ناصر الدين(ናሲሩዲን)
478 subscribers
557 photos
87 videos
6 files
369 links
[[ وَجَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا ]]

{እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።}

ሼር add በማድረግ የበኩላችን እንወጣ


https://t.me/joinchat/jhrmqQH66YtiOGFk
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአላህ በየአውቃቱ ነፈሀት አለው። ያቺ ነፈሀት ያገኘቹ ከሸቅይነት ነፃ ይወጣል።

አላህ ከነፈሀቱ ያገናኘን በዘመናችን ታላቅ ዓሊም ዛሂድ ተቅይ ነቅይ ሙሀቂቅ በሆኑት ሰይዲ ሙሀመድ ከቢሩ💚 ስም ዒድ ሙባረክ🌷🌷

https://t.me/ahlusunawelgema
·





በድጋሚ ዒድ ሙባረክ🌷
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሰላችሁበት ሰላምና በረከቱ ይስፈንባቹ…

ዒድ ሙባረክ
እኛ እስልምናን በተግባር ያስተማሩን…

አደብን ተዋዱዕን መተነናስን መተዛዘን ፍቅርን ሁሉም የሞላቸው ሳዳቶቻችን…አላህ ያቆይልን

የኢትዮጵያ ኢማሞች ኢማም እና የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም ሰይዲ ሰይድ ሀጅ ጧሃ

https://t.me/ahlusunawelgema
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዛን ላይ ተምጢጥ ተው ብንል አልሰማ ብላቹ … ይሃው ዶሮም ጀመረው😂

ለማንኛውም ሰላቶቻችን ያለ አዛን እንደምንሰግድ ታውቃላቹ?

መልካም ዒድ… የዒዱን በረካ አላህ ይስጠን

https://t.me/ahlusunawelgema
ሆቴል ማለት በአጭር አገላለፅ የዝሙት መንደር በተጨማሪ የኸምር መጠጫ ነው። … ሆቴል አልህ ዘንድ የተጠላ ቦታ ለመሆኑ ከዚህ በላይ ምን ሊሰራበት ነው የምትሹት
ነብዩ ሰዐወ የሀላል ንግድ የሚፈፀምባቸው ቦታዎችን እራሱ… አላህ ዘንድ የተጠላ ቦታ ገበያ ነው ብለው ገልፀውታል። ታድያ የዝሙትና የኸምር ቦታዎችስ

የመጅሊሱ አዳራሾች ለኢስላማዊ ጉዳይ መወያያ መመካከሪ ካልሆኑ ለኮንሰርት ነው እንዴ የተሰሩት
ዒድ ሙባረክ በሞሪታንያ ሻይ

ከኸይራቱ የሚያገናኘን ዒድ ያድርግልን
ጫት የማትቅሙ ሰዎች አትጀምሩ:: የጀመራችሁም እጅግ በጣም ቀንሱ:: አደብ ከሌለው እንኳንስ ጫት ምግብም ሶላትም ያስቀይማሉ:: ሥርዓት የሚያስይዘንና ጸባያችንን የሚያስተካክልልንን ሶላት ስንሰግድ ሥርዓት ካስፈለገ ወትሮም ከሥርዓት የሚያስወጣንን ጫት እንዴት ሊሆን ነው? አቀራርቤ እያወዳደርኩ አይደለም::

ጫት ከመደበኛ የአስተሳሰብ ምሕዋር እንደሚያስወጣ ይታወቃል:: የቻለ አይቅረበው:: የቀረበው ግን ከምንም በላይ ለሥርዓት ይጨነቅ:: ከምሕዋር ይወጣላ! ፈታ ለማለት እየቃምን የምን መጨነቅ ነው ትሉ ይሆናል:: ወንድሜ ሁሌ ፈታ ማለት የለም:: ዱንያ ላይ ጨምደድ የምትልበት ወቅት ይበዛል:: ፈታ ለማለት የምትቅመው ጫት ደግሞ ብዙ ነገርህን ያጨማድድብሃል:: ማጨማደድ ባሕሪው ነው:: ሰተት ብለህ ከገባህለት ይገባልሃል:: አምጣ ባለህ ቁጥር የምትሰጠው አባትህ ወይም እናትህ ወይም ልጅና ሚስትህ አይደለም:: ጫት እኮ አያዝንልህም:: ምን ብትሰጠው አይጠግብም::

