ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት🙏(ጫንጮ)
766 subscribers
84 photos
4 files
98 links
ሰንበት ትምህርት ቤት የመልካም ወጣት የመልካም ትውልድ መፍለቂያ ናት! ትውልድን ለበጎ ነገር የምታበቃ ናት፡፡


የጫንጮ ከተማ ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ቻናል
ለሀሳብ እና አስታየት @weldebirhanbot @ty1921 ይጠቀሙ

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
Download Telegram
ቅበላ ዓላማው ምንድን ነው?


ስለ ቅበላ ያለን አመለካከት በልማዳችን ውስጥ የተንሸዋረረ ነው። ከጾም ጋር ተያይዞ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ከሚፈጸሙ ተግባራት መካከል በአጽማት መግቢያ የሚደረገው የአቀባበለ ሥነ ሥርዓት ነው። ይህ ሥርዓት በራሱ መጸሐፍ ቅዱሳዊ ይዘት ያለውና በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያንም የተለመደ ትውፊታዊ ቅብብሎሽ ያለው ሥርዓት ነው። ይህ ግን አሁን ከምንፈጽመው የቅበላ ሥርዓት የተለየ ነበር። ጥቂት ማሳያዎችን እንመልከት።

1:- በመጸሐፍ ቅዱስ አይሁድ ቀዳሚት ሰንበት ከመግባቷ በፊት በዋዜማው የተለየ አቀባበል ያደርጉ ነበር። ዓርብ ፀሐይ ሲገባ ካህኑ ደውል
ይደውላሉ አሊያም በቤት ያለ የቤቱ አባወራ የሰንበት
መግቢያ ሰዓት መቃረቡን ድምጽ በማሰማት ያሳውቃል፡፡ በአካባቢው ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በአንድ ላይ ሆነው ወደ ፀሐይ መውጫ ይሰግዳሉ፡፡ ጸሎት ይደረጋል፡፡ ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል፣አሥርቱ ቃላት ሌሎችም ንባባት ይደገማሉ፡፡ ማብራት ተይዞ “ዕለተ ሰንበት እንኳን
ደህና መጣሽ” ብለው ያከብሯታል፡፡ ከሦስት ሰዓት በኋላእራት ይበላሉ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ እግዚአብሔርን
ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡" ከዚህም ጎን ለጎን ከግብጽ ባርነት መውጣታቸውን ምክንያት በማድረግ ለሚያከብሩት የፋሲካ ሏዓል በታዘዞት መሠረት ጠቦት አዘጋጅተው አቀባበል ያደርጉለት ነበር። ኦዘጸ 25:12

2:- ትክለኛው ቅበላ ግን ከሕሊና ዝግጅት ጋር ተያያዥነት ያለው ነው። ቀደምት አበው አጽዋማት ከመግባታቸው በፊት ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚሆኑ መገልገያዎችን ያዘጋጃሉ እነርሱም እራሳቸውን ለአገልግሎት ያዘጋጃሉ። ምእመኑም ሱባኤውን የሚያሳልፍበትን ቦታ መርጦ ይጠብቃል ንሰሐ ገብቶ እራሱን ለቅዱስ ቁርባን ያዘጋጃል። የቀማውን ይመልሳል የበደለውንም ይክሳል። ማጠናቀቅ ያለበትን ተግባረ ሥጋ ፈጽሞ ይጠብቃል። በጥቅሉ በጾም ወቅት ሊሟሉ የሚገቡ ውጫዊና ውስጣዊ ዝግጅቶችን በዋዜማው ይፈጽማሉ። ካገኙ በመጠኑ መቀበያ የፍስክ ምግብ ይመገባሉ ካላገኙ ግዴታ ስላልሆነ ጥሬ ቆሬጥመው ውሀ ተጎንጭተውም ቢሆን ይቀበሉታል።

3:-አሁን ያለው ደግሞ ፍጹም የተለየ አቀባበል ነው። በጾሙ ላይ ተሳትፎ የሌለውም ያለውም በጠቅላላ የህሊና ዝግጅት የለውም አቀባበል ሲባል ቀጥታ ግንኙነት ያለው ከመብላትና ከመጠጣት ጋር ይመስለዋል።


በየቦታው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲበላ ሲጠጣ ሲያልፍም ወዳልተገባ ሥጋዊ ስሜት ውስጥ ይገባል። ብዙ ነዳያን የሚቀምሱት ባጡበት ዘመን ከገደብ ያለፈ የአመጋገብ ሥርአት በቅበላ ወቅት የተለመደ ነው። ይህ ከክርስትናው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ሰው ለፈቃደ ስጋው ሲያደር የፈጠረው እንጂ። እግዚአብሔር ለቅበላው ስለበላነው እና ስላልበላነው ጉዳይ ሳይሆን ሚያሰበው የእኛ በኃጢአት መኖር መሆኑን ልብ እንበል። ስጋ በልቶ የተቀበል ቆሎ በልቶ ከተቀበለው ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ብልጫ የለውም። ከሁሉ ሚያሳዝነው በቅበላውም በፍቺውም የፍስከ ምግቦች ለመብላት የሚሰለፉት ማይጾሙት መሆናቸው ነው። ስለዚህ በቅበላ ጊዜ "የግድ እነዚህን ካለበላችሁ የሚል ህገ የለም ያገኘም በመጠኑ እና በማያስነውር መልኩ ቢመገብም ነውር የለውም። በአጽማት ስጋ መብሊት አለመብላት ግዴታ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ዝግጅቶች ምናደርግበት ነው።

JOINE JOINE

👇👇 👇👇
https://t.me/yeberhanljoche
ፍልሰታን የፆመ ይህቺን ፁሁፍ ለማንበብ ጊዜ አያጣም። ሳታነቡ እንዳታልፉ።

❖የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት ነሐሴ 16
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ነሐሴ 16 ቀን አስደናቂውን የእመቤታችንን የዕርገቷን በዓል ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፤ የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር ከቆየች በኋላ፤ ዓለምን ለማዳን በዕለተ ዓርብ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜም የሚወድዳት እናቱን ለሚወድደው ደቀ መዝሙር ለዮሐንስ “እነኋት እናትኽ” በማለት አደራ በመስጠት በዮሐንስ በኩል ለሚወድደን ለእኛ የአደራ ልጆቿ እንድንኾንና የአደራ እናታችን እንድትኾን ታላቅ ስጦታን በቀራንዮ በእግረ መስቀል ሥር ሰጠን (ዮሐ ፲፱፥፳፮‐፳፯)፡፡

በዚኽም መሠረት ሐዋርያትም ከአምላካቸው የተሰጠቻቸው የአምላካቸውን እናት ይዘው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ 72ት ቋንቋ ገልጾላቸው ታላቅ መንፈሳዊ ኀይልን ሰጣቸው (የሐዋ 1፥14)፤ ዮሐንስም በእናትነት የተቀበላት ቅድስት ድንግል ማርያምን በቤቱ 15 ዓመት አኑሯታል፡፡

በነገረ ማርያም በብራናው ላይ እንደተጻፈ 64 ዓመት ሲመላት ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት፤ ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደ ጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፡፡ ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፡፡

ጌታም እናቱን “እኔ ኹሉን መጋቢ የኾንኹትን ያጠቡ ጡቶሽን የተባረኩ ናቸው፡፡ እንዲኹም በከፍታ ቦታዎች ወደሚገኙ ሰማያዊ ስፍራዎች ወስጄሽ በአባቴ በመልካም ነገሮች እመግብሻለኊ፡፡ እስከዚያው በጉልበትሽ ላይ ያስቀመጥሺኝ ድንግል እናቴ ማርያም ሆይ በኪሩቤል ሠረገላ ላይ በማኖር ከእኔና ከቸሩ አባቴ ጋር ወደ ሰማያት እወስድሻለኊ፡፡

በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በሰይፈ ነበልባላቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡

የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ” አላት፡፡

ይኽነንም ልጇ እያላት ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች፤ ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ የከበረ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፡፡

ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ይኽነን ይዞ በድጓው ላይ “ፃኢ እምሊባኖስ ሥነ ሕይወት ርቱዕ አፍቅሮትኪ ቡርክት አንቲ እምአንስት ማኅደረ መለኮት ሰላም ለኪ፤ ማርያም እመ አምላክ ወልድኪ ይጼውዐኪ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር” (የሕይወት ደም ግባት የአምላክ እናት ከሊባኖስ ውጪ፤ ፍቅርሽ የቀና ነው፤ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ፤ የመለኮት ማደሪያ ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ የአምላክ እናት ማርያም ሆይ ልጅሽ ወደ ዘላለማዊ ሕይወትና ወደ ክብር መንግሥት ይጠራሻል) በማለት አመስጥሮታል፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያትም ሥጋዋን በክብር ገነዘዋል፤ ከኢትዮጵያ ሊቃውንት መኻከል ስለዚኽ በቅዱሳን ሐዋርያት ስለተደረገው የከበረ የሥጋዋ ግንዘት ቅዱስ ያሬድ አምልቶ አስፍቶ የጻፈ ሲኾን፤ በነሐሴ ፲፭ በአጫብሩ ድጓ ውስጥ በአስደናቂ መልኩ እንዲኽ ተጽፈዋል፡-

╬ “ሐዋርያት አመድበሉ
ሥጋ ድንግል ጠብለሉ
በሰንዱነ ብርሃን ዘላዕሉ
ልብሳ ተካፈሉ”
(ሐዋርያት ተሰበሰቡ፤ ከላይ በመጣ በፍታ (መጐናጸፊያ) የድንግል ሥጋን ጠቀለሉ፤ ልብሷንም ተካፈሉ)

╬ “በደመና ተጋቢኦሙ ሐዋርያት ለድንግል ንጽሕት
ገነዝዋ በክብር ወበስብሐት
ለቀበላሃ ወረዱ ኀይላት
ወቀበርዋ ውስተ ገነት”
(ሐዋርያት በደመና ተሰብስበው ንጽሕት ድንግልን በክብር በምስጋና ገነዟት፤ ለአቀባበሏ ኀይላት ወረዱ፤ በገነት ውስጥም ቀበሯት)

╬ “ተጋቢኦሙ ሐዋርያት እምኲለሄ
በደመናት ዘምሉእ ሡራኄ
ገነዙ በክብር ወበስባሔ
ሥጋ ድንግል ዘይምዕዝ እምርሔ”
(ብርሃንን የተመላ በኾነ በደመናት ሐዋርያት ከአራቱ ማእዝን ተሰብስበው ልብን ከሚመስጥ ሽቱ ይልቅ የሚሸትት የድንግልን ሥጋ በክብርና በምስጋና ገነዙ)

╬ “ተጋቢኦሙ በደመና ሰማይ
ሐዋርያት ሥርግዋን በዕበይ
ገነዝዋ ለድንግል በብዙኅ ግናይ
ዳዊት ዘመራ በመሓልይ”
(በገናንነት የተጌጡ ሐዋርያት በሰማይ ደመና ተሰብስበው ድንግልን በብዙ ምስጋና ገነዟት፤ ዳዊትም በምስጋና አመሰገናት፡፡)

╬“ተጋቢኦሙ አርድዕተ ወልዳ
በደመና ብርሃን ጸዐዳ
ገነዝዋ በስብሐት ለጽርሕ ሳይዳ”
(ጸዐዳ በኾነ በብርሃን ደመና የልጇ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበው፤ ውቢቱ አዳራሽን በምስጋና ገነዟት)

╬ “ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት
ብፁዓን ሐዋርያት
ቦኡ ኀቤሃ በሰላም አምኁ ኪያሃ
በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ”
(ንኡዳን ክቡራን ሐዋርያት ቅድስት የምትኾን የጌታ እናቱን ለመገነዝ በቅጽበት ተሰበሰቡ፤ ወደ ርሷ ገብተው በሰላምታ ርሷን እጅ ነሧት፤ ሥጋዋንም በምስጋና ገነዙ) በማለት ሊቁ ማሕሌታይ በሐዋርያት እጅ የተደረገ የሥጋዋን ግንዘት አምልቶ አስፍቶ ጽፏል፡፡

ሐዋርያት በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው ለምቀኝነት አያርፉምና ቀድሞ ልጇ ሞተ፣ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ እያስተማሩ ኖሩ ከመቃብሩም ተአምራት ይደረጋል፤ አሁን ደግሞ ርሷ ሞተች፣ ተነሣች፣ ዐረገች ብለው ሊያስተምሩ አይደል፤ “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት እናቃጥላለን ብለው በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡

ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ይቤ ዮሐንስ ወኢይገድፍ ምዕቅብናየ ወዘንተ ብሂሎ ወድቀ በላዕሌሃ” ይላል (ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡ ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና

ነጥቀው በገነት
በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡



ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” ይላል የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ “ወዕጥን ሥጋሃ ለማርያም መዓልተ ወሌሊተ” ይላል የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ “ወፍና ሠርክ ያመጽዕ ሎቱ ራጉኤል መልአክ ኅብስተ ሰማይ” ይላል ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡

ኋላም በጌታ ፈቃድ ከተቀሩት ሐዋርያት ጋር ተገናኘ፤ ሐዋርያትም የእመቤታችንን ነገር እንደምን እንደኾነ ሲጠይቁት ርሱም በገነት ያየውን ነገር ነገራቸው፤ እነሱም ይኽነን ታላቅ ምስጢር ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ሱባኤ ነሐሴ 1 ዠመሩ ነሐሴ 14 ቀን በኹለተኛው ሱባኤ ጌታ የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል፡፡

በተወደደች ዕለት ነሐሴ 16 “ወአዘዞሙ እግዚእነ ለሰብአቱ ሊቃነ መላእክት ከመ ይጸውዕዋ ለምድር” (ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ምድርን ይጠሯት ዘንድ አዘዛቸው) እነርሱም ምድርን “ይኤዝዘኪ እግዚእነ ከመ ታውጽኢ ሥጋሃ ለእሙ ቅድስት” (ጌታችን የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ ያዝሻል) አሏት፤ ያን ጊዜ ልጇ “ንዒ ኀቤየ ወላዲትየ ከመ አዕርጊ ውስተ መንግሥተ ሰማያት” (ወደ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ እናቴ ወደኔ ነዪ) አላት፤ ያን ጊዜ በልጇ ሥልጣን የቅድስት ድንግል ማርያም ነፍሷና ሥጋዋ ተዋሐዱ፤ ነሐሴ 16 ዕለትም ከሞት ተነሣች፡፡

ያን ጊዜ “ወረዱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት” ይላል ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ በታላቅ ግርማ ወረዱ፤ ነቢዩ ዳዊትም “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ” (ንግሥቲቱ ወርቀ ዘቦ ግምጃ ደርባ ደራርባ በቀኝኽ ትቆማለች) እያለ ይዘምርላት ነበር፤ አየሩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመላ፤ እጅግ የሚያስደንቅ መዐዛ አካባቢን ዐወደው፡፡

