ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት🙏(ጫንጮ)
766 subscribers
84 photos
4 files
98 links
ሰንበት ትምህርት ቤት የመልካም ወጣት የመልካም ትውልድ መፍለቂያ ናት! ትውልድን ለበጎ ነገር የምታበቃ ናት፡፡


የጫንጮ ከተማ ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ቻናል
ለሀሳብ እና አስታየት @weldebirhanbot @ty1921 ይጠቀሙ

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
Download Telegram
በበዓለ ሃምሳ ጾም፣ ስግደት እና ስንሐ ለምን ተከለከለ?

በበዓለ ሃምሳ ንስሐ ከሌለ፣ በኃጢአት ብንወድቅ መፍትሔው ምንድን ነው?

በበዓለ ሃምሳ መብልን በተመለከተ የአባቶቻችን ልምዳቸው ምን ይመስላል? እኛ ከእነሱ ምን እንማር?

ተወዳጆች ሆይ በዚህ በበዓለ ሃምሳ ብዙዎቻችሁ ጾሙ ወደ መብል ወይም ወደ ፍስክ፣ ስግደቱ ወደ እረፍት በመቀየሩ በሥጋ መንፈሳዊ ምቾት እንደሚነሳችሁ ይታወቃል፡፡ ‹‹በዓለ ሃምሳ፣ እጅ ታጥቦ ወደ ምሳ›› አይደል የሚባለው፡፡

በዓለ ሃምሳ በተለይ ጾም ስግደት እና የንስሐ ሕይወትን አጥብቀው ለሚይዙ እንዳቅማቸው ለሚጋደሉ ከእነዚህ ነገሮች ለወራት መገታት እንደሚከብዳቸው ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ሥርዓቱንና እንዴት ባለ መንፈሳዊ ሕይወት በዓለ ሃምሳን ማሳለፍ እንዳለብን እናያለን፡፡

ጌታችን ሞትን ድል ነስቶ ከሞት ተነስቶ የትንሳኤውን ብርሃን ስላሳየን  በበዓለሃምሳ በጾም በስግደት ድካመ ሥጋ የምንቀበልበት ሳይሆን በጌታ ትንሳኤ የምንደሰትበት ጊዜ ነው፡፡

አንድ ምዕመን በበዓለ ሃምሳ ልስገድ ልጹም ብሎ በግሉ ጾምንና ስግደትን ቢተገብር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከፈለለት ዘላለማዊ ዋጋ ሳይሆን በራሱ ጊዜያዊ ድካም ወይም ተጋድሎ ብቻ እድናለሁ ብሎ እንደማሰብ ነው፡፡

በነገራችን ላይ በበዓለ ሃምሳ ያሉት ሃምሳው ቀናት እንደ አንድ ዕለተ ሰንበት ነው የሚቆጠሩት፡፡ ለዛም ነው በእነሱ ውስጥ ያሉት የጾም ዕለታት የነበሩት አርብ እና ረቡዕ ጠዋት ለዛውም የፍስክ ምግብ የሚበላባቸው፡፡

በእርግጥ የመናፍስት ክፉ ውጊያ ላለበት ሰው በጾም በስግደት ለሚተጋ ሰው በዓለ ሃምሳ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ላይ ጫና እንደሚያሳድርበት አያጠያይቅም፡፡ ግን ከእኛ ድካም እና ገድል ይልቅ ጌታችን የከፈለልን ዘላለማዊ ዋጋ ተስፋ በማድረግ ድህነተ ሥጋና ድኅነተ ነፍሳችንን እንጠባበቃለን፡፡

በዚህ በበዓለ ሃምሳ ለምን አይሰገድም? አይጾምም? እያልን ለምንጠይቅ የበዓለ ሃምሳ ቀናቶች ምስጢራቸው ምንድን ነው? የሚለውንም ማየቱ መልካም ነው፡፡

የበዓለ ሃምሳ ሃምሳው ቀናት ዋና ምስጢር የሰማያዊ ዕረፍት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በመንግስተ ሰማያት ደግሞ ድካም መውጣት መውረድ እንደሌለ ሁሉ በበዓለ ሃምሳ ቀናትም መጾም መስገድ አይቻልም፡፡ ነገር ግን የዕለት ተዕለት የአምልኮት ስግደት መስገድ ይቻላል፡፡

በበዓለ ሃምሳ ስለሚኖረን የአምልኮት ስግደት እንዲሁም የሥጋ ጾር እና፣ የአጋንንት ውጊያ ለሚበዛበት  ሰው እንዴት መስገድ እንዳለበት እራሱን የቻለ አንድ ትምህርት አቀርብላቹኃለሁ፡፡
በበዓለ

ሃምሳ ጾም እና ስግደት የተከለከለበት ሌላው ምክንያት ጌታችን ‹‹እናንተ ደግሞ ሕግ አዋቂዎች አስቸጋሪ ሸክም ለሰዎች ስለምታሸክሙ ራሳችሁም በአንዲት ጣታችሁ ስንኳ ሸክሙን ስለማትነኩ ወዮላችሁ›› በማለት በሰዎች ላይ ሸክም እንዳናከብድ አዞናል፡፡ /በሉቃ 11÷ 46/

እንዲሁም ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናል›› ብለዋል፡፡ /ሐዋ 15÷28-29/  እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም›› ያሉት ጾም ለነፍስ መድኃኒት ቢሆንም ለሥጋ ግን አንደ ሸክም ስለሆነ ጾም በሚያስፈልግበት ጊዜ እንጂ ከጾም ፍቺ በኃላ ሌላ የጾም ሸክም አያስፈልግል ለማለት ነው፡፡