የቀድሞ አባቶቻችንን አቃቃም ከደረስክበት:- ቤት ለማሞቅ ይጎዘጉዛሉ:: ጥቂት ነው ቀመስ የሚያደርጉት:: ከሚቃመው ደርቆ የሚጣለው ይበልጣል:: ሲጀመር የሚጣልም ያህል አያመጡም:: እስኪመረቅኑ አይቅሙም:: እኛ አሁን በማኪያቶ ከምንመረቅነው አይዘልም ማለት ይቻላል:: በእርግጥ በዚያው ልክ አጋድመውና ተጋድመው የሚቅሙም ነበሩ::

ሰውነትህን ፕሮግራም ከሰጠኸው ወዲያው ይለምዳል:: ሽንት ባስለመድከው ፕሮግራም ብቻ ይመጣል:: እቤት ውስጥ መፍሳት ከለመድክ የትም ታንዛርጣለህ:: ከተውከውም ይተውሃል:: ምግብ ባስለመድከው ወቅት ብቻ ትበላለህ:: ሰውነታችን ችግር ይለምዳል, ሀብት ይለምዳል, ሀዘን ይለምዳል, መርሳት ይለምዳል, ብርድና ሙቀት ሳይቀር ይለምዳል:: ዋናው ከልብ መቁረጥ ነው::

አንተስ ትቅማለህ ወይ? ካልከኝ አልቅምም ብል ይቀላል:: ከማኪያቶ ሙቀት እንዲዘል አልፈቅድለትም:: ከምቅመው ይልቅ የምጥለው ያስደስተኛል:: አሁን ላይ ባለ 70 የሚሉት ላይ 1/5ኛውን አልፈጅም:: ቤት ያሞቅና እንጥለዋለን:: እርሱም ከዕለታት ባንዱ ቀን:: ለ25 ዓመታት ያቆምኩ ሰው ነኝ:: ከዚያ ለ25 ቀናት ወይም ለ25 ወራት ላልነካ እችላለሁ::

በእስልምና ስም መቃሙን እንኳ ተውት:: እስልምና ንጽሕና ነው:: ለጡሃራ ደግሞ ከውሃም ውስጥ ውሃ ይመረጣል:: ጫትም እስኪያቆሽሽህ ከቃምክ ስተሃል:: ወላሂ!

Hassan injamo
https://t.me/Haseniye

https://t.me/mneyuredulahe
ምን ትላላቹ
ጫት ስለበላህ ሱፍይ አትባልም። ስላልበላህም ውሃብይ አትባልም። በቀላሉ ከሀገር ውስጥ ሀረር ድሬዳዋ ብትሄድ ከሱፍያው በላይ የሚቅመው ውሃብዩ ነው። አዲስም ውስጥ የምናውቃቸው የሚቅሙ ውሀብዮች አሉ። ድሬ ወይም ሀረር ሄደህ ጫት ሀራም ነው ብትል ውሃብዩ ነው አፈር ድሜ የሚያስበላህ።

ወንድሞች ሲጀመር ጫት አይደለም ከሱፍይነት ከእስልምና ጋር ምንም አያገናኘውም። ስለቃመ ሙስሊም አይባልም። ስላልቃመም ክርስቲያን አይባልም።