ስለ አካላዊ ዕርገቷ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው በቊ ፹፪ ላይ፡-
“አመ ነሥኡኪ እምኤዶም አዕላፈ ማሕሌት ጾታ
እንዘ ይጼልሉኪ ድንግል በአክናፈ መባርቅት ከመ ወልታ
ሰራዊተ ሰማይ ይቤሉ ለክብረ ፍልሰትኪ ግርማ ትርሲታ
መኑ ይእቲ ዛቲ ዘገዳመ ጽጌ ዕጥነታ
ወከመ ሠርጸ ጢስ ዘስኂን ይምዕዝ ዕጥነታ”

(ድንግል ወገኖች አመስጋኞች መላእክት በየነገድ በየነገድ ኾነው በመባርቅት ክንፎች እንደ ጋሻ ጋርደው ከኤዶም ገነት በተቀበሉሽ ጊዜ የሚያስደንቅ ክብር ለተገለጸባት ለዕርገትሽ የሰማይ ሰራዊት አበባ ካለበት በረሓ የምትወጣ መዐዛዋም ከነጭ ዕጣን ይልቅ የሚሸትት አወጣጧም እንደ ጢስ አወጣጥ የኾነችይኽቺ ማናት? ይኽቺ ማን ናት ይላሉ (መሓ ፫፥፲፮)) በማለት በአስደናቂ መልኩ ዕርገቷን ገልጸዋል፡፡

ቅዱስ ያሬድም በዝማሬው ላይ “ፈለሰት ማርያም በስብሐት ውስተ ሰማያት መላእክት ወሊቃነ መላእክት ወረዱ ለተቀብሎታ” (እመቤታችን በምስጋና ወደዚያኛው ዓለም በተለየች ጊዜ ለአቀባበሏ መላእክትና ሊቃነ መላእክት ወረዱ) ይለዋል፡፡

ያን ጊዜ በታላቅ ክብር በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ሰማዩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመልቶ የአምላክ እናት በክብር ስታርግ ተመለከተ፤ ያን ጊዜ ነገሩ ረቆበት ምን ይኾን እያለ ሲል ቅዱሳን መላእክት የእመቤታችን ዕርገት እንደኾነና እጅ እንዲነሣ ነገሩት፡፡

ርሱም “ከቶ ምን አርጌ ይኾን፤ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ ቀረኊ ዛሬ ደግሞ የርሷን ትንሣኤ ሳላይ ልቅር” ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ይላል ተበጻብጾ ሊወድቅ ወደደ፤ እመቤታችንም “አይዞኽ አትዘን እነሱ ሞቴን አይተዋል እንጂ ዕርገቴን አላዩም አኹንም እመቤታችን ተነሣች ዐረገች ብለኽ ንገራቸው” ብላ ለበረከት ሰበኗን ሰጠችው፡፡

ርሱም በደስታ ተመልቶ ሐዋርያት ያሉበት በመኼድ የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ ብሎ ጠየቃቸው፤ እመቤታችን ሞተች ቀበርናት አሉት፤ “መቼ ሞተች?” አላቸው በጥር አሉት፤ “መቼ ቀበራችኋት?” አላቸው በነሐሴ አሉ፤ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይኽ ነገር እንዴት ይኾናል አላቸው፤ ቅዱስ ጴጥሮስም ቶማስን ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ አላምን ብለኽ የጌታን ጐን የዳሰሰ እጅኽ ተቃጥሎ ነበር፤ አኹን ደግሞ እኛ ብንነግርኽ አላምን ትላለኽ ብሎ፤ “ወነሥአ መክርየ” ይላል መቆፈሪያ ይዞ ኼዶ ይቆፍር ጀመር።

ርሱም የያዘውን ይዟልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፤ ቈፍረው ሲያጧት ደነገጡ፤ ቶማስም አይዟችኊ አትደንግጡ እመቤታችን እኮ በመላእክት ምስጋና ወደ ሰማይ አረገች ብሎ ሰበኑን አሳያቸው፤ እነርሱም ለበረከት ሰበኑን ተካፍለውታል፡፡ ዛሬም ሐዋርያዊት የኾነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ይኽነን በማሰብ በመስቀል ሥር የሰበኗ ምሳሌ የሚኾን ሰፊ ጨርቅ ታደርጋለች፡፡

ባመቱ ቶማስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በድጋሚ ሐዋርያት ሱባኤ ሲገቡ ክብር ይግባውና ጌታችን በደመና ነጥቆ ወስዶ ሥርዓተ ቊርባንን ፈጽሞላቸው፤ ስለ እናቱ ዕርገት በዓለሙ ኹሉ ዙረው እንዲያስተምሩ አዝዟቸዋል፡፡ እነርሱም ዓለምን ዞረው ወንጌልን ሲያስተምሩ የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገት ሰብከዋል አስተምረዋል፡፡

አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ወደ ምጡቅ ሰማይ ስለተደረገው ዕርገቷ ፡-
“እንዘ ይፀውረኪ በሐቂፍ ወይስዕመኪ በአፍ
አመ አፍለሰኪ ወልድ ውስተ የማኑ ለዐሪፍ
ጽጌ ዕፀ ገነት ማርያም ዘትጼንዊ ለአንፍ
እንዘ ይትጓድዑ አክናፈ በክንፍ
ለቀበላኪ ወረዱ አእላፍ”

(ለአፍንጫ መዐዛን የምትሰጪ የገነት ዛፍ ማርያም ሆይ፤ ልጅሽ በክንዱ ዐቅፎ በአፉ እየሳመ በቀኙ ሊያሳርፍሽ ባሳረገሽ ጊዜ፤ አንቺን ለመቀበል ክንፍ ለክንፍ እየተጋጩ እልፍ አእላፋት መላእክት ወረዱ) በማለት አስተምረዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ዳግመኛ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው በቊ፹፬ ላይ፡-
“ትእምርተ ፍልሰትኪ እምድረ ጽጌ ድንግል በክልኤ
በደመና ሰማይ አርአየ ዘሐዋርያት ጉባኤ
ወእለ ሞቱ አንቅሐ እምከርሠ መቃብር ቀርነ ጽዋዔ
ለነሰ እንዘ ይብሉ ሶበ ሰማዕነ ውዋዔ
መሰለነ ዘበጽሐ ትንሣኤ”

(በኹለት ወገን ድንግል የኾንሽ ማርያም ሆይ አበባ ካለበት ምድር ወደ ሰማይ የማረግሽ ተአምር በሰማይ ደመና የሐዋርያት ጉባኤን አሳየ፤ የሞቱትንም ከመቃብር ውስጥ በተአምር ነጋሪት ድምፅ አስነሣ፤ ለእኛስ የምስጋና ከፍተኛ ድምፅን በሰማን ጊዜ የሙታን መነሣት የደረሰ መሰለን እስኪሉ ድረስ) በማለት ሐዋርያትን ተሰብስበው ሳሉ ዕርገቷን እንዲያዩ እንዳደረጋቸው ጽፈዋል፡፡

ልጇ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትን ድል ነሥቶ እንደተነሣ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን ርሷ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ከልጇ ከንጉሡ ቀኝ በክብር ቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡

❖ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በነሐሴ ፲፮ የቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል ብሔራዊ በዓል ተደርጎ በተለያዩ ሀገራት ሲከበር ዕርገቷ ይታሰብባቸው ከነበሩ ሀገራት ውስጥም ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ አንዶራ፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ክሮሺያ፣ ኢኳዶር፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ሊባኖስ፣ ጣሊያን፣ ማልታ፣ ስሎቬኒያ፣ ፖላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ሩማኒያ፣ ቺሊ፣ ሳይፕረስ፣ ሀይቲ፣ ሴኔጋል ይጠቀሳሉ
https://t.me/yeberhanljoche
የሰርግ ልብስ
፨፨፨፨፨፨፨፨

አንድ ሰው መጥቶ እናንተ የምትለብሱትን አንዲት ቁራጭ ልብስ እንኳ ሳይሰጣችሁና ሰውነታችሁ በብርድና በዋዕየ ፀሐይ እየተቆራመደ ሳለ ቤታችሁን በወርቅና በተንቆጠቆጠ የመጋራጃ ዓይነት ቢያስጌጥላችሁ ምን ጥቅም አለው? እኛስ ነፍሳችን ዕራቁቷ ሳለች ሥጋችንን ወርቅ ብናለብሰው በወርቅ ብናስተኛው ምን ትርጉም አለው? ነፍሳችን በመሬት እየተንፏቀቀች ደሳለኝ ሥጋችን በከበሩ ሠረገሎችና የተለያዩ ማጓጓዣዎች ብትንፈላሰስ ምን ጥቅም አለው?ልጆቼ! እውነተኛውን ልብስ ልበሱ። የሰርጉን ልብስ ልበሱ። እስኪ ወደየገዳማቱ ሒዱና ይህን ከቅዱሳን አበው ወእማት ተማሩ።
እነዚህ ቅዱሳን በእልፍ ወትእልፊት ዕንቁ የተሽቆጠቆጡ ልብስ ብትሰጥዋቸው አይቀበልዋችሁም። ለምን?እነእረሱ ጋር ያለው ልብስ እናንተ ይዛችሁት ከሔዳችሁ ይልቅ በእጅጉ እንደሚበልጥ ስለሚያውቁ። ይኸውም የነፍሳቸው ልብስ ማለቴ ነው። ለነእርሱ ይዛችሁት የሔዳችሁት ልብስ ለአንድ ምድራዊ ንጉሥ ብትሰጡት እጅግ ያመሰግናችኋል። እነእርሱ ግን ከዚህ ንጉሥ በላይ በከበረ ልብስ ያጌጡ ናቸውና አይቀበልዋችሁም። ወርቃቸውን ወደሚያስቀምጡበት መዝገብ
/ልቡናቸው/ ገብታችሁ ስታዩማ ራሳችሁን ሰታችሁ ትወድቃላችሁ።የሀብታቸውን/ምግባር ትሩፋታቸውን/ ብዛት የወርቃቸውን ንጻት እንዲህ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። እናንተም ከእነእርሱ ተማሩና እውነተኛውን ልብስ ለመልበስ ተሽቀዳደሙ።
https://t.me/yeberhanljoche
🌼✞              🕯🕯🕯              ✞🌼                 

በቸርነትኽ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።
የምድረ በዳ ተራራዎች ይረካሉ፥ኰረብታዎችም በደስታ ይታጠቃሉ።

🌼 ✢     መዝ 64÷11-12      ✢ 🌼

ውድ የውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ ብዙ ሰዎች በህይወታቸው አንዲት የንስሐ ቀን በተሰጣቸው በተመኙ ነበር ግን አልቻሉም እኛ ግን ሳይገባን እንዲሁ ከወደደን ከእግዚአብሔር ሌላ 365 የንስሐ ቀናት በታላቅ ስጦታ መልክ ተሰቶናል እና እንጠቀምበት ይህ ዘመን ሀገራችን ሳላም ሆና የምናይበት ይሁንልን ለኛም መልካሙን የተመኘ ነውን ከኀጢአት በስተቀር አምላክ ይፈፅምልን መልካም አመት እንዲሆን መልካም ምኞቴ ነው።

      ከ ው/ሰ/ት/ቤት መልካሙን ሁሉ እመኝላቹሀለው መልካም አዲስ አመት።
ይቅርታ ምንድን ነው ?

የይቅርታ ጥጉስ እስከምን ነው ?

“ትርጉም የሌለው ይቅርታ ፈርዶ ከመግደል አይለይም” ዛሬ በህይወት ባይኖሩም ትምህርታቸው ግን ህያው ሆነው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል ፡- ብጹዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ፡፡

ሰው የግጭት አካል ነው፡፡ ፍጹም ተሆኖ አይኖርም፣ አይቻልምም፡፡ የሰው ሰውነቱ የሚለካው በስሁትነቱ ነው፡፡ ጻድቅ ጻድቅነቱ ሰባት ጊዜ ወድቆ ሰባት ጊዜ መነሳቱ የጽድቁ ልኬቱ እንደሆነ ሁሉ ማለቴ ነው፡፡ ይቅርታን መጠየቅ መጸጸት ሲሆን ይቅርታን ማድረግ ግን ታላቅነት ነው፡፡ ማመን ቀላል ሲሆን መታመን ደግሞ እጅግ ከባድ ሸክም ነው፡፡ ማመን ኃላፊነት መወጣት ነው፣ መታመን ግን ኃላፊነትን መሸከም ነው፡፡ ይቅርታ በማድረግ ውስጥ “ፍጹምነት” ሊኖር ግድ ነው፡፡ ይቅርታን የምታደርጉ ሁሉ ሸክምን ይቅርታችሁን ጠይቋችሁ ለሰጣችሁት ሰው እንዳሸከማችሁት እመኑ፡፡ ቅርታን ስታደርጉ “እዳው በአንተ ላይ ይሁን” ማለታችሁ ነው፡፡ ስለሆነም ወደ ኋላ ከመመለስ ይልቅ እንደ ጳውሎስ በፊታችሁ ያለውን ለመያዝ ሩጡ እንጂ ያስተፋችሁትን ቆሻሻ መልሳችሁ ለመቁጠር ወደ ኋላ ለመመለስ ቁጥር አትጀምሩ፡፡

እግዚአብሔር መሐሪ ነው፡፡ ምን ድረስ ? ልጁን ኢየሱስን እስከመስጠት ድረስ፡፡ ይቅር የምንል ሁሉ ይቅርታ የተደረገልን ነን፡፡ በወንጌል ላይ እዳው ተሰርዞለት በደስታ ዘልሎ ሳይጨርስ እሱ ደግሞ እዳ ያለበትን ባለእዳውን ሲመለከት የተሰረዘለት እዳው ተረስቶት ባለእዳውን ያነቀውን ሰው አስቡት፡፡ የእሱ እዳ እንደተሰረዘለት እሱም የሌላውን እዳ መሰረዝ ሲኖርበት እሱ ግን ባለ እዳዬ ያለውን በማነቁ ወደ ወኅኒ መጣሉን አስታውሱ፡፡ ከክፋት ሁሉ የከፋ ክፋት የሰጠነውን ይቅርታ መልሰን ለመንጠቅ የምናደርገው ነው፡፡ ይቅርታ ያልነውንና . በደል እያነሳን ማቁሰል እግዚአብሔርን አለማወቅ ክፉ ቂመኝነትም ነው፡፡ የእኛ ድርሻ በይቅርታ ውስጥ የይቅርታን ጌታ አስታውሶ በንጹህ ኅሊና መኖር ነው፡፡ “ትቼልሃለው” ብሎ ትቶ መኖር እንዴት ያለ ክርስትና መሰላችሁ ! እዳን ለባለ እዳ ተዉለት እንጂ የእዳ ተሸካሚ አትሁኑ፡፡ ክርስቶስ እዳን ሰረዘ እንጂ አልቆጠረም፡፡ ታዲያ የሰረዝነውን እዳ መልሰን የምንቆጥር እኛ ከማን ተምረን ነው ? በማመን ወደፊት ሂዱ እንጂ በመጠራጠር ወደ ኋላ አትመለሱ፡፡ እግዚአብሔር ተቆጣጥሮልን እንጂ እኛ ተከታትለን የምናሸንፈው ነገር የለም፡፡