ሌላው በገዳም ያሉ መናንያን በዓለም ያሉ ምዕመናን በጾም ወቅት በጾም በስግደት የተጎዳ ሰውነታቸው በጥሉላት ምግብ ካልተጠገነ ወጥቶ ወርዶ ማገልገል ሠርቶ መብላት ወደ ሌላ የተጋድሎ ሕይወት መግባት እንዳያቅታቸውም ነው፡፡ 

ሃምሳው ቀናት የጾም የስግደት ሳይሆን የእረፍት እና ደስታ የሆነው፡፡ ፍትሐ ነገሥትም በአንቀጽ 19 በቁጥር 639 ላይ ‹‹በመዋዕለ ሃምሳ የሚጾም ወይም ኀዘን ያይደለ መንፈሳዊ ተድላ ደስታ ልናደርግባቸው በሚገባን በጌታ በዓላት ቀን የሚያዝን እንደዚሁ ቅጣት ይገባል›› በማለት በበዓለ ሃምሳ መጾም ማዘን እንደሌለብን ይደነግጋል፡፡

እዚህ ላይ ፍትሐ ነገሥቱ ‹‹መንፈሳዊ ተድላ ደስታ›› በማለት የገለጸው መንፈሳዊ ተድላ ደስታ የምናገኘው ሥጋዊ ምግብ በመብላት ሥጋዊ መጠጥን በመጠጣት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ምግብ እና መጠጥ የሆነውን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን በመብላት ክቡር ደሙን በመጠጣት የምናገኘውን መንፈሳዊ ተድላና ደስታ ለማለት ነው፡፡

የበዓለ ሃምሳን ተድላ እና ደስታን አስመልክቶ ብዙዎቻችን የምናስተምረው ትምህርት ልክ ያልሆነ ነው፡፡ ‹‹በዓለ ሃምሳ የተድላ የደስታ የመብል የመጠጥ ጊዜ ነው፡፡ ለሃምሳ ቀን አርብ እና ረቡዕ ተሽሯል የደስታ ጊዜ ነው ብሉ ጠጡ›› እያልን እናስተምራለን፡፡ በእርግጥም አርብ እና ረቡዕ ለሃምሳ ቀናት ተሸረዋል፡፡

በእውነት የበዓለ ሃምሳ ደስታ ተድላ ሥጋችንን ብቻ በመብል በመጠጥ ማስደሰት ነው? እንደውም በበዓለ ሃምሳ ብዙዎቻችን ሥጋችንን አስደስተን ነፍሳችንን የምንጎዳበት ጊዜ ነው፡፡ የበዓለ ሃምሳ ተድላ ደስታ ማለት እኮ ሥጋዊ መብል እና መጠጥን ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ መብል እና መጠጥ የሆነውን ቅዱስ ቁርባንንም ያካተተ ነው፡፡

አንድ ኦርቶዶክስ በዓለ ሃምሳ ተድላ ደስታ የሚሆንለት የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን ሲበላ ክብር ደሙን ሲጠጣም ጭምር ነው፡፡ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን መብላት ክቡር ደሙን መጠጣት ትቶ ሥጋዊ መብል ብቻ ቢበላ ሥጋዊ መጠጥ ብቻ ቢጠጣ  በዓለ ሃምሳ የተድላ የደስታ ሳይሆን የፈተና ጊዜ ይሆንበታል፡፡
ለዚህም ነው ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹በመጠን ኑሩ›› ያለን፡፡ /በ1ኛ ጴጥ 4÷8/

መብሉ መጠጡ ተድላው ደስታው መጠን ሊኖረው ይገባል፡፡ አንድ ነገር አትርሱ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ በጽርሐ ጽዮን ከሰማይ የወረደላቸው ሰባ ሁለት ቋንቋ የተገለጸላቸው ሰማያዊ እና ምድራዊ ምስጢር የገለጸላቸው በዚህ በበዓለ ሃምሳ ነው፡፡

ስለዚህ በዓለ ሃምሳ በጸሎት በአምልኮት ስግደት እና በተለይም ቅዱስ ቁርባን በመቀበል እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የምንቀበልበት ጊዜም ነው፡፡

በበዓለ ሃምሳ ንስሐ ከሌለ በኃጢአት ብንወድቅ ወይም ኃጢአት ብንሠራ መፍትሔው ምንድን ነው? የሚለውን ስናይ
በዓለ ሃምሳ ለብዙዎች ከበድ የሚለው ንስሐ ስለማይሰጥበት ነው፡፡ ለዚህ ነው ብዙዎች ‹‹በበዓ ሃምሳ፣ ንስሐ መግባት የማይቻለው፣ ለምንድን ነው?›› በማለት የሚጠይቁት፡፡

በነገራችንላይ በበዓለ ሃምሳ ንስሐ መግባት ክልክል አይደለም፡፡ ንስሐ ገብተን ቀኖና ወይም ጾም ስግደት ነው መቀበል የማንችለው፡፡

የንስሐ ቀኖና የማይሰጠው ሃምሳው ቀናት እንደ አንድ ሰንበት የሚቆጠርበት  እና የደስታ የተድላ ጊዜ እንጂ የንስሐ ቀኖና ተቀብለን የምናዝንበት የምናለቅስበት ጊዜ ባለመሆኑ ነው፡፡ ንስሐን ንስሐ የሚያሰኘው በውስጥ የያዘው ጾም እና ስግደት ነው፡፡ ስለዚህ ጾም እና ስግደት በሌለበት የንስሐ ቀኖና የለም ማለት ነው፡፡