ጫት ልክ እንደ ሻይ ማክቶ ቡና ነው። ሌላ ምንም ለውጥ የለውም። ቡና ስለጠጣህ ሱፊ ሰለፊ አትባልም። ሻይም ማክያቶም ጫትም እንደዛው። ጫቱ ለአባቶች እንተወው። ዑለሞቹ ሲቅሙ ኪታብን ያቃራቸው ዘንድ አንድ ሁለት ነው የሚዙት።

አንተ የምትቅመው ቅራ ስንልህ ጊዜ የለኝም ያልከን ስትቅም የሚባክነው ጊዜስ ዑለሞች እኮ ያለ እውቀት የሚሰራ ዒባዳ ባጢል ነው። ተቀባይነት የለውም ብለዋል። እንደውም በፊቅህ በሻፊዕዮች ባፈድልን በሌሎች መዝሀቦችም በባፈድል ደረጃ ያለን ኪታብ ካልቀራ ሰላቱ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።❗️

👌ነገ የመጀመሪያ ሂሳብ የሚደረገው ሰላት ነው። ሰላቱ የተበላሻ ሁሉም ስራው ይበላሻል። ሰላቱ የተስተካከለ ሁሉም ስራው ይስተካከላል። ታድያ ሳትቀራ እንዴት ነው ሰላትህ የሚስተካከለው

አንዳንዱ ስለቃመ አረንጓዴ ስለለበሰ ሙስበሃ አንገቱ ላይ ስለደራረበ ወልይ ሱፍይ የሆነ ይመስለዋል። አትሸወድ ሱፍይነት በአጭር አገላለፅ
محاربة النفس لا سلم فيها
{ከነፍስያ ጋር ስምምነት የሌለው ጦርነት መክፈት ነው።}
አንተ ጃሂል ከሆንክ በመቅራት ነፍስያህ ጋር ጦርትነት መጀመር። በቀራሀው ለመስራት መታገል። ውስጥህም ውጭህም ለአላህ አሳልፈህ ለመስጠት የምታደርገው ጦርነት።

ብጣሽ ወረቀት ቀርተህ አፍህን በአላህ ባሮች እየከፈትክ ሱፍይነኝ ስትል አታፍርምተሰውፍነት ወሬ ሳይሆን ስራ ነው። ስራ ደግሞ የሚጀምረው ከዒልም ነው። ሰይዲ ኢማም ማሊክ
من تفقه ولم يتصوف فقد تفسق، ومن تصوف ولم يتفقه فقد تزندق
ዒልም ከስራ ጋር ስናገናኘው ውጤቱ ተሰውፍ ጋር ያደርሰናል። ዒልም እና ዐመል መነጣጠል የሚይችሉ የተሰውፍ መሰረቶች ናቸው።

የፈለገ ይቃም የፈለገ አይቃም መብቱ ነው። ቡናም የፈለገ ይጠጣ የፈለገ አይጠጣ መብቱ ነው። ሻይም ማክያቶም። ነገርግን ስለ ቃምክ ሱፍይ ሱፍይ አይሰራራህ።