ይቅርታ ዋጋ አውጥቷል፡፡ ይቅርታ ዋጋ ያeወጣልም ፡፡ የምንወደውን ሰው ይቅር ለማለት ዋጋ እንከፍላለን፡፡ ዋጋው የቀደመውን ፍቅርና ለይቅርታ ራቁቱን የተሰቀለውን ማሰብ፡፡ በአንድ ወቅት ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ጌታ ቀርቦ “ጌታ ሆይ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት?” አለው፡፡ ጴጥሮስ ግን ለጠየቀው ጥያቄ መልስ ከመጠበቅ ይልቅ የውስጥ ደንዳናነቱ እንዲጸድቅለት በማሰብ ይመስላል በትንሽዋ አእምሮው ያለውን የራሱን አስተያየት ሰጠ፡፡ “እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?” በዚያ የመስቀል ስቃይ ላይ ሆኖ የሰቀሉትን ይቅር ያለና ለሰቃዮቹ እንኳን የመዳንን ሀብት የሰጠ ጌታችን ግን እንዲህ አለ “እስከ 70 ጊዜ 7 እንጂ እስከ 7 ጊዜ አልልህም” ማቴ 18 ÷ 21-22 በሂሳብ ስሌት መሰረት በቀን 7 x 70 = 490 ጊዜ ይቅር ማለት ይጠበቅብናል፡፡ እውነተኛ ፍቅር ይህ ነው፡፡ እውነተኛ ፍቅር ይሰርዛል እንጂ አያከማችም፣ ኃጢአትን ያፈሳል እንጂ አይቋጥርም፣ ያቅፋል እንጂ አይወጋም፣ ያክማል እንጂ አያደማም፡፡ ይቅርታ ማድረግ ትክክለኛ ትርጉሙ “መተው” ወይንም “መርሳት” መሆኑን ክርስቶስ ተማሩ፡፡ ጠቢቡ እንዲህ ይላል “ሰውን ጠቢብ አእምሮው ከቁጣ ያዘገየዋል፣ በደለኛውንም ይቅር የሚል ክብር ይሆንለታል” ምሳ 19÷11

የይቅርታ ሰዎች የሆናችሁ የመንግስቱ ውራሾች ያድርገን አሜን መልካም ቀን
@yeberhanljoche @yeberhanljoche
@yeberhanljoche @yeberhanljoche
" ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ . . ." (2ኛ ጢሞ 1፥9)

መለኮታዊ የሆነውን ተልእኮ ለመፈጸም ከቶ የሰውን ፈቃድ መጠበቅ የለብንም። እግዚአብሔር ወደራሱ ሲጠራን ማንንም አላማከረም፤የእኛን የልብ ፈቃድ ከመመልከት ውጪ። ማንም ደግሞ እግዚአብሔር ወደራሱ እንዴት እንደሳበንና ልባችንን እንደነካው ፍጹም የሆነውን ሚስጥር አያውቅም፤ ከድንጋይ ይልቅ ጠጣራ፣ እንኳን የሰውን የአምላክን ማንነት ክዳ በምድረበዳ ልኖረችው ልባችን፡ እንዴት አድርጎ ክርስቶስ በፍቅሩ መዶሻ እንዳፈረከሳት የሚረዳም ሆነ የሚያውቅ ፈጽሞ የለም። እናም ሰውን ደስ ከማስኘት ይልቅ አምላክን መታዘዘ ብርቱ ከሆነ ኪሳራ አውጥቶ ዘላለማዊ ትርፍ የሚስገኝ ነገር መሆኑን ልብ ልንለው የሚገባ ነገር ነው።

በልብህም ይሁን በአእምሮ ጽላት ላይ የተጻፈውን መልኮታዊ አጀንድ፣ ለእግዚአብሔር ይህን በሕዝቤ መካከል አደርጋለው ብሎ ሲያመልክትክ ለልብህም ሲናገራት ማንን አማክሮ ነው? ባጠገብህስ ማንን ምስክር አስቀምጦ ነው? አምልካዊ እይታውን መንፈሳዊ አይኖችህን አብርቶ በመንግስቱ ውስጥ የድርሻህን እንድትወጣ ያየውን እንድታይ እና እንድትከውን ራዕይን ሲሰጥህ ማንን ተማምኖ ነው? ከዚያ ከውዳቂ ሰፈር እውጥቶ ወደ አላማ እና ግቡ ወደ ሚያደርሰው የከበረ ሰረገላ ላይ ሲያሳፍርክ እርሱን ለመታዘዝና ለመሄድ " አማላክ ሆይ ይህው እኔ ላከኝ" በሚል ልብ በፊት ከመሆን ይልቅ ስለምን በዙሪያ ያልውን ነገር ማይት አስፈለገ? ስለምንስ ካምላክ ይልቅ የሰውን ፍቃድ እንጠብቃልን?? አብርሃም አምላኩን እሺ ባይልና ባይታዘዝ ለዓለሙ መዳን ተስፋ የሆነው የክርስቶስ የኪዳን ዘር ምን ይመስል እንደነበረ ማሰብ ከባድ ነው። ዳዊት ስንቅን ሊያደርስ ሲሄደ ከአምላኩ ይልቅ፡ የሰማውንና የታዘዘው ውንድሞቹን ቢሆን ፍልስጤም በእስራኤል ላይ ምን ያደርግ ይሆን? ከደም መፍሰስ ነጻ ወጥታ የክርስቶስን እግር በሽቱ የጠበችው ማሪያም መቅደላዊት ያንን ለማደረግ ለቧ ከውሰነው ውሳኔ ይልቅ ለደቀመዛሙርቱና በቤቱ ለነበረው ማጉረምረም ታዛ ወደ ኋላ ብትል " ይህ ወንጌል በተነገረበት ስፍራ ሁሉ" የተባለው ስለ እርሷ የተነገረው ምስክርነት ይነገር ይሆን?።

እርግጥ ነው እንዳንድ ጊዜ ተመክሮዎችንም ይሁን ምክሮችን በመልካምነቱ ከሰዎች መቀበል ይሁን፣ መስማትና መተግበር አስፈላጊ ነው፤ ፍጹም በሆነ መንገድ ግን ሰምቶ መልኮታዊውን የአምላክ ትዕዛዝ ለመታዘዝ የሰውን ፍቃድ መጠበቅ ፈጽሞ ስህተት ነው። " ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ። ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።" ሐዋ 5፥29
ልንታዘዘው የተገባውን የመልኮትን እጀንዳ ጊዜና ውቅት ልንቀጥርለት አይገባም በፍጹም፤ ዘግይቶ መታዘዝ ካለመታዘዝ አይለይም። እርሱ ነውና ለአላማው የጠራችሁ እርሱን ታዘዙት።

" የሚጠራችሁ የታመነ ነው፥ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።" 1ተሰ 5፥24