ታዲያ በበዓለ ሃምሳ አንድ ሰው በኃጢአት ቢወድቅ ንስሐ መግባት ካልቻለ ምን መፍትሔ አለው? የሚልውን ጥያቄ መፍትሔው ሦስት ነው፡፡

አንደኛው ንስሐን ንስሐ አሰኝቶ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስርየት የሚያሰጠው በሠሩት ኃጢአት ከልብ በመጸጸት ነው፡፡ ጸጸት በራሱ ንስሐ እና አንድ የንስሐ መንገድ ስለሆነ፡፡

ስለዚህ ሰውነንና በዚህ ወራት በኃጢአት ብንወድቅ እግዚአብሔር ከበዓለ ሃምሳ በኃላ ለሚመጡት የቀኖና ቀናት ለንስሐ እንዲያበቃን በጸሎት እና በጸጸት ማሳለፍ ነው፡
https://t.me/yeberwhanljoche
የልደትሽ ቀን ልደታችን ልጅሽ ደሞ ህይወታችን ነው🙏🙏🙏

እንኳን አደረሳችው ግንቦት 1
#ከሐልዮ_ኃጢአት_መጠበቅ

ሰይጣን ነቅዓ ሐልዮን መጠበቅ ላልቻለ ወጣት በቀጣይ እርሱን የሚወጋበት ኹለተኛው ጦር ሐልዮ ኃጢአት ነው። “የሐልዮ ኃጢኣት ምን ትጎዳለች?” እያለ እንዲያስብ ያደርገዋል። በሐልዮ ኃጢአት ያዝለዋል። ይኸውም ደቂቀ ሴት ደቂቀ ቃኤልን ከመስማት አልፈው እንዲመለከቷቸው በማድረግ በዝሙት ፍላጻ እንደነደፋቸው ነው። ስለዚህ የተለያዩ ነገሮችን እንዲመለከት ያደርገዋል። ለምሳሌ ራስን በራስ ስለ ማጎሳቆል፣ ወይም ስለ ምስለ ሩካቤ፣ ወይም ስለሚያውቃት ሴት በዝሙት ሕሊና እንዲያስብ ያደርገዋል። ጓደኞቹ የተናገሩትን ነገር ወይም በመጽሔት ያነበበውን ወይም በተለያየ መንገድ ሲወራ የሰማውን “ይህ ምን ያረክሳል?” እያለ በሕሊናው እንዲያመላልሰው ያደርገዋል።

እንደዚህ በሚኾንበት ጊዜ በየትኛውም ቀን ቢሰግድ ፆሩ ይመለስለታል። አንድ ወንድሜ እንደ ነገረኝ፡ እንደዚህ ያለ ፆር ሲመጣበት በሩካቤ አካሉ አከባቢ ካለው ፀጕር የተወሰነውን ይነጫል። በጣም ያማል። በዚያ ሰዓትም ከፆሩ ይልቅ ሕመሙ ስለሚበልጥ ፆሩን ከማሰብ ይመለሳል። ሕሊናው አድርገኝ አድርገኝ ብሎ እንዳይገፋፋው፣ ነጉዶ የመጣውን ፆሩን በተግባር ለመፈጸም ሰይጣንን እንዳይታዘዘው ያደርገዋል። እንደ ነደ እሳት የሚያቃጥለውን የፍትወትን ፆር እንዳያስነሣበት ይከልለዋል።

የሐልዮ ኃጢኣት በተነሣ ጊዜ "ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ” እንደ ተባለው፥ ለዚህ ከሚዳርጉን ነገሮች (ቦታ፣ ኹኔታ) መራቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። “ይህ አሳብ የእኔ አይደለም” ብሎ ለመሸሽም የሐልዮ ኃጢአት የምታመጣውን መከራ የሚነግረን መምህር ወይም አበ ነፍስ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው (2ኛ ጢሞ.2፥22)። መካሪ መምህር ሳናገኝ ቀርተን ካዋልናትና ካሳደርናት ለሰይጣነ ፍትወት እጅ እንደ መስጠትና ወድቀን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ገቢር ልናልፍ እንችላለንና። ከክፉ አሳብ መራቁ ብቻውን በቂ አይደለም። ክቡር ዳዊት “ከክፉ ሽሽ” ካለ በኋላ በዚያ ሳያቆም ጨምሮ “መልካምንም አድርግ" ይላልና (መዝ.33፥14)። እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ናቸው። ስለዚህ አንዲት ሴት ጥሩ ልብሷን ተሸላልማ ተጊያጊጣ እየተኩነሰነሰች ስትሔድ አይቶ ፈላስፋው ዲዮጋንስ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች "ከዚች ክፉ ወጥመድ ሽሹ" እንዳላቸው ሸሽቶ ወደ በጎ ሥራ ፊትን ማዞር ይገባል። ከወደቁ በኋላ ከመጠበብ ሳይወድቁ መጠንቀቅ ይሻላልና።