https://t.me/ahlusunawelgema
ፕሮፍይል በማድረግ ላልደረሳቸው እንዲዳረስ ሰበብ ይሁኑ

https://t.me/DaralHijrataynIslamicSchool
በመጨረሻ ሰዓት
📢አስደሳች ዜና ለክረምት ኦን ላይን ደርስ

✍️አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ
ዳሩል ሒጅራተይን ኢስላማዊ ዕውቀት ማዕከል በተለያዩ የኢልም ዘርፎች አጭር የክረምት ኮርስ
መርሀ ግበር ሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭ
ላላቹህ በሙሉ ቁርአንን ማንበብ እና ማወቅ እየፈለጋቹህ እድሉን ላላገኛቹህ በሙሉ ታዳጊዎችን እንዲሁም አዊቂዎችን መሰረታዊ የዲን ዕውቀትን ለማስጨበጥ ዝግጅቱን ጨርሶ የናንተን መምጣት በመጠበቅ ላይ ነው
ልዩ ከሚያረጉን አንዱ ደርስ አሰጣጥ ላይ ሸሪዐውን ባማከለ መልኩ እውቅና ባላቸው ልዪ በሴት ኡስታዛዎች ለሴት ተማሪዎች ደርስ መስጠታችን ሲሆን በተጨማሪም ለወንድ ተማሪዎችም በወንድ ኡስታዞች በልዩ ሁኔታ ደርሶችን የምንሰጥ ይሆናል።ፍላጐታችን ውስን ተማሪ በጥራት ማፍራት ነውና ፈጥነው ይመዝገቡ !!!

📚 በኦን ላይን የክረምት መርሀ ግበር
◦ለልጆች/ ለታዳጊዎች
◦ ለሴቶች
◦ ለወጣቶች እንዲሁም ለአዋቂዎች በሙሉ


🗒 ኮርሱ የሚያካትታቸው ፦
* ቁርዐን
* ተጅዊድ
* ፊቅህ
* አቂዳ
* ሀዲስ እና
* ኢሰላማዊ ስነ- ምግባራት

➥ ምዝባው ፦ከሰኔ 27 - ሀምሌ 09/2014
ይሆናል።
➥ ደርስ የሚጀመርበት ጊዜ ከሀምሌ10 እስከ
መስከረም 05/2015 በአሏህ ፍቃድ
የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ለመመዝገብ👇👇 http://t.me/Assunnahislamicschool_bot/start



🗞በኮርሱ መጨረሻ ለተማሪዎቻችን
በውጤታቸው መሰረት ሰርተፍኬት የሚሰጣቸው
ይሆናል።


የቻናላችን መገኛ👇👇
https://t.me/DaralHijrataynIslamicSchool
አስተውል.....✍️

ለጉዳይህ ስትል ሶላትህን በጥድፊያ አትስገድ!
ምክንያቱም የቆምከው የቸኮልክለትን ጉዳይህን ጨምሮ ዱኒያን ሁሉ የያወው
ጌታህ ፊት ነውና።

@ahlusunawelgema
#መልካም_ጎደኛ
"ሁለት ውብ የሂወት ኡደቶችን ይለግሰሀል…"
"አንደኛው አዚህ ዱንያ ላይ ሲሆን"
"ሁለተኛው ደግሞ ጀነት ውስጥ ይሆናል"
# መልካም_ጎደኞች
«ወደ አሏህ መንገድ… ይጠሩሀል…»
«ከጠፋህባቸው… ይፈልጉሀል…»
«ከተዘናጋህ… አስታውሱሀል»
«…በዱአቸው ውስጥ…ያካቱሀል»
«ልክ እንደ ከዋክብቶች…
መርከብህ መንገድ ከሳተች…ይመሩሀል…»
«ነገ ከአሏህ አርሽ ስር…ኢንሸአላህ…ይጠብቁሀል…»
«ጀነት ውስጥ ፈልገውህ ካጡህ…አሏህን ወደነሱ
እንዲቀላቅልህ ይለምኑልሀል»

👌ወንድሜ ዛሬ ላይ ከፊትህ ስቆ ዞር ስትል የሚያማህ ውስጥህ ያለ ጥበብና ችሎታህን ደብቆ ባገኘው አጋጣሚ ጉደለቶችህን የሚያያሳይህ እና የበታችነት እንዲሰማህ ለማድረግ የሚሞክርን ሰው አይደለም ልብህ ጆሮህን አትስጠው።

"አሏህ ሶሊሆቹን አድርጎ ከሶሊሆቹ ያወዳጀን ከሶሊሆቹ
ጎደኞቻችን አይነጥለን በያሉበት ይጠብቅልን "
#አሚን

ለዱንያህ ለቀብርህ ለአኼራህ የሚሆንህን ሰው ምረጥ።

https://t.me/ahlusunawelgema