ኃጢአት የኀሊናና የመንፈስ ሞት ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ‹‹የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው›› (ሮሜ.፮፥፲፫) ሰው በዚህች በዓለም ውስጥ ሲኖር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ኃጢአት ይሠራል፤ በመታገስ ኃጢአትን ማሸንፍ አቅቶት ክፉት ሲሠራ ለኃጢአት ይሸነፋል፡፡  ይህም ከልጅነቱ ያርቀዋል፡፡ አዳም ከልጅነቱ ተዋርዶ ከገነት የወጣው ለኃጢአት በመሸነፉ ነበር፡፡ ‹‹ክፉን በመልካም አሸንፉ እንጂ በክፉ አታሸንፉ›› (ሮሜ.፲፪፥፳፩) ከአባቱ ቤት የወጣ ልጅ፣ ከእረኛው የተለየ በግ፣ ባለቤት የሌለው ገንዘብ ነውና ኃጢአተኖች የጠፉ ናቸው፤ ዓለማዊ ሕይወት የሚያሸንፋቸው ይጠፋሉና፤ ‹‹ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም››፡፡ (፩ ዮሐ. ፪፥፲፮)
ኃጢአት የሚሠራ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር የለውምና ከፈጣሪው ይርቃል፤ ለዚህም ነው ኃጢአትም ከእግዚብሔር መለየት ነው የተባለው፤ ‹‹ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?፤ ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?›› ( ፪ ቆሮ.  ፮፥፲፬-፲፭)
ኃጢአት እግዚብሔርን ማጣትም ነው፤ በኃጢአት የሚኖር ሰው ራሱንና ልቡናውን ከእግዚአብሔር በመለየቱ እግዚአብሔርን ያጣል፤ ‹‹የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል››፤ (ዮሐ.፲፬፥፳፫)  ፈጣሪን የማያምን ግን ኃጢአትን አብዝቶ ይሠራል፤ መጥፎ ሥራዎችን የሚሠራ ሰው መንፈስ ቅዱስ ይርቀዋል፤ የመንፈስ ቅዱስንም ሥራ ይቃወማል፡፡ ‹‹ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ›› (ኤፌ.፬፥፴) መንፈስ ቅዱስ በሰው ልቡና ውስጥ ሥራውን ካልሠራ ሰው ንስሓ ሊገባ አይችልም፤ ሰው በኃጢአቱ እንደተጸጸተና ንስሓ እንዲገባ የሚያበረታው መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ ኃጢአተኛ ሰው የሕይወትን ትርጉም አያውቅም፤ ስለንስሓ ቢነገረው ‹በሕይወቴ እንድደሰት ተውኝ› ይላል፤ ምድራዊና ዓለማዊ ደስታ ሕይወት እንደሆነ ያስባልና፡፡
በኃጢአት ውስጥ የኖረ ሰው ውስጣዊ ሰላም የለውም፤ ‹‹ለክፎዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር›› (ኢሳ. ፵፰፥፳፪) ልቡናውም በጭንቀት ስለሚሞላ ፈሪ ይሆናል፡፡ መጥፎ ባሕርይን ይወርሳል፡፡ አዳም ኃጢአትን በሠራ ጊዜ ከዚያ በፊት ያልነበሩ ሦስት ነገሮችን ገንዘብ አደረገ፤ ፍርሀት፣ ድንጋጤና ሰላም ማጣት፤ ፍርሀት የሥነ ልቡና ሕመምተኛ ያደርጋል፤ ኃጢአት ሕሊናን ያደክማል፡፡ ጻድቃን ግን በሰላም፣ በፍቅርና በድስታ ይኖራሉ፡፡ የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነውና፤(ገላ. ፭፥፳፪-፳፫)
በዚህ ምድር ስንኖር ሕገ እግዚአብሔርን በመተላለፍ የተነሳ መርገሞች የሚያስከትሉአቸው ቅጣቶች ብዙ ናቸው፡፡ ‹‹የዚህን ሕግ ቃሎች ያደርግ ዘንድ የማያጸና ርጉም ይሁን…››(ዘዳ. ፳፰፥፳፮) ሰው ንስሓ ሳይገባ ለድንገተኛ ሞት ሊዳረግ ይችላል፤ በበሽታ ይቀጣል፤ ረኃብ፣ ቸነፈርና ድኅነት ይበዛበታል፤ በደልም ይደርስበታል፡፡
ሰው ንስሓ ከገባ ከዘለዓለማዊ ቅጣት ይድናል፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር የተወሰነበትን ምድራዊ ቅጣት መቀበል ይኖርበታል፡፡ ያም የሚወሰነው ከሚሠራው የኃጢአት ዓይነት ነው፡፡ በእርግጥ የኃጢአት ትንሽና ትልቅ የለውም፤ ሆኖም ሰው ዐሥርቱ ትእዛዛትን በተላለፈበት መጠን ይቀጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሳ የሚመጣ ቅጣትና በፍትሐ ብሔር ወይም በቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ቅጣት ሊቀበል ይቻላል፡፡ ይህም ለተወሰነ ጊዜ ከቅዱስ ቁርባን መከልከና ቤተክርስቲያን እንዳይገባ መከልከል ሊሆን ይችላል፡፡
 ኃጢአትን አብዝቶ መሥራት በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ መሆንን ያስቀራል፤ የኅሊና ነጻነትንና የልቡና ንጽሕናንም ያሳጣል፡፡ ‹‹እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› (ዘሌ.፲፩፥፵፬) ኃጢአትን የማይተው፣ እስከዕለተ ሞቱም ንስሓ የማይገባ ሰው ግን የዘላለም ቅጣት ይፈረድበታል፡፡ እግዚአብሔር መሓሪና ምሕረቱም የበዛ እንደሆነ ሁሉ ፍርዱም እውነትና ፍጹም መሆኑን፣ በደልን ይቅር የሚል፣ ኃጢአትንም የማይወድ መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡ ከእግዚአብሔር ቸርነትና ምሕረት አንጻር ፍርዱንና ቅጣቱንም አስቦና ተረድቶ ወደ ንስሓ መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ቸርነቱን በመተማመን ጭከናውን መርሳት፣ ምሕረቱንም ተስፋ በማድረግ ፍርዱንም ደግሞ መዘንጋት አይገባም፡፡ ‹‹እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭከና ተመልከት፤ጭከናውም በውድቀቱ ላይ ነው፤ በቸርነቱ ግን ጸንተህ ብትኖር የእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ላይ ነው፤ ያለዚያ አንተ ደግሞ ትቆረጣለህ›› (ሮሜ. ፲፩፥፳፪)
እግዚአብሔር እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ ፍርዱም በትክክል ነው፤ ንስሓ ገብተን ከፊቱ ብንቆም የእግዚአብሔርን ቸርነት እናያለን፡፡ በግድ የለሽነት የምንኖር ንስሓ የማንገባ ሆነን በፊቱ ብንቆም ደግሞ በጭካኔውና በፈራጅነቱ እግዚአብሔርን እናየዋለን፡፡
የዓለም ፍጻሜ የፍርድ ቀን አስደንጋጭና አስፈሪ ነው፤ ‹‹እነሆ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፣ ኃጢአተኞቿንም ከእርሷ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቁጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል›› (ኢሳ. ፲፫፥፱) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ ጣኦቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ፡፡ እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ሰዎችን ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ  ዋሻና ወደ ምድር ንቃት ውስጥ ይገባሉ፡፡ (ኢሳ.፪፥፲፯-፳) ፭ኛው የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳም እንዳሉትም ‹‹ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃውንም ብታውቅ ትሸሸዋለህ››፡፡ ጻድቃን መንግሥተ ሰማያትን ሲወርሱ ኃጥኣን ግን ዘለዓለማዊ ቅጣት ወዳለበት ገሀነመ እሳት ውስጥ ይጣላሉ፡፡ ‹‹እነዚያም ወደ ዘለዓለም ቅጣት፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ›› (ማቴ.፳፭፥፵፮)
በዚያች በፍርድ ቀን ለቅሶ፤ ዋይታና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤ ሆኖም ሁሉም የማይጠቅም ጩኸት ነው፡፡ ጨለማውና የማይጠፋው እሳት እጅግ ከባድና አስፈሪ ነው፡፡ ከባድነቱንም ለመረዳት የሚቻለው ግን የጻድቃንን ሕይወት በማየት፣ በመረዳትና በማወቅ ነው፡፡
ምንጭ፤ የንስሓ ሕይወት መጽሐፍ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ  የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፤ ውርስ ትርጉም ቀሲስ እሸቱ  ታደሰ ወንድምአገኘሁ በ፳፻፱ ዓ.ም.