በሌላ መልኩ ደግሞ ተፈጥሮ ስለኾነ እነዚያ ስሜቶች ለምን መጡ ማለት አይቻልም። ስሜቶቹን ግን መቀደስ ስለሚቻል ከክፉ ሸሽቶ መልካም በማድረግ መቀደስ ይቻላል። አንድ ፈረስን የሚጋልብ ሰው፥ ፈረሱ ወደ ገደል ቢያመራ ጋላቢው የሚያደርገው ልጓሙን ማጥበቅ ብቻ አይደለም፤ ፈረሱ በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድም ይመራዋል እንጂ። ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ሲመጡብን ከመራቅ ባሻገር ወዲያው መንፈሳዊ ተግባር ማከናወንም አስፈላጊ ነው። ጸሎት ሊኾን ይችላል፤ ስግደት ሊኾን ይችላል፤ መጽሐፍ ማንበብ ሊኾን ይችላል፣ መንፈሳዊ አባት ጋር መደወል ሊኾን ይችላል።

ከበረኻ አባቶች ከተሰጡት ምክሮች አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦“ሌላ እኁም ከሰይጣነ ዝሙት ጋር ይጋደል ነበር። በሌሊት ተነሥቶም ከአረጋውያኑ ወደ አንዱ መጥቶ ስለ ሕሊናው ነገረው። አረጋዊውም ይታገሥ ዘንድ መከረው። በዚህ መንገድ እገዛ አግኝቶም ወደ በዓቱ ተመለሰ። ለኹለተኛ ጊዜም ወደ አረጋዊው መጥቶም እርዳታ አግኝቶ ወደ በዓቱ ተመለሰ። ውጊያው ለሦስተኛ ጊዜ ሲመጣበትም እንደገና  በሌሊት ወደዚያ አረጋዊ ሔደ። አረጋዊውም ወጣቱን አላሳዘነውም፤ እንደሚጠቅመው መክሮ ዘክሮ ነገረው እንጂ፤ እንዲህ ሲል፡- ምንም ዕድል እንዳትሰጠው። ሰይጣነ ዝሙት በፈተነህ በማናቸውም ሰዓት ወደ እኔ ና። ከዚያም ታጋልጠዋለህ። ስታጋልጠው ሸሽቶ ይሔዳል። ሰይጣነ ዝሙት እነዚህን አሳቦች የሚደብቃቸውንና የማይገልጣቸውን ሰው ያህል የሚፈትነው የለምና።" ያ እኁም በዚያች ሌሊት እርዳታ ፈልጎ ዓሥራ አንድ ጊዜ ወደ አረጋዊው እየተመላለሰ አሳቦቹን ተቃወማቸው። አረጋዊውም ሰይጣነ ዝሙቱ ከእርሱ እንደ ራቀ ነገረው። ነገር ግን ወደ በዓቱ በተመለሰ ጊዜ ውጊያው እንደ ገና መጣበት። ከብዙ ጊዜ ምልልስ በኋላም ያ እኁ አረጋዊውን:- አባ! ቸርነትህ ይደረግልኝ፡ እንዴት አድርጌ መኖር እንዳለብኝ ምከረኝ አለው። አረጋዊውም፡- ልጄ ፥ በርታ! እግዚአብሔር ፈቃዱ ከኾነ የእኔ ሕሊና ወደ አንተ ይመጣል። ከዚያም በኋላ ንጹሕ ሕሊና ይዘህ ትሔዳለህ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ አትፈተንም' አለው። ይህን ብሎ ሲጨርስም እግዚአብሔር ሰይጣነ ዝሙቱን እስከ ወዲያኛው ከዚያ እኁ አራቀለት።”

ስለዚህ ሰይጣነ ዝሙት መጥቶ ሲያሳስበን ወይም በሌላ መንገድ ያየነውንና የሰማነውን በሕሊናችን እንድናመላልሰው በሚፈልግበት ጊዜ ምንም ሳንሰለችና ዕድል ሳንሰጥ ወደ አበ ነፍሳችን መሮጥ እንዳለብን ያስረዳል። አበ ነፍሶችም በትዕግሥት ልጆቻቸውን የመርዳት መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው። ወላጆቻችንም ሊያግዙን ይችላሉ።

የሐልዮ ኃጢአት በእኛ ላይ እንዲነግሥ ከሚያደርጉ ነገሮች ኣንዱ ለብቻና ሥራ ፈት መኾን ነው። ሥራ ፈትተን ለብቻችን ስንኾን ሰይጣን መጥቶ ያንን ኃጢአት በደንብ እንድናስብበት፣ ተግብረው ተግበረው ይለናል። ልክ ለሔዋን በለስን የምታስጎመጅ አድርጎ እንዳሳያት፥ በእኛም የማስተዋል ሕሊናችንን አጣምሞ ከዚያ ኃጢአት ስለምናገኘው ደስታ ያሳስበናል። “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀድዶ ይሰፋል” የተባለው መነኰሴ ሥራ ላለመፍታትና ከሓልዮ ኃጢኣት ለመራቅ ሲል ይህን ስለሚያደርግ ነው። ስለዚህ ዝም ብለን መቀመጥ አይገባንም። ይልቅስ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመሳተፍ፣ ሌሎች በጎ ሥራዎችንም በመሥራት እንጠመድ።

