት ሰራተኞች ደመወዝተኞ ሆንና! ዛሬማ ጊዜ የለንማ፣ ትላልቆች ሆነን አግብተን ወልደን ከበድና፣ ዛሬማ ዕድሜያችን ገፍቶ አልባሳት ለብሶ ማገልገል ያሳፍረናላ፣ ጡረታ ወጣና! ያሳዝናል።
ግን የቤተክርስቲያን ፍቅር እና አገልግሎት በእውቀት ለገባው ምንም ነገር ላለማገልገል ምክንያት አይሆነውም። ብዙዎች መንፈሳዊው እውቀት ላይ ደካሞች ስለሆኑ ተበተኑ። የገባቸው ግን ምንም አይገድባቸውም። ልክ እንደኚህ አባት!በአገልግሎት እንበርታ ከደጁ አንራቅ የወለድናቸው ልጆችም በአብነት ትምህርት ቤትሰንበት ትምህርት ቤት እንውሰዳቸው ።
ይህን ከአደረግን አባቶቻች መቃብር ላይ ሄደን አባ ይፍቱኝ፤ የምንልበትን ዘመን እናስቀራለ፤ን ይህ ባይሆን ግን የተማረ አባት ጠፍቶ ፤ቀብራቸው ላይ ሄደን አባ ይፍቱኝ የምንልበት ዘመን ቅርብ ነው።
ለአባታችን ረዥም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን።
@yeberhanljoche