https://t.me/yeberhanljoche
* ሀልወተ እግዚአብሔር *
ሀልወተ እግዚአብሔር ማለት የእግዚአብሔር መኖር ማለት ነው ። እግዚአብሔር የሚባል ነገር የለም የሚሉ አሉና ከሱ እንጀምር ። ታዲያ የእግዚአብሔር መኖር በምን ይታወቃል ? ቢሉ ። 1ኛ.በስነ ፍጥረት ይታወቃል ። ም/ቱም ፍጡር ካለ ፈጣሪ አለና ። ስዕል ካለ ሰዓሊው አለ ፣ ቤት ካለ አናፂ አለ ፣ ሙዚቃ ካለ ሙዚቀኛው አለ ማለት ነው ። ስለዚህ በዚ መሰረት ስናየው ይሄ ሁሉ ስነ ፍጥረት አስገኚ አካል ወይም ፈጣሪ አለው ማለት ነው ። 2ኛ. የሰው ልጆች ዝንባሌ ነው ።ይህም ማለት ግማሹ ሙስሊም ፣ ግማሹ ቡዲስት ፣ ግማሹ ክርስቲያን ፣ ግማሹ ባዕድ አምልኮ አምላኪ የሆነው ነብሱ ከውስጥ የፈጠራት አካል እንዳለ ስለምትጮህ ነው ። ስለዚ ይህም አንዱ የፈጣሪ መኖር ማስረጃ ነው ። 3ኛ.የቀናትና የወቅቶች መፈራረቅ ነው ። ይህም ለምሳሌ መብራት ሲጠፉና ሲመጣ መብራት ሀይል የሚባል አካል እንዳለ እንደምንረዳው ሁሉ ፡ የቀንና የማታ የበጋና የክረምት መፈራረቅም አምላክ እንዳለ ማስረጃ ናቸው ። ፀሀይን በቀን ጨረቃን በማታ ያሰለጠነ ቀኑን ለሰራዊት ሌሊቱን ለአራዊት ያደረገ አምላክ መሆኑን እናውቅበታለን ።የስነ ፍጥረት አይነቱ ብዛቱ ድንቅ ነው ። 1ፀሀይ ሆና ለአለም ሁሉ እንድታበራ ማን አደረጋት ? የዛፎቹ አይነት አንዳንዱ ቅጠሉ ሰፊ አንዳንዱ ቅጠሉ ቀጭን ፣ የአእዋፏቱ አይነት ፣ የአሶችና የሌሎች ባህር ውስጥ ያሉ ነብሳት መኖር ፣ ስናይ ፈጣሪ እንዳለ እንረዳበታለን ። ለውቅያኖሶች ዳርቻዎቻቸውን የወሰነላቸው ሰማይን በከዋክብት ምድርን በአበቦች ያስጌጠ ስራው ድንቅ የሆነ አምላክ የመኖሩ ማስረጃ ናቸው ። ሸክላና ተሽከርካሪ ፣ መርከብና አየር በራሪ ፣ ድልድይና አስፓልት ፣ መኪናና ሌሎችም ሞተር ነክ ነገሮች ፣ ታሪካውያን ህንፆዎች ፣ የሚያስገርሙ ነገሮች ሁሉ ያለ ሰሪ ፣ አትክልትና አዝርዕት ያለ መሬትና ያለ ዘሪ ፣ ልጅ ያለ እናትና አባት እንደማይገኝ ሁሉ ግዑዛንና ግዙፉን ጥቃቅንና ረቂቃን ፍጥረት ሁሉ ያለ ፈጣሪ እንዳልተገኙ እናምናለን ። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "የሚታየው ከማይታየው እንደሆነ እናምናለን" እንጂ ዳዊት በመዝሙር 13:1 "ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል" እንዳለው አምላክ የለም አንልም
https://t.me/yeberhanljoche
✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ገዳማዊ "ቅዱስ አባ ባውላ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ አባ ባውላ መስተጋድል +"+

=>ቅዱሱን የመሰሉ አባቶች "መስተጋድላን" ይባላሉ በግዕዙ:: ለሃይማኖታቸው እስከ ደም ጠብታና እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ መጋደላቸውን የሚያሳይ ነው:: መጋደል ጐዳናው ብዙ ዓይነት ነው::

+ከራሱ ጋር የሚጋደል አለ:: ከዓለም ጋር የሚጋደልም አለ:: የቅዱሳኑ ተጋድሎ ግን በዋነኝነት ከ2 አካላት ጋር ነው:: በመጀመሪያ ፍትወታት እኩያትን (ኃጣውዕን) ከሚያመጡ አጋንንት ጋር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ሃይማኖቸታችሁን ካዱ: ለጣዖትም ስገዱ" ከሚሉ ከሃድያን ጋር የሚደረግ ትግል ነው::

+በተለይ 2ኛው እስከ ሞት የሚያደርስ ውሳኔን ይጠይቃል:: ታላቁ አባ ባውላ ገዳማዊ ጻድቅ እንደ መሆኑ ትግሉ የነበረው ከአጋንንት ጋር ነው:: የዚህን ቅዱስ ሕይወት ለመረዳት ግን አንድ ነገርን ልብ እንድትሉልኝ እፈልጋለሁ::

+ያለንበት ዘመን ክርስትና በራድ (ቀዝቃዛ) በመሆኑ የቀደሙ አባቶች የጸና ተጋድሎ አንዳንዴ ግራ ሲያጋባን ተመልክቻለሁ:: ቅዱሳኑ ሁሌም አንድ ነገርን እያሰቡ ይኖራሉ:: ይኼውም በዘመኑ በርካቶቻችን የረሳነው: ወይም ማስታወስ የማንፈልገው ነገር ይመስላል::

+ሰማያዊው አምላክ ከዙፋኑ ወርዶ በተዋሐደው ሥጋ በቃል ሊገለጽ የማይችል መከራን ስለ እኛ ተቀብሏል:: ክርስትና ማለት ቀራንዮን በልብ ውስጥ መሳል ነው:: ፍቅረ መስቀሉን: የጌታንም ውለታ የሚያስብ ማንኛውም ሰው: የትኛውም ዓይነት መከራ ቢመጣበት አይታወክም::

+ቅዱሳኑም የፍቅራቸውና የትእግስታቸው ምሥጢር ይኼው ነው:: ጌታ "የሚወደኝ ቢኖር የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" (ማቴ. 16:24) እንዳለው: ቅዱሳኑ ይህንን ቃል በቃል ሲፈጽሙት እነሆ እንመለከታለን::