በዚህ ከተጎዱት ሰዎች መካከል አንዱ ነቢዩ ዳዊት ነው። ነቢዩ ዳዊት ወጣት ኾኖ በጎችን በሚጠብቅበት፣ ለሳኦል ጋሻ ጃግሬው ኾኖ በገና እየደረደረ በሚያገለግልበት፣ ሳኦል በምቀኝነት ተነሥቶበት በሚያሳድደው፣ ወደ ንግሥናው መጥቶ መንግሥቱ እስከ ተደላደለ ጊዜ ድረስ በዝሙት አልወደቀም ነበር። መንግሥቱ ተደላድሎ ከተመሠረተ፣ ክብሩ ከጨመረ በኋላ ግን ሥራ ፈትቶ በሰገነት ላይ ሲመላለስ የኦሪዮን ሚስት ቤርሳቤህን ስትታጠብ ተመለከታት። ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ፡- “ሰውነት ሥራ ሲፈታ፥ ሕሊናም ሥራ ይፈታል” እንዳለው፥ ንጉሥ ዳዊት ሥራ ፈትቶ ስለ ነበረም በቀላሉ በነቅዓ ሐልዮ ሳያበቃ ስለ እርሷ በማሰብ ወደ ሐልዮ ኃጢኣት ገባ። ስለዚህም “መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፣ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ" (2ኛ ሳሙ.11፥4)።

በመኾኑም ራሳችንን ሰይጣን ወደ ሕሊናችን የሚያስገባውን የሐልዮ ኃጢአትን ከላይ በጠቀስናቸው መንገዶች በማራቅ፥ ንጽሕናችንን ጠብቀን ከሴት ከወንድ ርቀን እስከ ጋብቻ ድረስ መጽናት ይኖርብናል።

አንዳንድ ጊዜ በሕልማችን ሩካቤ ስንፈጽም ልናይ እንችላለን። በዚህ ጊዜ እኛ ራሳችን ቀን ላይ ያሰብነው አሳብ አለመኾኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በቀን ያሰብነው ሌሊት ቀጥሎ ከኾነ ከአበ ነፍስ ጋር ተነጋግሮ አሳቡን ማራቅ፣ ከዚያ ውጭ ግን ወጣቶች በመኾናችንና “ፒቱታሪ” የተባለው ዕጢ የዘር ፈሳሽ ማመንጨቱና አንዳንድ ጊዜ በራሱ ተስፈንጥሮ ስለሚወጣ በዚህ መነሻነት ወደ ሌላ ኣሳብ እንዳንሔድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

(ገብረ እግዚአብሔር ኪደ  ከተጻፈው #ትንሿ_ቤተክርስቲያን መጽሐፍ - ገጽ 161-163)
‹‹ ዕርገተ ክርስቶስ ››

ክርስቶስ በተነሳ በአርባኛው ቀን ዓርጓል ። ዓረገ ማለት ስራውን ጨረሰ ማለት ነው ። በ፵ ቀን ያረገው ማነው የሚለውን መተርጉማን ለቃል ይሰጡታል። በጸሎት ሃይማኖት ዓርገ በስብሐት ያለውን ሲተረጉሙ። የስጋ ርገት በማሕፀን የቃል ርገት በዓርባ ቀን ብለዋል ፥ ሃይ.አበ.ም.፲፯፥፱። ይሄንንም ቃል የኔታ ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ ሲያብራሩ ፥ ሊቁ የስጋ ርገት በማሕፀን ነው ማለቱ ፥ ስጋ በዓለመ ቃል መኖር የጀመረው ከፅንስ ጀምሮ ስለኾነ ነው ። የቃል ርገት በዓርባ ቀን ያሰኘው ቃል በዓለመ ስጋ መኖር መጨረሱን ወደ ዓለመ  ርእሱ መመለሱን ለመናገር ነው ብለዋል። ዓለመ ቃል ማለት ረቂቅነት  ፥ ሙሉዕነት ፥ ሁሉን ማወቅ ፣ አምላክነተ ፣ ናቸው ስጋ እነዚህን ገንዘብ በማድረግ በዓለመ ቃል መኖር የጀመረው ጊዜ ፅንስ በማሕጸን በመሆኑ ርገት ስጋ በማሕፀን ነው   ተባለ ። ዓለመ ስጋ የሚባለውም መራብ ፣ መጠማት ፣ መድከም ፣ መተኛት ... ነው ስግው ቃል እነዚህን ከዕርገት በኋላ አያደርጋቸውም ርገተ ቃል በዓርባ ቀን ነው ተባለ ። ይህን ሊቁ ኤጲፍንዮስ ዘቆጵሮስ ሲያብራራ ፥ ኢኮነት በስጋ አላ በመንፈሰ እምትንሳኤ ምውታን ኢየሱስ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚእነ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ አንድ ወገን ሁኖ መኖሩ "በአምላክነት ግብር "ነው እንጅ "በግዘፍ" አይደለም ተረ.ቄር.ም.፲፮.፲፭። ሊቁ "አንድ ወገን ሆኖ " ማለቱ ከተዋሕዶው በተጨማሪ የሚያስረዳው ስግው ቃል በዚህ ዓለም ሳለ አንድ ጊዜ የሰውነቱን አንድ ጊዜ የአምላክነቱን ስራ ያደርግ እንደ ነበር ነገር ግን ከትንሳኤ በኋላ አንድ ወገን በአምላክነት ግብር መኖሩን ያስረዳል ። ሲኖር ግን ሰውነቱ ጠፍቶ አይደለም ገዜ ተዋሕዶ ሰውነት በማሕፀን ድንግል ገንዘብ የባሕርይ አምላክነት ጸንቶ "አምላክ ወሰብእ" <<ወልደ አብ ወልደ ማርያም >> ሲባል ለዘለዓለሙ ይኖራል።

(ኦርያሬስ ገፅ 191 መምሕር ሳሙኤል አለሙ)

እንኳን አደረሳቹ ። 🙏

ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን ።
#_ግንቦት_26_ለዓለም ብርሃን የሆኑ  #ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ሀብተ_ማርያም_ልደታቸው_ነው፡፡

በመብረቅ፣ በቸነፈር፣ በረሃብ፣ በወረርሽኝ፣ በእሳት ቃጠሎ ላይ ቃል ኪዳን የተሰጣቸውን የእኒህን ጻድቅ #ታሪካቸውን_መልክአቸውና_በ ቃሌ ተራራ ደብረ መድኀኒት አቡነ ሀብተማርያም ገዳም( አዲስ አበባ ከዊንጌት ትምህርት ቤት አካባቢ) የሚቆመውን ሥርዓተ ማኀሌት እንሆ ብለናል፡፡
                          #share
አቡነ ሀብተማርያም
፠፠በማዕጠንታቸው የታወቁ፤
፠፠በጽድቅ ሥራቸው የተደነቁ፤
፠፠5ት መቅሰፍቶችን የሚያርቁ ታለቅ አባታችን ናቸው፡፡፡፨

፠በመራ ውዕይ (ሸዋ ፥ ቡልጋ) ከአባታቸው #ፍሬ ቡሩክና ከእናታቸው ቅድስት #ዮስቴና ነው የተወለዱት፡፡ ወላጆቹ በተለይም እናቱ ከማግባቷ በፊት መንና ነበር፡፡ ጻድቁን እንደምትወልድ በበቃ ባሕታዊ ተነግሯት ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ #7_አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡

፠አቡነ ሀብተማርያም በሕፃንነታቸው ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል፤ ጓደኞቻቸው የሌላ ሰው እሸት እየነቀሉ ሲበሉ እርሳቸው ግን አይበሉም ነበር፡፡ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በአየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡

፠ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ቤተ ሰቦቻቸው ሚስት አጩለት፤ እርሱ ግን ወደ አፋር ከአባ ሳሙኤል ዘንድ ሂዶ ለ12 ዓመታት ረድዕ ሆኖ ተቀመጠ፡፡ ከአፋርም ወደ ምኔት ወደሚባል ቦታ መጥቶ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሰ፤ ከአፋር ወደ ይነውፋ፥ ከይነውፋ ወደ ጉሐርብ ወደሚባል ሃገር ሂዶ ምናኔን፣ ትሩፋትንና ተጋድሎን ሠራ፡፡
ለአብነትም፤
ባሕር ውስጥ ሰጥሞ 500 ጊዜ ይሰግዳል፤
በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያል፤
በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባል፤
ምግቡ ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው፤
በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋል፤
ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላል፥ ክቡር ደሙን ይጠጣል፤
በልቡ ውስጥ በፍጹም ቂምን፣ መከፋትን አያሳድርም፡፡
የብረት ሰንሰለት በወገቡ ታጥቆ ይሰግዳል ይጸልያልም፡፡
"ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሀብተ ማርያም"  የተባለላቸው ታላቅ አባታችን ናቸው   ፡፡

፠ዲቁናን ከጳጳሱ አቡነ ይስሐቅ ዘንድ ተቀበሎ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡
፠ኋላ ቆይቶም እንደገና ከአቡነ ይስሐቅ ዘንድ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ወደ ጓና ወደ ምትባል ሀገርም ሂዶ ተቀመጠ፡፡ ቀጥሎም ጐላጐት ወደ ምትባል አገር ሂዶ ተቀመጠ፡፡
*የአፄ ናዖድ የንስሐ አባት ነበረና ንጉሡን ያስተምረውና ይገስጸውም ነበር፡፡
፠ጌታችንም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቶት በዚያ እየበረረ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔድ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው::

"*ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: *ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: *ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: *ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: *ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: *ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"

"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ በርእስየ' ብዬሃለሁ" አላቸው::

+ቅዱሳን መላእክትም "ሀብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: መላእክትም ዝማሬም ወሰዷት::

 ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤
፩ኛ. #መብረቅ
፪ኛ. #ቸነፈር
፫ኛ. #ረሃብ
፬ኛ. #ወረርሽኝ
፭ኛ. #የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡

፨በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርክ ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡
በግንቦት 26 ተወልዶ፤ በ1490 ዓ.ም. በወርኀ ኅዳር 26 ባረፈ ጊዜም፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በደብረ ሊባኖስ ቀበሩት፡፡
(ከወርቅ ንፁህ ከብርም የጠራ ከሁሉ የሚበልጥ የተመረጠ ሃብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡)

ክብርት በሆነችው ጸሎቱና ምልጃው ይማርን ይጠብቀን፡፡

#ሰላም_ለጽንሰትከ_እማኅፀነ_ቅድስት_ዮስቴና
#በብሥራተ_ጻድቅ_ባሕታዊ_ሠናየ_ዜና፡፡
#ሀብተማርያም_ጴጥሮስ_ሐዋርያ_ወልደ_ዮና
#መሐረኒ_ምግባረ_ጽድቅ_ወጸግወኒ_ልቡና
#አፍቅሮ_ቢጽ_እኅሥሥ_ዘምስለ_ፍጽመት_ትሕትና፡፡
https://t.me/yeberhanljoche
ወዳጄ ሆይ! ኃጢአተኛ ከኾንህ በደልህን ትናዘዝ ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ጻድቅም ከኾንህ ከጽድቅ (ጎዳና) እንዳትወድቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ቤተ ክርስቲያን የኃጥኡም የጻድቁም ወደብ ናትና፡፡