+ታላቁ አባ ባውላ የተወለደው በላይኛው ግብጽ አካባቢ ሲሆን ዘመኑም 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ከክርስቲያን ወላጆቹ መንፈሳዊ ነገሮችን ተምሮ በወጣትነቱ መንኗል:: ያ ዘመን እልፍ አእላፍ ቅዱሳን የነበሩበት ነውና ወደ ጠመው አካባቢ ሔዶ ምናኔን ተምሯል::

+ሥርዓተ ገዳምን ማለትም:- አገልግሎትን: ፍቅርን: ተጋድሎንና የመሳሰሉትን ከተማረ በሁዋላም ደቀ መዝሙሩን አባ ሕዝቅኤልን አስከትሎ ለዋናው የተጋድሎ ሕይወት ወደ በርሃ ወጣ:: አባ ባውላ ዘወትር በፍቅረ ክርስቶስ ይመሰጥ ነበርና የተጋድሎ ምርጫው ልዩ ሆነ::

+አንድ ቀንም እንዲህ ሲል አሰበ:- "ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ለኃጥአን ኃፍረተ መስቀልን ታግሠህ: ሞትን ከሞትክልን እኛ ደግሞ ስለ ንጹሑ አምላክ ስንል እልፍ ሞትን መታገስ አለብን::"

+ይህንን ብሎ ከወትሮው በተለየ መንገድ ሊጋደል ጀመረ:: በዚህ እጅግ የጸና ተጋድሎው ምክንያትም 7 ጊዜ ሙቶ 7 ጊዜ ተነሳ::

1.እግሩን ከረዥም ዛፍ ላይ አስሮ: ወደ ታች ተዘቅዝቆ ይጸልይ ጀመረ:: እህልም: እንቅልፍም: ዕረፍትም አልነበረውምና ደሙ በአፍ: በአፍንጫው ፈሶ አለቀ:: እንዲህ በሆነ በ40ኛው ቀንም ሞተ:: መልአከ እግዚአብሔር መጥቶ ከሞት አስነሳው::

2.ጥልቅ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ እንዳስለመደ ይጸልይ ጀመረ:: ከባሕሩ ሳይወጣ: ከቆመ ሳያርፍ: ከዘረጋም ሳያጥፍ ለ40 ቀናት ጸለየ:: በዚያው ሳለም ለ2ኛ ጊዜ ሞተ:: ቅዱስ መልአክ መጥቶ ከሞት አስነሳው::

3.እርሱ በሚኖርበት ጠመው አካባቢ ረዥም ተራራ ነበርና ወደዚያ ወጣ:: ከተራራው ጫፍ ሆኖ ወደ ታች ተመለከተ:: የተጠራረቡ ድንጋዮች በየመንገዱ ተሰልፈው ነበር:: በዚያች ቅጽበት የጌታ ኅማማት ከፊቱ ቢደቀንበት ከላይ ወደ ታች ተወርውሮ ሔደ::
በየመንገዱ ያሉት ጥርብ ድንጋዮች ቢቀበሉት አካሉ እየተነተፈና እየተቆራረጠ በየመንገዱ ቀረ:: በዚህም ሞተ:: አሁንም ፈጣሪው ከሞት አስነሳው::

4.አንድ ቀን ደግሞ (ዕለቱ ዓርብ ነበር) የጌታን ኅማማት እያሰበ የሚያደርገው ጠፋው:: ከቆመበት አካባቢ ትልቅ ዛፍ ነበርና ወደዚያ ወጥቶ ሲመለከት ከመሬት ላይ የተነጠፈ ትልቅ ድንጋይ አየ:: ከላይ ወደ ታች ሲወድቅና ድንጋዩ ላይ ሲያርፍ ለሁለት ተከፍሎ ሞተ:: አሁንም በፈጣሪ ትዕዛዝ ተነሳ::

5.በሌላ ቀን ደግሞ በዕለተ ዓርብ ጭንቅላቱን ከእግሩ ጋር አሥሮ ይጸልይ ገባ:: ያለ ምንም እህል: ውሃና እንቅልፍ ለ40 ቀናት ቆይቶ ሞተ:: እንደገናም ተነሳ::

6.እጅግ ሊመለከቱት እንኩዋ በሚከብድ የጉድጉዋድ ውሃ ውስጥ ገብቶ ለ40 ቀናት እጆቹን ዘርግቶ ቢጸልይ ከጭንቁ ብዛት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች::

7.አንድ ቀንም እንደዚሁ የጌታን ሕማማት እያሰበ ወደ ጽኑ ቆላ ወረደ:: በአካባቢው ከአሸዋ በቀር ምንም አልነበረምና ቆሞ ሲጸልይ አሸዋው ውጦ ደፈነውና ለ7ኛ ጊዜ ሞተ:: በዚህ ጊዜ ግን ሊያስነሳው የመጣው እንደ ወትሮው ቅዱስ መልአክ ሳይሆን ራሱ የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ ነበር::

+ጌታችን አባ ባውላን ከሞተበት አስነስቶ:- "ወዳጄ ባውላ! ስለ እኔ ፍቅር እጅግ ተሰቃየህ" አለው:: ቅዱሱ ግን "ጌታየ ሆይ! የእኔ መከራ በአንተ መከራ ሲታሰብ ኢምንት ነውና እባክህ ስለ ስምህ ሌሎች መከራዎችን እንድቀበል ፍቀድልኝ? ገና ሕማምህን አስቤ አልረካሁምና" አለው::

+ጌታ ግን "የለም! መከራው ይበቃሃል:: መጥቼ እስክወስድህ ድረስ ከአባ ብሶይ ጋር ቆይ" ብሎት: ባርኮት ዐረገ:: አባ ባውላም እንደ ታዘዘው በአባ ብሶይ ገዳም ከቅዱስ ብሶይ ጋር ቆይቶ በዚህች ቀን ዐርፏል::

+ይህቺውም ዕረፍቱ ለ8ኛ ጊዜ ሆና ተቆጥራለች:: የቅዱሱን ዜና የጻፈው ደቀ መዝሙሩ አባ ሕዝቅኤል ሲሆን ያሰፈረው እንባው እንደ ዥረት እየወረደ ነው:: አባቶቻችን ሊቃውንትስ ታላቁን ጻድቅ ሲያመሰግኑት እንዲህ አይደለምን!
"ውስተ ገድል ጽኑዕ ዘአልቦ ምምዐ:
ወደቀ ስብአ: ወተንሳእከ ስብአ::"

=>አምላከ አባ ባውላ በጻድቁ ላይ ያሳደረውን ፍቅሩን ያሳድርብን:: ከበረከቱም ያድለን::

=>ጥቅምት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ባውላ መስተጋድል
2.አባ ሕዝቅኤል ጻድቅ
3.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ሐናሲ ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

=>+"+ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል:: ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ: ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? +"+ (ማቴ. 16:24)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/yeberhanljoche
.💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

#ኪዳነ ምህረት

ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡

ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡

እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡

ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ በራሴ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ስም ቀል እገባልሻለው ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል።

በዚህም የተነሳ እመቤታችን እኛን በምልጃዋ የምታስምርበተ ፣ ጥያቄያችንን የምታስመልስበት ፣ እንቆቅልሻችንን የምታስፈታበት የምህረት ኪዳን የካቲት 16 ተቀብላለች እና ኪዳነ ምህረት እንላታለን ።


💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛https://t.me/yeberhanljoche