ኃጢአተኛ ነህን? ተስፋ አትቁረጥ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህም ንስሐ ግባ፡፡ ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው፡፡

እስኪ ንገረኝ! “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ ምን ውጣ ውረድ፣ ምን ዓይነት የሕይወት መርሕ፣ ምንስ መከራ አለው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት (ኃጢአት ሠርተህ ሳለ) በደለኛ አይደለሁም የምትል ከኾነ ዲያብሎስም አንተን አይወቅስህም፡፡ (በድያለሁ ብለህ ንስሐ የምትገባ ከኾነ ግን) ይህን (ዲያብሎስ ሊወቅስህ እንደሚችል) አስቀድመህ አስብ፡፡ …

ስለዚህ ክብርህን እንዳይወስድብህ ለምን አትከለክለውም? ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም?

ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” ብለህ ንገረው፡፡ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስም፡- “ንግር አንተ ኃጣውኢከ ቅድመ ከመ ትጽደቅ - ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል (ኢሳ.43፡26)፡፡ ስለዚህ ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፡፡

ይህን ለማድረግ ውጣ ውረድ የለውም፤ ዙሪያ ጥምጥም የቃላት ድርደራም አያሻህም፤ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም፤ ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም፡፡ አንዲት ቃል ተናገር፤ በደልህን በአንቃዕድዎ አስባት፤ “በድያለሁ” ብለህም ተናዘዛት፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
https://t.me/yeberhanljoche
+  መልአኩ ነው +

       ሰዓቱ ሌሊት ነው ፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዚያ ሌሊት መላው የቤተሰባችን አባል አምሽቶ እየተጫወተ ነው፡፡ ከዚህ የቤተሰብ ስብስብ መካከል ሳይገኝ የቀረው አንድ በወኅኒ ቤት የታሰረ ወንድማችን ብቻ ነበር፡፡ ድንገት ግን የጊቢው በር በተደጋጋሚ ተንኳኳና ሁላችንም ጨዋታችንን አቋረጥን፡፡ በሌሊት የሚያንኳኳው ማን ነው ?

ሠራተኛችን ሮጣ ሔደች:: ወዲያው ግን በሩን ሳትከፍተው ተመልሳ እየሮጠች መጣች፡፡ በደስታ ሰክራ ‹‹የታሰረው ልጃችን በር ላይ ቆሟል!›› ብላ ተናገረች፡፡ "በድምፁ አወቅኩት!› እያለች ዘለለች፡፡ ከሁኔታዋ የተነሣ ‹አብደሻል እንዴ!?› አላት ቤተሰቡ ሁሉ፡፡

እስዋ ግን በእርግጠኝነት ተናገረች! በቀን የታሰረው ልጅ በሌሊት ተፈቶ መምጣቱ ፈጽሞ ሊታመንን የማይችል ነገር ነው፡፡ ቤተሰቡ ሁሉ የታሰረው ልጅ መጣ ብሎ አላመነም፡፡ ባይሆን የመንግሥት ወታደሮች የቀረነውን ሊወስዱን ይሆን? ማን ሊሆን ይችላል? ብሎ ተብሰለሰለ:: በመጨረሻም የሁሉም ግምት አንድ ነገር ላይ አረፈ:: ሁሉም ሰው በአንድ ድምፅ አንድ ቃል ተናገረ "መልአኩ ነው!"

  መልአኩ የሰው ስም አይደለም:: ቤተሰቡ የተስማማው "ደጅ የቆመው የታሰረው ልጃችን ሳይሆን እሱን ለመጠበቅ ከእግዚአብሔር የተሠጠው ጠባቂ መልአኩ ይሆናል›› ብሎ ነበር፡፡ የበሩ መንኳኳት አሁንም ስላልቆመ ቤተሰቡ ግር ብሎ ወጣና ተቻኩሎ በሩን ከፈተ፡፡ በደጅ የቆመው ግን እንደተባለው የታሰረው ልጅ ራሱ ነበር፡፡ ሁሉም ተደሰተ!!!

      ይህ ገጠመኝ በአሁን ዘመን የተፈጸመ ነው ብዬ ብናገር ማን ያምነኛል? እውነት በሌሊት የቤታችን በር ሲንኳኳ  መልአክ ነው ብለን እንገምታለን? ይህ ቤተሰብ ምን ዓይነት ቤተሰብ ነው?

በብዙዎቻችን አእምሮ ውስጥ መጀመሪያ የሚመጣው ጥርጣሬ ‹ሌባ ሊገባ ይሆን?› የሚል ስለሚሆን ዱላ ፍለጋ እናማትራለን፡፡ ወይ ደግሞ ሌሊቱ ወደ መንጋቱ እየተቃረበ ከሆነ ‹‹የምን መርዶ ሊያረዱኝ ይሆን? የቱ ዘመዴ ሞቶ ይሆን?› የሚል ጭንቀት ይፈጠራል፡፡

‹የሚያንኳኳው የእግዚአብሔርመልአክ ይሆናል› ብሎ የሚጠረጥር ሰው ግን በዚህ ዘመን ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ እንዲህ ብሎ ግምቱን የሚናገር ሰው ከቤተሰባችንመካከል ቢገኝ እንኳን እንደ ዕብድ ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ታዲያ ይህን ገጠመኝ ከየት አመጣኸው ትሉኝ ከሆነ መልሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚል ነው፡፡

      በሐዋርያት ዘመን ሔሮድስ የተባለው ንጉሥ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስን ወኅኒ ቤት ውስጥ ወርውሮት ነበር፡፡ የቀሩት ደቀመዛሙርትና ክርስቲያኖች በዚያ ሰሞን ሲጸልዩ ከርመዋል፡፡ በአንድ ሌሊት በማርቆስ እናት ቤት ውስጥ ተሰብስበው አምሽተው ነበር፡፡ ድንገት የቤቱ በር ሲንኳኳ ሮዴ የምትባል የቤት ሠራተኛ ደጁን ልትከፍት ወጣች፡፡ ማነው ብላ ስትሰማ የቆመው እስረኛው ቅዱስ ጴጥሮስ መሆኑን በድምፁ አወቀች፡፡ ደስታ ግራ ሲያጋባት በሩን መክፈትን ረስታ ወደ ውስጥ ሮጠችና ጴጥሮስ መምጣቱን ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን አላመኑአትም፡፡ ጤንነቷን ተጠራጥረው ‹አብደሻል› አሏት፡፡ እርግጠኛ ሆና ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን መልሰው ‹‹የቆመው ጴጥሮስ ሳይሆን መልአኩ ነው፡፡›› አሉ፡፡ ይደንቃል የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እንዲህ በር ሲንኳኳ ‹መልአክ ነው› ብለው የሚገምቱ መንፈሳዊያን ነበሩ፡፡ (ሐዋ. 12፡12-15)

      ቅዱሳንመላእክት እኛ የሰው ልጆች ከመፈጠራችን ቀድመው የተፈጠሩ ታላቅ ወንድሞቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም ምድርና የሰው ልጅ ሲፈጠር ደስ እያላቸው ‹‹እልል›› ይሉ ነበር፡፡ (ኢዮ. 38፡6) ቅዱሳን መላእክትን እግዚአብሔር ለእንዳንዳችን ጠባቂዎች አድርጎ ሠጥቶናል፡፡ ከክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብለው የተማሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ መላእክት ጠባቂነት ጋር ይህን ያህል እምነት ከነበራቸው እኛም የመላእክቱን ጠባቂነት ማመን ለዚህ ዘመን ክርስቲያኖችም ምን ያህል ይገባን ይሆን? ቅዱሳን መላእክት በክርስትና ሕይወት ለሚኖርሰው ሁሉ የመላእክት ረዳትነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለሁሉ ብርታት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በሥጋው ወራት በተያዘባት ምሽት ሲጸልይ ‹‹ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ሉቃ. 22፡43) ይህም ቀርበው አገለገሉት‹ለከ ኃይል› እያሉ አመሰገኑት ማለት ሲሆን ለእኛም የመላእክት ርዳታ አያስፈልገኝም እንዳንል የሚያስተምረን ነው፡፡

ቅዱሳን መላእክት በምድር የሚሆነውን ያውቃሉ:: (2 ሳሙ 14:20) በበደላችን ስንጸጸት "ኃጢአትህ ተሠረየችልህ" ይላሉ (ኢሳ 6:7) በክፋታችን ጸንተን ከቀጠልን ደግሞ "ይቅር አይሉም" (ዘጸ 23:20)
ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ቆመው "የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?" ብለው ያማልዳሉ:: (ዘካ 1:12)

ባለንበት ዘመን በዓለም ሁሉ በበሽታ የሚሠቃየው ብዙ ነው::  በሕመም ለሚሠቃየው ሁሉ

"መልአክ ቢገኝለት እየራራለት [ለእግዚአብሔር] ፡— ቤዛ አግኝቻለሁና ወደ ጕድጓድ እንዳይወርድ አድነው፡ ቢለው፥ ሥጋው እንደ ሕፃን ሥጋ ይለመልማል፤ ወደ ጕብዝናውም ዘመን ይመለሳል" ኢዮ 33:23-25
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ ሚካኤል - 2007 ዓ ም የተጻ
+++ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። +++

                + ሰኔ21


እንኳን ለአዳም ለዘር ሁሉ ድኅነት ለተደረገባት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በስሟ የተሰራችው የመጀመርያ ቤተ ክርስቲያን በልጇ በወዳጇ እጅ ለተቀደሰችበት ለከበረችበት ዓመታዊ በዓሏና በዓለም ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን መታነጽ መታሰቢያ ታላቅ በዓል፣
እመቤታችን ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ለተገለጠችለትና ሥዕሏን እንዲያሠራላት ለነገረችውና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ላደረገች፣
ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት ባረድዋት በአንዲት ሴት ላይ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ በዓል፣
ለምስር አገር ለሆነ ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና
ለእስክድርያ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ከላድያኖስ ለዕረፍት በሰላም በሰላም አደረሰን።
በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ሜሮን ከተገኘችበትና የአስታፍን ዐፅም ከተገኘችበት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

+++ሰኔ 20 እና 21

ከእመቤታችን 33 ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸችው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ። ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የንጉሥ ሰሎሞን ቤተመቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር። ቤተክርስቲያናችን ዕለቱንም ህንጸተ ቤተክርስቲያን በማለት ታከብረዋለች።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።+++

ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም መራዕተ ክርስቶስ ከተሰኘች ቅድስት ቤተክርስትያን ረድኤት በረከት ይክፈለን።

                        + + +